2 months ago
IGAD Election Observation Mission Outlines Key Successes of Ethiopiau2019s 7th General Election
u200b#ethiopia #elections2026 #igadobservation #ebcdotstream ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
IGAD Election Observation Mission Outlines Key Successes of Ethiopia’s 7th General Election
#ethiopia #elections2026 #igadobservation #ebcdotstream
2 months ago
የኢጋድና የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ትዝብት ሪፖርታቸውን ዛሬ ረፋድ በቀጥታ ስርጭት ለዓለም ይፋ አድርገዋል። የኢጋድና አፍሪካ ኅብረትን ታዛቢነት እውቅና እሰጣለሁ ያለው የአውሮፓ ኅብረትም አዲስ መግለጫ ይዞ ብቅ ብሏል። #ethiopia #generalelection #igad #au
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
2 months ago
IGAD Congratulates Ethiopia on Peaceful and Orderly 7th General Election
#ethiopia #igad #ethiopianelection #democracy #stabilityandprogress
3 months ago
ኢጋድ የጋራ የውሃ ሀብቶችን ለትብብርና ለጋራ ብልጽግና ለማዋል ቁርጠኛ መሆኑን አስታወቀ
**************************
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) በቀጣናው የሚገኙ የጋራ የውሃ ሀብቶች የውጥረት ሳይሆን የትብብር ድልድይ እንዲሆኑ ከአባል ሀገራት ጋር በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገለጸ።
ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ውሃ ድንበር እንደማያውቅ ጠቅሶ፤ በኢጋድ ቀጣና ውስጥ የሚገኙ የውሃ ሀብቶች ማህበረሰቦችን፣ መተዳደሪያን፣ ስነ-ምህዳርንና ኢኮኖሚን የሚያስተሳስሩ ወሳኝ መሰረቶች መሆናቸውን አመልክቷል።
በቀጣናው የሚስተዋሉ ተደጋጋሚ የድርቅና የጎርፍ አደጋዎች፣ የአየር ንብረት ለውጥ ጫና እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የውሃ ፍላጎት ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ትብብርን አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንዳደረጉትም ተገልጿል።
ይህ ትብብር ለማህበረሰቦች ጽናት፣ ለቀጣናዊ ሰላም እና ለጋራ ብልጽግና ወሳኝ ሚና እንዳለው ኢጋድ አስገንዝቧል።
ተቋሙ በውይይት፣ በመረጃ ልውውጥ፣ በጋራ እቅድና በትብብር ማዕቀፎች አማካኝነት የጋራ የውሃ ሀብቶች ዘላቂ አስተዳደር እንዲጠናከር ከአባል ሀገራት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
ይህም ውሃ የውጥረት ምንጭ ከመሆን ይልቅ የትብብር ድልድይ እንዲሆን ለማስቻል ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
ኢጋድ በቀጣናዊ መፍትሄዎች ላይ ትኩረት በማድረግ፣ የጋራ የውሃ ሀብቶችን ወደ የጋራ እድሎች ለመለወጥ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በድጋሚ አረጋግጧል።
በላሉ ኢታላ
#igad #watercooperation #eastafrica #regionalintegration #watermanagement #peaceandprosperity

Sponsored by
Surafel
6 months ago
ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ እና የሱዳኑ የRSF መሪ ሄሜቲ በዩጋንዳ ተገናኝተው ተወያዩ
የዩጋንዳው መሪ ዩዌሪ ሙሴቬኒ የሱዳን ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች (RSF) መሪ ከሆኑት ጄነራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) ጋር በኢንቴቤ በሚገኘው የመንግሥት ቤተ መንግሥት ተገናኝተው መክረዋል።
ሙሴቬኒ በሱዳን ለሦስት ዓመታት ገደማ የዘለቀውንና አሰቃቂ ሰብአዊ ቀውስ ያስከተለውን ጦርነት በአስቸኳይ ለማቆም በጠረጴዛ ዙሪያ መወያየት ብቸኛው አማራጭ መሆኑን ገልጸዋል።
ጄነራል ሄሜቲ በሱዳን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ፣ በግጭቱ ምክንያት እየደረሰ ያለውን ሰብአዊ ቀውስ እና ጦርነቱን ለማቆም ያላቸውን ዝግጁነት ለሙሴቬኒ አስረድተዋል።
"ሱዳን አዲስ ምዕራፍ እንድትጀምርና ሰላም እንዲሰፍን ያለኝን ራዕይ ለፕሬዝዳንቱ አካፍያለሁ" ሲሉ በኤክስ (X) ገጻቸው አስፍረዋል።
ዩጋንዳ በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (IGAD) በኩል በሱዳን ሰላም እንዲመጣ ከሚጥሩ ሀገራት አንዷ ናት።
ይህ ስብሰባም በኢጋድ ጥላ ስር የሚደረገው የሰላም ጥረት አካል ተደርጎ ተወስዷል።
ይህ ጉብኝት ጄነራል ሄሜቲ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ውጭ ሀገር ካደረጓቸው ጉዞዎች አንዱ በመሆኑ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ትርጉም ተሰጥቶታል።
በሱዳን ጦር እና በRSF መካከል ያለው ግጭት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለስደትና ለረሃብ የዳረገ ሲሆን፣ እንዲህ ያሉ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች ግጭቱን ለማርገብ ተስፋ ይጣሉባቸዋል።
ምንጭ፦ The East African / AFP

አክሽን ፎር ዘ ኒዲ ኢን ኢትዮጵያ የምግብ ድጋፍ ፕሮጀክትን ይፋ አደረገ
#ethiopia | ድርጅቱ ከ8 ሺህ 700 በላይ ችግረኛ አባወራዎችን ለመደገፍ የሚያስችል የምግብ ድጋፍ ፕሮጀክትን በዛሬው እለት በኦሮሚያ ክልል በዳሌቲ ወረዳ አስጀምሯል።
በዛሬው እለት በተደረገው የፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ ከኪንግ ሰልማን የሰብአዊ እርዳታ እና የመርጃ ማእከል በተገኘ ድጋፍ ለችግረኛ አባወራዎች የዘይትና ዱቄት ድጋፍ የመስጠት መርሀገብርም ተካሄዷል።
ይህ የድጋፍ ፕሮጀክት በየአመቱ እንደሚካሄድና በቦረና ፣ በወሊሶና በሶማሌ ክልልም እንደሚካሄድ የአክሽን ፎር ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ ሳሊሁ ሱልጣን ቢሎ ገልጸዋል።
አቶ ሳሊሁ አክለውም ፕሮጀክቱ ለ5ተኛ ጊዜ የሚካሄድና 40 ሺህ የሚደርሱ ችግረኞችን ለማዳረስ ያለመ ነው ብለዋል።
አክሽን ፎር ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ አሁንም ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ስደተኞችን፣ ተፈናቃዮችን እና ሌሎች በጣም ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰቦችን እያገለገለ መሆኑን አቶ ሳሊሁ ሱልጣን ቢሎ ገልጸዋል።
ድርጅቱ አሁን ላይም ከተለያዩ የመንግስት ባለድርሻ አካላት ጋር ከ UN ኤጀንሲዎች፥ ከአለም አቀፍ እና ሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር በትብብር ዘርፈ ብዙ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ውስጥ እና በIGAD አባል ሀገራት ውሰጥ እያከናወነ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
አክሽን ፎር ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ (ANE) ላለፉት 13 ዓመታት ስደተኞችን፤ ተፈናቃዮችን እና በተለያየ ምክንያት የተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎችን ይገኛል።
