የውጭ ሀገር ዜጎችን በመያዣነት ይዘው ገንዘብ የጠየቁ ወንጀል ፈፃሚዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
በኢትዮጵያ የስሪላንካ ኤምባሲ ተወካይ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ/ም ለስራ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሦስት የስሪላንካ ዜጎቹ እንደተሰወሩ እና ሲሪላንካ ከሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ተደውሎ እያንዳንዳቸው 30ሺ ዶላር እንዲከፍሉ መጠየቃቸውን ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ/ም ለቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ሪፖርት አደረጉ።
በአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ምክትል ዋና ጠቅላይ መምሪያ ወንጀል ፈፃሚዎቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል የክትትልና የምርመራ ቡድን በማዋቀር ወደ ስራ ገብቷል።
ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ ጉዳይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ባሰባሰበው መረጃ ሦስቱ ግለሰቦች በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2C- 40461 አ/አ በሆነች ሱዚኪ ዲዛየር መኪና ከኤርፖርት ተሳፍረው መሄዳቸው አረጋግጧል።
የክትትል ቡድኑ አባላት አሽከርካሪውን ጨምሮ ሁለት ኢትዮጵያውያንን እና አራት የፓኪስታን ዜግነት ያላቸውን ስድስት ወንጀል ፈፃሚዎች በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል፡፡
ወንጀል ፈፃሚዎቹ ሦስቱን የሲሪላንካ ዜጎች በሻሸመኔ ከተማ ወረዳ ቡቄ ቀበሌ 4 ልዩ ቦታው ደራርቱ ሆቴል ጀርባ አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ አንድ ክፍል ውስጥ ዘግተውባቸው እንደተገኙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቆ ምርመራውን አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል።
ወንጀል ፈፃሚዎቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተሰራው ስራ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ በኦሮሚያ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሻሸመኔ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንዲሁም የአዳማ ፈጣን መንገድ ኢንተርፕራይዝ ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጋቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ገልጾ ለተቋማቱ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
Addis Ababa police

8 days ago