25 days ago
የነገው የጎዳና ሩጫ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች
***************
ነገ ሐምሌ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስተባባሪነት የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ የጎዳና ሩጫ ይደረጋል።
ውድድሩ መነሻውን ከመስቀል አደባባይ በማድረግ በገሀር፣ ሜክሲኮ አደባባይ፣ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል፣ ብሔራዊ ቴአትር፣ ኢትዮጵያ ሆቴል፣ ንግድ ባንክ፣ ጋንዲ ሆስፒታል እና ጊዮን ሆቴል አቋርጦ በመስቀል አደባባይ ፍጻሜውን ያገኛል።
በመሆኑም ነገ እሁድ ከንጋቱ 11:30 - ሰዓት ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ፦
• ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)
• ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን አደባባይ ላይ) ለከባድ ተሽከርካሪ (አጎና ሲኒማ ላይ)
• ከAU መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጥይት ቤት መስቀለኛ ላይ)
• ከፓርላማ መብራት ወደ ኮንሰን መታጠፊያ (ፓርላማ መብራት ላይ)
• ከኮንሰን መታጠፊያ ወደ ገብርኤል (ኮንሰን መታጠፊያ ላይ)
• ከጥይት ቤት ወደ ገብርኤል በጀርባው (ጥይት ቤት መታጠፊያ ላይ)
• ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ (ሴቶች አደባባይ ላይ)
• ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል (ሴቶች አደባባይ ላይ)
• ከ22 አደባባይ ወይም ዘሪሁን ህንፃ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ ላይ)
• ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ደንበል (ጋዜቦ አደባባይ ላይ)
• ከቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ ወደ ለገሃር መብራት (ቂርቆስ ቤ/ክርሰቲያን ነርክ ተራ ላይ)
• ከላንድ ማርክ ሆስፒታል መታጠፊያ ገነት ሆቴል ወይም ወደ ገነት መብራት (ላንድ ማርክ ሆስፒታል መስቀለኛ ላይ)
• ከጠማማ ፎቅ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጠማማ ፎቅ መስቀለኛ ላይ)
• ከኤዩ መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ሜክሲኮ ጥይት ፋብሪካ መስቀለኛ ላይ)
• ከከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ላይ)
• ከሠንጋ ተራ 40/60 ወደ ሠንጋ ተራ መብራት (ሠንጋ ተራ 40/60 መታጠፊያ ላይ)
• ከጎማ ቁጠባ መብራት ወደ ብ/ቲያትር (ጎማ ቁጠባ መብራት ላይ)
• ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ፖስታ ቤት መብራት (ሜትሮዎሎጂ መታጠፊያ ላይ)
• ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢምግሬሽን (ጥቁር አንበሳ ሼል ላይ)
• ከጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢሚግሬሽን (ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ላይ)
• ከአገር አስተዳደር መብራት ወደ ብሔራዊ ቲያትር (አገር አስተዳደር መብራት ላይ)
• ከንግድ ማተሚያ ወደ ኦርማ ጋራዥ (ንግድ ማተሚያ መስቀለኛ ላይ) መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
በተጨማሪም በተገለፁት መስመሮች ላይ መኪና ለአጭርም ይሁን ለረጅም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑን ዋና ጠቅላይ መምሪያው አስታውቋል።
ሕዝቡ ለጸጥታው ሥራ እያደረገ ላለው ቀና ትብብር ምስጋናውን አቅርቦ፤ አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥማቸው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተላልፏል።
#ethiopia #addisababa #police #streetrace #ebc

2 months ago
የመጀመሪያው የኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በባህርዳር ከተማ ሊካሄድ ነው
#ethiopia | የመጀመሪያው የኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር የፊታችን እሁድ ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ በደመቀ ሁኔታ እንደሚካሄድ ተነገረ።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በውድድሩ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ፣ የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ የቴክኒክ ባለሙያዎች ወደ ስፍራው በማቅናት አስፈላጊውን ዝግጅት እያከናወኑ እንደሚገኙ አስታውቋል።
ይህ የውድድር መድረክ በዋናነት አዳዲስ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራትና የውድድር እድሎችን ለመፍጠር ያለመ መሆኑም ተገልጿል።
በዚሁ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ላይ የግል ተሳታፊዎችን ጨምሮ ከ6 የተለያዩ ክለቦች የተውጣጡ 91 አትሌቶች እንደሚሳተፉ ታውቋል። በውድድሩ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ለሚያጠናቅቁ አትሌቶችም የገንዘብ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ተገልጿል።
ይህንን ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የውድድርና ተሳትፎ ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ጊዜ አድነው እና አቶ መሐሪ ነጋሽ በጋራ የሰጡት ሲሆን፣ ውድድሩ በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በቀጥታ ስርጭት ለተመልካች እንደሚተላለፍ ታውቋል።
#ethiopianathletics #bahirdar #streetrace #10krun #ethiopiansport #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments