2 days ago
የእንጦጦ-ቀጨኔ መድኃኔዓለም የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋ ተመርቋል።
22.25 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው ይህ ፕሮጀክት፣ የተጎዱ አካባቢዎችን ወደ ማራኪ እና የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚችሉ ለምለም አረንጓዴ ሥፍራዎች የቀየረ ነው።
የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ምሰሶዎች፦
ሥነ-ምህዳርን መልሶ ማቋቋም እና የከተማ ግብርና፦
ፕሮጀክቱ በባሕር ዛፍ ምክንያት የተጎዳ 36 ሄክታር መሬትን ጨምሮ፣ በአጠቃላይ 438 ሄክታር የተጎዳ መሬትን አክሞ ዳግም አቋቁሟል። በተጨማሪም የከተማ ግብርና እና ብዝሃ-ሕይወትን ለማጠናከር አዲስ የ9.5 ሄክታር የፍራፍሬ ፓርክ እና 210 ዘመናዊ የንብ ቀፎዎችን አካቷል።
የውሃ ማጣሪያ እና መሠረተ-ልማት፦
በእንጦጦ-ቀጨኔ ኮሪደር ላይ 39 የወንዝ መገደቢያዎችን እና ሦስት የወንዝ ውሃ ማጣሪያ ሥርዓቶችን በመገንባት የአካባቢ ጥበቃና ዘላቂነት እንዲጠናከር ተደርጓል።
የአረንጓዴ ትራንስፖርት አማራጮች እና ቱሪዝም ፦
አረንጓዴ የትራንስፖርት አማራጮችንና መዝናኛን በማስፋፋት፣ ፕሮጀክቱ 19.4 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገዶችን፣ 7.7 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መስመሮችን እና 4 ኪሎ ሜትር የተራራ መውጫ (የእግር ጉዞ) መንገዶችን ያካተተ ሲሆን፣ ይህም ጤናማ፣ ምቹ እና ንቁ ማኅበረሰብ ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
#pmoethiopia #ethiopiadelivers
8 days ago
አዲስ አበባ ባለፉት 5 ዓመታት የልማት አብዮት አካሂዳለች - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መዲናችን አዲስ አበባ ባለፉት 5 ዓመታት የልማት አብዮት አካሂዳለች አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
ከንቲባዋ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ በባለፉት 10 ቀናት ብቻ 11 ፕሮጀክቶችን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ብለዋል።
ለአብነትም ፦
1. በኢንዱስትሪ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ፤ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። ይህ ፓርክ ከ20 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል የሚፈጥር ነው።
2. የማህበራዊ ልማት (የመኖሪያ ቤቶች)፤ ሶስቱ የበጎነት መንደሮችን በአዲስ ከተማ፣ በኮልፌ ቀራንዮ እና የካ ክፍለ ከተሞች የተገነቡ የመኖርያ ቤቶች ለሀገር ባለውለታዎች፣ ለአቅመ ደካማዎች እና ለአካል ጉዳተኞች የማስተላለፍ ስራ ተሰርቷል፡፡
3. የመዝናኛ እና የህዝብ ፓርኮች ፤በአዲስ ከተማ (አስኮ አዲስ ሰፈር) በ30 ሺህ ካሬ ሜትር እና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ18 ሄክታር ቦታ ላይ የተገነቡ የወንዝ ዳርቻ እና የህዝብ መዝናኛ ፓርኮች ተመርቀዋል። እነዚህ ማዕከላት ህፃናትን፣ ወጣቶችን እና አረጋውያንን ያካተቱ፣ ማህበረሰቡ በጋራ የሚጠቀምባቸው ናቸው።
4. የኑሮ ውድነትን ለማቃለል የግብይት ማዕከላትን የማስፋት ስራ አካል የሆነው 7ኛው የለሚ ሁለገብ የገበያ ማዕከል፣ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል።
5. ዘመናዊ የገበያና የትራንስፖርት ማዕከል፤ አይነቱ የመጀመሪያ የሆነው የአድዋ የገበያ ማዕከል እና ዘመናዊ የትራንስፖርት ተርሚናል ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል። የዚህ ማዕከል ሱቆች እና ካፍቴሪያዎች ለፒያሳ ልማት ተነሺዎች በዕጣ ተላልፈዋል።
6. በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ3 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባውን ፣ 16 ሱቆችን እና 18 ሼዶችን የያዘ የተቀናጀ የከተማ ግብርና ማዕከል አገልግሎት ክፍት ተደርጓል ።
7. የስፖርት እና የወጣቶች ማዕከል፡ በቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የለሚ ኮሚኒቲ ስታዲየም፣ 5 ስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ 95 የህፃናት መጫወቻዎች፣ 6 የህፃናት ማቆያ (Daycare) ማዕከላት፣ ካፍቴሪያዎች እና አምፊ ቲያትሮችን ጨምሮ ለወጣቶች ተጠቃሚነት የሚያገለግሉ መሠረተ ልማቶችን አሟልቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
8. በልደታ ክ/ከተማ ለትውልድ ግንባታ መሰረት የሚጥሉ ሁለት ት/ቤቶች እና ሶስት የህፃናት ማቆያ ማእከል ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደረገዋል ።
9. የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከላት ተጠቃሚዎች ለነበሩ 400 ነዋሪዎቻችን መነሻ ካፒታልና የመስሪያ ቁሳቁስ በማሟሟላት ከተረጂነት ወደ የስራ እድል ተጠቃሚነት እንዲሸጋገሩ ተደርጓል።
10. 7ኛውን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት በላፍቶ ክፍለ ከተማ ተመርቋል።
11. ዘመናዊ የጤና አገልግሎት ፤ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የሆነው፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂ የተደገፈው እና እጅግ ዘመናዊ የሆነው የላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለምርቃት በቅቷል።
አንዳንዶች እነዚህ ፕሮጀክቶች ለምርጫ ተብሎ እንደተከናወነ ያነሳሉ ያሉት ከንቲባዋ፤ ነገር ግን እውነታው ቀድሞ ያልተሰራ ለምርጫም ሊደርስ አይችልም፤ ተሰርቶም ለምርጫ ከዋለ ዋናው ህዝቡና ሀገር ተጠቃሚ ይሁን እንጂ ችግር የለውም ብለዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
የቦረና ብሔራዊ ፓርክ
ይህ ተፈጥሯዊ ይዘቱ የተጠበቀ ስፍራ ለዱር እንስሳት ግዙፍ መጠለያ ከመሆኑም ባለፈ ለቱሪዝም ዘርፍ ሰፊ ዕድል የሚከፍት ነው።
ተፈጥሯዊ ሥነ-ምህዳርን ጠብቆ የያዘና ፣ የአጥቢ እንስሳት ዝርያዎች፣ ለተለያዩ የወፍ ዓይነቶች እንዲሁም የዕፅዋት ዓይነቶች እንደ ዋነኛ መኖሪያነት ያገለግላል።
8 days ago
ጤና ሚኒስቴር ከጣሊያን ሀገር የመጡ በጎ ፈቃደኛ ሐኪሞች ላከናወኑት የሕፃናት ነጻ የልብ ቀዶ ሕክምና ምስጋናና ዕውቅና ሰጠ
የጤና ሚኒስቴር በኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ አማካይነት ከጣልያን ሀገር የመጡ በጎ ፈቃደኛ ባለሙያዎች፣ ከኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል የሕክምና ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት 80 የልብ ሕሙማን ሕፃናት በሁለት ጊዜ ምልልስ
በ15 ቀናት ጊዜያት ውስጥ የነጻ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት
በመስጠታቸው የምስጋናና የእውቅና ሠርተፊኬት ሰጠ።
ትላንት ግንቦት 18/2018 ዓ.ም በአራዳ ፓርክ በተከናወነው መርሐግብር ባለሙያዎቹ አገልግሎቱን የሰጡት በሁለት ዙር ተልእኮ መኾኑ የተጠቀሰ ሲሆን 48 ሕፃናት በአዲስ አበባ ኢትዮ-ኢስታንቡል ሆስፒታል፣ 9 ሕፃናት በጂግጂጋ እንዲሁም 23 ሕፃናት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል (በጎንደር ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠ) የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መኾናቸው ተነግሯል።
በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ለተሰጠው አገልግሎት በጤና ሚኒስቴር፣ በራሳቸው ስምና ከሁሉም በላይ በዚህ ሕክምና ተጠቃሚ በሆነው ማህበረሰብ ስም ላቅ ያለ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ይህ መልካም ተግባር ቀጣይነት እንዲኖረው የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል። በቀጣይም ለሚከናወኑ መሰል ተግባራት ጤና ሚኒስቴርም አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ለዚህ ዓላማ መሳካት አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት በተለይም ለኸርት ቱ ኸርት ችልድረን ኤይድ በገንዘብ እና በቴክኒክ ላበረከተው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ይህ የበጎ ፈቃድ አገልግከሎት በ45 ቀናት ለ175 ሕፃናት የልብ ቀዶ ሕክምና ለመስጠት በጤና ሚኒስቴር፣ በኸርት ቱ ኸርት ችልድረንስ ኤይድ እና በተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት መካከል የተደረገ ስምምነት አካል ነው።
አቶ ብርሃን ተድላ የኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ በበኩላቸው የጤና ሚኒስቴር የተከናወነውን የበጎ ተግባር ትልቅ ዋጋ መስጠቱ ሌሎችም ተመሳሳይ ተልእኮዎች በአርአያነት የሚታይ መሆኑን ጠቅሰዋል። ኽርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ በገባው ቃል መሰረት ስራዎቹ በአጭር ጊዜያት እንደሚያጠናቅቅም አቶ ብርሃን ተናግረዋል።
በአጠቃላይ ለስራው የስምምነቱ አካል የኾኑ የመንግስት፣ የግል ሆስፒታሎችና የጤና ተቋማት ያበረከቱት አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛ መኾኑን በማስታወስ የስራው አጠቃላይ ሪፖርት እኤአ ጁን 10 ከተጠናቀቀ በኋላ ሌላ የምስጋና መርሐግብር እንደሚኖር ዶ/ር አስቻለው ወርቁ የጤና ሚኒስቴር አማካሪ አረጋግጠዋል።

