(ዘ-ሐበሻ ዜና) የዱባይ ፖሊስ ስለታማ መሳሪያዎችን በመጠቀም አደገኛ በሆነ የርስበርስ ግጭት ውስጥ የተሳተፉ ወጣቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። በተጨማሪም ይህንን የድብድብ ክስተት በቪዲዮ ቀርጾ በማህበራዊ ሚዲያ ያሰራጨ ሌላ ግለሰብም በፖሊስ ተይዟል። ፖሊስ ለካሊጅ ታይምስ እንደገለጸው፣ በሁሉም ተጠርጣሪዎች ላይ አስፈላጊው ህጋዊ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፣ ጉዳያቸው ለሚመለከተው የፍትህ አካል ተላልፏል።
የጸጥታ አካላቱ የህዝብን ደህንነት ለማስጠበቅ ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሚ በማረጋገጥ፣ ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል አጠራጣሪ ወይም ህገወጥ ድርጊቶችን ሲመለከት በዱባይ ፖሊስ የስማርት ስልክ መተግበሪያ ላይ በሚገኘው የ“Police Eye” አገልግሎት በኩል ወይም በቀጥታ ወደ 999 የስልክ መስመር በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ አሳስበዋል።
የ“Police Eye” አገልግሎት ነዋሪዎች ማንነታቸው በሚስጥር ተጠብቆ ጥቆማዎችን እንዲሰጡ ያስችላቸዋል። ተጠቃሚዎች ፎቶዎችን፣ ቪዲዮዎችን ወይም የድምጽ መልዕክቶችን ከጥቆማቸው ጋር አያይዘው እንዲሁም የቦታውን አድራሻ ገልጸው መላክ ይችላሉ። ይህ አገልግሎት እንደ ረብሻ፣ ድብድብ፣ ከዕፅ እና መጠጥ ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን እንዲሁም ሌሎች ህገወጥ ድርጊቶችን ሪፖርት ለማድረግ ያገለግላል።
በመጨረሻም ፖሊስ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።
የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲህ ያሉ ህገወጥ ድርጊቶችን በቪዲዮ ቢቀርጹ እንኳ በቀጥታ ለጸጥታ አካላት ከመላክ ባለፈ፣ በምንም አይነት ሁኔታ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መለጠፍም ሆነ ማሰራጨት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን አስጠንቅቋል።
ዱባይ ያላችሁ ጥንቃቄ አድርጉ።

6 days ago