ድርጅቱ በምግብና በውሃ፣ በመጠለያ እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ድጋፍ፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በአካባቢ ልማት እና በሌሎችም ተቀራራቢ ዘርፎች ድጋፍ አድርጓል።
አክሽን ፎር ዘ ኒዲ ኢን ኢትዮጵያ በሀገራችን የተለያዩ ክልሎቹ በለደተኞች ጉዳይ ላይ የሚሰራና እንዲሁም በርካታ የሰብዓዊና የልማት ሥራዎችን በማከናወን ይገኛል።
ድርጅቱ ከሲቪል ማሀበረሰብ ኤጀንሲ በቁጥር 2825 በኢትዮጵያ ነዋሪዋች የበጎ አድራጎት ስም የተመዘገበ ተቋም ነው፡፡
#getutemesgen #getu #ጌጡ

7 months ago
ኳታር እና ሶማሊያ፡ የባህረ ሰላጤው ንፋስ በአፍሪካ ቀንድ
በሞቃዲሹ ሰማይ ስር የነፈሰው የዲፕሎማሲ አየር መቀየር ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል። የአፍሪካ ቀንድ ልክ እንደ አንድ ግዙፍ የቼዝ ሰሌዳ ሆኗል። በሰሌዳው ላይ ያሉት ጠጠሮች ደግሞ የሀገራት ሉዓላዊነት፣ የወደብ ጥቅሞች እና የድሮ ቅያሜዎች ናቸው።
ትዕይንቱ የሚጀምረው በዶሃ ውብ አዳራሾች ውስጥ ነው። የሶማሊያ እና የኳታር የመከላከያ ሚኒስትሮች ብዕራቸውን አውጥተው ስምምነቱን ሲፈርሙ፣ ድርጊቱ ወታደራዊ ሰነድ መፈረም ብቻ አልነበረም፤ ለዓመታት በአቡ ዳቢ (UAE) እና በሞቃዲሹ መካከል የነበረውን "የጋብቻ ስምምነት" በይፋ የመፍታት የፍቺ ደብዳቤም ጭምር ነበር።
ሶማሊያ ለኤምሬትስ "ከእንግዲህ አንፈልግሽም!" ስትል በሩን ስትዘጋ፣ ኳታር ደግሞ በፈገግታ የጓሮ በሯን ከፍታ ተቀበለቻት። ይህ ታሪክ ግን የሁለት ሀገራት ወዳጅነት ብቻ አይደለም፤ የቀጠናው የሀይል ሚዛን የሚናጥበት፣ የጥንት ወዳጆች ጠላት፣ የጥንት ጠላቶች ደግሞ የልብ ወዳጅ የሚሆኑበት መድረክ ነው።
የፖለቲካ ትችት፡ የሉዓላዊነት ወይስ የጥገኝነት ሽግግር?
ይህ ስምምነት በገጽታው ላይ ለሶማሊያ የደህንነት ዋስትና የሚሰጥ ቢመስልም፣ በጥልቀት ሲመረመር ግን የሚከተሉት ወሳኝ ትችቶች ይነሱበታል።
1. "ከአሮጌው ጌታ ወደ አዲሱ ጌታ"
ሶማሊያ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስን "በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ ትገባለች" በሚል ስትከስ ቆይታለች። ሆኖም አሁን ያደረገችው ስምምነት ከጣልቃ ገብነት ነጻ ያደርጋታል ወይ? የሚለው ጥያቄ አጠራጣሪ ነው። ኳታር እና ቱርክ ለሶማሊያ የሚያደርጉት ድጋፍ "ከክፍያ ነጻ" አይደለም። ሶማሊያ የራሷን ራሱን የቻለ ጠንካራ መከላከያ ከመገንባት ይልቅ፣ የአረብ ሀገራት ሽኩቻ ሰለባ እየሆነች ትገኛለች። ትላንት በኤምሬትስ ስትሰለጥን የነበረችው ሶማሊያ፣ ዛሬ በኳታር እና በቱርክ ልትሰለጥን ነው። ይህ "የጥገኝነት ሽግግር" እንጂ የሉዓላዊነት ማረጋገጫ አይደለም።
2. የ"ባዕድ ሀገር የጦር ሜዳ" የመሆን አደጋ
የአፍሪካ ቀንድ የራሱ የሆኑ ውስብስብ ችግሮች (እንደ አል-ሸባብ እና ድንበር) አሉበት። ሶማሊያ የባህረ ሰላጤውን ሀገራት (ኳታር vs ኤምሬትስ) ቅራኔ ወደ ደጃፏ መጋበዟ፣ ሀገሪቱን የውጭ ሀይሎች የጥላቻ መላላኪያ (Proxy War) ሜዳ ያደርጋታል። ኳታር ሶማሊያን የምትረዳው ለሶማሊያ ህዝብ ካላት ፍቅር ብቻ ሳይሆን፣ የቀጠናውን ተቀናቃኞቿን ለመቀጥቀጥ በምትጠቀምበት ስልታዊ ቦታ ምክንያት ነው።
3. የኢትዮጵያ እና የግብፅ "ቀዝቃዛ ጦርነት" ማቀጣጠያ
ሶማሊያ ከኳታር ጋር ወታደራዊ ስምምነት አድርጋ ወደ ግብፅ መጠጋቷ፣ በናይል ውሃ ጉዳይ የተኳረፉትን ኢትዮጵያን እና ግብፅን ይበልጥ ያፋጥጣል። ሶማሊያ የራሷን የባህር በር ጉዳይ ለመከላከል ስትል፣ የአባይን ፖለቲካ ወደ ቀጠናው ማምጣቷ "እሳት በጭድ ላይ" የመጨመር ያህል አደገኛ ነው። ይህ አካሄድ የቀጠናውን ትብብር (IGAD) ሽባ ያደርገዋል።
4. የሶማሊላንድን ጉዳይ ማወሳሰብ
