የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ በመምሰል የማታለል (በተለምዶ ሿሿ) ተብሎ የሚጠራውን ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 9 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 1:40 በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ሪቼ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው።
የግል ተበዳይ ከአጎና ወደ እስታዲየም ለመሄድ በማሰብ ኮድ 3-83620 ኦሮ ነጭ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በማስቆም ትገባለች። ተጠርጣሪዎችም የግለሰቧን ወደ ተሽከርካሪው መግባት ተከትለው በማዋከብ እና ትኩረቷን በማሳጣት ይዛው ከነበረው ቦርሳ ውስጥ 32 ሺ ብር ግምት ያለው ሳምሰንግ ስልክ ሰርቀው ጥለዋት ይሄዳሉ።
ይህን የተመለከቱ የትራፊክ ፖሊሶች ተሽከርካሪውን በማስቆም እና ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ ሰርተዋል።
ተጠርጣሪዎቹ ከተያዙ በኋላ በተሽከርካሪው ውስጥ በተደረገ ፍተሻ 7 ስልኮች መገኘታቸውን የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታውቋል።
ከተጠርጣሪዎቹ መካከል ነፍሰ ጡር መኖሯ የተገለጸ ሲሆን የቀን ውሎ አበል በመክፈል እና ተሽከርካሪ በመከራየት ወንጀሉን የሚፈፅሙ ግለሰቦች እንዳሉ ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ትራንስፖርት ሲጠቀም ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
Addis Ababa police

26 days ago