(ዘ-ሐበሻ ዜና) የተመድ ሰብአዊ መብት ምክር ቤት የኤርትራ ራፖርተርን የስራ ዘመን በአንድ አመት አራዘመ፡፡ በተመድ የኤርትራ የሰብአዊ መብት ራፖርተር የሆኑት መሀመድ አብዲሰላም ባቢከር ባለፈው 6 አመት የስራ ዘመናቸው በኤርትራዊያን በኩል በ2 መልክ ሲታዩ ቆይተዋል፡፡
አንደኛው መልክ በመላው አለም በሚገኙ ኤርትራዊያን እይታ የሚንፀባረቅ ሲሆን እሳቸው በየአመቱ በጄኔቫ የሚያቀርቡት ሪፖርት በአገራቸው ውስጥ ያለውን ስቃይ፣ ግፍና ሰቆቃ ለአለም የሚያሳይ ብቸኛው መንገድ አድርገው ይቆጥሩታል፡፡ ሁለተኛው መልክ ደግሞ በኤርትራ መንግስት በኩል ሰውየው የሚገለፁበት ነው፡፡ የኤርትራ መንግስት እኚህ ራፖርተር በተደጋጋሚ ዘልፈዋቸዋል፡፡
ከአደጉ አገራት በሚሰጣቸው ትእዛዝ በማደግ ላይ ባሉ አገራት ላይ ጫና የሚያሳድሩ፣ ብሄራዊ ሉአላዊነትን ለመጣስ የሚሞክሩና በአጠቃላይ የኤርትራን ደህንነት አደጋ ውስጥ የሚከቱ መሆናቸውንም ይገልፃሉ፡፡ በመሆኑም ራፖርተሩ ከሀላፊነታቸው እንዲነሱ ያላሰለሰ ጥያቄ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ ይህንን ተከትሎም ሰሞኑን እኚህን ራፖርተር ለመተካት 8 እጩዎች እየተገመገሙ መሆኑን የሚገልፁ ዘገባዎች በስፋት ሲሰራጩ ነበር፡፡
ነገር ግን ዛሬ በጄኔቭ በተካሄደው የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ እኚህ ራፖርተር ለተጨማሪ አንድ አመት በሀላፊነታቸው እንዲቀጥሉ ውሳኔ ተላልፏል፡፡ የውሳኔውን ረቂቅ ያቀረበው የአውሮፓ ህብረት ሲሆን በተሰጠው ድምፅ አሰጣጥ 23 የምክር ቤቱ አባላት ውሳኔውን ሲደግፉ፣ 17ቱ ደግሞ ድምፀ ተአቅቦ በማድጋቸውና 6 አገራት የተቃውሞ ድምፅ በመስጠታቸው ውሳኔው ፀድቋል፡፡ ውሳኔው እንዳይፀድቅ ተቃውሞ ድምፅ የሰጡት 6 አገራት ግብፅ፣ ብሩንዲ፣ ቻይና፣ ኩባ፣ ህንድና ፓኪስታን ናቸው፡፡

1 month ago