የሶማሊያ መንግስት በቁጣ ተነሳስቶ ከኤምሬትስ ጋር መጣላቱ፣ ኤምሬትስ በበቀል ስሜት ሶማሊላንድን ይበልጥ እንድትደግፍ እና እውቅና እንድትሰጥ በር ይከፍታል። ፖለቲካ በስሜት ሳይሆን በጥቅም የሚመራ መሆን ነበረበት። ሞቃዲሹ ሁሉንም በሮች ዘግታ በአንድ ወገን መወሰኗ፣ የዲፕሎማሲ አማራጮቿን አጥብቦባታል።
ማጠቃለያ
የሶማሊያ እና የኳታር ስምምነት በወታደራዊ ቋንቋ "ትብብር" ይባላል፤ በፖለቲካ ቋንቋ ግን "የጎራ መለየት" ነው። ሶማሊያ በኳታር፣ በቱርክ እና በግብፅ ጥላ ስር ለመጠለል ስትሞክር፣ በሌላ በኩል ኤምሬትስ፣ እስራኤል እና ሶማሊላንድ አዲስ ግንባር እየፈጠሩ ነው።
ታሪኩ የሚያሳየን በአፍሪካ ቀንድ ላይ ሰላም የሚመጣው ከባህረ ሰላጤው በሚመጡ "ነጻ ስጦታዎች" ሳይሆን፣ የቀጠናው ሀገራት (ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ጅቡቲ) በራሳቸው ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው የጋራ ጥቅማቸውን ማክበር ሲችሉ ብቻ ነው። ካልሆነ ግን፣ ሶማሊያ የአረብ ሀገራት ቼዝ የሚጫወቱባት "ሰሌዳ" ሆና ትቀጥላለች

"አክሽን ፎር ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ" (ANE) ያገኘው ዓለም አቀፍ እውቅና
ድርጅቱ በሰብዓዊ አገልግሎት ዘርፍ ላሳየው ብቃት ለ3ኛ ተከታታይ ጊዜ ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸንፏል
🏆 የሽልማቱ እና የስኬቱ ዋና ዋና ነጥቦች
የሽልማቱ መድረክ | World Sustainability Congress (ናይሮቢ፣ ታህሳስ 2025)
|የተሸለመበት ዘርፍ | Social Welfare (ማህበራዊ ደህንነት)
የስራ ዘመን | 13 ዓመታት
ተደራሽነት | ከ 4.5 ሚሊዮን በላይ ወገኖች
|ቅርንጫፎች | በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የሚገኙ 13 ቅርንጫፎች
🌍 የተቋሙ የትኩረት መስኮች (Key Focus Areas)
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳሊሁ ቢሎ እንደገለጹት ተቋሙ በሚከተሉት ዘርፎች የላቀ ድጋፍ አበርክቷል።
* መሰረታዊ ፍላጎት: መጠለያ፣ የምግብ ዋስትና እና ንጹህ የመጠጥ ውሃ (WASH)።
* ማህበራዊ አገልግሎት: ጤና፣ የአመጋገብ ስርዓት እና ትምህርት።
* አካባቢ ጥበቃ: የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የደን ልማት እና አማራጭ የኃይል አቅርቦት።
* ፈጣን ምላሽ: ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች በሚያጋጥሙበት ወቅት ለገጠራማ አካባቢዎች ፈጣን እርዳታ ማድረስ።
🚀 የ2026 ግቦች እና ጥሪ
1. አድማስን ማስፋት (Regional Expansion):
በ2026 በኢትዮጵያ ያለውን ስራ ከማጠናከር በተጨማሪ፤ Action for the Needy Africa (ANA) በተሰኘው ቀጣናዊ ተቋሙ በኩል በአፍሪካ ቀንድ እና በIGAD ቀጣና ስራውን በስፋት ይተገብራል።
2. የትብብር ጥሪ:
ይህንን ራዕይ ለማሳካት ለጋሾች፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች (UN) እና የዲያስፖራው ማህበረሰብ አብረው እንዲሰሩ ጥሪ ቀርቧል።

8 months ago
ሦስት ኢትዮጵያውያን ተሸላሚ ሆነዋል
#ethiopia | አዲስአበባ በተካሄደው የ 2025 IGAD Secretariat ሚዲያ አዋርድ ሦስት ኢትዮጵያውያን ተሸላሚ ሆነዋል ።
የምንወዳት የምናከብራት የሸገር FM አንጋፋ ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ሆናለች ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎቱ ጌትነት ሸንቁጥ በዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ : የኦቢኤኑ ሽመክት ለገሰ ደግሞ በአገርበቀል ቋንቋ ዘርፍ ተሸላሚ ሆነዋል ።
እንኳን ደስ አላችሁ !
