Logo
FastMereja

በውሃው ላይ ልክ እንደ ደረቅ መሬት የሚራመዱትን አባት ታውቋቸዋላችሁ?
ጣናን በሚያክል ሀይቅ በድንጋይ ታንኳ መሻገር ምንኛ ድንቅ ነው? እኚህ ጻድቅ አባት የገደሙት ገዳም ውስጥ አሁን ትልቅ ታሪክ ሊሠራ ነው::

ጎንደር ጎርጎራን ስናስብ ጥንታዊውንና ታሪካዊውን የጣና ሞገስ የሆነውን የማን እንደ አባ አቡነ ያሳይ መድኃኔዓለም አንድነት ገዳምን በዓይናችን ላይ እንስላለን::

ይህ ገዳም በውስጡ የመድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ያለው ሲሆን ከግዝት ቅጥር ውጭ እህቶችና እናቶች እንዲቆርቡ የሚያስችል በቂ ስፍራ በቤተክርስቲያን ስለሌለ ሥርዓቱ የሚፈጸመው በድንኳንና በዳስ ነው:: በተለይም መስከረም 14 እና መጋቢት 27 ለበዓለ ንግሥ ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ ከተለያየ ሥፍራ ስለሚመጣ ከፍተኛ የሆነ መጨናነቅ ይፈጠራል:: አባቶች ክቡር ስጋውንና ቅዱስ ደሙን በውጭ ያቀብላሉ:: ይህ ደግሞ ለሥርዓተ ቤተክርስቲያን ከመቆርቆር አንጻር ሲታይ ደግሞ ልብ ዝቅ ያደርጋል:: ይህንን እሳዛኝ ሁኔታ በቦታው ተገኝቶ ማየትም ቁጭት ውስጥ ይከታል::

እናቶቻችና እህትቻችን በሚገባ የሚገለገሉበትን የእመቤታችን የእመ ቅዱሳን የቅድስት ድንግል ማርያምን ቤተክርስቲያን ለመገንባት አሁን መሰረት ተጥሏል:: ይህንን ቤተመቅደስ በአጭር ጊዜ ገንብተን የአበው መነኮሳትን ድካም መቀነስ ይገባናል:: ከእመቤታችን የምናገኘው በረከትና ረድኤት ብዙ ነውና ሁላችንም ከበረከቱ በመሳተፍ ስማችንን በወርቅ እምድ እናጽፍ::

አባቶችችን ታሪክ ሠርተውልንና ለዘመናት የሚነገርለትን ድንቅ ቅርስ አስቀምጠውልን አልፈዋል:: እኛ አዲስ ታሪክ መጻፍ ባንችል እንኳን እነርሱ የሠሩትን ግማሹን ደግመን በመሥራት ልንመስላቸው ይገባናል:: ለጣና ሀይቅ ተጨማሪ ሞገስ እንጨምርለት::

ድጋፍ ለማድረግ:
ንግድ ባንክ: 1000731553134

ስልክ: -
0918240454
0906632367
0921612653

Tiktok: https://www.tiktok.com/@us...

Website: www.abuneyasay.com
Online Donation link: https://chapa.link/donatio...
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.