10 days ago
በ108 ዓመታቸው የመኪና መሪ አልለቅም ያሉት የእድሜ ባለፀጋዋ ሜሪ
መሪ በቀላሉ የምንደሰት ከሆነ የማይቻል ነገር የለም ይላሉ
#ethiopia | በአሜሪካ አሪዞና ግዛት ነዋሪ የሆኑት የ108 አመት ባለፀጋዋ መሪ በሰሞኑ የመንጃ ፍቃዳቸውን እስከ ፈረንጆቹ 2033 ድረስ አሳድሰዋል።
108 ዓመታቸው ላይ የሚገኙት መሪ በራሳቸው መኖሪያ ቤት ብቻቸው ከመኖራቸውም በላይ መኪናቸውንም እያሽከረከሩ ይገኛሉ።
ሜሪ ፍሊፕ የተባሉት እኚህ ባለታሪክ ለረጅም እድሜ የበቁበትና ጤናማ የሆኑበትን ምስጢር አካፍለዋል።
በቅርብ ጊዜ የመንጃ ፈቃዳቸውን እስከ ፈረንጆቹ 2033 ድረስ ያደሱት ሜሪ ሙሉ በሙሉ ነፃነታቸውን ጠብቀው በራሳቸው መኖር እንደሚወዱ ይናገራሉ።
ራሴን ሙሉ በሙሉ በራሴ ነው የምንከባከበው የሚሉት ሜሪ በየቀኑ ቀለል ያሉ እንቅስቃሴዎችን መስራት እንደሚያዘወትሩ ይናገራሉ።
ሜሪ እረጅም ዕድሜ የመኖራቸው ምክንያት ሲናገሩ በሕይወታችን ውስጥ ከባድ ችግሮች ሲገጥሙን አዎንታዊ ጎኑን ማየትና ሁልጊዜም ፈገግታን ማብዛት ጤናማ ህይወት መኖር ይቻላል ብለዋል።
በሰው ላይ አለመደገፍ እና የራስን የቤት ውስጥ ስራዎች በተቻለ መጠን በራስ መወጣት ያስፈልጋልም ሲሉ ተናግረዋል።
በቀላሉ ልንደሰትባቸው በሚያስችሉን አነስተኛ ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ እና ጭንቀትን ማስወገድ እንደሚገባም ተናግረዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #centenarian #drives #longlife #merryfelipe

17 days ago
የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የፈሩት ታሪካዊ ምክክር
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በየዘመናቱ ከቅርብም ከሩቅም የተከፈቱባቸውን ጦርነቶች በመመከት ሀገር የማጽናት የወል ታሪክ ያላቸው ኢትዮጵያውያን፥ ታሪክ ራሱን ይደግም ዘንድ የሰላምና የልማት ደንቃራ ለሆኑ ችግሮች መላ ለማበጀት ተሰባስበዋል።
ኢትዮጵያ ግጭቶችን ተመካክሮ የመፍታት የዳበረ እሴት ያላቸው ሕዝቦች መገኛ ሆና ሳለ፤ አለመግባባት በተፈጠረ ቁጥር የራሳቸውን ድብቅ አጀንዳ አስርገው ለሚያስገቡ ጠላቶች የምንመች ሆነን የመቆየታችን እንቆቅልሽ የሚፈታበት ጊዜ ላይ ነን፡፡
ሀገራችን የሰው ኃይል ሀብቷን፣ የተፈጥሮ ጸጋና ቀደምት የሥልጣኔ መሠረት አጣምራ ወደፊት እንዳትራመድ ሰቅዘው ከያዟት የዘመናት ችግሮች ተላቅቃ አንገቷን ቀና ታደርግ ዘንድ ዜጎቿ ሀሳብ እንዲያዋጡ ትሻለች።
የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያን አላራምድ ብሎ ይዞ የቆየውን ውስብስብ እንቆቅልሽ መፍታት ጊዜ የማይሰጥ የገዘፈ አጀንዳ መሆኑን በወጉ ተገንዝቦ መንገድ ጀምሯል፡፡
ኢትዮጵያ ወደማይቀረው ከፍታዋ የምትወጣው ሕዝቦቿ ተደምረው፣ ቅራኔዎቻቸውን አስረድተው፣ መፍትሔ የሚሏቸውን ሀሳቦች አዋጥተው እንቆቅልሹን በልኩ መፍታት ሲችሉ ነው፡፡
የመደመር መንግሥት የዚህ የዘመናት እንቆቅልሽ መፍቻው ቁልፍ የሚገኝበትን ሀገራዊ ምክክር ከጠነሰሰበት ዕለት አንስቶ የኢትዮጵያን ውድቀት የሚመኙና የልማት ጉዞዋ እረፍት የሚነሳቸው ጠላቶቿን ሲያቃዣቸው ከርሟል፡፡
ከትናንት እስከ ዛሬ ስር እየሰደዱ የሀገራችንን ርምጃ የሚያዘገዩ ችግሮች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍትሔ ከተበጀላቸው ጠላቶቿ መግቢያ ያጣሉ፡፡
ይህንን ጠንቅቀው የተረዱት እኚሁ ታሪካዊ ጠላቶች ሂደቱን ለማደናቀፍና ኢትዮጵያውያንን ከጀመሩት ታሪካዊ ጉዞ ከመንገድ ለማስቀረት መሸረብን የሙሉ ጊዜ ሥራቸው አድርገውታል፡፡
ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ጉዳይ አንድ ላይ ተሰባስበው ሲመክሩ የሚፈጥሩት የአንድነት አቅም ብሔራዊ ጥቅማችንን ለማስከበር ትልቅ ኃይል መሆኑን ተረድተው ከወዲሁ ብርክ ብርክ ይላቸው ጀምሯል፡፡
የኢትዮጵያን በጋራ የመልማት መሻት አሻፈረኝ ብለው በጥፋት የተጠመዱት እኚህ ኃይሎች፥ "ምክክሩ አልተጀመረም፤ ችግር ገጥሞታል" እያሉ በሀሰት ፕሮፓጋንዳ ኢትዮጵያውያንን ከሀሳባቸው ለማናጠብ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡
ዳሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ማስጀመሪያ ላይ እንዳሉት፥ በእነዚህ አጀንዳዎች ኢትዮጵያውያንን ከጉዟቸው ማስቆም የሚቻል አይደለም፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው "በቀላሉ በማይበጠስ ገመድ የተሰናሰለችና ለሺህ ዓመታት ጸንታ የኖረች ኢትዮጵያ አሁን ባለው ፕሮፓጋንዳ ጥቅሟን አሳልፋ ትሰጣለች ብሎ ማሰብ ከንቱ ምኞት ነው" ነበር ያሉት፡፡
ኢትዮጵያ በመደመር መንገድ ከግጭት አዙሪትና ከድህነት ቅርቃር ወጥታ የቀደምት ሥልጣኔ ከፍታዋን ዳግም ትንሳኤ የምታበስርበትና የሚፈራ ኃይል ባለቤት የምትሆንበት ምዕራፍ እነሆ ተጀምሯል፡፡ ይኸውም ሀገራዊ ምክክር ነው፡፡

18 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) እስራኤል አዞዎችን ከዱር አራዊትነት ዝርዝር አወጣች፡፡ የእስራኤል አካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ኢዲት ሲልማን አዞዎች ከዱር አራዊትነት ዝርዝር ውስጥ መውጣታቸውንና በእንስሳት ማቆያ ውስጥ ተዳቅለው ያደጉ የዱር እንስሳት በሚል ውስጥ መካተታቸውን አስታወቁ፡፡ እንደኤኤፍፒ ዘገባ ይህ ውሳኔ እነዚህን ተሳቢ እንስሳት ከእስር ቤት የማምለጥ ሙከራን ጨምሮ ለተለያዩ የደህንነት ስራዎች ለማዋል መንገድ የሚጠርግ ነው፡፡
ውሳኔውን የእስራኤል ብሄራዊ ደህንነት ሚኒስትር የሆኑት ኢታማር ቤን ጂቨር በደስታ መቀበላቸውን ገልፀዋል፡፡ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገፃቸው ላይ በኤአይ የተቀናበረ ራሳቸውን ከአዞ ጋር ተቃቅፈው የሚያሳይ ምስል ለጥፈው ‹‹ከእስር ቤት ማምለጥ የሚፈልግ ደግሞ ያስብበት›› የሚል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ እኚህ ሚኒስትር በዲሴምበር ወር በፍሎሪዳ የሚገኘውን ‹‹አሊጌተር አልካታራዝ›› የኢሚግሬሽን ማቆያ እንደምሳሌ ጠቅሰው በአገራቸው የሚገኙ የፍሊስጤም እስረኞች በአዞ እንዲከበቡ ምክረ ሀሳብ አቅርበው ነበር፡፡
ቻናል 13 የተሰኘው የእስራኤል ቴሌቪዥን እንደዘገበው ሚኒስትሩ ይህንን ሀሳብ ባቀረቡበት ወቅት በርካታ ባለስልጣናት እንደፌዝ ቆጥረውት ነበር፡፡ ሀሳቡን የእስራኤል የተፈጥሮ ፓርኮች ባለስልጣንም አጥብቆ መቃወሙን አውስቷል፡፡ ይሁንና አሁን አዞዎች ከዱር አራዊትነት መውጣታቸው እነዚህን እንስሳት ለ‹‹ደህንነት አገልግሎት›› መጠቀምን ይፈቅዳል፡፡

26 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ትንሿን የባህረ ሰላጤዋን ሀገር በዓለማችን ላይ እጅግ ባለጸጋ እና ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ ወደ ሆነች ግዙፍ ሀገርነት የቀየሩት የቀድሞው የኳታር አሚር ሼክ ሐማድ ቢን ኻሊፋ አል ታኒ በ74 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ማራኪ ስብዕና እና ወዳጃዊ አቀራረብ የነበራቸው እኚህ "አባት አሚር"... የዘመናዊቷ ኳታር እውነተኛ አርክቴክት ተብለው በሰፊው ይወደሳሉ።
እ.ኤ.አ በጥር 1952 በዶሃ የተወለዱት ሼክ ሐማድ፣ ከብሪታንያው ሮያል ሚሊተሪ አካዳሚ ከተመረቁ በኋላ የኳታር የጦር ኃይሎች አዛዥ በመሆን አገልግለዋል። በ1977 አልጋ ወራሽ እና የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙ ሲሆን፣ በሰኔ 27፣ 1995 ደግሞ የሀገሪቱን የስልጣን መንበር በይፋ ተረከቡ። ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ሀገራቸው ያላትን እጅግ ሰፊ የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት በመጠቀም ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ማሻሻያዎችን ያካተተ ትልቅ የልማት ራዕይ ነድፈው በተግባር አሳይተዋል።
በሳቸው የስልጣን ዘመን የኳታር አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ከ24 እጥፍ በላይ በሚያስገርም ፍጥነት አድጓል። በተለይም ከኖርዝ ፊልድ የተገኘው ምርት፣ ኳታርን እ.ኤ.አ በ2006 የዓለማችን ትልቋ የፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ (LNG) ላኪ ሀገር እንድትሆን አድርጓታል። በመንግስት መረጃ መሰረት... ይህች ትንሽ ሀገር በአጭር ጊዜ ውስጥ የማምረት አቅሟን በዓመት ወደ 77 ሚሊዮን ቶን ማድረስ ችላ ነበር።
የሼክ ሐማድ የአመራር ዘመን በለውጥ የተሞላ ነበር። የኳታር ፋውንዴሽን መመስረት፣ በ1996 የዓለምን የሚዲያ ትኩረት የሳበው የአልጀዚራ የዜና ቻናል መከፈት፣ በ2004 የመጀመሪያው ቋሚ የኳታር ህገ-መንግስት መጽደቅ እና ሴቶች የመምረጥና የመመረጥ መብት ያገኙበት የማዘጋጃ ቤት ምርጫ መጀመር የሳቸው ትሩፋቶች ናቸው። ከዚህም በላይ ኳታር በ2022ቱን የፊፋ ዓለም ዋንጫ የማስተናገድ መብት እንድታገኝ ያደረጉት ጥረት፣ አንዲት አረብ ሀገር ይህንን ታላቅ ውድድር ስታስተናግድ በታሪክ የመጀመሪያው እንዲሆን አስችሏል።
ሼክ ሐማድ ኳታርን የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ማዕከል እና የሰላም አደራዳሪ እንድትሆን ሰፊ ራዕይ ነበራቸው። በሱዳን ዳርፉር ክልል፣ በሊባኖስ የውስጥ ትርምስ፣ እንዲሁም በፍልስጤሙ ሃማስ እና ፋታህ መካከል ለተፈጠረው ስምጥ ኳታር ቁልፍ አደራዳሪ ሆና አገልግላለች። ስልጣን ከመልቀቃቸው በፊትም በአሜሪካ ጥያቄ መሰረት ታሊባን በኳታር ጽህፈት ቤት እንዲከፍት አድርገዋል፤ ይህም በመጨረሻ ኔቶ እና አሜሪካ በ2021 ከአፍጋኒስታን ለወጡበት ታሪካዊ ድርድር በር ከፋች ሆኖ አልፏል።
በአረብ ጸደይ ወቅት ኳታር ከህዝባዊ አመጾች ጎን ከቆሙ ጥቂት ሀገራት አንዷ ነበረች። በግብፅ፣ አልጀዚራ የስርጭት እገዳን ጥሶ የዲሞክራሲ ደጋፊዎችን ድምፅ ለዓለም አሰምቷል። በሶሪያ፣ ሼክ ሐማድ መጀመሪያ ላይ ፕሬዝዳንት ባሻር አል አሳድ ስልጣን እንዲለቁ ለማሳመን ቢሞክሩም፣ የመንግስት ኃይሎች ሰልፈኞችን መግደላቸውን ተከትሎ ዶሃ ከደማስቆ ጋር ያላትን ግንኙነት አቋርጣለች። በሊቢያ ደግሞ የረጅም ጊዜ መሪ የነበሩትን ሙአመር ጋዳፊን ከስልጣን ያወረደውን የኔቶ ወታደራዊ ዘመቻ በመደገፍ ኳታር ትልቅ ሚና ተጫውታለች።
እ.ኤ.አ ሰኔ 25፣ 2013 ሼክ ሐማድ ባልተለመደ ሁኔታ እና በፍጹም ፈቃደኝነት ስልጣናቸውን ለ33 ዓመቱ ልጃቸው ለሼክ ታሚም ቢን ሐማድ አል ታኒ አስረከቡ። እንዲህ ዓይነቱ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በመካከለኛው ምስራቅ እጅግ ያልተለመደ እና ብርቅ ክስተት ነበር። ስልጣን ሲለቁም "ወጣቱ አመራር ባንዲራውን ከፍ አድርጎ ወደሚያውለበልብበት አዲስ ዘመን ስትገቡ፣ የወደፊቱ ጊዜ በፊታችሁ አለ" በማለት ለሀገሪቱ ልጆች ተስፋ ሰጥተዋል።
ከሁሉም በላይ ግን ለልባቸው እጅግ ቅርብ የነበረው የፍልስጤም የነጻነት ትግል ነው። ከዓመታት በኋላ የጋዛ ሰርጥን በመጎብኘት የመጀመሪያው የሀገር መሪ የሆኑት እሳቸው ነበሩ። ለፍልስጤም ህዝብ ላደረጉት ድጋፍ ክብር ሲባል፣ በጋዛ እና በደቡብ ሊባኖስ የሚገኙ ከተሞች በስማቸው ተሰይመዋል። ሼክ ሐማድ ቢን ኻሊፋ አል ታኒ ያሳደሩት ተጽዕኖ ከኳታር ድንበር እጅግ የራቀ ነበር፤ ህልፈታቸውም ልክ እንደ ህይወት ዘመናቸው ሁሉ በመላው ቀጠናው እና ከዚያም ባለፈ በዓለም ዙሪያ በጥልቅ የሚታወስ ይሆናል።