#igadmediaaward2025
Three Ethiopians were award winners at the 2025 IGAD Secretariat Media Awards ceremony held here in Addis Ababa.
Our beloved and respected veteran Sheger FM journalist, Meaza Biru, received the Lifetime Achievement Award.
Getnet Shenkute of the Ethiopian News Agency (ENA) won in the Digital Media category, and Shimekit Legese of OBN (Oromia Broadcast Network) won in the Indigenous Language category.
📷 Abdi Ali Ibrahim

አንጋፋዋ ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን የህይወት ዘመን ጋዜጠኛ ሽልማት ተሰጣቸው
የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ራዲዮ መስራችና ስራ አስኪያጅ መዓዛ_ብሩ ሽልማቱ የተሰጣቸው የኢጋድ(IGAD) ዓመታዊ የሚዲያ ሽልማት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በተካሄደበት ወቅት ነው።
ሽልማቱንም ከኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስና ከኢጋድ ዋና ፀሀፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር ) ተቀብለዋል።
ኢጋድ በየዓመቱ በተለያዩ ዘርፎች የአባል ሀገራን የተመለከቱ ዘገባ የሰሩ ጋዜጠኞችን የሚሸልም ሲሆን ዘንድሮም የአየር ንብረት ለውጥን የተመለከቱ ዘገባዎች የሰሩ ጋዜጠኞች ስራ አወዳድሮ ሸልሟል።
Balageru Tv

9 months ago
በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባህር ቀጠና፣ ግብፅ የበላይነቷን ለማስጠበቅ "በጂኦፖለቲካዊ" (ወታደራዊና ፖለቲካዊ) ጣልቃገብነት ላይ ስታተኩር፣ ኢትዮጵያ በበኩሏ "በጂኦኢኮኖሚያዊ" (በልማት ኮሪደሮች እና በግንኙነት) ላይ ያተኮረ አዲስ አካሄድ እየተከተለች መሆኑን አንድ ትንታኔ አመለከተ።
በተመራማሪው ኑርዬ ያሲን የቀረበው ይህ ትንታኔ፣ የሁለቱን ሀገራት ፍጹም ተቃራኒ ስትራቴጂዎች ይተነትናል።
የግብፅ "የመክበብ" ስትራቴጂ
በተመራማሪው እይታ፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) መገንባት የግብፅን የቆየ የአባይ የበላይነት (Pax Arabica) ያቆመ ሲሆን፣ ግብፅ ይህን አዲስ እውነታ ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነችም።
በምላሹም ግብፅ የሚከተሉትን እርምጃዎች እየወሰደች ነው ተብሏል፦
# ኢትዮጵያን ማግለል፡ ቀይ ባህርን "ባለድርሻ" (littoral) እና "ባለድርሻ ያልሆኑ" (non-littoral) በማለት በመክፈል፣ ኢትዮጵያን ከቀጠናው የጸጥታ መዋቅር ለማስወጣት ትጥራለች።
# ወታደራዊ መገኘት፡ በኢትዮጵያ ዙሪያ ባሉ የአፍሪካ ቀይ ባህር ዳርቻዎች ላይ ወታደራዊ እና ሎጂስቲካዊ መሠረቶችን በመገንባት፣ የኢትዮጵያን የንግድ፣ የኃይል እና የዲጂታል መስመሮችን "ለመቁረጥ" (cut off) እና ለመቆጣጠር ትሰራለች።
በኢትዮጵያ እና በባህር ዳርቻ ሀገራት መካከል "ሽብልቅ ለመንዳት" (driving a wedge) ትሞክራለች። አላማውም፣ "የአስመራ የሶስትዮሽ ስምምነትን" (Asmara Tripartite Alliance) ዳግም በማንቀሳቀስ ኢትዮጵያን "ከሁሉም አቅጣጫ ለመክበብ" (encircle) የሚያስችል ቅንጅት መፍጠር ነው።
