Logo
EBC
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ18 ሄክታር ላይ የተገነባው የወንዝ ዳርቻ እና ፓርክ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
***************

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ18 ሄክታር ቦታ ላይ የተገነባው የወንዝ ዳርቻ እና ፓርክ ትላንት ምሽት መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።

ፓርኩ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶችን፣ ድልድዮችን፣ ስድስት የተለያዩ የስፖርት ማዘውተሪያዎችን እንዲሁም ሰባት የህፃናት መጫወቻዎችን ያካተተ ነው።

ከዚህ በተጨማሪም ሰፊ አረንጓዴ ስፍራና የአትክልት አጸዶች፣ ስድስት ካፌቴሪያዎች፣ ሦስት አንፊ ቲያትሮች፣ ልዩ ልዩ መናፈሻዎች እና በርካታ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ መሰረተ ልማቶች ተገንብተውበታል።

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባስተላለፉት መልዕክት ይህ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ እውን የሆነው ግዙፍ ፕሮጀክት በሁሉም ደረጃ የሚካሄዱ የልማት ስራዎችን አካታች እና ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል እንደ ፍላጎቱ የሚጠቀምባቸው እንዲሆኑ የተቀመጠው አቅጣጫ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለፓርኩ መሳካት በጋራ በመሆን ድንቅ ስራ ላከናወኑት ለለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አመራሮች እና ነዋሪዎች የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
#addisababa #lemikura #greendevelopment #riversidepark #ethiopianbroadcastingcorporation

11 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.