Sponsored by
Surafel
1 month ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) "ተገድለዋል" የተባለላቸው የቀድሞው የኢራን ፕሬዝደንት በአያቶላ ሆሚኒ የቀብር ስነስርአት ላይ ታዩ፡፡ የቀድሞው የኢራን ፕሬዝደንት መሀመድ አህመዲንዳጅ ከጦርነቱ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በቴሄራን አደባባይ ላይ ለመታየት ችለዋል፡፡ ፌብሩዋሪ 28 ቀን የተጀመረውን ጦርነት ተከትሎ በርካታ የኢራን ፖለቲካዊና ወታደራዊ ባለስልጣናት መገደላቸው የሚታወቅ ሲሆን ከዚያን ጊዜ አንስቶ እኚህ የቀድሞው ፕሬዝደንት ታይተው አያውቁም፡፡
ይህንን ተከትሎ በተለያዩ ሚዲያዎች መገደላቸው ወይንም መቁሰላቸው በስፋት ተዘግቧል፡፡ ነገር ግን በዚህ ዘገባ ላይ ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ ያልተሰጠ መሆኑ በርካቶችን ሲያነጋግር ሰንብቷል፡፡ ይሁንና ትላንት በቴሄራን አደባባይ በተከናወነው የአያቶላው የቀብር ስነስርአት ከተገኙት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ውስጥ አህመዲንጃድ አንዱ ሆነዋል፡፡ የኢራን ቴሌቪዥን ምስላቸውን በግልፅ ያሳየ ሲሆን የቀድሞ ፕሬዝደንቱ ጃኬት ለብሰውና አንገታቸውን በማክስ ሸፍነው ታይተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የሟቹ አያቶላ ሆሚኒ ልጅ የሆኑት ሞጅታባ ግን እስካሁን በአባታቸው የቀብር ስነስርአት ላይ ሊታዩ አልቻሉም፡፡

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የተመድ ሰብአዊ መብት ምክር ቤት የኤርትራ ራፖርተርን የስራ ዘመን በአንድ አመት አራዘመ፡፡ በተመድ የኤርትራ የሰብአዊ መብት ራፖርተር የሆኑት መሀመድ አብዲሰላም ባቢከር ባለፈው 6 አመት የስራ ዘመናቸው በኤርትራዊያን በኩል በ2 መልክ ሲታዩ ቆይተዋል፡፡
አንደኛው መልክ በመላው አለም በሚገኙ ኤርትራዊያን እይታ የሚንፀባረቅ ሲሆን እሳቸው በየአመቱ በጄኔቫ የሚያቀርቡት ሪፖርት በአገራቸው ውስጥ ያለውን ስቃይ፣ ግፍና ሰቆቃ ለአለም የሚያሳይ ብቸኛው መንገድ አድርገው ይቆጥሩታል፡፡ ሁለተኛው መልክ ደግሞ በኤርትራ መንግስት በኩል ሰውየው የሚገለፁበት ነው፡፡ የኤርትራ መንግስት እኚህ ራፖርተር በተደጋጋሚ ዘልፈዋቸዋል፡፡
ከአደጉ አገራት በሚሰጣቸው ትእዛዝ በማደግ ላይ ባሉ አገራት ላይ ጫና የሚያሳድሩ፣ ብሄራዊ ሉአላዊነትን ለመጣስ የሚሞክሩና በአጠቃላይ የኤርትራን ደህንነት አደጋ ውስጥ የሚከቱ መሆናቸውንም ይገልፃሉ፡፡ በመሆኑም ራፖርተሩ ከሀላፊነታቸው እንዲነሱ ያላሰለሰ ጥያቄ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ ይህንን ተከትሎም ሰሞኑን እኚህን ራፖርተር ለመተካት 8 እጩዎች እየተገመገሙ መሆኑን የሚገልፁ ዘገባዎች በስፋት ሲሰራጩ ነበር፡፡
ነገር ግን ዛሬ በጄኔቭ በተካሄደው የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ እኚህ ራፖርተር ለተጨማሪ አንድ አመት በሀላፊነታቸው እንዲቀጥሉ ውሳኔ ተላልፏል፡፡ የውሳኔውን ረቂቅ ያቀረበው የአውሮፓ ህብረት ሲሆን በተሰጠው ድምፅ አሰጣጥ 23 የምክር ቤቱ አባላት ውሳኔውን ሲደግፉ፣ 17ቱ ደግሞ ድምፀ ተአቅቦ በማድጋቸውና 6 አገራት የተቃውሞ ድምፅ በመስጠታቸው ውሳኔው ፀድቋል፡፡ ውሳኔው እንዳይፀድቅ ተቃውሞ ድምፅ የሰጡት 6 አገራት ግብፅ፣ ብሩንዲ፣ ቻይና፣ ኩባ፣ ህንድና ፓኪስታን ናቸው፡፡

አራት ልጆቻቸውን እሰከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ አስተምረው የልጅ ልጆችም ያዩት የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኝ እናት
ከላይ በምስሉ የምታያቸው ወ/ሮ አልማዝ አሻራው ይባላሉ። በጌዴኦ ዞን የገደብ ወረዳ ነዋሪ ሲሆኑ፣ በቤተሰብ ጫና ምክንያት በ1982 ዓ.ም ከ4ኛ ክፍል ትምህርታቸውን እንዳቋረጡ ይገልጻሉ።
በ1983 ዓ.ም ትዳር የመሰረቱት ወ/ሮ አልማዝ የስምንት ልጆች እናት ናቸው። አራት ልጆቻቸውን እሰከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ አስተምረዋል፣ የልጅ ልጆችም አይተዋል።
የቀሩት አራት ልጆቻቸው ደግሞ ከ5ኛ እሰከ 12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ትምህርታቸውን ዳግም መማር ያሰቡት ትላንት ያላሳኩትን፣ ያልኖሩትን ህልማቸውን ዳግም ለመኖር እንደሆነ ወ/ሮ አልማዝ ይገልጻሉ።
እኚህ ብርቱ እናት ዘንድሮ እየተሰጠ የሚገኘውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው፣ በመጀመሪያው ዙር በበይነ መረብ ፈተናቸውን መውሰድ ጀምረዋል። ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ወደ ዩኒቨርሲቲ ገብተው ተምረው መመረቅ ህልማቸው እንደሆነም ይናገራሉ።
Seledadotio

2 months ago
በጅማ ዩኒቨርስቲ ታሪክ የመጀመሪያ ሴት ሙሉ ፕሮፌሰር ፅጌ ከተማ
በጅማ ዩኒቨርሲቲ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ሙሉ ፕሮፌሰር እና በባዮሜዲካል ሳይንስ (Biomedical Sciences) ዘርፍ የታወቁ አንጋፋ ኢትዮጵያዊት ተመራማሪ ናቸው። እ.ኤ.አ. በነሐሴ 2020 የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያገኙት እኚህ ምሁር፣ በዩኒቨርሲቲው በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንትነትም ጭምር አገልግለዋል።
የትምህርትና የህይወት ታሪክ
የትውልድ ቦታ፦ በአርሲ ዞን፣ ዲክሲስ/ሀምዳ ከተማ ተወለዱ።
የመጀመሪያ ዲግሪ፦ በጅማ ዩኒቨርሲቲ (እ.ኤ.አ. 2005) ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የፒን (Pin) ሽልማት አግኝተዋል።
ሁለተኛ ዲግሪ፦ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (እ.ኤ.አ. 2008) በባዮሜዲካል ሳይንስ ማስተርሳቸውን ሰርተዋል።
የዶክትሬት ዲግሪ (PhD)፦ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የባዮሎጂ ትምህርት ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ በመሆን ፒኤችዲያቸውን አጠናቀዋል።
ዋና ዋና የምርምር ዘርፎች
ፕሮፌሰር ፅጌ በዋናነት በወባ በሽታ (Malaria) ዙሪያ በርካታ ዓለም አቀፍ ምርምሮችን አድርገዋል። በተለይም
በኢትዮጵያ በድርቅ ለተጠቁ አካባቢዎች የአኖፊሊስ ስቴፈንሲ (Anopheles stephensi) የወባ ትንኝ ስርጭትን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት (Early Warning System) በመቅረጽ ላይ ይገኛሉ።
በፕላዝሞዲየም ቫይቫክስ (P. vivax) ወባ ሳቢያ በሚከሰት የደም ማነስ (Anemia) እና ተያያዥ የጤና ችግሮች ላይ ሰፊ ጥናት አሳትመዋል።
ሽልማቶችና ዓለም አቀፍ እውቅናዎች
ባበረከቱት ከፍተኛ የሳይንስ አስተዋፅኦ በርካታ ዓለም አቀፍ የክብር ሽልማቶችንና የምርምር ፈንዶችን አግኝተዋል
የኦደብሊውኤስዲ (OWSD) ሽልማት፦ በታዳጊ ሀገራት ውስጥ ካሉ 15 ድንቅ ሴት ሳይንቲስቶች አንዷ በመሆን የ2024 የቅድመ-ሥራ ዘመን ፌሎውሺፕ (Early Career Fellowship) አሸናፊ ሆነዋል።
የሎሪያል-ዩኔስኮ (L'Oréal-UNESCO) ሽልማት፦ እ.ኤ.አ. በ2012 ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ለውጤታማ ሴት ሳይንቲስቶች የሚሰጠውን ሽልማት በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ተቀብለዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት (WHO/TDR) ፌሎውሺፕ፦ በስፔን ባርሴሎና ግሎባል ጤና ኢንስቲትዩት የክሊኒካዊ ምርምር ፌሎውሺፕ አጠናቀዋል።
የጀርመን አካዳሚክ ልውውጥ (DAAD)፦ የ ProGrant እና የሀገር ውስጥ ስኮላርሺፕ አሸናፊ ነበሩ።
Via: Doch HD