#ethiopia | የጤና ሚኒስቴር በኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ አማካይነት ከጣልያን ሀገር የመጡ በጎ ፈቃደኛ ባለሙያዎች፣ ከኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል የሕክምና ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት 80 የልብ ሕሙማን ሕፃናት በሁለት ጊዜ ምልልስ በ15 ቀናት ጊዜያት ውስጥ የነጻ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት በመስጠታቸው የምስጋናና የእውቅና ሠርተፊኬት ሰጠ።

Sponsored by
Surafel
10 days ago
11 days ago
ሻምፒዮኑ አርሰናል ዋንጫውን ተረከበ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ22 ዓመታት በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን የሆነው አርሰናል በዛሬው ዕለት ዋንጫውን ተረክቧል፡፡
ባለፉት ሦስት የውድድር ዓመታት በሊጉ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው አርሰናል÷ በዚህ ዓመት አንድ ጨዋታ እየቀረው ሻምፒዮን መሆኑን ማረጋገጡ ይታወሳል፡፡
በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመራው የሰሜን ለንደኑ ክለብ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ የሊጉን የመጨረሻ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ከክሪስታል ፓላስ ጋር በማድረግ 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
በጨዋታው የአርሰናልን ግቦች ጄሱስ እና ማዱኬ ሲያስቆጥሩ ማቴታ የክሪስታል ፓላስን ግብ ከመረብ አሳርፏል።
በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የቡድን ግንባታ ሒደት ከ22 ዓመታት በኋላ ከሊጉ ዋንጫ ጋር የተገናኙት መድፈኞቹ ዛሬ ምሽት በሴልኸረስት ፓርክ ነው ዋንጫውን በክብር የተቀበሉት፡፡

መድፈኞቹ የክብር ዋንጫቸውን ዛሬ ያነሳሉ፤ ሻምፒዮኑ አርሰናል ወደ ክሪስታል ፓላስ ሜዳ ያቀናል
***********************
መድፈኞቹ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን በበላይነት ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ፣ የድል ምልክት የሆነውን የሊጉን ባለወርቅ ዋንጫ ዛሬ በደመቀ ሁኔታ ይረከባሉ።
አርሰናል የሊጉን ዋንጫ አስቀድሞ ማረጋገጥ ቢችልም፣ የስኬቱ መሀንዲስ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ትኩረት ግን አሁንም ጨዋታው ላይ ብቻ በመሆኑ ቡድኑ ዛሬ ወደ ሴልኸርስት ፓርክ አቅንቶ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ምሽት 12:00 ሰዓት ላይ ፍልሚያውን ያደርጋል።
ተጫዋቾቹን በስታዲየም በአካል ለማየት በጉጉት ለሚጠብቁ ደጋፊዎች ዛሬ ሜዳው በደስታ ማዕበል እንደሚሞላ ይጠበቃል።
የቡድኑ የልብ ትርታ የሆነው ጠንካራው ተከላካይ ዊሊያም ሳሊባ ስለ አስደናቂው ስኬት ሲናገር፣ ከመጋቢት ወር ጀምሮ እንደሚያሸንፉ ይሰማው እንደነበርና በተለይም ከኤቨርተን ጨዋታ በኋላ ነገሩ ፍንትው ብሎ እንደታየው ገልጿል።
ሳሊባ አክሎም “አሁን እኛ ሻምፒዮኖች ነን፤ ቀጣዩ ኢላማችን ደግሞ ፒኤስጂን አሸንፈን ታሪክ መስራት ነው” በማለት ቡድኑ ለአውሮፓ መድረክ ያለውን ከፍተኛ መነሳሳትና መተማመን ለደጋፊዎቹ አብስሯል።
የመድፈኞቹ ስኬት ከተቀናቃኞቻቸው ዘንድም ትልቅ አድናቆትን እያስገኘ ይገኛል። የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ለአርሰናል ያላቸውን ክብር ሲገልጹ፣ በእንግሊዝ ሊግ ማሸነፍ እጅግ ከባድ መሆኑን ጠቅሰው አርሰናል ድንቅ ስራ መሥራቱን መስክረዋል።
#arsenal #champions #premierleague #arteta #saliba #coyg