ትንታኔው ኢትዮጵያ የምትከተለው አካሄድ የተለየ መሆኑን ይጠቅሳል፦
ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት (ሶማሊያን ጨምሮ) ጋር በኢጋድ (IGAD) እና በአፍሪካ ህብረት (AU) መድረኮች በኩል ትብብርን ታስቀድማለች።
በኤርትራ "ቅስቀሳዎች" ፊት ኢትዮጵያ "ራስን የመግዛት" (restraint) እና "ውጥረትን የማርገብ" (de-escalation) ፖሊሲ እንደምትከተል ተገልጿል።
ኢትዮጵያ የባህር በር ብታጣም፣ የቀጠናው ጸጥታ "የማይነጣጠል" (indivisible security) እንደሆነ ታምናለች። ይህም ማለት፣ "የባህር ዳርቻ ሀገራት ጸጥታ፣ የሌሎች (የባህር በር የሌላቸው) ሀገራትን ጸጥታ አደጋ ላይ በሚጥል መልኩ ሊረጋገጥ አይችልም" የሚል መርህ ታራምዳለች።
ትንታኔው ሲያጠቃልል፣ "የአፍሪካ ቀንድ ለግብፅ ብቸኛ ፍላጎት ሊገዛ አይችልም" ያለ ሲሆን፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያን ተጋላጭነት እንዲረዳ እና ግብፅና ኤርትራ "ቀጠናውን የሚበታተነውን የተሳሳተ ስትራቴጂ" እንዲያቆሙ ማበረታታት እንዳለበት አሳስቧል።
seledadotio

ኢትዮጵያ የበጎችና ፍየሎች ደስታ መሰል በሽታ በመቆጣጠር ላይ ትገኛለች ተባለ
የበጎችና ፍየሎች ደስታ መሰል በሽታ በአብዛኛው የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ላይ ስለሚገኝ በሽታውን በ2030 ለማጥፋት በትብብር ሊሰራ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
የምስራቅ አፍሪካ በጎችና ፍየሎች ደስታ መሰል በሽታ መከላከልና ማጥፋት ፕሮግራም አስተባባሪ ዶክተር ውብሸት ዘውዴ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት የአፍሪካ ዜጎች በምግብ ራሳቸውን እንዲችሉና አጀንዳ 2063ን ለማሳካት የእንስሳት ሀብቱ ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።
በገዳይነቱ የሚታወቀዉ የበጎችና ፍየሎች ደስታ መሰል በሽታ ድንበር ዘለል በመሆኑ በ2030 በምስራቅ አፍሪካ በሽታውን ለማጥፋት ግብ ተጥሎ እየተሰራ መሆኑን ዶ/ር ውብሸት ገልጸዋል።
የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በተለይም ኢትዮጵያ የግዙፍ የእንስሳት ሀብት ባለቤት መሆኗን ጠቅሰው በእንስሳት ጤና ላይ በትብብር መሥራት እንደሚገባ አስተባባሪው ጠቁመዋል።
በሽታው በምስራቅ አፍሪካ ሁሉም ሀገራት ላይ እንደሚስተዋል አስተባባሪው ገልፀው እንደ ደቡብ ሱዳን ያሉ ሀገራት በአንደኛ ደረጃ፣ ኬንያ ደግሞ በ2ኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ ኢትዮጵያም ካሉት ሀገራት የተሻለ ስራን እየሰራች ያለች መሆኗን ተናግረዋል።
በዚህም በ3ኛ ደረጃ ማለትም በሽታውን በመቆጣጠር ላይ እንደምትገኝ የተገለፀ ሲሆን በሽታውን ለመከላከል እንስሳቱን የመከተብ ስራዎችን መስራቷ ተነግሯል።
የአፍሪካ ሕብረት ፣ የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት (IGAD) እና የምስራቅ አፍሪካ አገሮች የበጎችና ፍየሎች ደስታ መሰል በሽታን እ.ኤ.አ በ2030 ለማጥፋት በትብብር እየሰሩ ይገኛሉ ተብሏል ።
እንደዚሁም በኢጋድ አስተባባሪነት ድንበር ዘለል በሽታዎችን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ከጎረቤት ሀገራት ጋር በመተባበር እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች ለውጥ እያስመዘገቡ መሆናቸው ተገልጿል ።

Comments