♦️የታሪክ ግጥጥሞሽ ከ16 ዓመታት በኋላ በዛሬው ቀን
♦️የጀርመንና የኮትዲቯር የዛሬ ጨዋታ ትኬት ጥብስ ሆኗል
♦️ከ5ሺ በላይ የጀርመን ደጋፊዎች የቶሮንቶን ጎዳና አጣበዋል
#ethiopia | አቤት ጊዜው እንዴት ይሮጣል?ዕድሜም ሳይታወቀን ላፍ ይላል፤ ልክ በዛሬው ቀን June 20/2010 በፊፋ የምስረታ ታሪክ ከ102 ዓመታት ጥበቃና ትዕግስት በኋላ በአፍሪካ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው በ2010ሩ የዓለም ዋንጫ የዲዲዬ ድሮግባዋን ኮትዲቯርን በደቡብ አፍሪካው ግዙፍ ስታዲየም ሶከር ሲቲ ስታዲየም ከብራዚል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ በአካል ተገኝቼ ከተመለከትኩ ድፍን 16 ዓመት ሞላው።
ዛሬ ደግሞ ኮትዲቯር በብራዚል 3ለ1 የተሸነፈችበትን፣ዲዲዬ ድሮግባ ከሽንፈት ያላዳነች ግብ ያስቆጠረበት፣በዕምነቱ ጠንካራ የሆነው የመሀል ሜዳው ሞተር ብራዚሊያዊው ካካ ድንቅ ጨዋታውን ብቻ ሳይሆን አመለ ቢስ ሆኖ በቀይ ካርድ ከሜዳ የተወገደበት፣ሉዊስ ፋቢያኖ ሁለት ጎል ሲያስቆጥር በሶከር ሲቲ ስታዲየም ተገኝቼ የታደምኩበት ጨዋታ በታሪክ ግጥጥሞሽ ከ16 ዓመታት በኋላ ኮትዲቯር ከ ጀርመን የምታደርገውን ጨዋታ ለመመልከት ለሚዲያ በተዘጋጀው አውቶብስ(Shuttle Bas)በBMO Field ቶሮንቶ ስታዲየም ድንገት የተከሠተ ኢትዮጵያዊ ሆኛለሁ።
ምን ውጤት ይመዘገባል? የሚለውን ለጊዜው ላቆየውና ከዛሬ 16 ዓመት በፊት ኮትዲሻርን ያየሁበት June 20/2010 ዛሬ መልኩን፣ ሀገሩን፣ስታዲየሙንና ተጋጣሚውን ቀይሮ ኮትዲቯር በአዲሱ ትውልድ የምታደርገውን ፍልሚያ ከ16 ዓመታት በኃላ ሊያሳየኝ የሠዓታት ቀጠሮ ይዞልኛል፤አይ የቀን መገጣጠም ከማለት ውጪ ምን ይባላል?
♦️ስለ ጀርመንና ኮትዲቯር ጨዋታ 10 ነጥቦች በእግረ መንገድ
👉ተጠባቂውን የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ የፓራጓይ ዜግነት ያላቸው የ43 ዓመቱ ጆዋን ጋብርኤል ቤኒቴዝ በመሃል ዳኝነት ይመሩታል፤እኚህ የአለም ዋንጫን ሲመሩ የመጀመሪያቸው ነው
👉ከ5,000 በላይ የጀርመን ደጋፊዎች ቶሮንቶ መግባታቸውን ተከትሎ የስታዲየሙ ድባብ ብቻ ሳይሆን ከሜዳ ውጪ ያለው ድባብም ተቀይሯል፤ሌክ ሾርና ባትረስ ስትሪቶች ላይም ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅና የመንገዶች መዘጋጋት ተፈጥሯል፤ነውጠኞቹ የጀርመን ደጋፊዎች ቶሮንቶ ስታዲየምን በድጋፍ ይንጡታል።ከጨዋታው በፊትም የጀርመን ብ/ቡድን ያረፈበትን ሆቴልም ከበው ሲያጨናንቁ፣የተያዩ ጎዳናዎችንም ሲያጣብቡ ተስተውሏል፤
👉የዛሬው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የትኬት ዋጋ የሚቀመስ አልሆነም፤ትኬቶች ሙሉ በሙሉ ተሸጠው ማለቃቸው እየተነገረ ሲሆን የትኬቶች ዋጋ ከ1043 እስከ 6,732 የካናዳ ዶላር(ከ166ሺ -1ሚሊዮን 77ሺ እንዲሁም በሌላ አማራጭ ከ227ሺ እስከ 1ሚሊዮን 104ሺ የኢትዮጵያ ብር)ድረስ ዋጋ የሚያወጡ መሆናቸው ብዙዎችን አነጋግሯል
👉በ2009 በዋናው ብ/ቡድን ተገናኝተው 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት ከተለያዩ በኋላ ዛሬ በአለም ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ቶሮንቶ ላይ ሲገናኙ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው
👉በወዳጅነት ጨዋታ 2ለ2 ሲለያዩ ከአራቱ ጎሎች ሶስቱን ለየሀገራቸው ያስቆጠሩት የአርሰናልን ማልያ ለብሠው የተጫወቱት ሉካስ ፖዶሎስኪ(2)፣ኢማኑኤል ኤቡዬ(1) ናቸው
👉ሁለቱም ቡድኖች የምድባቸውን ሁለተኛ ጨዋታ የሚያደርጉት በአሸናፊነት የድል ስሜት ውስጥ ሆነው ነው ጀርመን ኩራካኦን 7ለ1 ኮትዲቯር ኢኳዶርን በአስገራሚ የመጨረሻ ሠዓት ድል 1ለ0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ተስፋየውን አስፍተው ነው የሚገናኙት
👉የማሸነፍ ግምቱን ለአራት ጊዜ የአለም ዋንጫ አሸናፊዋ ጀርመን ቢሠጥም ኮትዲቯር ቀላል ተፎካካሪ እንደማትሆን እየተነገረ ነው፤እንደ Opta የጨዋታ ግምት ከሆነ የአሸናፊነቱን ቅድሚያ 44.2% በመስጠት ቀዳሚ አድርጓቷል
👉የጀርመን ተጫዋቾች ዛሬ ከአይቮሪኮስት ጋር ከሚያደርጉትን የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ቀደም ብሎ ቶሮንቶ ሲደርሱ ጥብቅ የጸጥታ ቁጥጥር ተደርጎባቸዋል፤ተጫዋቾቹ ከጀርባም ከፊትም ጥብቅ በሆነ የደህንነት ፍተሻ ሲደረግባቸው መታየቱ ከጨዋታው በፊት የብዙዎች የመነጋገሪያ አጀንዳ አድርጎአቸዋል
👉ወደ ካናዳ ይገባል አይገባም በሚል ሲያከራክር የቆየው የኮትዲቯሩአጥቂ ኤልዬ ዋሂ ካናዳ የመግባት ፍቃድ በማግኘቱ በኋላ ለዛሬው ጨዋታ ዝግጁ ሆኗል፤ፈረንሳይ የተወለደው የ23 ዓመቱ ኤልዬ ዋሂ ከመጀመሪያው ጨዋታ ጀምሮ መመለሱ ለአጥቂው ክፍል ጥንካሬ ወሳኝነት ስላለው የካናዳን መሬት እንዲረግጥ ፍቃድ ማግኘቱና ቡድኑን መቀላቀሉ ብዙዎችን አስደስቷል፤የቀድሞ የኢንትራክት ፍራንክፈርት ኤልዬ ዋሂ ወደ ፈረንሳዩ ኒስ በትውስት ተሠጥቶ በሊግ 1 በመጫወት ላይ ይገኛል
👉ሁለቱ ቡድኖች በፊፋ የወሩ ደረጃ(Ranking)ጀርመን 9ኛ፣ኮትዲቯር 30ኛ ደረጃን ይዘው የሚያደርጉት ተጠባቂ ጨዋታ ነው
✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)ከከናዳ ቶሮንቶ ስታዲየም

(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) የጃኖ ባንድ መስራች፣ የዳሎል ባንድ አባል የነበሩት ሙዚቀኛ ዘለቀ ገሰሰ ወንድም እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ስማቸው የገነነ ታዋቂው የሙዚቃ ፕሮዲውሰር እና ማኔጀር አቶ አዲስ ገሰሰ፣ በኒው ጀርሲ፣ አሜሪካ ባደሩበት በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የቅርብ ወዳጆቻቸው አሳዝነው አስታውቀዋል። የሞታቸው ምክንያት ገና በውል ያልታወቀ ሲሆን፣ አስከሬናቸው ወደ ውዲቷ ሀገራቸው ኢትዮጵያ እንደሚሸኝም መረጃዎች ያመለክታሉ።
አቶ አዲስ ገሰሰ በሙዚቃው ኢንደስትሪ ውስጥ ጉልህ አሻራ ያሳረፉ፣ የብዙዎችን ህይወት የቀየሩ እና የኢትዮጵያን ስም በዓለም አደባባይ ከፍ አድርገው ያቆሙ ታላቅ ሰው ነበሩ። እኚህ የሙዚቃ ማኔጅመንት ባለሙያ፣ ዓለም አቀፍ ዝና ያተረፉትን የሬጌው ንጉስ የቦብ ማርሊ ቤተሰቦችን ጨምሮ የበርካታ ታዋቂ ሙዚቀኞች የጀርባ አጥንት በመሆን አገልግለዋል። የእሳቸው የህይወት ጉዞ ከኢትዮጵያ ጀምሮ፣ በቺካጎ፣ ጃማይካ፣ ኒው ዮርክ እና በመጨረሻም ኒው ጀርሲን ያዳረሰ ረዥም እና አስደናቂ መንገድ ነበር።
አቶ አዲስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተመረቁ በኋላ፣ ከ30 ዓመታት በፊት ወደ አሜሪካ አቅንተው ማኔጅመንት አጠኑ። ከዚያም ወንድሞቻቸው ሲከተሏቸው፣ ህይወታቸውን ሙሉ ለሙሉ ለወንድሞቻቸው የሙዚቃ ስኬት አዋሉ። ወንድሞቻቸውና ጓደኞቻቸው የመሰረቱት "ዳሎል" የተሰኘው ባንድ፣ ከኢትዮጵያዊ ሙዚቃ ወደ ሬጌ በማዘንበል፣ በአቶ አዲስ አመራር ስር በቺካጎ ስሙን ማግነን ጀመረ።
በ1982 የቦብ ማርሊ ባለቤት ሪታ ማርሊ ባቀረበችላቸው ጥሪ መሰረት፣ ዳሎል ባንድ በጃማይካ ኪንግስተን በተካሄደው የመጀመሪያው የቦብ ማርሊ መታሰቢያ ላይ ለመጫወት በቅቷል። አቶ አዲስ ሪታ ማርሊ በባለቤቷ ሞት እያዘነች በነበረችበት ወቅት የሰጧት ድጋፍ፣ ጠንካራ ወዳጅነትን ፈጠረ። ይህ ግንኙነት ዳሎል ባንድ ከ1988 እስከ 1991 ድረስ የዚጊ ማርሊ ይፋዊ ባንድ እንዲሆን አስችሎታል። ዳሎል ባንድ በ "Conscious Party" አልበም ፕላቲነም፣ እና በ "One Bright Day" አልበም ጎልድ ደረጃ በመድረስ፣ ይህን ታሪካዊ ስኬት ያገኘ የመጀመሪያው የኢትዮጵያውያን ባንድ ለመሆን በቅቷል።
አቶ አዲስ ከሪታ ማርሊ ጋር በመሆን የቦብ ማርሊን 'Legend' አልበም ዓለም አቀፍ ጉብኝት አደራጅተዋል። ከሁሉም በላይ ግን፣ አቶ አዲስ በ2005 በአዲስ አበባ የተካሄደውንና ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህዝብ የታደመበትን ታሪካዊውን "Africa Unite" ኮንሰርት በዋናነት የጠነሰሱት እሳቸው ነበሩ። ይህ ኮንሰርት የቦብ ማርሊን 60ኛ የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ፣ የቦብ ማርሊ ቤተሰብ፣ አንጀሊክ ኪጆን ጨምሮ በርካታ ከዋክብትን በአዲስ አበባ ያሰባሰበና ስለ ኢትዮጵያ አዎንታዊ ገጽታ ለዓለም ያሳየ ታላቅ ኩነት ነበር።
አቶ አዲስ የዓለም አቀፍ ከዋክብትን ከማስተዳደር ባሻገር፣ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ወደ ዓለም መድረክ ለማሸጋገር ትልቅ ህልም ነበራቸው። ለዚህም ነው "አዲስ ማኔጅመንት" የተሰኘውን ድርጅታቸውን መስርተው በርካታ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶችን የደገፉት።
ታዋቂውን ድምጻዊ ቴዲ አፍሮን በማግኘትና ለረጅም ጊዜ ማኔጀሩ በመሆን አገልግለዋል። እንዲሁም፣ ታዋቂዋን ድምጻዊት ጂጂን በአጋጣሚ ቤታቸው ውስጥ ካገኟት በኋላ፣ ችሎታዋን አይተው፣ ኒው ዮርክ እንድትመጣ በመምከር፣ ከታዋቂው የአይላንድ ሪከርድስ መስራች ክሪስ ብላክዌል ጋር አስተዋውቀዋት፣ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ውል እንድትፈራረም አድርገዋል።
አቶ አዲስ ዓለም አቀፍ ኔትዎርክ ያላቸውና ስኬታማ ቢሆኑም፣ እንደቅርብ ወዳጆቻቸው ምስክርነት እጅግ ትሁት ነበሩ። ኒው ጀርሲ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው፣ ሹራብና አጭር ሱሪ ለብሰው ከሶስት ዓመት ልጃቸው ሀና ጋር ጊዜ ማሳለፍን የሚወዱ አባት ነበሩ። ከሙዚቃ ስራቸው በተጨማሪ በቺካጎ የሬጌ ክለብ፣ በኢትዮጵያ የእርሻ ስራ እና በ "One Love Africa Foundation" አማካኝነት በኢትዮጵያ ገጠራማ ክፍሎች ትምህርት ቤቶችን የመገንባት ሰፊ ራዕይ ነበራቸው።
አቶ አዲስ ገሰሰ ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ በክብር ያስጠሩ፣ የሙዚቃውን ኢንደስትሪ ያሳደጉ እና ለብዙዎች መነሻ የሆኑ ታላቅ ሰው ናቸው። በድንገተኛ ህልፈታቸው የሙዚቃው ዓለም፣ ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጆቻቸው፣ እንዲሁም አድናቂዎቻቸው ጥልቅ ሀዘን ላይ ይገኛሉ።
ነፍስ ይማር! አቶ አዲስ ገሰሰ፣ ስራዎ እና አሻራዎ ለዘለዓለም ሲታወስ ይኖራል።