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኢራን ከ100 በላይ ሙሽሮች በአንድ ላይ የተዳሩበት ‹‹ፒንክ›› የሰርግ ስነስርአት ተከናወነ፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት በኢራን ዋና ከተማ ቴሄራን ለየት ያለ የሰርግ ስነስርአት መከናወኑን ዘታይምስ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ እንደዘገባው ይህንን የሰርግ ስነስርአት ያዘጋጀው የኢራን አብዮታዊ ዘብ ነው፡፡
ሙሽሮቹ በሙሉ ከእስራኤልና ከአሜሪካ ጋር በሚደረገው ጦርነት ተሰልፈው ለአገራቸው መስዋእትነትን ለመክፈል ፈቃደኛ የሆኑ መሆናቸውን የጠቀሰው ዘገባው የሰርግ ስነስርአቱ አስገራሚ ነገሮች እንደታዩበት አስታውቋል፡፡ ሁሉም ሙሽራና ሙሽሪት ፒንክ ቀለም ባላቸው ጂፕ መኪናዎች ውስጥ ተቀምጠው በከተማው ውስጥ ሲንሸራሸሩ የታዩ ሲሆን መኪናዎቹ ዲኮር የተደረጉትም በፒንክ አበባዎችና ፊኛዎች ነበር፡፡
በሁሉም የመኪናዎቹ የፊት መስታወት ላይ የቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላ ሆሚኒና የልጃቸው የአሁኑ ጠቅላይ መሪ ፎቶዎች እንዲሰቀሉ መደረጋቸውን ያስታወቀው ዘገባው የአባትና ልጅ ምስል በፒንክ ቀለም የተሰራ መሆኑን አስረድቷል፡፡ ሙሽሮቹ በከተማው ውስጥ በሚዘዋወሩበት ወቅት በፒንክ ቀለም የተዘጋጁ የተለያዩ ጦር መሳሪያዎችን ይዘውም ታይተዋል፡፡ የሰርግ ስነስርአቱ 110 ጥንዶች በተገኙበት በቴሄራን በሚገኘው ፈርዶስ ፓርክ ውስጥ በደመቀ ስነስርአት በሚከናወንበት ወቅትም ፒንክ ቀለማት ብዙ ቦታዎች ላይ ጥቅም ላይ መዋላቸውን ዘገባው አስታውቋል፡፡

u12e8u1229u12cbu1295u12f3 u12f6u12adu1270u122eu127d u1260u12a0u122bu12f3 u1353u122du12ad u12ebu12f0u1228u1309u1275 u1309u1265u129du1275
#aradapark #addisababa #rwandainethiopia ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
የሩዋንዳ ዶክተሮች በአራዳ ፓርክ ያደረጉት ጉብኝት
#aradapark #addisababa #rwandainethiopia
11 days ago
ሻምፒዮኑ አርሰናል ዋንጫውን የሚረከብበት ዕለት…
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ22 ዓመታት በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን የሆነው አርሰናል በዛሬው ዕለት ዋንጫውን ይረከባል፡፡
ባለፉት ሦስት የውድድር ዓመታት በሊጉ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው አርሰናል በዚህ ዓመት አንድ ጨዋታ እየቀረው ሻምፒዮን መሆኑን ማረጋገጡ ይታወሳል፡፡
በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመራው የሰሜን ለንደኑ ክለብ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ የሊጉን የመጨረሻ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ያደርጋል፡፡
አስቀድሞ የወርቅ ጓንቱን ያሸነፈው ስፔናዊው የአርሰናል ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ በጨዋታው ግቡን ሳያስደፍር ለመውጣት ወደ ሜዳ ይገባል።
ዴቪድ ራያ በጨዋታው ግብ የማይቆጠርበት ከሆነ በአንድ የውድድር ዓመት በሊጉ ለአርሰናል 20 ጨዋታዎች ላይ ግብ ያልተቆጠረበት ቀዳሚው ግብ ጠባቂ ይሆናል፡፡
በወድድር ዓመቱ እስካሁን በሊጉ በ19 ጨዋታዎች ግብ ያልተቆጠረበት ዴቪድ ራያ በክለቡ ታሪክ ከመድፈኞቹ የቀድሞ ግብ ጠባቂ ዳቪድ ሲማን ጋር ክብረወሰን መጋራቱ ይታወሳል፡፡
በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የቡድን ግንባታ ሒደት ከ22 ዓመታት በኋላ ከሊጉ ዋንጫ ጋር የተገናኙት መድፈኞቹ ዛሬ ምሽት በሴልኸረስት ፓርክ ዋንጫውን በክብር ይቀበላሉ፡፡

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ18 ሄክታር ላይ የተገነባው የወንዝ ዳርቻ እና ፓርክ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
***************
የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ18 ሄክታር ቦታ ላይ የተገነባው የወንዝ ዳርቻ እና ፓርክ ትላንት ምሽት መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
ፓርኩ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶችን፣ ድልድዮችን፣ ስድስት የተለያዩ የስፖርት ማዘውተሪያዎችን እንዲሁም ሰባት የህፃናት መጫወቻዎችን ያካተተ ነው።
ከዚህ በተጨማሪም ሰፊ አረንጓዴ ስፍራና የአትክልት አጸዶች፣ ስድስት ካፌቴሪያዎች፣ ሦስት አንፊ ቲያትሮች፣ ልዩ ልዩ መናፈሻዎች እና በርካታ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ መሰረተ ልማቶች ተገንብተውበታል።
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባስተላለፉት መልዕክት ይህ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ እውን የሆነው ግዙፍ ፕሮጀክት በሁሉም ደረጃ የሚካሄዱ የልማት ስራዎችን አካታች እና ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል እንደ ፍላጎቱ የሚጠቀምባቸው እንዲሆኑ የተቀመጠው አቅጣጫ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለፓርኩ መሳካት በጋራ በመሆን ድንቅ ስራ ላከናወኑት ለለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አመራሮች እና ነዋሪዎች የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
#addisababa #lemikura #greendevelopment #riversidepark #ethiopianbroadcastingcorporation

