የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኛዋን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል የተሰወረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ
የሰንዳፋ በኬ ከተማ ነዋሪ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሌልቱ ቅርንጫፍ ሠራተኛ የሆነችውን ወ/ሮ አዳነች ኩምሳ ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል የተሰወረው ፀጋዬ አሳልፈው ጎንጤ የተባለው ተጠርጣሪ በደብረ ብርሃን ከተማ በቁጥጥር ሥር ውሏል።
ሟች እና ተጠርጣሪ ታህሳስ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በምሽት በሆቴል ውስጥ ምግብ ሲመገቡ በመካከላቸው አለመግባት በመፈጠሩ ሟች ተጠርጣሪውን ጥላ በመሄዷ ተከትሏት ወደ መኪና ውስጥ ካስገባት በኋላ ''ጎማጣ" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሽጉጥ ትኩሶ ገድሏት ጥሎ በመጥፋቱ የሟች አስክሬን በዱር አራዊት ተበልቶ ጭንቅላቷ ብቻ መገኘቱን የፖሊስ የምርመራ መዝገብ ያመላክታል።
ተጠርጣሪው ወንጀሉን የፈጸመበትን መኪና እና ሽጉጥ በአሌልቱ ከተማ ጥሎ መሰወሩን የደረሰበት ፖሊስ በመኪናው ውስጥ የደም ዱካ እና ሽጉጡን እንደ ማስረጃ በመጠቀም ግለሰቡን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ከሌሎች የፀጥታና ደህንነት ኃይሎች እንዲሁም ከሰንዳፋ በኬ ከተማ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት ባደረገው ከፍተኛ ክትትል ተጠርጣሪው የተለያዩ ሐሰተኛ መታወቂያዎችን በማውጣት በደብረ ብርሃን፣ በከሚሴ፣ በሸዋ ሮቢትና በአጣዬ ከተሞች ውስጥ ሰላማዊ ሰው መስሎ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ሥር ሊያውል ችሏል።
ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ምርመራውን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ማንኛውንም ወንጀል ፈጽሞ ከፖሊስ ለመሰወር የሚሞክር ወንጀለኛ ከሕግ ማምለጥ እንደማይችል ገልጿል። ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ሥር ለማዋል በተደረገው ጠንካራ ክትትል ትብብር ላደረጉ ኣካላት በሙሉ ምስጋናውን አቅርቧል።
Ethiopian Federal police

3 months ago