ሰላም! እንደምን አደራችሁ?
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም የዜጎች ድርሻ...
አንድነት በብዙ ፈተናዎች ውስጥ አልፎ ሀገር በማጽናት ለትውልድ ለማስተላለፍ ትልቅ አቅም መሆኑን ለማስረዳት ኢትዮጵያውያን ህያው ምስክር ናቸው።
የአንድነትን ምስጢር ከመተረክ ባለፈ የሀገራቸውን ዳር ድንበር፣ ታሪክና የተፈጥሮ ሀብት ለማስከበር ከሀገር በፊት በመሰዋት በተግባር ኖረውታል።
ትናንት ኢትዮጵያን ለማጽናት ከቅኝ ገዢዎች ጋር ተፋጠው በዓድዋ የድል ታሪክ አትመዋል፤ በኋላም የፋሺስት ጣሊያንን ዳግም ወረራ እምቢኝ በማለት በዱር በገደል ተዋድቀዋል።
እነዚህ ደማቅ ድሎች የዛሬው ብሎም የነገው ትውልድ በሀገሩ እንዲኮራ ከማድረግ የተሻገረ የአንድነትን ጉልበት በተግባር የገለጡ የታሪክ ምስክር ናቸው።
ኢትዮጵያ የትውልድ ድርሻቸውን በመወጣት ፈንታ ትናንትን ብቻ በማየት የተጠመዱ ዜጎች አይበጇትም፤ የዚህ ትውልድ ድርሻ ከትናንት በመማር፣ ዛሬ ላይ በመትጋት ለነገ የተሻለች ሀገር ማቆየት ነው።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ይህን የተገነዘበ ሀገራዊ ርዕይ ተሰንቆ ኢትዮጵያን በቀጣናው ብሎም በአህጉሪቱ የብልጽግና ምልክት ለማድረግ ብዙ ርቀት መጓዝ ተችሏል።
ኢትዮጵያ በዋዛ ፈዛዛ የተነጠቀቻቸውን ታሪካዊና ስትራቴጂያዊ ሀብቶቿን ለማስመለስ የጀመረቻቸው የዲፕሎማሲ ጥረቶች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ማግኘት ከጀመሩ ሰነባብተዋል።
ይህ ትውልድ እነዚህ መልካም ጅምሮች ፍሬ አፍርተው ኢትዮጵያን የብልጽግና ተምሳሌት በማድረግ ረገድ በቀደምት አባቶቹ የህይወት መስዋዕትነት የተረከበው አደራ አለበት።
ትውልዱ አደራውን እና የዜግነት ድርሻውን በወጉ እንዲወጣና ከዳር ድንበር ሉዓላዊነት ባሻገር በኢኮኖሚ ጫና ያልጎበጠች ሀገር ለነገ ለማቆየት የሚችልበትን ቁልፍ ጭምር መውረሱን ልብ ይሏል።
ይህ ቁልፍ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በማስከበር ለባዕዳን የማትንበረከክ ጠንካራ ሀገር ለልጆቹ ለማውረስ በጎሳና በሀይማኖት፤ በብሔርና በመደብ ሳይለያይ በአንድነት የመቆም ኃይል ነው።
ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሀገራቸውን ከማጽናት ባለፈ ለአፍሪካውያን የነጻነት ተጋድሎ አርዓያ ሆነዋል፤ ውቅያኖስ ተሻግረው በደም መስዋዕትነት ለወዳጅ ሀገራት ጋሻ ሆነዋል።
ኢትዮጵያ የምታነሳቸው የብሔራዊ ጥቅም ጥያቄዎች የህልውና ጉዳይ በመሆናቸው ከመንግስት የዲፕሎማሲ ርምጃዎች ባሻገር የሕዝቦቿን አንድነት በጽኑ ትሻለች።
ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ከፍታ በአንድነት መቆማቸው የሚኮሰኩሳቸው አንዳንድ የውጭ ኃይሎች የሁለንተናዊ ብልጽግና ጉዞዋን ለማደናቀፍ የሚገለገሉባቸው የውስጥ ባንዳዎች እዚም እዚያም ሲፍጨረጨሩ ይስተዋላል።
ኢትዮጵያ በዘመናት መካከል ጠላቶቿን ድል እየነሳች ጸንታ የዘለቀችው ባንዳዎች ስላልነበሩ ሳይሆን የሕዝቧን የአንድነት ገመድ መበጠስ ስላልተቻላቸው ነው።
አበው "ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው" እንዲሉ፥ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተመዘገቡ አስደናቂ ለውጦችን የካደ አሉባልታ በመንዛት ሕዝቡን ከልማት ለማናጠብ የሚኳትኑ አካላት ተበራክተዋል።
ሕዝቡ እኚህ የባዕዳን ተቀላቢ ባንዳዎች በተለያዩ መንገዶች ለሚያሰራጩት መሰረተ ቢስ ወሬ ጆሮ ሳይሰጥ አንድነቱን አጥብቆ በጀመረው የልማት መንገድ መጓዝን መርጧል።
የኢትዮጵያ መጪ ዘመናት ባዕዳን እንደደገሱላት የጥፋት ምኞት ሳይሆን በሕዝቧ ከአለት የጠነከረ አንድነት ጸንታ በከፍታ የምትታይበት እንደሚሆን መላው ኢትዮጵያውያን በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያሳዩት ቁርጠኝነት እማኝ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያውያን በምርጫው የነበራቸውን ተሳትፎ በማውሳት "ተዓምረኛ ሕዝብ" በማለት መግለጻቸውም ሕዝቡ የአንድነትን ኃይል በቅጡ መረዳቱን የሚያጠይቅ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፥ "የዳበረ ባህል፣ እጅግ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል" ነበር ያሉት።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኡጋንዳው ጄኔራል ህወሀት ድጋሚ ጦርነት እንዳይጀምር ተማፀኑ፡፡ የኡጋንዳ መከላከያ ሀይል ዋና አዛዥ የሆኑት ጄኔራል ሙሁዚ ኪያንሩግባ ዛሬ በኤክስ ገፃቸው ላይ ኢትዮጵያን የተመለከተ አስተያየት አስፍረዋል፡፡
ይህ የጄኔራሉ መልእክት በቀጥታ ህወሀትን የሚመለከት ሲሆን ሲናገሩም ‹‹በትግራይ የሚገኙ ታላላቅ ወንድሞቼ ሌላ ጦርነት እንዳይጀምሩ እለምናቸዋለሁ፡፡ በጣም እወዳቸዋለሁ ግን ጦርነት ሰልችቶናል›› ብለዋል፡፡ አክለውም ‹‹አሁን ወንድሜን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን እደግፋለሁ›› በማለት አስታውቀዋል፡፡ የፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ልጅ የሆኑት እኚህ ጄኔራል አወዛጋቢ አስተያየቶችን በመስጠት የሚታወቁ ናቸው፡፡

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያውያን የልብ ትርታ የሆነው፣ ባህልና ስፖርትን አዋህዶ በየዓመቱ የሚያገናኘን ታላቁ የኢትዮጵያ ስፖርት እና ባህል ፌስቲቫል (ESFNA) ወደ ሚኒሶታ ሲመጣ፣ ዘንድሮ ከወትሮው የተለየ ደማቅ የሙዚቃ ፌሽታን ይዞ መጥቷል።
"ታዲያ በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ ማንን እናያለን?" ብላችሁ በጉጉት ለምትጠብቁ...
የናፍቆት እና የትዝታ ማዕበልን የሚያመጣው በመድረክ ላይ ባለው ልዩ ንቃት እና ሞቅታ የሚታወቀው ተወዳጁ ድምጻዊ ዳዊት መለሰ አየሩን በዜማ ሊያናውጠው ወደ ሚኒሶታ እየመጣ ነው! ያ ብቻ አይደለም፤ ልብን በሚያማልሉ... ጥልቅ እና ለዛ ባላቸው ዜማዎቹ የምናውቀው ድንቁ ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህም በዚህ ደማቅ የኢትዮጵያውያን ስብስብ ላይ ተገኝቶ ነፍስን የሚያረካ የሙዚቃ ግብዣ ሊያቀርብልን ጓዙን ጠቅልሏል።
ይህ ታላቅ የሙዚቃ እና የባህል ምሽት ሐሙስ፣ ጁላይ 2 ቀን 2026 (Thursday, July 2, 2026) የሚካሄድ ሲሆን... እኚህ ሁለት ከዋክብት ሚኒሶታን በዜማ ሊያደምቋት ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል!
ነገር ግን ይህ ገና ጅምር ነው! የዘንድሮው ፌስቲቫል የጥበብ ሰራዊት በዚሁ አያበቃም፤ መድረኩን የሚያደምቁ ሌሎች ድንቅ አርቲስቶችንም በተከታታይ ይዘንላችሁ እንቀርባለን።
የዘንድሮውን ESFNA እንዳያመልጣችሁ፤ ቀኑን በቀን መቁጠሪያችሁ ላይ አስፍሩ፣ ጫማችሁን አዘጋጁ፣ ለጭፈራ ተነሱ! ሚኒሶታ ዘንድሮ በኢትዮጵያዊያን ዜማ፣ ፍቅር እና ፌሽታ ልትደምቅ ነው! #esfna #minnesota #esfna2026 #esfnamn

"ደከመኝ!?"
የእማማ ገሎ የፅናት ጉዞ ...
#ethiopia | እጅን ለሰው ከመዘርጋት ይልቅ በጥረታቸው መኖርን የመረጡት የእኚህ እናት ታሪክ ለብዙዎች ትልቅ አስተምህሮት የሚሰጥ ነው።
መለመን በሰፋበት በዚህ ዘመን እሳቸው ግን ክብራቸውን አስጠብቀው በጥቂት ሎሚዎች ንግድ ራሳቸውን ለማስተዳደር ፀሐይን ተቋቁመው ይገኛሉ።
አራት ፍሬ ሎሚዎችን ብቻ ይዘው ወደ ገበያ የወጡት እኚህ እናት አንዱን ፍሬ በአስር ብር በመሸጥ በአጠቃላይ አርባ ብር ለማግኘት ነበር የደከሙት።
በአሁኑ ወቅት ይህ ገንዘብ ለአንድ ዳቦ ግዢ እንኳን የማይበቃ ቢሆንም፣ የእሳቸው ምርጫ ግን የሰው ፊት ከማየት ይልቅ በላባቸው መኖር ሆኗል።
እናትህ / እናትሽ
እርዳታን ከመጠባበቅ ይልቅ የራሳቸውን ጥረት እንደ ምክንያት በመጠቀም በክብር ማደርን መርጠዋል።
እናቴ!
እማማ ገሎ ወይም ገሎ ከበሺ ይባላሉ። በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሃያ ዓመታት በላይ የኖሩ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የሚግባቡት በጉራጊኛ ቋንቋ ነው። ይህንን ያህል እድሜ ቢያስቆጥሩም ዛሬም ድረስ በላስቲክ በተሰራ መጠለያ ውስጥ ህይወታቸውን በጉሊት ንግድ እየደገፉ ይኖራሉ።
በዕለቱ አራት ፍሬ ሎሚዎችን ይዘው የወጡት እሷ ተሸጣላቸው ለልጆቻቸውና ለልጅ ልጆቻቸው እንጀራ ገዝተው ለመግባት ነበር። በዚህ እድሜ ድጋፍ እንጂ ድካም ባልተገባቸው ነበር።
እናትህ / እናትሽ
ለወጣቱ ትውልድ የሥራ ፍቅርንና የፅናትን ትልቅ ትምህርት የሚያስተምሩ ቢሆንም፣ በአሁኑ ሰዓት አቅማቸው የደከመ በመሆኑ ሰብአዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።
በመሆኑም እናቴን
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
በሂሳብ ቁጥር
1000769117125
በስማቸው (Gelo Kebeshi) በተከፈተው አካውንት ድጋፍ ማድረግ ይቻላል።
በተጨማሪም ለክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በኩል ለእኚህ አረጋዊ እናት ተገቢው መጠለያ እንዲሰጣቸው ጥሪ ቀርቧል።
#ሰብአዊነት #አረጋውያን #ድጋፍ #ኢትዮጵያ #አዲስአበባ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