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ ከባህር ማዶ መጥቶ እንደ ግብጹ "የአባይ ውሃ ዘመዳችን" መሀመድ ሳላህ የጎል መረብን ያንቀጠቀጠ የለም፤ 193 የማይታመኑ ጎሎች! ታሪኩ የሚጀምረው ነሐሴ 12 ቀን 2017 ነው። ሊቨርፑል ዋትፎርድን ሲገጥም፣ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ አዲስ ፈራሚውን «ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንኳን በደህና መጣህ!» በሚል አጭርና ግልጽ መልዕክት ወደ ሜዳ ሰደዱት። ያኔ የተጠነሰሰው አስፈሪው የሳላህ፣ ማኔ እና ፊርሚኖ የአጥቂ መስመር ጥምረት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላን ጭምር «ያናውጡኛል፣ አደገኞች ናቸው» እስኪል ድረስ ዓለምን ጉድ አሰኝቷል።
ሳላህ እና ማኔ የቅርብ ጓደኛሞች ባይሆኑም፣ በመካከላቸው የነበረው ጤናማ ውድድር እና ፊርሚኖ በሁለቱ መሀል የሚነሳውን እሳት በማጥፋት የተጫወተው ሚና፣ የሊቨርፑልን የድል ጉዞ የጀርባ አጥንት ሆኗል። የቡድኑ አጋሮቹ «ለእግር ኳስ የተፈጠረ» ብለው የሚመሰክሩለት ሳላህ፣ በምሳሌነት የሚመራ [ይላል] እና ለዝርዝር ነገሮች ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ ጽኑ ተዋጊ ነው። ዋትፎርድን 5 ለ 0 ባሸነፉበት ጨዋታ ላይ፣ ጨዋታው እንደተጠናቀቀ ግብ ጠባቂውን ቤን ፎስተርን «ፍጹም ቅጣት ምት ቢሆን ኖሮ ወደየትኛው አቅጣጫ ትዘል ነበር?» ብሎ መጠየቁ ለስራው ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።
በአንፊልድ ቆይታው አንዳንዴ ተስፋ መቁረጥ እና ቁጣ ታይቶበት ያውቃል። ባለፈው ታህሳስ ከዋና አሰልጣኙ አርኔ ስሎት ጋር የነበረው አለመግባባት አሁን ላለው ስንብት መነሻ ሆኗል። ይህ የውድድር ዘመን ለሊቨርፑል ስብስብ እጅግ ከባድ የነበረ ሲሆን፣ የቡድን አጋሩ ዲዮጎ ጆታ ህይወት ማለፍ ሳላህን ክፉኛ ጎድቶታል። «ከእረፍት በኋላ ወደ ሊቨርፑል መመለስ እንደዚህ ያስፈራኛል ብዬ አስቤ አውቅም» ሲል ሀዘኑን ገልጾ፣ በአንፊልድ ፊት እምባውን በማፍሰስ ሰብዓዊነቱን አሳይቷል።
በሜዳ ላይ ግን ሳላህ ከተፈጥሮ በላይ ነበር። በአንፊልድ የመጀመሪያ የውድድር ዘመኑ 58 የጎል ተሳትፎዎችን (በየ 71 ደቂቃው አንድ ጎል ላይ ተሳትፎ) በማድረግ ሜሲ እና ሮናልዶ ካሉበት ደረጃ ደርሷል። ማድሪድ ላይ ቶተንሃምን አሸንፈው የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ሲያነሱ፣ በጉዲሰን ፓርክ ኤቨርተን ላይ የፑስካስ አዋርድ ያሸነፈባትን ጎል ሲያገባ፣ እና በኦልድ ትራፎርድ ማንችስተር ዩናይትድ ላይ ያሳየው ጀብዱ... ትዝታዎቹ ማለቂያ የላቸውም። የሲቲው አይሜሪክ ላፖርት ጭምር «ሳላህ በእኛ ላይ ሁልጊዜ እሳት ይተፋ ነበር፤ ለመከላከል ከገጠሙኝ ከባድ ተጫዋቾች አንዱ ነው» በማለት ይመሰክራል።
ሸሚዙን አውልቆ ደስታውን ሲገልጽም ሆነ በሱጁድ ፈጣሪውን ሲያመሰግን፣ የሳላህ ምስሎች መቼም አይረሱም። የቀድሞው አምበል ስቲቨን ጀራርድ «ቁጥሮቹ፣ ዋንጫዎቹ እና የገነባው ባህል የራሳቸው ታሪክ ይናገራሉ። መሀመድ ሳላህ በሁላችንም ዘንድ የተወደደ የክለቡ እውነተኛ ጀግና ነው» ሲል አወድሶታል። ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድም ለክለቡ ያላቸውን ዋጋ ሲገልጽ ሳላህን እና ጀራርድን በእኩልነት አንደኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧቸዋል።
የ2024-25 የውድድር ዘመን ሊቨርፑል 20ኛውን የሊግ ዋንጫ ሲያነሳ፣ ሳላህ ከፍተኛ ጎል እና አሲስት በማድረግ በእንግሊዝ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ አሳርፏል። አሁን ግን ሁሉም ነገር ፍጻሜ አለው። ከግብጽ የናይል ዴልታ የተነሳው የዚህ ድንቅ ተዋጊ ጉዞ፣ በሜርሲሳይድ አንፊልድ ላይ የማይረሳ ታሪክ ጽፎ ወደሚቀጥለው ምዕራፍ ተሸጋግሯል። የርገን ክሎፕ እንዳሉት፣ «ሲመጣ ሰዎች ምን እንደሚያስቡ ሳይሆን፣ ሲሄድ ምን እንደሚያስቡ ማወቁ ነው ትልቁ ነገር»። መሀመድ ሳላህ... ለአንፊልድ ትክክለኛው ተዋጊ፣ በትክክለኛው ጊዜ የመጣው ጀግና!

12 days ago
የቡኖ ማላ ዓለም አቀፍ ኤክስፖ በዲላ ከተማ በደመቀ ሁኔታ መካሄድ ጀመረ
#ethiopia | በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቡኖ ማላ ዓለም አቀፍ ኤክስፖ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ በሚገኘው የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በይፋ ተከፍቷል።
ይህ ታላቅ መድረክ የጌዴኦን የቡናና የሥጋ ምርት ሀብት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ፣ የዲላን የኢንቨስትመንት ሳቢነት ለማሳደግ እንዲሁም በየአካባቢው የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለዓለም ማህበረሰብ በሰፊው ለማስተዋወቅ ያለመ ነው።
ትናንት በተከናወነው የዝግጅቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የፌደራል እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የጌዴኦ ዞንና የዲላ ከተማ አመራሮች እንዲሁም በርካታ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ኤክስፖው ዛሬም በተለያዩ ባለድርሻ አካላትና ጎብኚዎች መጎብኘቱን የሚቀጥል ሲሆን፣ ልዩ ልዩ የኪነ-ጥበብ እና የመዝናኛ ዝግጅቶችን በማካተት እስከ አመሻሹ ድረስ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ታውቋል።
#bunomalaexpo #dilla #gedeo #southethiopia #coffeeexpo #tourismethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ቡኖ ማላ ዓለም አቀፍ ኤክስፖ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ በዲላ ኢንዱስትሪያል ፖርክ ተከፈተ።
የጌዴኦን የቡና እና ሥጋ ሀብት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ፣ የዲላን የኢንቨስትመንት የሥበት ማዕከልነት ከፍ ለማድረግና የቱሪዝም መዳረሻዎቹን ለዓለም በስፋት ለማሳየት ያለመው ይህ ግዙፍ መድረክ ዛሬ ከቀኑ 9:00 በዲላ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሲከፈት የፌደራል እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች የጌዴኦ ዞንና የዲላ ከተማ አመራሮች እና በርካታ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ኤክስፖው በነገው እለትም በበርካታ ባለድርሻ አካላት እየተጎበኘ በኪነ-ጥበባትና መዝናኛ ዝግጅቶች እየተዋዛ እስከ አመሻሽ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

