10 days ago
የኢትዮጵያ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እመርታ
****************
ኢትዮጵያ ግብርና መር ኢኮኖሚዋን ወደ ማኑፋክቸሪንግ እና ኢንዱስትሪ ለማሸጋገር በምታደርገው ጥረት፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ማሳደጓ ጠንካራ መዋቅራዊ መደላድል እየፈጠረ ይገኛል።
በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ማዕቀፍ የተተገበሩት ፖሊሲዎች የፓርኮቹን አስተዳደር ወደ ግል ዘርፉ በማሸጋገር የሀገራችንን የኢንዱስትሪ መዋቅር ሙሉ በሙሉ እየቀየሩት ነው።
ይህ ታሪካዊ ሽግግር በተለይም አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በመሳብ ረገድ አስደናቂ ውጤት አስመዝግቧል።
በማሳያነትም በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት ብቻ ከ750 ሚሊዮን ዶላር በላይ የመነሻ ካፒታል ያስመዘገቡ 166 አዳዲስ ባለሀብቶች ወደ ዘርፉ ተቀላቅለዋል።
ይበልጥ ተስፋ የሚሰጠው ደግሞ ከእነዚህ ውስጥ 84 በመቶ የሚሆኑት የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች መሆናቸው ነው። ይህ አዲሱ የኢኮኖሚ ሪፎርም የፈጠረውን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና አቅም በግልጽ የሚያሳይ ነው።
ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖቹ በሥራ ዕድል ፈጠራ በኩል የዜጎችን በተለይም የወጣት ሴቶችን ሕይወት በተጨባጭ እየቀየሩ ነው። በመላው ሀገራችን በሚገኙ ፓርኮች ውስጥ ከ100 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቀጥተኛና ቋሚ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።
በኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ትክክለኛ የኢንዱስትሪ ግብዓት ትስስር በመፍጠር የአርሶ አደሩን ምርት ከፋብሪካዎች ጋር በቀጥታ ማስተሳሰር ተችሏል። እስካሁን ባለው ሂደት ከ100 ሺህ በላይ አምራቾች እና አርሶ አደሮች ከትላልቅ ገዢዎች ጋር በቀጥታ ተገናኝተዋል።
በዚህም በአርሶ አደሮች እና በፋብሪካዎች መካከል ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የንግድ ግብይት መፈጸሙ፣ የኢንዱስትሪው ትስስር ምን ያህል ወደ ታችኛው የኅብረተሰብ ክፍል እንደወረደ ያመላክታል።
የውጭ ምንዛሬን በማመንጨት እና የገቢ ምርቶችን በመተካት በኩል የተመዘገቡት ስኬቶች የኢትዮጵያን የማክሮ-ኢኮኖሚ መረጋጋት በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ።
በ2018 በጀት ዓመት ፓርኮቹ ከወጪ ንግድ 266.9 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት በታሪካቸው ከፍተኛ የተባለ ውጤት አስመዝግበዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ከ26.7 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን የገቢ ምርቶች በሀገር ውስጥ በመተካት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወደ ውጭ እንዳይወጣ ታድገዋል።
ይህ በፓርኮች የታየው ስኬት በሀገር አቀፍ ደረጃ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስተባባሪነት እየተተገበረ ካለው "ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ ጋር ተጣምሮ ታላቅ ሀገራዊ ውጤት አምጥቷል።
ንቅናቄው የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ዕድገት ከ4.8 በመቶ ወደ 13 በመቶ ያሳደገው ሲሆን፣ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ የገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት አስችሏል።
ለእነዚህ ተጨባጭ ለውጦች እና ስኬቶች በዋናነት በምክንያትነት የሚጠቀሰው በቅርቡ የፀደቀው የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አዋጅ እና መንግሥት ያቀረባቸው ሰፊ ማበረታቻዎች ናቸው።
አዲሱ የሕግ ማዕቀፍ ፓርኮቹን በጨርቃጨርቅ ምርት ላይ ብቻ ከነበረ ጥገኝነት አውጥቶ ግብርናን፣ ሳይንስን እና የሎጂስቲክስ አገልግሎትን እንዲያካትቱ አድርጓል።
ከዚህም በተጨማሪ የጉምሩክ ቀረጥ ነፃ መብቶች፣ የዜሮ ምጣኔ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ለኤክስፖርት አምራቾች የተሰጡ የአምስት ዓመት የግብር እፎይታዎች፣ እንዲሁም የውጭ ሀገር ባንኮች በዞኖቹ ውስጥ በነፃነት እንዲሠሩ መፈቀዱ ዘርፉን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ አድርጎታል።
የጥራት፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የሠራተኞች ደህንነት (ISO) ደረጃዎችን ያካተተ የተቀናጀ የአመራር ሥርዓት መዘርጋቱም የኢትዮጵያን የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ዕድገት ቀጣይነት የሚያረጋግጥ ጽኑ መሠረት ነው።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #industrialparks #specialeconomiczones #investinethiopia #ethiopiatamirt

3 months ago
የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማፋጠን የአምራች ዘርፉን አቅም ለማሳደግ ትልቅ መሠረት እየጣሉ ያሉት የኢንዱስትሪ ፓርኮቻችን
************
እያደገ በመጣው የኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የኢንዱስትሪ ፓርኮችና የልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ሚና በዋናነት ተጠቃሽ ነው።
ሀገራችን በአሁኑ ወቅት ሁሉንም ዓይነት ኢንቨስትመንት ተቀብለው ማስተናገድ የሚችሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት ባለሃብቶችን ተቀብላ በማስተናገድ ላይ ትገኛለች።
እነዚህ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በተለይም ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለሚደረገው ሽግግር ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።
አሁን ባለው ሁኔታ የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ምርቶቻቸውን በዋናነት ለዓለም ገበያ እንዲያቀርቡ ይበረታታሉ።
በዚሁ መሠረት እንደ ጨርቃ ጨርቅ፣ አልባሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ያሉ ምርቶችን ለዓለም ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ በማምጣት ላይ ይገኛሉ።
እነዚህ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ከኢኮኖሚ ምንጭነታቸው ባሻገር ለበርካታ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችና ባለሙያዎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸውን በተግባር አሳይተዋል።
በፓርኮቹ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የሀገር ውስጥ የሰው ኃይልን በስፋት የሚጠቀሙ በመሆናቸው፣ ወጣቱ ትውልድ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀምንና የላቀ የኢንዱስትሪ አመራር ክህሎትን በቀጥታ እንዲቀስም ምቹ መድረክ ፈጥረውለታል።
ይህም የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማፋጠን የአምራች ዘርፉን ሀገራዊ አቅም ለማሳደግ ትልቅ መሠረት እየጣለ ይገኛል።
ትናንት በይፋ የተመረቀው የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክም የኢትዮጵያን ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ ለዓለም ይበልጥ ተደራሽ የሚያደርግ ነው።
ከተመሠረተ 11 ዓመታትን ብቻ ያስቆጠረው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ እንደ ቻይና ያሉ ሀገራትን ተሞክሮ በመቀመር በመላው ሀገራችን ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ 14 ልዩ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ገንብቶ በማስተዳደር ላይ ይገኛል።
በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #manufacturing #industrialparks #specialeconomiczones #ebc

Comments