(ከተዋሕዶ ወርልድ) የአርሲ ተራሮች ለዘመናት የሰላም፣ የግብርና እና የአብሮነት ምልክት ሆነው ኖረዋል። የጠዋቱ ጸሐይ ሲወጣ የከብቶች ጩኸት፣ የእረኞች ዜማ እና የቤተ ክርስቲያን የደወል ድምፅ ተቀናጅተው መንፈስን የሚያድስ ተስፋን ይሰጡ ነበር። ዛሬ ግን... ዛሬ ከእነዚህ ተራሮች ጀርባ የሚወጣው ጭስ የዕጣን አይደለም፤ የቃጠሎ ነው። ዛሬ የሚሰማው ድምፅ የዝማሬ ሳይሆን የእንባ እና የዋይታ ነው። ከግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሺርካ እና በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች ላይ ያንዣበበው የሞት ጥላ፣ ንጹሐንን በግፍ ቀጥፏል፤ ታሪካዊ መቅደሶችንም ወደ አመድነት ቀይሯል።
ይህ የተዋህዶ ወርልድ ትንታኔ የቁጥሮች ድምር አይደለም፤ የ13 የከበሩ የሰው ልጆች ሕይወት መነጠቅ፣ የ101 ዓመት ታሪክ መቃጠል፣ እና የ280 ዜጎች በባዶ እጅ መሰደድ ታሪክ እንጂ። ይህ፣ ሃይማኖት እና ማንነትን መሠረት አድርጎ የሚፈጸም አክራሪነት የሰውን ልጅ ምን ያህል ወደ አውሬነት እንደሚቀይረው የሚያሳይ የዘመናችን ህያው ማሳያ ነው።
የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንን እናስበው። ለ101 ዓመታት ሙሉ፣ አባቶች እና እናቶች በደጃፉ ተንበርክከው ፈጣሪያቸውን ተማጽነዋል። በዚያ መቅደስ ውስጥ ስንቱ ተጠምቋል? ስንቱ ተክሊል አስሯል? ስንቱስ በጸሎት ተጽናንቷል? ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ የቆመው ይህ የጸጋ ቤት፣ የበርካታ ትውልዶች የእምነት ማህደር ነበር። ነገር ግን፣ ጥላቻ ታሪክን አያውቅም፤ ክፋት ቅድስናን አይረዳም። በአንድ ጀንበር፣ ያ ሁሉ ታሪክ፣ ያ ሁሉ የእንጨት ጠረንና የዕጣን መዓዛ፣ በጭካኔ እሳት ተበላ።
በሌላ በኩል ደግሞ የካራ ኩፍተና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ዕጣ ፈንታ ሌላ ልብ ሰባሪ ትዕይንት ነበር። ታጣቂዎች መቅደሱን ሲዘርፉ፣ አማኞች የራሳቸውን ሕይወት እና ንብረት ለማዳን አልተጣደፉም። ይልቁንም፣ መኖሪያ ቤታቸው እያዩት በእሳት ሲጋይ፣ የዕድሜ ልክ ጥሪታቸው፣ ከብቶቻቸውና ማሳቸው ሲዘረፍ፣ እነርሱ ግን ከሁሉ የሚያስበልጡትን የቤተ ክርስቲያኑን ጽላት (ታቦት) በደረታቸው አቅፈው በጨለማ ወደማያውቁት ስደት መጓዝን መረጡ።
ይህ ትዕይንት ወደ ኋላ መለስ ብለን የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪክ እንድናስታውስ ያደርገናል። እስራኤላውያን ታቦተ ጽዮንን ተሸክመው በበረሃ እንደተጓዙት ሁሉ፣ የአርሲ ምእመናንም አምላካቸውን በደረታቸው አቅፈው መከራውን ተቀበሉ።
ሞት በቁጥር ሲገለጽ ስሜት አይሰጥም፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ቁጥር ከጀርባው ቤተሰብ፣ ተስፋ እና ህልም አለው። በአጠቃላይ 13 ንጹሐን ኦርቶዶክሳውያን በግፍ ተገድለዋል።
የ80 ዓመቱን አቶ አማረ በላይነህን እንመልከት። እኚህ አረጋዊ በህይወት ዘመናቸው ስንት መንግስታትን አይተዋል? ስንት የሀገር መከራን አሳልፈዋል? በስተእርጅናቸው ዘመን ክፋት አላርፍ ብሎ አስጨናቂ ሞትን አመጣባቸው። የ70 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ የሆኑት አቶ ደምረው አበራ፣ አቶ ሐይሉ ንጉሴ እና አቶ ሰሙ አባይነህም እንዲሁ የዚህ ጭካኔ ሰለባ ሆነዋል። እነዚህ አባቶች ለሀገር ምርቃት እንጂ መርገም ያልነበሩ፣ በእምነታቸው ጸንተው የኖሩ የሰላም ሰዎች ነበሩ።
እንደነ እሸቴ ዳመና (42 ዓመት) እና አበባየሁ ዳኜ (42 ዓመት) ያሉ የጎልማሳነት ዘመናቸው ላይ የነበሩ አባወራዎች ሲገደሉ፣ ከጀርባቸው ስንት ቤተሰብ በትነው እንደሄዱ ማሰብ ያሳምማል። ገና ለሀገር እና ለወገን ይደርሳሉ የተባሉ ወጣቶችም የዚህ ጽዋ ቀማሾች ሆነዋል። ተሬ ደሴ (የ25 ዓመት ወጣት)፣ ገነነ ጥላሁን እና ሙርቴሳ ጥላሁን በሺርካ ወረዳ ሕልማቸው ተጨናግፎ፣ ደማቸው በመሬት ላይ ፈሷል።
አቶ ንጉሱ ማንደፍሮ፣ አቶ በቀለ ኃ/ሚካኤል፣ ከፈለኝ ልክየለው... እነዚህ ስሞች ዝም ብለው በወረቀት ላይ የሰፈሩ አይደሉም። እነዚህ አባቶች ያሏቸው፣ እናቶች ያሳደጓቸው፣ ልጆች የሚጠብቋቸው ነፍሶች ነበሩ። በሃይማኖታቸው ምክንያት ብቻ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።
ይህ ዓይነቱ እምነትን መሠረት ያደረገ መከራ፣ በዓለማችን ታሪክ አዲስ አይደለም። የሰው ልጅ በፈጣሪው በማመኑ ብቻ የተከፈለው ዋጋ ብዙ ነው።
ወደ ሩቅ ጎረቤት ሀገር ግብጽ ስንሄድ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ለዘመናት በእምነታቸው ምክንያት ከፍተኛ ዋጋ ሲከፍሉ ኖረዋል። በተለይም እ.ኤ.አ. በ2015 በሊቢያ የባህር ዳርቻ አይ ኤስ በተባለው አሸባሪ ቡድን የታረዱት 21 የግብጽ ኮፕቲክ ክርስቲያኖችን ዓለም መቼም አይረሳም። ቢላዋ በአንገታቸው ላይ ሲያርፍ እንኳን የፈጣሪያቸውን ስም እየጠሩ በድፍረት ሰማዕትነትን ተቀብለዋል። የአርሲዎቹም ሰማዕታት ከዚሁ የጽናት መንገድ የወጡ አይደሉም። ኢትዮጵያውያንም በተመሳሳይ በሊቢያ እንዲሁ።
ወደ ምዕራብ አፍሪካ ስናቀና ደግሞ ናይጄሪያ እናገኛለን። በቦኮሃራም እና በአክራሪ የፉላኒ ታጣቂዎች አማካኝነት በሰሜን እና በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍል በሺዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች አብያተ ክርስቲያናቶቻቸው ተቃጥለውባቸው፣ መንደራቸው ወድሞ በግፍ ተጨፍጭፈዋል።
የአርሜንያ የዘር ማጥፋት ታሪክም ሌላው ትልቅ ትምህርት ነው። በ1915 በኦቶማን ኢምፓየር ዘመን፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ አርመናውያን በክርስትና እምነታቸው እና በማንነታቸው ምክንያት ብቻ በግፍ ተጨፍጭፈዋል፣ በበረሃም ተሰደው አልቀዋል። ነገር ግን ዛሬ አርሜንያውያን ከየትኛውም ጊዜ በላይ አብበው፣ እምነታቸውንም አጽንተው ይገኛሉ። ጥይት እና እሳት ስጋን ሊገድል ይችላል፣ እምነትን እና መንፈስን ግን መቼም ሊያጠፋ አይችልም።
ታዋቂው የጥንት ቤተ ክርስቲያን ጸሐፊ ቴርቱሊያን እንዳለው፡-
"የሰማዕታት ደም የቤተ ክርስቲያን ዘር ነው።"
በአርሲ ተራሮች ላይ የፈሰሰው የነ አቶ አማረ፣ የነ ወጣት ተሬ ደሴ ደም በከንቱ አይቀርም። የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚያስተምረን፣ መከራ በበዛ ቁጥር፣ መቅደሶች በነደዱ ቁጥር፣ የእምነት ስር ይበልጥ ይጠልቃል እንጂ አይደርቅም።
በእንደዚህ ዓይነት ጥልቅ ሀዘን እና የሰብአዊነት ውድቀት ውስጥ ስናልፍ፣ የሰው ልጅ ታሪክ ካፈራቸው ታላላቅ መሪዎች እና ፈላስፎች የምንማረው ብዙ ነገር አለ። ጭካኔን በጭካኔ መመለስ የትም አያደርስም።
የሰብአዊ መብት ታጋዩ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር (የተናገረው ኃያል ቃል በዚህ ጊዜ ትዝ ይለናል፡-
"ጨለማ ጨለማን ሊያባርር አይችልም፤ ይህንን ማድረግ የሚችለው ብርሃን ብቻ ነው። ጥላቻ ጥላቻን ሊያጠፋ አይችልም፤ ይህንን ማድረግ የሚችለው ፍቅር ብቻ ነው።"
በአርሲ የተፈጸመው ድርጊት የጨለማ እና የጥላቻ ፍሬ ነው። ነገር ግን የተፈናቀሉት ምዕመናን ጽላቱን አቅፈው መውጣታቸው፣ ብርሃንን እና ፍቅርን ምርጫቸው እንዳደረጉ ያሳያል።
የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊው እና የሆሎኮስት (የአይሁዳውያን ጭፍጨፋ) ተራፊው ኤሊ ዊሰል ስለ ግፍ ዝምታ ሲናገር፡-
"ዝምታ ሁልጊዜም የሚጠቅመው አጥቂውን እንጂ ተጠቂውን አይደለም። ገለልተኝነት የሚረዳው ጨቋኙን እንጂ ተጨቋኙን አይደለም።" ብሎ ነበር።
ስለሆነም የነዚህን ንጹሐን መገደል፣ የ101 ዓመት ታሪካዊ ቅርስ መቃጠል፣ እና የ280 ሰዎች መፈናቀል እንደ ቀላል ዜና አልፈነው ልንሄድ አይገባም። ህመማቸውን ልንጋራ፣ ድምጻቸው ልንሆን ይገባል።
ታላቁ የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ደግሞ ስለ መጽናት እንዲህ ይላሉ፡-
"ትልቁ የህይወት ክብር ያለው ፈጽሞ ባለመውደቅ ውስጥ ሳይሆን፣ በወደቅን ቁጥር ተመልሶ በመነሳት ውስጥ ነው።"
ኦርቶዶክሳውያኑ ዛሬ ቤታቸው ፈርሶ፣ ዘመዶቻቸው ተገድለውባቸው ሜዳ ላይ ወድቀው ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን እምነታቸው እስካለ ድረስ፣ ነገ ከአመዱ ላይ ተመልሰው ይነሳሉ።
በአሰኮ ወረዳ ብቻ ከ280 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ተፈናቅለዋል። መፈናቀል ማለት መጓዝ ብቻ አይደለም። መፈናቀል ማለት ትዝታን፣ ልፋትን፣ የልጅነት የቦረቁበትን አፈር፣ እና የዘመዶችን መቃብር ትቶ መሄድ ማለት ነው። እነዚህ ሰዎች አሁን ያሉት ሜዳ ላይ ነው። የለበሱት ልብስ ብቻ ነው ያላቸው። የሌሊቱ ብርድ ሲቆራርጣቸው፣ የጠዋቱ ጸሐይ ሲያቃጥላቸው፣ የልጆቻቸው ርሃብ አንጀታቸውን ሲበላው... ያላቸው ብቸኛ መጽናኛ በደረታቸው ያቀፉት እምነታቸው ብቻ ነው።
"ስለ አንተ ሁልጊዜም ተገድለናል እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል" (መዝሙር 43:22)። የአርሲና ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሀዘን መግለጫቸውን የጀመሩት በዚህ የዳዊት መዝሙር ነበር። ይህ ቃል የዛሬን ብቻ ሳይሆን የዘመናትን የክርስቲያኖችን ህይወት የሚገልጽ ነው።
በእርግጥም እንደ በግ ለመታረድ የተሰለፉት እነዚህ ወገኖች ጥፋታቸው ምንድን ነው? ከማንም ጋር ያልተጣሉ፣ የፖለቲካ አጀንዳ የሌላቸው፣ ኑሯቸውን ለማሸነፍ መሬት የሚጭሩ ምስኪን ገበሬዎች ነበሩ። ነገር ግን በአክራሪነት የታወረው አእምሮ ይህንን ሊረዳ አይችልም።
እሳት ሁሉንም ነገር ያወድማል፤ መጽሐፍትን ያቃጥላል፣ ግድግዳን ያፈርሳል፣ ስጋን ያጠፋል። ነገር ግን እሳት እምነትን ሊያቃጥል አይችልም። የ101 ዓመቱ የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ዛሬ በአካላዊ ገጽታው ባይኖርም፣ ያ መቅደስ የሰራው መንፈሳዊ ህንጻ ግን አሁንም በምዕመናኑ ልብ ውስጥ ጸንቶ ይገኛል።
የ13ቱ ሰማዕታት ነፍስ በሰላም ታርፋለች፤ ደማቸው ግን ለትውልድ የሚተላለፍ የጽናት ትምህርት ሆኖ ይኖራል። የተሰደዱት ወገኖቻችን ዛሬ ሜዳ ላይ ቢሆኑም፣ የታሪክ ጌታ የሆነው አምላክ ነገን አዲስ አድርጎ ይሰራላቸዋል። የጥላቻ ኃይሎች በክፋታቸው መቅደሱን አፍርሰውታል፤ ሆኖም እውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን የድንጋይ እና የእንጨት ክምር ሳትሆን፣ ያቺ በስደት መሃልም ጽላቷን አቅፋ የምትጓዘዋ የሰው ልጅ ልብ ናት።
እስከዚያው ግን እንደ አቡነ ኤልሳዕ ጸሎት፤ ፈጣሪ የሞቱትን ነፍስ በመንግሥተ ሰማያት ያሳርፍ፣ የተፈናቀሉትን፣ የተራቡትን እና የተራቆቱትን ደግሞ በምህረት እጁ ይጎብኝ፣ ያጽናናም። ከጭስ እና ከአመድ በስተጀርባ፣ ብርሃን አለና።