13 days ago
ከአዲስ አበባ እምብርት ሌላ አዲስ ድንቅ ውበት! አዲሱ ኢኮ ፓርክን ጎብኝተውታል? #addisecopark #addisababa #beautifuladdis #addiscorridor
14 days ago
ከዚህ ቀደም በተለያዩ ሀገራት አይተን የተመኘናቸውን ነገሮች ከአሰብነው በላይ ማሳካት ችለናል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
*******************
በአዲስ አበባ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለበርካታ ዓመታት የቆሻሻ መጣያ የነበረና ያለ አግባብ ተይዞ የቆየ ስፍራ ወደ ዘመናዊ የጋራ መገልገያ ኢኮ ፓርክ በመቀየር ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት ተደርጓል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜና በጥራት ተጠናቅቆ ለውጤት በመብቃቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፤ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ሀገራት የተለያዩ የልማት ሥራዎችን በመመልከት እኛም እንዲህ ባደረግን የሚል ምኞት እንደነበር አንስተዋል።
አሁን ላይ ግን ኢትዮጵያ የራሷን ከተሞች በላቀ ደረጃ በማልማት ላይ መሆኗን አክለዋል።
ታታሪ ሕዝብ፣ ለም መሬትና ያልተጠቀምንበት ሰፊ ሀብት አለን ያሉት ከንቲባዋ፤ በልማት ሥራዎች ሀገራችን አሁን ላይ ከሌሎች ሀገራት የተሻሉ ውጤቶችን እያስመዘገበች መሆኗን ተናግረዋል።
ኢኮ ፓርኩ በውስጡ ፋውንቴይን፣ የእግር ኳስ ሜዳ፣ የህጻናት መጫወቻ፣ አምፊ ቲያትር፣ ዘመናዊ ካፍቴሪያ፣ ሱቆች፣ የጁስ ባር፣ ፓርኪንግ፣ ዘመናዊ ሻወር እና መጸዳጃ ቤት እንዲሁም የእግር ጉዞ የሚደረግበት ሰፊ መንገድ ተሟልተውለት በጥራት መገንባቱን ገልጸዋል።
ይህ ፕሮጀክት የትውልድ ግንባታ አካል መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይ የመክፈል አቅም የሌላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችና ሕፃናት በእኩልነት ስሜት የሚዝናኑበት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
ቀደም ሲል ቦታው የቆሻሻ መጣያና ለጎርፍ አደጋ የተጋለጠ እንደነበር አንስተው፤ አሁን ግን ለአእምሮ ምግብ የሚሆን ጤናማ አካባቢ መፈጠሩን ተናግረዋል።
ነዋሪዎች ይህን የጋራ ሀብት እንዲንከባከቡና እንዲጠብቁ አደራ ብለው፤ ለፕሮጀክቱ መሳካት ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ የክፍለ ከተማው አመራሮችና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል።
በቢታኒያ ሲሳይ
#ethiopia #addisababa #addisecopark #ebc

u12a8u1295u1272u1263 u12a0u12f3u1290u127d u12a0u1264u1264 u1260u12a0u12f2u1235 u12a2u12ae u1353u122du12ad u121du122du1243u1275 u1225u1290-u1225u122du12d3u1275 u120bu12ed u12ebu1235u1270u120bu1208u1349u1275 u1218u120du12d5u12adu1275 #adanechabiebie #addisecopark #addisababa #ethiopia ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ ኢኮ ፓርክ ምርቃት ሥነ-ሥርዓት ላይ ያስተላለፉት መልዕክት #adanechabiebie #addisecopark #addisababa #ethiopia
Sponsored by
Surafel
14 days ago
የምርጫ ጸሎት እና ዱአ ሊደረግ ነው!
የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ መጪውን ምርጫ አስመልክቶ፣ ሰባት የሃይማኖት ተቋማት የሚሳተፉበት የጸሎት መርሀ ግብር ማዘገጀቱን መሆኑን አስታውቋል፡፡
ግንቦት 16/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ፓርክ በሚካሄው የምርጫ ጸሎት መርሀግብር ላይ ሰባት የሃይማኖት ተቋማት የሃይማኖት አባቶች ባሉበት እንደሚከናወን ተገልጿል። በተመሳሳይ ሰዓት በሁሉም ክልሎች የጸሎት ሥነ ሥርዓት እንደሚከናወንም የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ቀሲስ ታጋይ ገልጸዋል።
የአደባባይ ጸሎቱ በዋናነት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ በማሰብ የሚካሄድ መሆኑም የጉባኤው ጸሐፊ ገልጸዋል። ጉባኤው ያዘጋጀው መርሀግብር ከ1 ሺሕ በላይ ዜጎች የሚሳተፉበት የጸሎት እና የዱአ መርሃግብር መሆኑን ተናግረዋል፡፡(አንድ አፍታ)
seledadotio

ምርጫ ሰላም እንዲሰፍን ከ1 ሺሕ በላይ ዜጎች የሚሳተፉበት አገር አቀፍ የጋራ ጸሎት ሊደረግ ነው
#fastmereja I የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መጪውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ፣ ከ1 ሺሕ በላይ ዜጎችና የሰባት የሃይማኖት ተቋማት አባቶች የሚሳተፉበት ታላቅ የጋራ የጸሎት እና የዱአ መርሃግብር ማዘጋጀቱን በይፋ አስታወቀ።
ይህ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው የአደባባይ የጸሎት ስነ-ስርዓት በቀጣዩ እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ በአራዳ ፓርክ በድምቀት እንደሚከናወን ተገልጿል። የአደባባይ ጸሎቱ ዋና ዓላማ መጪው አገራዊ ምርጫ ሁከትና ግጭት ተወግዶለት በሰላማዊ ድባብ እንዲጠናቀቅ ለመማጸን መሆኑን የጉባኤው ጠቅላይ ጸሐፊ ቀሲስ ታጋይ ታደሰ አስታውቀዋል። ከዋናው ማዕከል በተጨማሪ በተመሳሳይ ሰዓት በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች የሚገኙ የሃይማኖት አባቶችና ምዕመናን በየአካባቢያቸው በጋራ ጸሎት እንደሚያደርጉ ተረጋግጧል።
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መሰል አገራዊ አጀንዳዎች እና የጋራ ስጋቶች ሲደቀኑ ምዕመናንን ያስተባበረ የጋራ ጸሎት ሲያደርግ የመጀመሪያው አይደለም። ቀደም ሲል የኮቪድ-19 ወረርሺኝ አገርን በፈተነበት ወቅት ተመሳሳይ የአደባባይ የጸሎት መርሃግብር በማዘጋጀት ህዝቡን ለፈጣሪው እንዲጮህ ማድረጉ ይታወሳል። ጉባኤው አገራዊ አንድነትን ለመጠበቅና ሰላምን ለማስፈን መሰል የጋራ የጸሎት መርሐግብሮችን በተከታታይ ማድረጉን እንደሚቀጥልበትም ጠቅላይ ጸሐፊው አክለው ገልጸዋል ሲል ሀገሬ ቲቪ ነው የዘገበው።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሀገር አቀፍ የሰላምና የጸሎት መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ሊያካሂድ ነው
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሀገር አቀፍ የሰላምና የጸሎት መርሃ ግብር ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ አራዳ ፓርክ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሀገር አቀፍ የሰላምና የጸሎት መርሃ ግብርን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የጉባኤው ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በመግለጫቸው፣ ሀገር አቀፍ የሰላምና የአብሮነት የጸሎት መርሃ ግብሩ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በጋራ የሚሳተፉበት ነው።
በመርሐ ግብሩ የሰላም እና የአብሮነት መልዕክቶችን ማስተላለፍ፣ የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ፣እንዲሁም በህዝቦች መካከል ሰላምና አብሮነትን ማጠናከርና ለሀገር መቆም ዋነኛ ትኩረቱ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ኅብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ በማግኘት በመርሐ ግብሩ ላይ እንዲሳተፍ የመገናኛ ብዙኃን ኋላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ግንቦት 16 ቀን 2018 ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚካሄደው መርሐ ግበር የጋራ እሴቶችና አንድነትን የሚያጎሉ መልዕክቶች እንደሚተላለፉም ጠቅሰዋል፡፡
ለሀገር ዘላቂ ሰላም፣ለሕዝቦች መተሳሰብ እና አብሮነት መጽናት በጋራ ጸሎት እንደሚካሄድም ተናግረዋል፡፡
ጉባኤው ከዚህ ቀደምም በተለያዩ ወቅቶች መሰል ሀገር አቀፍ የጸሎት መርሐ ግብሮችን ሲያካሂድ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡
በዚህ መርሃ ግብር ላይ የሁሉም የጉባኤው አባል ቤተ-እምነት ተቋማት የሃይማኖት መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉ ጠቅሰዋል።
#ኢዜአ

