4 days ago
መሣሪያን በብዕር የተኩ እጆች፤ የሀገራዊ ምክክር ታሪካዊ ምዕራፍ
***************
የግጭትን መንገድ ትቶ ወደ ሰላማዊ ውይይት በመምጣት በአንድ መድረክ ላይ በእጃቸው መሳሪያ ሳይሆን ብዕርን በመያዝ ሀሳባቸውን ለማስፈር መላው ኢትዮጵያውያን ተገናኝተዋል።
የሀገር ግንባታ መሠረቱ የሚጠነክረው በግጭት ሳይሆን በመደማመጥ፣ እንዲሁም በጋራ በሚገነባ የሀሳብ ራዕይ መሆኑን በማስረፅ።
በዚህ እሳቤ መሠረት ነው የሀገራዊ ምክክር ሂደት "የሁሉም ሀሳብ ለኢትዮጵያ ያስፈልጋል" በሚል መርህ የሁሉንም ድምፅ ለማዳመጥ በር የከፈተው።
ሀገራዊ ምክክር ዓላማው ልክ እንደ ውድድር አሸናፊና ተሸናፊ መለየት ሳይሆን በሕዝቦች ዘንድ የተወከሉ ተወካዮች ተጠናክረው የጋራ መፍትሔ በመፈለግ በሁሉም ውስጥ ኢትዮጵያን አሸናፊ ማድረግ ነው።
ለዚህም ዋና ማሳያ የሆነው ከ4 ሺህ በላይ ተመካካሪዎች በስምንት ዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ከመላው ኢትዮጵያ የተወከሉ በቡድን ተከፋፍለው እየተወያዩ ይገኛሉ።
ዓመታትን በትጥቅ ትግል ያሳለፉ ተመካካሪዎች ዛሬ መሣሪያን አስቀምጠው ብዕር በመያዝ ሐሳባቸውን በውይይት እያቀረቡ ይገኛሉ፤ ይህ የሚጠቁመው ምልክት የጦርነትን ኃይል ሳይሆን በመመካከር ችግሮች ሊፈቱ እንደሚችሉ የሚያሳይ ተስፋ ሰጪ ምልክት እና የሰላም መንገድ ለሁሉም ክፍት መሆኑን ያረጋግጣል።
ተመካካሪዎቹ ከ250 አባላት ወደ 50 አባላት፣ በመጨረሻም ወደ 10 አባላት በመከፋፈል ሁሉም ተመካካሪ ያመጣውን የማኅበረሰብ ጥያቄና ሐሳብ ያለ ግፊት፣ ያለ ፍርሃት እና ያለ ተፅዕኖ በነፃነት እንዲያቀርብ ዕድል ተፈጥሮለታል።
ልዩነታቸው ውበታቸው የሆነው የኢትዮጵያውያን ሐሳቦች ሲገናኙ፣ ልዩነቶች ሲከበሩ እና ሁሉም ድምፅ የመደመጥ ዕድል ሲያገኝ፣ የነገዋ ኢትዮጵያ በተስፋ እና በመተማመን የተመሠረተች ትሆናለች። ለዘመናት የቆዩ ቁርሾዎችን በጠረጴዛ ዙሪያ በመፍታት የሰላም ባህልን ማጠናከር የዚህ ሂደት ትልቁ ስኬት ነው።
በዚህ መድረክ ላይ የሚጻፉት ቃላት በወረቀት ላይ ብቻ አይቀሩም፤ ወደ ታሪክ በመሻገር ከአዳራሹ አልፈው የቀጣዮቹን ትውልዶች ሊመሩ የሚችሉ እና ተስፋን፣ ይቅርታን፣ የጋራ ራዕይን የሚተክሉ ናቸው።
በዚህም ሀገር የምትገነባው በዜጎቿ የተረጋጋ ውይይት በመሆኑ ወደ ምክክር መምጣት የድክመት ምልክት ሳይሆን የብስለት፣ የኃላፊነት እና የጋራ የወደፊት ዕጣ ፈንታን በሰላማዊ መንገድ ለመወሰን የተወሰደ ጠንካራ እርምጃ ነው።
መሣሪያን በብዕር የተኩ እጆች የሚጽፉት የአንድ ቡድን ታሪክ አይደለም፤ የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ የወደፊት ምዕራፍን ነው።
በልዩ እሸቱ
#nationaldialogue #peacebuilding #futureethiopia #inclusion #unityindiversity #reconciliation