"ኢትዮጵያ በመከፋፈል ሳይሆን በአንድነት የደመቀ... አገር ሆና እንድትቀጥል ለማየት ነው ምኞታችንና ጸሎታችን!!"
#ethiopia | የዘንድሮውን የ7ኛ ዙር አገራዊ ምርጫ ለመታዘብ የሚያስችለኝን ዕድል አግኝቼ ነበር። እናም በግልና የተለያዩ ተቋማትን ወክለን የመጣን የአገር ውስጥ ታዛቢ ቡድን አባላት ምርጫውን ለመታዘብ ከመጡ የአፍሪካ ኅብረት እና የኢጋድ የታዛቢ ቡድን አባላት ጋር በስካይ ላይት ሆቴል የትውውቅና ሰፋ ያለ የጋራ ውይይት አድርገን ነበር።
በዚህ ውይይት ላይም የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪና የቀድሞ የኡጋንዳ የቀድሞው ምክትል ፕሬዚደንት የነበሩት ዶ/ር ዋንዲራ ካዚብዌ በምክር መልኩ ለወጣቶች ያነሱት ሐሳብ ቀልቤን ገዛው። እናም ከእኚህ ጉምቱ ፖለቲከኛ አፍሪካዊ እናት ከሐሳባቸው ጥቂት ሰበዞችን ለመምዘዝ ወደድኹ።
በአገራቸው ኡጋንዳ ፖለቲካ ውስጥ የሴቶችን/የእናቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ትርጉም ባለው መንገድ በመቀየር ጉልህ አሻራ ያኖሩት የህክምና ሳይንስን ከሥነ-መንግሥት ትምህርት ጋር ያጣጣሙ እኚህ አፍሪካዊ ምሁር እናት በውይይታችን መካከል እንዲህ አሉን።
"When women lead, even water climbs uphill."
"ሴቶች ሲመሩ ውኃ ሳይቀር እንኳን ሽቅብ ይፈሳል፤" የሚል አፍሪካዊ አባባል አለ።
መቼም ለዚህ አባባል እናንት ኢትዮጵያውያን ሕያው ምስክሮች ናችሁ። ከኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ሳባ፣ የዐድዋውን ጦርነት በሴትነት ብልሃት ከመሩት እቴጌ ጣይቱ ድረስ የአገራችሁ የፖለቲካ ታሪክ በሴቶች ጉልህ ተሳትፎና አሻራ የደመቀ ነው።
በእውነት በእነዚህ ጀግኖች እናቶቻችሁ ታሪክ ልትኮሩ፤ ልትደነቁ ይገባችኋል።
ዶ/ር ካዚብዌ ቁጭት በቀላቀለ ስሜት ያነሱትን ሌላኛው የሐሳባቸውን ሰበዝ ለዚህች አጭር ማስታወሻ መደምደሚያ ይሆነኝ ዘንድ መረጥኩት።
እኛ አፍሪካውያን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን እንደ ሸቀጥ ዕቃ ሙሉ በሙሉ ከምዕራቡ ዓለም ለማስገባት የምናደርገውን ልፋት ቆም ብለን መፈተሽ ይገባናል። ከሌሎች የምንቀበለውን ያህል እኛ አፍሪካውያን ለተቀረው ዓለም ልንሰጠው የምንችላቸው በርካታ ነገሮች አሉን።
አፍሪካ ለሺህ ዓመታት የቆየ የራሷ የሆነ ግዙፍ ታሪክ፤ ገናና ሥልጣኔ፤ በዘመናት ተፈትኖ ያለፈ የዳበረ ባህላዊ የፖለቲካ ሥርዓት ያላት አህጉር ናት። እናንት ኢትዮጵያውያን ደግሞ በዚህ የአኅጉራችን የአፍሪካ የሺህ ዘመናት ታሪክና ባህል ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ ትወስዳላችሁ።
ከአክሱም ገናና ሥልጣኔ የቅኝ ገዢዎችንና የተስፋፊዎችን ቅስም እስካንኮታኮተው የዐድዋ ድል ድረስ አኩሪ ታሪክ ያላችሁ ታላቅ ሕዝብ ናችሁ።
አብዛኛው የታሪካችሁ ምዕራፍ ሲገለጽም- የአንድነትን፤ የኅብረትን ኃይል ቀድሞ የተረዳችሁ ጠቢባን ሕዝቦች መሆናችሁን ነው የሚመስክረው። እናም ዛሬ ልዩነታችሁን በማጥበብ አንድነታችሁን አጠናከሩ፤ ኅብረታችሁን አጎልብቱ። አንድነት ኃይል ነው!!
ኢትዮጵያ በመከፋፈል ሳይሆን በአንድነት የደመቀ፤ በጦርነት ሳይሆን በሰላም ያሸበረቀ፤ በጥላቻ ሳይሆን በፍቅር የተዋበ አፍሪካዊ ተምሳሌትነቷንና እናትነቷን ያስመሰከረች አገር ሆና እንድትቀጥል ነው ምኞታችን፤ ተስፋችንና ጸሎታችን።
እግዚአብሔር አፍሪካን ይባርክ፤ አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!!
ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ አበው፤ ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን በመጡ ማግሥት- ኢትዮጵያውያን እናቶች ይጸልዩልኛል፤ የእናቶቼ ጸሎታቸውና ምርቃታቸው ያግዘኛል፤ ጉልበት ይሆነኛል። የሚል ቃልን አብዝተን ከአንደበታቸው አንሰማ ነበር። ዛሬስ...?!
ታላቁ መጽሐፍ፤ "የእናት ምርቃት ቤትን ያጸናል፤" እንዲል በእናቶቻችን ምርቃትና ጸሎት የሁላችን ቤት የሆነች ኢትዮጵያ፤ አፍሪካ የአንድነት መሠረቷ ጸንቶና ሰላሟ ተጠብቆ በአንድነት ጸንታ ትኖር ዘንድ በመመኘት ልሰናበት።
ሰላም!!
በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን)፤

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ‹‹አለም አቀፍ ሚዲያዎች በምርጫው ዙሪያ ያልተመጣጠነ አሉታዊ ትረካ እያቀረቡ ነው›› ሲሉ የኢዜማ መሪ ገለፁ፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ መሪ የሆኑት አቶ እዮብ መሳፍንት አለም አቀፍ ሚዲያዎች ከምርጫው በፊት ያልተመጣጠነ አሉታዊ ትርክት እያቀረቡ መሆኑን በመግለፅ ወቀሱ፡፡
እኚህ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ሚዲያዎቹ ‹‹የአገር ውስጥ እድገትንና የመራጮችን ተስፋ ችላ በማለት በአሉታዊ ዘገባዎች ላይ ተጠምደዋል›› በማለትም ገልፀዋል፡፡ አቶ እዮብ ከራይዝ ኤንድ ሻይን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ምርጫው በግጭት የተሸፈነ፣ አነስተኛ ተሳትፎ ያለበትና ተአማኒነት እንደሚያንሰው በስፋት በአለም አቀፍ ሚዲያዎች የተዘገበውን አጣጥለውታል፡፡
በአንዳንድ አካባቢዎች በተለይም በትግራይ ክልልና በአማራ ክልል ውስጥ ባለው አለመረጋጋት ምርጫ አለመካሄዱን ያረጋገጡት መሪው ይሁንና እነዚህ አካባቢዎች ከአጠቃላይ ምርጫው የተወሰነ ክፍል እንደሚሸፍኑ ገልፀዋል፡፡ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል ምርጫው በመካሄዱ የምርጫው ውጤት በመንግስት ምስረታ ላይ ተፅእኖ እንደማይፈጥር መናገራቸውን ቻናል አፍሪካ ካቀረበው ዘገባ ተመልክተናል፡፡

3 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በለንደን ኢትዮጵያዊው ላይ የግድያ ክስ ተመሰረተበት፡፡ ስካይ ኒውስ እንደዘገበው የ60 አመቱ እንግሊዛዊ ሚክላስ ኪራኩ በለንደን ጎዳና ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው ሀሙስ ሜይ 14 ቀን ነበር፡፡ ፖሊሶች በስፍራው ደርሰው እኚህን ግለሰብ በአምቡላንስ ወደሆስፒታል ከወሰዷቸው በኋላ የህክምና ክትትል ማድረግ ይጀምራሉ፡፡
ፖሊሶችም በእኚህ ግለሰብ ላይ አደጋውን ማን እንዳደረሰው የማጣራት ስራቸውን ይቀጥሉና እሁድ እለት የ36 አመቱ ኢትዮጵያዊ ቢንያም ተወልደ ነጋሽ በጉዳዩ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ይውላል፡፡ በቢንያም ላይ የመግደል ሙከራ ክስ ተመስርቶበት ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ ቀጠሮ ተሰጥቶት አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኝ ዘገባው አስረድቷል፡፡
ይሁን እንጂ የለንደን ሜትሮፖሊቲያን ፖሊስ እንደገለፀው በሆስፒታል ህክምናቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ተጎጂው ከ8 ቀናት በኋላ ትላንት አርብ ህይወታቸው አልፏል፡፡ በመሆኑም በእስር ላይ የሚገኘው ቢንያም ላይ በግድያ ሙከራ የሚለው ክስ ሰው መግደል ወደሚል መቀየሩን ፖሊስ አስታውቆ በመጪው ሰኞ በአዲሱ ክስ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ አስረድቷል፡፡

አበበች ጎበና የእልፎች እናት
#ethiopia | አፍሪካዊቷ ማዘር ቴሬዛ በመባል የሚታወቁት ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና ከሀገር ባለውለታነት አልፈው ለሰው ልጆች ትልቅ ክብርን በመስጠት በተለያዩ ምክንያቶች ወላጆቻቸውን ላጡ ልጆች እናትም አባትም ሆነው ሰው ከወደቀበት ቀና እንዲል አድርገዋል።
ክቡር የሆነውን የሰውን ልጅ ከጎዳና እያነሱ አጥበው፣ አብልተው፣ አስተምረው በርካታ ልጆችን ለቁም ነገር ማብቃት የቻሉ ጀግና ሴት ነበሩ።
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ግራር ጃርሶ ወረዳ ውስጥ ሸበል አቦ በተባለ የገጠር መንደር በ1928 ዓ.ም የተወለዱት ክብርት ዶ/ር አበበች ጐበና፤ በወቅቱ በነበረው ባህልና ልማድ በ11 ዓመታቸው ትዳር እንዲይዙ የቀረበላቸውን ጥያቄ በብቸኝነት በመቃወም ወደ አዲስ አበባ ገቡ፡፡
በአዲስ አበባ ስራ ሳይንቁ በግለሰቦች ቤት ከማገልገል ጀምሮ በተቋም ውስጥ ተቀጥረው እስከ ምርት ክፍል ኃላፊነት አገልግለዋል፡፡
ክብርት ዶ/ር አበበች (በልጆቻቸው አጠራር እዳዬ) በአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉ አብያተ ክርስትያናትን በማገልገል ከፍተኛ አበርክቶ ነበራቸው፡፡
በዚህም አጋጣሚ በ1972 ዓ.ም ለመንፈሳዊ ጉዞ በሄዱበት በሀገራችን ተከስቶ በነበረው የተፈጥሮ ድርቅ ሳቢያ ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ሁለት ህፃናትን በመያዝ አበበች ጐበና ህፃናት ክብካቤና ልማት ማህበርን መሰረቱ፡፡
ክብርት ዶ/ር አበበች (እዳዬ) ለ41 ዓመታት በሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናትን ተንከባከበው ለቁምነገር ያበቁ ሲሆን፤ ከዚህ ባሻገር ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ሰጥተዋል፡፡
በመሆኑም በተለያዩ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ መድረኮች ታላላቅ ሽልማቶችና እውቅናዎችን እንዲሁም ከጅማ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ በሰብዓዊነት ዘርፍ አግኝተዋል፡፡
ክብርት ዶ/ር አበበች (እዳዬ) ድህነትን በተለይም የህፃናት ጉስቁልናን መቅረፍ የሚቻለው በግለሰብ ደረጃ ለምፅዋት በሚወረወሩ ሽርፍራፊ ሳንቲሞች ሳይሆን በአንድነት በማበር እንደሆነ ያምናሉ።
በመሆኑም ያለውን አቅም በማሰባሰብ በችግር ላይ ያሉ ወገኖችን በተለይም ሴቶችን መደገፍና ማብቃት ይገባል የሚል ጽኑ እምነት ነበራቸው፡፡
እኚህ ለእልፎች እናትም አባትም ሆነው ለነገ ተስፋቸው መንገድ የጠረጉ እናት በሰኔ ወር 2013 ዓ.ም በኮሮና በሽታ ምክንያት በተወለዱ በ85 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ክብርት ዶክተር አበበች ጎበና ቢያልፉም አበበች ጐበና ህፃናት ክብካቤና ልማት ማህበር ዛሬም ድረስ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት እየቀየረ ይገኛል።
አበበች ጎበና ለብዙ ኢትዮጵያውያን የቸርነት፣ የጥንካሬ እና የፍቅር ተምሳሌት ሆነው በበጎ አድራጎት ስራቸው ትውልድ ሲዘክራቸው ይኖራሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #fmc

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አፍሪካዊቷ ማዘር ቴሬዛ በመባል የሚታወቁት ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና ከሀገር ባለውለታነት አልፈው ለሰው ልጆች ትልቅ ክብርን በመስጠት በተለያዩ ምክንያቶች ወላጆቻቸውን ላጡ ልጆች እናትም አባትም ሆነው ሰው ከወደቀበት ቀና እንዲል አድርገዋል።