በአስኮ ሁለገብ የሕዝብ መዝናኛ ፓርክ በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመረቀ
#fastmereja I የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ የሕዝብ መዝናኛና አረንጓዴ ስፍራዎችን ለማስፋፋት የጀመረውን ፕሮጀክት አካል በማድረግ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ያስገነባውን ፓርክ ዛሬ በይፋ አስመርቋል።
ይህ በአስኮ አዲስ ሰፈር የተገነባው ሁለገብ ፓርክ፣ ከዚህ ቀደም የአካባቢውን ነዋሪዎች ለአደጋና ለብክለት ይዳርግ ከነበረ የቆሻሻ መጣያነት ወደ ንጹህና መንፈስን የሚያድስ ስፍራነት የተቀየረ የልማት ፕሮጀክት መሆኑ ተገልጿል።
ፓርኩ የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት ፍላጎት ለማሟላት ተገቢው ጥራት ተሰጥቶት የተገነባ ሲሆን፣ በውስጡ በርካታ ዘመናዊ የአገልግሎት መስጫዎችን አካቷል።
ከእነዚህም መካከል ውብ የውሃ ፏፏቴ (ፋውንቴይን)፣ መደበኛ የእግር ኳስ ሜዳ፣ የሕፃናት መጫወቻ ስፍራዎች፣ የባህልና የኪነጥበብ ዝግጅቶች ማቅረቢያ አምፊ ቲያትር፣ ዘመናዊ ካፌዎች፣ የጁስ ባሮችና የተለያዩ ሱቆች ይገኙበታል። በተጨማሪም ሰፊ መኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ)፣ ንጽህናቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የሻወርና የመጸዳጃ ቤት አገልግሎቶች እንዲሁም ነዋሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴና የእግር ጉዞ የሚያደርጉባቸው ሰፋፊ መንገዶች ተሟልተውለታል።
የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፓርኩን በይፋ ለሕዝብ ክፍት ባደረጉበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና መላው የከተማዋ ማኅበረሰብ ይህንን ከፍተኛ ወጪና እሴት የተጨመረበትን ሁለገብ መዝናኛ ፓርክ በአግባቡ እንዲጠቀሙበትና የጋራ ንብረታቸው አድርገው እንዲንከባከቡት አደራ ብለዋል።

ኢትዮጵያ፡ የዓለም ቀጣዩ የቱሪዝም መናገሻ
**************************
የቀደሙ አባቶቻችን ክብር የትውልድ ኩራት ነው፡፡ የዛሬው ትጋት ደግሞ የነገው መተኪያ የሌለው ቅርስ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የሥልጣኔ ማዕዘን፣ የሰው ዘር በኩር መገኛና የታሪክ ማኅደር መሆኗን ዓለም አውቆት፣ እኛም ደግመን ደጋግመን ተርከነው የኖርነው እውነት ነው።
ሆኖም ግን "ያለፈው ታሪክ ለዛሬ ስንቅ እንጂ መኖሪያ አይሆንም" እንደሚባለው በትናንት ታሪክ ማማ ላይ ብቻ ተቀምጦ መኖር የጉዞ መዳረሻን አያሰፋም።
ዛሬ ሀገራችን ኢትዮጵያ የታሪኳን አቧራ አራግፋ፣ የተፈጥሮ ዝናዋን በሥራ ጥበብና በፈጠራ አድሳ የቱሪዝም ተስፋዋ እንደ አዲስ ፋክቶ የሚታይበት የትንሳኤ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች።
ትናንት በሙዚየሞችና በጥንታውያን ገዳማት ብቻ ዓይኑን ጥሎብን የነበረው ዓለም ዛሬ በጉልበትና በእውቀት በለሙት አዳዲስ መዳረሻዎቻችን ሳቢያ ቀልቡን ወደ እኛ መልሷል።
ይህ የቱሪዝም ሽግግር ለሀገራችን የኢኮኖሚ ሞተር ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያዊነትን አዲስ ከፍታ ለዓለም የምናሳይበት የገጽታ ግንባታችን አውራ መንገድ ሆኗል። "ጉልበት ካለ ድንጋይም ይፈጫል፤ እውቀት ካለ ምድርም ይለማል" ነውና የኢትዮጵያ የቱሪዝም ጉዞ ከነበረበት የቆመና ታሪክን ብቻ ከመተረክ ወጥቶ ወደ ተንቀሳቃሽ ልማት ተሸጋግሯል። በዚሁ እውነት መሠረት፣ የገበታ ለሸገር ፕሮጀክቶች አዲስ አበባን ከኮንክሪት ጫካነትና ከትካዜ ድባብ አውጥተው ወደ አረንጓዴ፣ ሕያውና ሳቢ የቱሪስት ማዕከልነት ቀይሯታል።
ይህ ስኬት ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ሳይወሰን ወደ ክልሎች ተሻጋግሮ የተፈጥሮ ጸጋዎችን በዕውቀትና በሥነ-ሕንጻ ጥበብ በመደመር እሳቤ በማልማት ለዓለም ዕይታ ማብቃት ተችሏል። እነዚህ ልማቶች መሬት ላይ ያለውን እምቅ ሀብት ከዘመኑ የፈጠራ ጥበብ ጋር በማቀናጀት የነገውን ትውልድ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የብልጽግና ተምሳሌቶች ናቸው።
ከዚህም ባሻገር አሁን ላይ በአዲስ ጉልበት እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት የከተሞቻችንን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ፣ የቱሪዝም ኢንዱስትሪው ዋነኛ ማነቆ የነበረውን የመሰረተ ልማት ምቾት እጥረት በዘላቂነት የፈታ ታላቅ ሀገራዊ ሥራ ነው።
"መንገድ ካለ አገር አለ" እንዲሉ ጽዱና ሰፋፊ መንገዶች፣ ማራኪ የእግር ጉዞ ትራኮችና ማራኪ የፓርክ አገልግሎቶች ቱሪስቶች በሀገራችን የሚቆዩበትን ጊዜ እንዲያራዝሙና በቆይታቸውም የልብ እርካታን እንዲያገኙ የሚያስችሉ የለውጥ አውታሮች ሆነዋል። ውበትና ጥራት፣ ምቾትና ደህንነት ሲደመሩ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ እያደረጓት ነው። ለዚህም በቅርቡ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ የዲጂታል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች አዲስ አበባ በመገኘት መደነቃቸውን በተለያዩ መንገዶች ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም የቱሪዝም ልማት ለእኛ ቁሳዊ ገቢ ብቻ ሳይሆን ዘርፈ-ብዙ ፋይዳ ያለው የስትራቴጂ ዘርፍ ነው። በአንድ በኩል፣ የውጭ ምንዛሬን በማስገኘትና ለሚሊዮን ወጣቶች የሥራ ዕድልን በሰፊው በመክፈት የኢኮኖሚው የጀርባ አጥንት ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያ ካላት የዲጂታል አቅምና ቴክኖሎጂ ጋር ተዳምሮ፣ ሀገራችንን የዓለም የሥራ፣ የጉባኤና የዕረፍት መዳረሻ በማድረግ የሀገርን ገጽታ በአዲስ መልክ እየገነባ ይገኛል።
ሲጠቃላል የኢትዮጵያ ቱሪዝም ትንሳኤ የመንግሥት የፖሊሲ ውጤት ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱ ዜጋና የዘርፉ ባለሙያ የጋራ ጥረትና የቅንጅት ፍሬ ነው። "ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲሉ ነባሩን ጥንታዊ ቅርስ ከአዲሱ የፈጠራ ስራ ጋር ደምረን፣ ኢትዮጵያን የዓለም የቱሪዝም ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ የምናደርገው ጉዞ አሁን ካለንበት ከፍታ በላይ እንደሚሻገር ቅንጣት ታህል ጥርጥር የለንም። እናም እያንዳንዱ ዜጋ ሀገሩን በመወከል ይህንን ታላቅ ሀገራዊ ትርክትና የልማት ፍሰት በዓለም አደባባይ ማስተጋባትና ማሳወቅ ይጠበቅበታል።
የሀገራችንን አዲስ ትንሳኤ በጋራ እናብስር።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