28 days ago
የምክክር ድባብ የሞቃት አዲስ አበባ፤ የኢትዮጵያ ልጆች ለዘላቂ መግባባት በአንድ ማዕከል እየተሰባሰቡ ነው
***************
ዛሬ ልዩ ቀን ነው፤ በክረምቱ መዲናችን አዲስ አበባ በታሪካዊው የምክክር ድባብ ተሟሙቃለች። ሰማዩ ደመና አዝሎ፣ ቆፈኑ አይሎና ዝናብ ምድሪቱን እያረሰረሰ ባለበት በዚህ የክረምት ወቅት፣ ኢትዮጵያችን ደግሞ የታላቅ የምክክር ድግስ ጠንስሳ አዲስ አበባን ሞቅ ደመቅ እያደረገችው ትገኛለች።
የሀገራዊ ምክክር ተሳታፊዎች የምክክር ስንቅ ሸክፈውና የመግባባት ዓላማን አንግበው ወደ አዲስ አበባ መግባት የጀመሩ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ልጆች ተመካክረው ለመግባባት በአንድ ማዕከል ተሰባስበዋል።
ከመላው ኢትዮጵያ በሀገር ጉዳይ ላይ ስለ ሀገር ለመምከር የተሰናዱ ኢትዮጵያዊያን የማረፊያ ቦታቸውን እየያዙ በመሆናቸው በአሁኑ ወቅት ያለው ድባብ እጅግ ልዩ ነው።
ተሳታፊዎቹ ረዥም ኪሎሜትሮችን አቆራርጠው ቢመጡም ሀገርን ለማጽናትና ለማቅናት ስለተጓዙ ፊታቸው ላይ የሚነበበው ትልቅ ደስታና ተስፋ ብቻ ነው። ጥንታዊቷ እና የአናብስት ምድር ኢትዮጵያ ልጆቿ ዛሬም በአደራ ጠብቀው ለቀጣዩ ትውልድ ሊያሻግሯት እየተዘጋጁ ይገኛሉ።
በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ የማረፊያ ሥፍራዎች ሁሉን ነገር አሟልተው እንግዶችን እየተቀበሉ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሠራተኞች፣ በጎ ፈቃደኞችና የጸጥታ ኃይሎች በመቀናጀት የምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎችን በፈገግታና በከፍተኛ እንክብካቤ እያስተናገዱ ነው።
ከአራቱም አቅጣጫ ወደ ዋና ከተማቸው የተመሙት ኢትዮጵያውያን የክረምቱን ቅዝቃዜ አስረስተው አዲስ አበባን ሞቅ ደመቅ ያደረጓት ሲሆን፣ ዘመናትን የተሻገሩ ያለመግባባት መንስኤዎች ሁሉ በምክክር የሚሻሩበት ቀን ተቆርጧል።
መላው ኢትዮጵያውያን በተስፋ የሚጠብቁት ይህ ታሪካዊ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ይጀመራል።
ሀገራዊ ምክክር፤ ለሀገራዊ መግባባት!
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን!
#nationaldialogue #nationalconsensus #addisababa #unityindiversity #ethiopia #ethiopianbroadcastingcorporation

3 months ago
የኢትዮጸጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የጸሎት እና የአብሮነት መርሐግብር ግንቦት 16 በአራዳ ፓርክ ያካሂዳል #prayerandsolidarity #aradapark #ethiopiancouncilofreligions #unityindiversity #peaceforethiopia
7 months ago
🌳 ቴፒን በጋራ እናልማ
የ"ትንሿ ኢትዮጵያ" ዳግም ውልደትና የልማት ጥሪ
#ethiopia | የታሪክ ድርሳናት እንደሚነግሩን ቴፒ ከተማ በ1911 ዓ.ም የተቆረቆረች፣ የኢትዮጵያ የዘመናዊነት አውራ ጎዳና ቀዳሚ ተጠቃሚ የነበረች ታሪካዊ የንግድ ማዕከል ናት። ገና በ1960ዎቹ የአውሮፕላን ትራንስፖርት፣ በ1966 የጤና ጣቢያና የጠጠር መንገድ የነበራት ቴፒ፤ ዛሬም ያንን ገናና ታሪኳን አድሳ ወደ ከፍታ ለመመለስ ቆርጣ ተነስታለች።
🇪🇹 ቴፒ፦ የብዝሃነትና የተፈጥሮ ዕንቁ
አረንጓዴ ካባ የደረበችው ቴፒ፣ "ትንሿ ኢትዮጵያ" ተብላ ትጠራለች። ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በፍቅርና በመከባበር የሚኖሩባት፣ የቡናና የቅመማ ቅመም ምርቷን ለዓለም ገበያ የምታቀርብ የኢኮኖሚ ምሰሶ ናት።
🚧 የልማት እንቅፋትና አዲስ ተስፋ
ከተማዋ በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ምርት የምታቀርብ ብትሆንም፣ የዘመናዊ መንገድ መሠረተ ልማት እጥረት ትልቅ ፈተና ሆኖባት ቆይቷል። ይህንን ችግር ለመፍታት፦
ከሚዛን፣ ከማሻ-ጎሬ እና ከሽሽንዳ የሚመጡ ዋና ዋና መንገዶች በፍጥነት እየተገነቡ ይገኛሉ።
ነገር ግን፦
የከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች የሁላችንንም እገዛ ይሻሉ።
🤝 የ"ህብረት" ጥሪ ለቴፒ ልጆችና ለኢትዮጵያውያን በሙሉ!
የቴፒ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን ነባራዊ እድገትና ቀደምት ስልጣኔ ባገናዘበ መልኩ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በራስ አቅም ለመገንባት ፕሮጀክት ነድፎ ወደ ተግባር ገብቷል።
በሀገር ውስጥና በውጭ የምትገኙ የቴፒ ተወላጆች፣ ወዳጆችና የልማት አጋሮች በሙሉ፦ "ዘንድሮ የምትሞሸረውን ቴፒን በጋራ እናስውብ!" ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
💰 የልማት ተሳትፎዎን በሚከተለው የባንክ አካውንት ያድርጉ፦
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)፦ 1000731791558
የአካውንቱ ስም፦ ቴፒ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎ አስፓልት ግንባታ
💡 መፈክራችን፦ "በኅብረት ሁሉን እንችላለን!!"
የከተማችን መልማት የሀገራችን ብልፅግና መሠረት ነው። ዛሬ ለቴፒ የምናደርገው ድጋፍ ለነገው ትውልድ የምናስቀምጠው ትልቅ አሻራ ነው።
የቴፒ ከተማ አስተዳደር፤
በመምህር ኃይማኖት ተስፋዬ እና
በናትናኤል ዳኜ በኩል የተላለፈ መልዕክት
#tepi #ethiopia #development #communityservice #infrastructure #coffeeland #unityindiversity #ethiopiaprogress #tepicity

Sponsored by
Surafel
Comments