ዝነኛው የተፈጥሮ ተመራማሪ ዴቪድ አተንበራ 100ኛ ዓመት ልደታቸውን አከበሩ
*****************
ታዋቂው ብሪታንያዊ የተፈጥሮ ተመራማሪ እና የዶክመንተሪ አዘጋጅ ሰር ዴቪድ አተንበራ 100ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን አክብረዋል።
በዝነኞቹ "Planet Earth" እና "Blue Planet" ፊልሞቻቸው የምናውቃቸው እኚህ ታላቅ ሰው፣ ለሰባት አስርተ ዓመታት ዓለምን ስለ ተፈጥሮ ሲያስተምሩ ቆይተዋል።
"መጠበቅም ሆነ ማጥፋት እንችላለን፣ ምርጫው የእኛ ነው" በማለት ለተፈጥሮ ጥበቃ የሚሟገቱት አተንበራ፣ ዛሬም በ100 ዓመታቸው ለዓለም ተስፋን እየሰጡ ይገኛሉ።
ሰር ዴቪድ አተንበራ፦
• በቴሌቪዥን ታሪክ ረጅሙን የሥራ ዘመን በማሳለፍ የጊነስ ወርልድ ሪከርድ ባለቤት ናቸው።
• ሁለት ጊዜ የ"ሰር" ማዕረግ ያገኙ ሲሆን፣ ለኖቤል የሰላም ሽልማትም ታጭተዋል።
• ቴሌቪዥን ከጥቁር እና ነጭ ወደ ቀለም፣ ከዚያም ወደ HD እና 4K ሲቀየር በሁሉም ዘመን ሽልማት ያገኙ ብቸኛ ሰው ናቸው።
• እ.አ.አ በ1979 ከጎሪላዎች ጋር ያደረጉት ዝነኛ ቆይታ በተፈጥሮ ዶክመንተሪ ታሪክ ውስጥ የማይረሳ ትዕይንት ነው።
• ከ40 በላይ የሚሆኑ የእፅዋት እና የእንስሳት ዝርያዎች በእርሳቸው ስም ተሰይመዋል።
• ገዳይ እባቦችንና ጊንጦችን የማይፈሩት ሰር ዴቪድ አተንበራ፣ አይጥ በጣም ይፈራሉ።
#davidattenborough #100years #nature #planetearth #ebc

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአሜሪካ 16 ወታደራዊ ጦር ሰፈሮች ላይ ጉዳት መድረሱ ተዘገበ፡፡ ሲኤንኤን ቴሌቪዥን ባቀረበው ዘገባ ፌብሩዋሪ 28 በተጀመረው እስራኤልና አሜሪካ በኢራን ላይ በከፈቱት ጦርነት ቢያንስ 16 የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጿል፡፡ ይህንን ጉዳት ያደረሱት ኢራንና አጋሮቿ መሆናቸውንና ጉዳቱም በ8 በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ የጦር ሰፈሮች ላይ ያጋጠመ መሆኑን አስረድቷል፡፡ ቅርበት ያላቸውን ምንጮቹን የጠቀሰው ዘገባው ጉዳቱ ካጋጠማቸው ጦር ሰፈሮች ውስጥ አንዳንዶቹ ጥቅም መስጠት በማይችሉበት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡
አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያለው የኮንግረስ ምንጭ ለሲኤንኤን ሲናገር ‹‹በደረሰው ጉዳት ላይ የተለያዩ ግምገማዎች ተደርገዋል፡፡ ግምገማዎቹ መላው በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች በመውደማቸው ሊዘጉ ይገባል ከሚለው አንስቶ ከሚሰጡት ጥቅም አኳያ መጠገን ይኖርባቸዋል እስከሚለው የመሪዎች ሀሳብ ድረስ ናቸው›› ብለዋል፡፡ ዘገባው የሳተላይት ምስሎችን ጠቅሶ እንደገለፀው የቴሄራን መንግስት ዋና ኢላማዎች የነበሩት የአሜሪካ ዘመናዊ የራዳር ስርአቶች፣ የመገናኛ ሲስተሞችና አውሮፕላኖች ሲሆኑ አብዛኛዎቹ ውድና ለመተካት አስቸጋሪ ናቸው፡፡
ምንጩ ጨምረው እንዳሉት በመካከለኛው ምስራቅ አሜሪካ የነበራት የራዳር ስርአት እጅግ ውድ ከመሆኑም በላይ በጣም ውስን ከሚባሉት ሀብቶች መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡ እኚህ ምንጭ እንደምሳሌም በባህሬን የሚገኘው የአሜሪካ ፊፍዝ ፍሊት ባህር ሀይል ላይ የደረሰውን ጉዳት አንስተዋል፡፡ ይህንን የባህር ሀይል ሰፈር ለመጠገን 200 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡

የሕውሓቱ ጀነራል የፌዴራል መንግስቱ ላይ ዛቱ፡፡
ብልጽግናን ለማስወገድ ተዘጋጅተናል ሲሉ በአደባባይ ወጥተው ተናግረዋል፡፡ የጀነራል ታደሰን እንቅስቃሴ እግር በእግር እንዲከታተሉ ትእዛዝ የተሰጣቸው እኚህ ጀነራል፤ ሁሉም ነገር አልቋል በቅርቡ ጠብቁን ብለዋል፡፡ ይህ የጀነራሉ ዛቻ የተሰማው ከአሜሪካ እስከ አውሮፓ ህብረት ጦርነት እንዳይፈነዳ እያስጠነቀቁ ባለበት ወቅት ነው፡፡
የሕውሓት ፖለቲካዊ አመራሮች እና ወታደራዊ አዛዦች 4ኪሎ ላይ የሚያሰሙትን ዛቻ ቀጥለውበታል፡፡ ከሰሞኑ የቡድኑ አመራር አዲስአለም ባሌማ ‹‹ለሁሉም ነገር ተዘጋጅተናል፤ ሎጀስቲክ አዘጋጅተናል፤ከፋኖም ከሻብያም ጋር ተጣምረናል›› ማለታቸው አይዘነጋም፡፡ ዛሬ ደግሞ ከሕውሓት ወታደራዊ አዛዦች መሀል አንዱ የሆኑት የአርሚ 60 አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ህንፃ ወልደጊዮርጊስ ብልጽግናን ለመጣል ተዘጋጅተናል የሚል ከፕሪቶሪያ ስምምነት ያፈነገጠ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
ጀነራሉ የህወሓት ልሳን ለሆነው ወይን ሚዲያ በወቅታዊ ጉዳይ በሰጡት ማብራሪያ፣ “ማንም መጠራጠር የሌለብት ሁሉም ነገር አልቋል” ሲሉ ፉከራ አሰምተዋል፡፡ ጀነራሉ ብዙዎች ተሰውተውለታል ያሉትን በተናጠል ክልላዊ ምርጫ የተመሰረተውን፣ የህወሓት መንግሥት መመለስ የህልውና ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡
የሁለት ዓመቱን ደም አፋሳሽ ጦርነት መሬት ለማስመለስ ሳይሆን፣ 2.8 ሚሊዮን ህዝብ የመረጠጠውን መንግሥት ለማስመለስ ነው ያሉት ጀነራሉ፤ በጦርነቱ አንድ ሚሊዮን ገደማ ሰው ሞቷል የሚባለውን አስተባብለው፤ “አንድ ሚሊዮን ሰው ሞቷል የሚለውን ተውት፣ የተገደሉት በሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ጀነራሉ መስዋእት ከፍለንበታል ያሉትን ህወሓት መራሹን መንግሥት ለመመለስ ሙሉ ዝግጁ አለን ብለዋል፡፡ ዳግም ጦርነት ይቀሰቀሳል ተብሎ ከፍተኛ ስጋት ስለፈጠረው ውጥረት ማብራሪያ የሰጡት ጀነራሉ፣ “ድጋሜ ከተዋጋን የነብረውን መንግስት ለመመለስ ነው” ይላሉ፡፡
የፕሪቶሪያው ስምምነት ከዚህ በኋካ ዋጋ እንደሌለው የገለጹም ሲሆን፤ ከዚህ በኋላ ወደኋላ የሚመለስን ኃይል የለም ብለዋል፡፡ የፌደራል መንግሥት በስምምነት ሰበብ ትግራይ ከፋፍሏል በማለት የከሰሱ ሲሆን፣ እንደ ጌታቸው ረዳ ያሉ ግለሰቦችንም እንደ ጠላት እንታገላቸዋለን ብለዋል፡፡
ጀነራሉ ትግራይ ከድተዋል ያሏቸውን ኃይሎች ከፌደራል መንግሥት ጎን ተሰልፈው፣ የህወሓት አመራሮችን ለማጥቃት እየተዘጋጁ ነው በማለት ከሰዋል፡፡ በዚህም የህወሓት አመራሮች የጥቃት ኢላማ በመሆናቸው በነጻነት መንቀሳቀስ እንዳይችሉ መሆኑን የጠቆሙ ሲሆን፣ በእነ ደብረጽዮን በኩል ከወዲሁ ደብብቆሽ መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡
ከባለፈው ጦርነት ተምረናል ያሉት ጀነራሉ፣ ዳግም ውጊያ ከተቀሰቀሰ እንደበፊቱ በቀላሉ እጅ አንስጥም ብለዋል፡፡ የህወሓትን መንግሥት በመመለስ የቤት ሥራችንን ጨርሰናል ያሉት እኚሁ ወታደራዊ አዛዥ፣ ቀጣዩ ጉዞ የትግራይን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር ነው ብለዋል፡፡
seledadotio