15 days ago
የኢትዮጸጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የጸሎት እና የአብሮነት መርሐግብር ግንቦት 16 በአራዳ ፓርክ ያካሂዳል #prayerandsolidarity #aradapark #ethiopiancouncilofreligions #unityindiversity #peaceforethiopia
16 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) እስኪ ያንተን የሰዓት እጅ ወደኋላ አሽከርክረው፤ አርሰን ቬንገር በስታዲየሙ መሀል ቆመው፣ ቲየሪ ኦነሪ መረቡን ሲቀደው፣ ፓትሪክ ቪዬራ መሀል ሜዳውን ሲገዛው እና ያ የማይበገረው የ"ኢንቪንሲብልስ" ስብስብ ወርቃማውን ዋንጫ ወደ ሰማይ ሲሰቅለው የነበረው ያ ድንቅ ዘመን! ያኔ 2003/04 ላይ ነበር። ከዚያ በኋላ ግን በመድፈኞቹ ቤት ዘመኑ የረሃብ፣ የናፍቆት እና የእንባ ሆነ። ያ ሁሉ ስቃይ፣ ያ ሁሉ መከራ ግን ዛሬ ማክሰኞ ምሽት አበቃለት!
ትዕይንቱ የተደገሰው በለንደን ሳይሆን በቪታሊቲ ስታዲየም ነበር። ማንቸስተር ሲቲ ዋንጫውን ከአርሰናል እጅ ለመንጠቅ የመጨረሻ የተስፋ ፍርሃቱን ይዞ ወደ ቦርማውዝ አቅንቶ ነበር። ሆኖም ግን የፔፕ ጋርዲዮላ ማሽን በቦርማውዝ ብረት ለበስ መከላከያ ፊት ተሰባበረ። ጨዋታው 1 ለ 1 በሆነ እኩል ውጤት ፍጻሜውን ሲያገኝ፣ ሰማያዊዎቹ የለንደኑን ንጉሥ ማሳደድ የማይችሉበት የነጥብ እርቀት ላይ መውደቃቸውን አረጋገጡ። በዚያችው ቅጽበት የለንደን ሰማይ በቀይና በነጭ ርችቶች ደመቀ፤ አርሰናል ከ22 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢንግሊሽ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑ በይፋ ታወጀ!
ይህ ዋንጫ ዝም ብሎ የመጣ አልነበረም። ለአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ እና ለልጆቹ ፍጹም የእሳት እራት የመሆን ያህል ከባድ ፈተና የተሻገሩበት ነው። በዘንድሮው የውድድር ዘመን አብዛኛውን ጊዜ የሊጉን አናት ተቆጣጥረውት የነበረ ቢሆንም፣ በሚያዝያ ወር ግን ያ የለመዱት የፍርሃት ጥላ ዳግም አጥልቶባቸው ነበር። ማንቸስተር ሲቲ እንደ ከርከሮ ከበስተጀርባቸው ይተነፍስባቸው ጀመር። ይባስ ብሎ በኢቲሃድ ስታዲየም 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በሲቲ ሲሸነፉ፣ ብዙዎች "ታሪኩ ተደገመ፣ አርሰናል ዘንድሮም ዋንጫውን አሳልፎ ሰጠ" ብለው ፈርደውባቸው ነበር።
ነገር ግን የዘንድሮው ስብስብ የተለየ ብረት የተገነባ ነበር! ከተሸነፉበት ማግስት ጀምሮ እንደ ቆሰለ አንበሳ አገገሙ፤ አንዳችም ነጥብ ሳይጥሉ እስከ መጨረሻው ተዋጉ። ያንን የጋርዲዮላን አስፈሪ ሰራዊት አስከብበው በመያዝ፣ ከስድስት ዓመታት የዋንጫ ድርቅ በኋላ የክለቡን ታላቅ ታሪክ መልሰው ጻፉት። ይህ ድል ለአርሰናል በታሪኩ 14ኛው የሊግ ዋንጫው ሲሆን፣ ለአርቴታ ደግሞ በኤምሬትስ ስታዲየም ሁለተኛው ትልቅ የስኬት ማማው ነው።
አሁን መድፈኞቹ በ37 ጨዋታዎች 82 ነጥብ ሰብስበው የሊጉን አክሊል ደፍተዋል። ሰንጠረዡ እንደሚያሳየው ሲቲ በ78 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ እና አስቶን ቪላ ደግሞ ተከታዮቹን የቻምፒዮንስ ሊግ ቦታዎች ይዘዋል። አርሰናል ይህንን ታላቅ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ እሁድ ዕለት በሴልኸርስት ፓርክ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ከሚያደርገው የዓመቱ የመጨረሻ ጨዋታ በኋላ በይፋ ርክክብ ያደርጋል።
ነገር ግን ታሪኩ በዚህ አያበቃም! ለሰሜን ለንደኑ ክለብ ከፊት ለፊቱ ሌላ ታላቅ የክብር ማዕድ ተደግሶለታል። መድፈኞቹ በክለቡ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ለመጨበጥ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም (ማለትም ቅዳሜ ሜይ 30) በቡዳፔስት ከፈረንሳዩ ሀብታም ክለብ ፒኤስጂ ጋር ለፍጻሜ ይፋለማሉ።
አርሰናል አሁን አምኗል፤ ደጋፊዎቹም በደስታ ሰክረዋል። የ22 ዓመታት የበርሃ ጉዞ አብቅቶ፣ መድፈኞቹ ወደ ተስፋይቱ ምድር በክብር ገብተዋል!
ሊሊ ሞገስ - የዘ-ሐበሻ ስፖርት አዘጋጅ

