Logo
Getu Temesgen
"ደከመኝ!?"
የእማማ ገሎ የፅናት ጉዞ ...
#ethiopia | እጅን ለሰው ከመዘርጋት ይልቅ በጥረታቸው መኖርን የመረጡት የእኚህ እናት ታሪክ ለብዙዎች ትልቅ አስተምህሮት የሚሰጥ ነው።

መለመን በሰፋበት በዚህ ዘመን እሳቸው ግን ክብራቸውን አስጠብቀው በጥቂት ሎሚዎች ንግድ ራሳቸውን ለማስተዳደር ፀሐይን ተቋቁመው ይገኛሉ።

አራት ፍሬ ሎሚዎችን ብቻ ይዘው ወደ ገበያ የወጡት እኚህ እናት አንዱን ፍሬ በአስር ብር በመሸጥ በአጠቃላይ አርባ ብር ለማግኘት ነበር የደከሙት።

በአሁኑ ወቅት ይህ ገንዘብ ለአንድ ዳቦ ግዢ እንኳን የማይበቃ ቢሆንም፣ የእሳቸው ምርጫ ግን የሰው ፊት ከማየት ይልቅ በላባቸው መኖር ሆኗል።

እናትህ / እናትሽ

እርዳታን ከመጠባበቅ ይልቅ የራሳቸውን ጥረት እንደ ምክንያት በመጠቀም በክብር ማደርን መርጠዋል።

እናቴ!

እማማ ገሎ ወይም ገሎ ከበሺ ይባላሉ። በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሃያ ዓመታት በላይ የኖሩ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የሚግባቡት በጉራጊኛ ቋንቋ ነው። ይህንን ያህል እድሜ ቢያስቆጥሩም ዛሬም ድረስ በላስቲክ በተሰራ መጠለያ ውስጥ ህይወታቸውን በጉሊት ንግድ እየደገፉ ይኖራሉ።

በዕለቱ አራት ፍሬ ሎሚዎችን ይዘው የወጡት እሷ ተሸጣላቸው ለልጆቻቸውና ለልጅ ልጆቻቸው እንጀራ ገዝተው ለመግባት ነበር። በዚህ እድሜ ድጋፍ እንጂ ድካም ባልተገባቸው ነበር።

እናትህ / እናትሽ

ለወጣቱ ትውልድ የሥራ ፍቅርንና የፅናትን ትልቅ ትምህርት የሚያስተምሩ ቢሆንም፣ በአሁኑ ሰዓት አቅማቸው የደከመ በመሆኑ ሰብአዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።

በመሆኑም እናቴን
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
በሂሳብ ቁጥር
1000769117125
በስማቸው (Gelo Kebeshi) በተከፈተው አካውንት ድጋፍ ማድረግ ይቻላል።

በተጨማሪም ለክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በኩል ለእኚህ አረጋዊ እናት ተገቢው መጠለያ እንዲሰጣቸው ጥሪ ቀርቧል።
#ሰብአዊነት #አረጋውያን #ድጋፍ #ኢትዮጵያ #አዲስአበባ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.