የክቡር መቶ አለቃ ለማ አሰፋ የላቀ የሥራ ስኬትና የላቁ ተግባራት በቢሾፍቱ ከተማ ተዘከሩ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የግብርናና የኢንዱስትሪ ዘርፎች ውስጥ ለሰላሳ ዓመታት በሳቅ መሪነትና በታታሪነት ሲሰሩ የቆዩት የክቡር መቶ አለቃ ለማ አሰፋ የሕይወት ጉዞና የሥራ ውጤቶች የሚዘከርበት መርሃ ግብር ዛሬ በቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዷል።
በዕለቱም የቤተሰቦቻቸውን የሥራ ቅብብሎሽ ይፋ የማድረግ ስነ ስርዓት ተከናውኗል።
ባለፈው የካቲት ወር 2018 ዓም በድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት መቶ አለቃ ለማ አሰፋ በ1969 ዓም የኢትዮጵያ አየር ኃይልን በመቀላቀል እስከ መቶ አለቃ ማዕረግ ድረስ ሀገራቸውን በታማኝነት ያገለገሉ የጦር መኮንን ነበሩ።
ከወታደራዊ ግዳጃቸው ጎን ለጎንም በአሥመራ ዩኒቨርሲቲ በሕዝብ አስተዳደር የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በመያዝ እውቀታቸውን ያዳበሩ አንጋፋ ሰው ነበሩ።
በግል የንግድ ዘርፍም ቀዳሚ ከሆኑት መካከል አንዱ የነበሩት እኚህ ባለሀብት በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ የዶሮና የእንስሳት መኖ ማምረቻ ድርጅት ከመመስረታቸው ባሻገር አለማ ፋርምስ እና ሊዮስ የምግብ ዘይት ፋብሪካን የመሳሰሉ ግዙፍ ተቋማትን በማቋቋም በግብርናው ዘርፍ የሚታየውን የግብዓት እጥረት ለመቅረፍ ግንባር ቀደም ሆነው ሰርተዋል።
ከግማሽ ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠሩትና በተለያዩ የሙያ ማህበራት የቦርድ አመራር በመሆን ለሀገር ኢኮኖሚ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱት መቶ አለቃ ለማ በጥረታቸውና በእውቀታቸው ለኢትዮጵያ ወጣቶች ትልቅ አርአያ ሆነው ማለፋቸው በመታሰቢያው ፕሮግራም ላይ ተገልጿል።
ክቡር አቶ አባዱላ ገመዳ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች እንዲሁም ታዋቂ ባለሀብቶች በተገኙበት በዚህ መድረክ ላይ ሊዮስ የምግብ ዘይትና አኩሪ ምርቶች ድርጅት በቢሾፍቱ ለሚገኘው የኛ ለኛው የአረጋውያን መርጃ ማዕከል የ500 ሺህ ብር ድጋፍ በማድረግ የሟቹን በጎ አድራጊነት በግብር አሳይቷል።
#ቢሾፍቱ #አለማፋርምስ #ሊዮስዘይት #ኢንቨስትመንት #በጎአድራጎት #ኢንዱስትሪ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የመቶ አለቃ ለማ አስፋው የሥራ ስኬቶች ተዘከሩ!
#fastmereja :በኢትዮጵያ የግብርናው ዘርፍ በተለይም በእንስሳት እርባታና በምግብ ዘይት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ከፍተኛ አሻራ ያሳረፉት የመቶ አለቃ ለማ አስፋው የሥራ ስኬቶች የሚዘከሩበትና የቤተሰቦቻቸውን የሥራ ቅብብሎሽ ይፋ የሚያደርግ መርሃ-ግብር በዛሬዉ እለት ተካሂዷል።
በዛሬዉ እለት በተከናወነው በዚህ መርሃ-ግብር ላይ የተከበሩ አቶ አባዱላ ገመዳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ታዋቂ ባለሀብቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ባለፈዉ የካቲት 4 ቀን 2018ዓ.ም በድንገተኛ አደጋ ህይወታቸዉ ያለፉት መቶ አለቃ ለማ አስፋው፣ በአየር ኃይል መኮንንነት ካበረከቱት አገልግሎት ባሻገር በግሉ ዘርፍ ''አለማ ፋርምስ'' እና ''ሊዮስ የምግብ ዘይት'' የመሳሰሉ ግዙፍ ተቋማትን በመገንባት ከ500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠሩ ታታሪ ባለሀብት እንደነበሩ ተገልጿል።
በተጨማሪም መርሃ-ግብሩን ምክንያት በማድረግ "ሊዮስ የምግብ ዘይትና አኩሪ ምርቶች" ድርጅት በቢሾፍቱ ከተማ ለሚገኘው ''ለየኛ ለኛው የአረጋውያን መርጃ ማዕከል" የ500 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።
መቶ አለቃ ለማ አስፋው ከንግድ ሥራቸው ጎን ለጎን በኢትዮጵያ የእንስሳት መኖ፣ የወተትና የዘይት አምራቾች ማህበራት ውስጥ በቦርድ አመራርነት በማገልገል ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የሀገር ባለውለታ እንደነበሩ በዕለቱ ተገልጿል።
በጋቶ ተወልደው፣ በአስመራ ዩኒቨርሲቲ ተምረው፣ በአየር ኃይል አገልግለውና በንግዱ ዓለም ስኬታማ ሆነው ያለፉት እኚህ ሰው፤ ለኢትዮጵያ ወጣቶች "በታታሪነትና በዕውቀት ማንኛውንም ከፍታ መድረስ ይቻላል" የሚል ትልቅ የህይወት ትምህርት ትተው ማለፋቸዉ ነዉ የተገለፀዉ።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ኢንዴፕዝ ኒውስ የተሰኘው ድረ ገፅ ላይ ዛሬ የቀረበውን ይህንን ጥናት ያከናወኑት ዳንኤል ተስፋ፣ ስሂም ማሻ፣ ጆሊ ስቶከርና መሪያም ቫን ሬሰን የተሰኙ ጋዜጠኞች ሲሆኑ ጉዳዩን በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡ እነዚህ ጋዜጠኞች እንደሚገልፁት ይህንን ጥናት ያከናወኑት ከማርች 9 ቀን እስከ ኤፕሪል 11 ባሉት ቀናት ነው፡፡ በጥናታቸው ከማእከላዊ ትግራይ ዞን አድዋን፣ ኢንትጮን፣ እድጋ አርቢናና አክሱምን ማካለላቸውን፣ ከምስራቅ ትግራይ ዞን ሀውዜን ከተማ መግባታቸውንና በደቡባዊ ዞን ደግሞ ነቅሰኝ ወረዳንና ከሰሜን ምእራብ ዞን ሽሬ መሄዳቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በማእከላዊ ትግራይ ዞን እዳጋ አርቢ ወረዳ የሚገኙት አንድ አባት ለዜና አውታሩ በሰጡት መግለጫ የህወሀት ካድሬዎች የግዳጅ ምልመላ ለማድረግ ወደአካባቢያው መምጣታቸውን ገልፀዋል፡፡ ሲናገሩም ‹‹ማህበረሰቡን ለመቀስቀስ የህወሀት ካድሬዎች መጥተው ነበር፡፡ ነገር ግን ልጆቻችንን ለጦርነት አንልክም ብለን ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርገናል›› ብለዋል፡፡ እኚህ አባት ጨምረው እንደገለፁት ልጆቻቸውን እንዲያዋጡ ለመቀስቀስ የተጠራው ስብሰባ በተቃውሞ ከተበተነ በኋላ የህወሀት ካድሬዎች ፖሊስና ታጣቂ ሀይል አሰማርተው እድሜያቸው ከ15 አመት በላይ የሆኑትን መዝግበዋል፡፡ እሳቸው ግን ‹‹ይሰሩኝ እንጂ ከዚህ በኋላ ልጆቼን ለጦርነት አልሰጥም›› በማለት ተናግረዋል፡፡
የ17 እና የ15 አመት እድሜ ያላቸው እኚህ አባት ልጆቻቸውን ከትምህርት ቤት ማስቀረት ባይችሉም በትምህርት ቤቶች ውስጥ የግዳጅ ምልመላ መኖሩ ስጋት እንዳሳደረባቸው አስታውቀዋል፡፡ በአህፈሮም ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ አረፈ ወልዳይ በበኩላቸው ‹‹እድሜያቸው ከ15 አመት በላይ የሆኑትን ልጆች መዝግበው ሄደዋል፡፡ እየተመለከትን ያለነው የጦርነት ምልክት ነው›› ያሉ ሲሆን የወረዳው ማህበረሰብ በግዳጅ እህል፣ ጥሬ ገንዘብና ምግብ እንዲያዋጣ እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
ጨምረውም ‹‹እያንዳንዱ ነዋሪ 25 ኪሎ እህል፣ 500 ብር፣ ምስርና እንቁላል እንዲያቀርብ ትእዛዝ ተሰጥቶታል፡፡ በትግራይ ጦርነት ወቅት ለሞቱት ልጆቻችን እያዘንን እንዴት ሌላ ዙር ጦርነት ልንቋቋም እንችላለን?›› የሚል ጥያቄም አንስተዋል፡፡ አቅም ያላቸው የወረዳው ነዋሪዎች ልጆቻቸውን ወደአዲስ አበባ መላካቸውን ገልፀውም እሳቸው ግን ይህን ለማድረግ የሚያስችል ገንዘብ እንደሌላቸው አስረድቷል፡፡ በአክሱም የሚገኙት የቀድሞው የቲዲኤፍ አባል አቶ መስፍን ሀደራ በበኩላቸው የተሰናበቱ ታጣቂዎች በስልታዊ ዘዴ የመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አቶ መስፍን ጦርነቱ እንዳበቃ በዲዲአር ከተሰናበቱት መካከል አንዱ ቢሆኑም ‹‹የቀድሞ ወታደራዊ ክፍሌ አግኝቶ አናግሮኛል፡፡ ሌሎች እንደኔ የተሰናበቱም የስልክ ጥሪ ደርሷቸዋል›› ብለዋል፡፡ እንደገለፁትም ይህ ጥሪ የሚደረገው በማማለልና በማስፈራራትም ጭምር ነው፡፡
ሲናገሩም ‹‹ወደጦር ሀይሉ ለሚመለሱ መሬት እንደሚሰጡና የስራ እድል እንደሚፈጥሩ እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ ለዚህ ፈቃደኛ ያልሆኑትን ደግሞ ከሀዲ የሚል ስም እየሰጧቸው ነው›› ያሉት አቶ መስፍን የቀድሞ የቲዲኤፍ አባላት ጋር ወታደራዊ አዛዦችና የህክምና ባለሙያዎች እየተላኩ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ ዘገባው እንዳለው በደቡባዊ ዞን ነቅሴጌ ወረዳ የቀድሞ የቲዲኤፍ አባላት ወደነበሩበት ወታደራዊ ክፍሎች እንዲቀላቀሉ የሚጠይቅ ማስታወቂያ ተለጥፏል፡፡ ይህ ማስታወቂያም ‹‹በትግራይ ህዝብ ላይ የታወጀውን የጄኖሳይድ ጦርነት ተቃውማችሁ የታገላችሁ በሙሉ›› በሚል የሚጀምር ሲሆን ለጦርነት ዝግጁ የሆኑ እንዲመለሱ የሚገልፅ መሆኑን አሳይቷል፡፡ እንዲህ አይነት ማስታወቂያዎችን በሌሎች ወረዳዎች መመልከቱንም አስረድቷል፡፡ የትግራይ ማእከላዊ ዞን የህወሀት ፅህፈት ቤት ለአድዋ ወረዳ ትምህርት ቢሮ በፃፈው ደብዳቤ ደግሞ ‹‹የመንግስት ሰራተኛ የሆኑ የቀድሞ ተዋጊዎች ወደወታደራዊ ክፍሎቻቸው እንደሚመለሱ› የሚል ትእዛዝ መያዙን ገልጿል፡፡

ከመቃብር በላይ የሚውል መልካም ስም
በአሰላ የመጋቤ በረከት ግርማ ደምሴ መታሰቢያ ሙዚየም ተመረቀ!
#ethiopia | ባለፉት ጥቂት ሰዓታት በአርሲ ዞን አሰላ ከተማ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ አንድ ታሪካዊ ክስተት ተከናውኗል።
በሀገርና በቤተክርስቲያን ዘንድ እጅግ የሚከበሩትና "መጋቤ በረከት" የሚል ማዕረግ የተሰጣቸው የታላቁ አባት የመጋቤ በረከት ግርማ ደምሴ የመታሰቢያ ህንፃ ሙዚየም በታላቅ ድምቀት ተመርቋል።
የልጆች ስጦታ፦
እኚህ ታላቅ አባት ካረፉ አንድ ዓመት ሲሞላቸው ልጆቻቸው ከአባታቸው የተረከቡትን በጎነት ለታሪክ እንዲተርፍ ከ62 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበትን ባለ ሁለት ወለል ሙዚየም ገንብተው ለምረቃ አብቅተዋል።
"ጊዳድ" መጽሐፍ፦
የአባታቸውን የህይወት ጉዞ፣ የንግድ ስኬትና የቤተሰብ አመራር ጥበብ የሚዳስሰው "ጊዳድ" የተሰኘው መጽሐፍ በጸሐፊ ሌሊሳ ኢድሪስ ተዘጋጅቶ በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ለንባብ በቅቷል።
ታሪካዊ ምስክርነት፦
ሙዚየሙ የአባቱን መልካም ስራዎች የሚገልጹ ፎቶግራፎች፣ ቁሳቁሶችና መረጃዎችን የያዘ ሲሆን፤ አዳራሽና ቢሮዎችንም ያካተተ ዘመናዊ ህንፃ ነው።
መጋቤ በረከት ግርማ ደምሴ (1949 - 2017 ዓ.ም)
በአርሲ ዞን ተወልደው በንግዱ ዓለም ስኬታማ የነበሩ ሲሆን፤ አምስት ልጆችን በስነ-ምግባር አሳድገው ለሀገር ያበቁ ታላቅ አባት ናቸው።
በቤተክርስቲያን ግንባታ፣ በማህበራዊ ልማትና በሽምግልና ስራቸው "የቱሩፋት አበጋዝ" ተብለው ይወደሳሉ።
እውነትን በመናገርና ችግረኞችን በመርዳት የሚታወቁት እኚህ አባት፣ በ68 ዓመታቸው ሚያዚያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ማረፋቸው ይታወሳል።
ሀብት ለራስ ብቻ ሳይሆን እንዲህ ለታሪክና ለወገን ሲተርፍ ትልቅ ትርጉም ይኖረዋል። የመጋቤ በረከት ግርማ ልጆች ለአባታቸው ያደረጉት ይህ ተግባር፣ ማንኛውም ሰው በህይወት ዘመኑ የሚዘራው በጎነት እንዲህ በክብር እንደሚታጨድ ማሳያ ነው። አሰላ ዛሬ የአንድ ብርቱ አባት ታሪክ ህያው ሆኖ ሲታደስ ውላለች!
መልካም ስራ ከመቃብር በላይ ይውላል!
#getu #megabebereketgirma #asella #legacy #gidatbook #ethiopianhistory #ethiopianorthodox #arsi #inspiration #መጋቤበረከትግርማ #አሰላ #ታሪክ #ጊዳድ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

4 months ago
በውሃው ላይ ልክ እንደ ደረቅ መሬት የሚራመዱትን አባት ታውቋቸዋላችሁ?
ጣናን በሚያክል ሀይቅ በድንጋይ ታንኳ መሻገር ምንኛ ድንቅ ነው? እኚህ ጻድቅ አባት የገደሙት ገዳም ውስጥ አሁን ትልቅ ታሪክ ሊሠራ ነው::
ጎንደር ጎርጎራን ስናስብ ጥንታዊውንና ታሪካዊውን የጣና ሞገስ የሆነውን የማን እንደ አባ አቡነ ያሳይ መድኃኔዓለም አንድነት ገዳምን በዓይናችን ላይ እንስላለን::
ይህ ገዳም በውስጡ የመድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ያለው ሲሆን ከግዝት ቅጥር ውጭ እህቶችና እናቶች እንዲቆርቡ የሚያስችል በቂ ስፍራ በቤተክርስቲያን ስለሌለ ሥርዓቱ የሚፈጸመው በድንኳንና በዳስ ነው:: በተለይም መስከረም 14 እና መጋቢት 27 ለበዓለ ንግሥ ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ ከተለያየ ሥፍራ ስለሚመጣ ከፍተኛ የሆነ መጨናነቅ ይፈጠራል:: አባቶች ክቡር ስጋውንና ቅዱስ ደሙን በውጭ ያቀብላሉ:: ይህ ደግሞ ለሥርዓተ ቤተክርስቲያን ከመቆርቆር አንጻር ሲታይ ደግሞ ልብ ዝቅ ያደርጋል:: ይህንን እሳዛኝ ሁኔታ በቦታው ተገኝቶ ማየትም ቁጭት ውስጥ ይከታል::
እናቶቻችና እህትቻችን በሚገባ የሚገለገሉበትን የእመቤታችን የእመ ቅዱሳን የቅድስት ድንግል ማርያምን ቤተክርስቲያን ለመገንባት አሁን መሰረት ተጥሏል:: ይህንን ቤተመቅደስ በአጭር ጊዜ ገንብተን የአበው መነኮሳትን ድካም መቀነስ ይገባናል:: ከእመቤታችን የምናገኘው በረከትና ረድኤት ብዙ ነውና ሁላችንም ከበረከቱ በመሳተፍ ስማችንን በወርቅ እምድ እናጽፍ::
አባቶችችን ታሪክ ሠርተውልንና ለዘመናት የሚነገርለትን ድንቅ ቅርስ አስቀምጠውልን አልፈዋል:: እኛ አዲስ ታሪክ መጻፍ ባንችል እንኳን እነርሱ የሠሩትን ግማሹን ደግመን በመሥራት ልንመስላቸው ይገባናል:: ለጣና ሀይቅ ተጨማሪ ሞገስ እንጨምርለት::
ድጋፍ ለማድረግ:
ንግድ ባንክ: 1000731553134
ስልክ: -
0918240454
0906632367
0921612653
Tiktok: https://www.tiktok.com/@us...
Website: www.abuneyasay.com
Online Donation link: https://chapa.link/donatio...

Comments