ከ80 በላይ አገራትና ተቋማት ተወካዮች የኢትዮጵያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ጎበኙ
*******************
የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት እና የዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ተወካዮች ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን ጎብኝተዋል።
ልዑካኑ የኮሙኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (ICT) ፓርክን፣ የቦሌ ለሚ እና የቂሊንጦ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ጨምሮ የተለያዩ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን ነው የጎበኙት።
ከ80 በላይ ከሚሆኑ ኤምባሲዎች የተውጣጡ አምባሳደሮች፣ የሚሲዮን መሪዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም የዓለም አቀፍ የልማት አጋር ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተ የመስክ ምልከታ እየተካሄደ ይገኛል።
ጉብኝቱ ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ያለችበትን ደረጃ ለማሳወቅና ያሉትን እምቅ ሀብቶች ለማስተዋወቅ ያለመ ነው።
በዚህ ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሮዛ የሩቅነህ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዘርፏን ይበልጥ እያጠናከረች ትገኛለች።
ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ባከናወናቸው ስራዎች ቀዳሚ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት (FDI) ማዕከል መሆን መቻሏንም አምባሳደሯ ገልጸዋል።
በአባዲ ወይና
Ethiopian Broadcasting Corporation #

17 days ago
የመዲናችን የብልጽግና ጉዞ የሚለካው ያልተጠቀምንባቸውን ሀብቶች የልማት ማዕከል በማድረግ ጭምር ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመዲናችን የብልጽግና ጉዞ የሚለካው ያልተጠቀምንባቸውን ሀብቶች የልማት ማዕከል በማድረግ ጭምር ነው አሉ።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ‘ገላን ጉራ የብልጽግና አሻራ!’ በሚል ባስተላለፉት መልዕክት፤ የዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የመዲናችን የብልጽግና ጉዞ ስፋትና ጥልቀት የሚለካው የከተማዋን እምብርት በማስዋብ ብቻ ሳይሆን፣ ትናንት በአግባቡ ያልተጠቀምንባቸውን ሀብትና አካባቢዎችን ዓይናችንን ገለጥ በማድረግ ተመልክተን የልማትና የዕድገት ማዕከል በማድረግም ጭምር ነው ብለዋል።
ከ5 ዓመት በፊት ምንም የሚታይ መሠረተ ልማት ያልነበረው የገላን ጉራ አካባቢ ዛሬ ላይ የታሪክ ምዕራፉ ተቀይሮ የከተማችንን ሁለንተናዊ የልማት ከፍታና መዋቅራዊ ሽግግር የሚያሳይ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ መስተጋብር ማዕከል ሆኗል ሲሉ ገልጸዋል።
ዛሬ በዚህ ስፍራ ያረፈው አሻራችን የኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ ሳይሆን የአካባቢውን ገጽታ እና የነዋሪዎቹን ሕይወት ሙሉ በሙሉ ከስር መሠረቱ የለወጠ ነው በማለት ተናግረዋል።
ለአብነትም:-
1. በአዲስ አበባ የመጀርያው እና ትልቁ ባለ 325 ሜትር ርዝመት እና 60 ሜትር ስፉት ዘመናዊ ድልድይ፣
2. 21.73 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው (ቃሊቲ ቀለበት -ቱሉዲምቱ እና ቃሊቲ ቀለበት - ቂሊንጦ አደባባይ) የኢትዮጵያ የንግድ ኮሪደርን ያሳለጠ እና ቀጥታ ከአየር መንገድ ካርጎ የሚያገናኝ ዘመናዊ የመንገድ መሠረተ ልማት፣
3. የከተማችንን የመኖርያ ቤት አቅርቦት ችግር ለማቃለል አዲስ ከተማን የመገንባት ያህል የሆነ 60 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ፣
4. ከካዛንቺስ አካባቢ ለልማት ለተነሱ ነዋሪዎቻችን የገነባነው ምቹና የተቀናጀ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር የሚገኝበት፣
5. የኅብረተሰባችንን ጤና በላቀ ደረጃ ለመጠበቅ በከተማችን በትልቅነቱ ቀዳሚ የሆነው የገላን ትሯማ ሆስፒታል ግንባታ፣
6. በአካባቢው ለዚሁ ልማት ለእርሻ ሲጠቀሙበት የነበረውን መሬት ለለቀቁልን አርሶ አደሮች የተቀናጀ ዘመናዊ የግብርና ልቀት ማዕከል ግንባታ፣
7. መንፈስን የሚያድሱ ሰፋፊ አረንጓዴ ስፍራዎች እና ፓርኮች እንዲሁም
8. የስፖርት ማዘውተርያዎችና የልጆች መጫወቻዎች፣ ለእናቶች ሰፊ የስራ ዕድል የሚፈጥር የእንጀራ ፉብሪካ ግንባታ እና የመሳሰሉት የብልፅግና አሻራዎች ደምቀው አካባቢውን ከመሐል ከተማ የበለጠ ተመራጭ አድርገውታል ብለዋል በመልዕክታቸው።

18 days ago
የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማፋጠን የአምራች ዘርፉን አቅም ለማሳደግ ትልቅ መሠረት እየጣሉ ያሉት የኢንዱስትሪ ፓርኮቻችን
************
እያደገ በመጣው የኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የኢንዱስትሪ ፓርኮችና የልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ሚና በዋናነት ተጠቃሽ ነው።
ሀገራችን በአሁኑ ወቅት ሁሉንም ዓይነት ኢንቨስትመንት ተቀብለው ማስተናገድ የሚችሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት ባለሃብቶችን ተቀብላ በማስተናገድ ላይ ትገኛለች።
እነዚህ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በተለይም ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለሚደረገው ሽግግር ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።
አሁን ባለው ሁኔታ የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ምርቶቻቸውን በዋናነት ለዓለም ገበያ እንዲያቀርቡ ይበረታታሉ።
በዚሁ መሠረት እንደ ጨርቃ ጨርቅ፣ አልባሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ያሉ ምርቶችን ለዓለም ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ በማምጣት ላይ ይገኛሉ።
እነዚህ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ከኢኮኖሚ ምንጭነታቸው ባሻገር ለበርካታ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችና ባለሙያዎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸውን በተግባር አሳይተዋል።
በፓርኮቹ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የሀገር ውስጥ የሰው ኃይልን በስፋት የሚጠቀሙ በመሆናቸው፣ ወጣቱ ትውልድ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀምንና የላቀ የኢንዱስትሪ አመራር ክህሎትን በቀጥታ እንዲቀስም ምቹ መድረክ ፈጥረውለታል።
ይህም የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማፋጠን የአምራች ዘርፉን ሀገራዊ አቅም ለማሳደግ ትልቅ መሠረት እየጣለ ይገኛል።
ትናንት በይፋ የተመረቀው የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክም የኢትዮጵያን ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ ለዓለም ይበልጥ ተደራሽ የሚያደርግ ነው።
ከተመሠረተ 11 ዓመታትን ብቻ ያስቆጠረው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ እንደ ቻይና ያሉ ሀገራትን ተሞክሮ በመቀመር በመላው ሀገራችን ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ 14 ልዩ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ገንብቶ በማስተዳደር ላይ ይገኛል።
በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #manufacturing #industrialparks #specialeconomiczones #ebc