Logo
FBC
እያንዳንዱ ወጣት በምርጫው በንቃት እንዲሳተፍ ፌዴሬሽኑ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) እያንዳንዱ ወጣት በነገው ዕለት በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት እንዲሳተፍ የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ጥሪ አቀረበ፡፡

ፌዴሬሽኑ ምርጫውን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ በርካታ ወጣቶች በእጩነት፣ በምርጫ ታዛቢነት እንዲሁም በመራጭነት በመመዝገብ በንቃት መሳተፋቸውን አስታውቋል፡፡

ከአጠቃላይ መራጮች ውስጥ ከ15 ሚሊየን በላይ ወጣቶች መሆናቸውን የገለጸው ፌዴሬሽኑ፥ ከተለያዩ የፖለቲካ ፖርቲዎች በእጩነት ከቀረቡት ውስጥ 40 በመቶ ያህሉ ወጣቶች ናቸው ብሏል፡፡

32 ሺህ 500 ታዛቢዎችን ማሰማራቱንና 20 ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መስራቱን አመልክቷል፡፡

ምርጫ ወጣቱ የራሱን ዕጣ በራሱ የሚወስንበት በመሆኑ ሁሉም ወጣት በነገው እለት ድምፅ እንዲሰጥ ፌዴሬሽኑ ጥሪ አቅርቧል።

በቤተልሄም መኳንንት
#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያትመርጣለች #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል #election #fanadigital #ethiopia #ethiopiavotes #democracy #fanatelevision

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.