(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) የጃኖ ባንድ መስራች፣ የዳሎል ባንድ አባል የነበሩት ሙዚቀኛ ዘለቀ ገሰሰ ወንድም እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ስማቸው የገነነ ታዋቂው የሙዚቃ ፕሮዲውሰር እና ማኔጀር አቶ አዲስ ገሰሰ፣ በኒው ጀርሲ፣ አሜሪካ ባደሩበት በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የቅርብ ወዳጆቻቸው አሳዝነው አስታውቀዋል። የሞታቸው ምክንያት ገና በውል ያልታወቀ ሲሆን፣ አስከሬናቸው ወደ ውዲቷ ሀገራቸው ኢትዮጵያ እንደሚሸኝም መረጃዎች ያመለክታሉ።
አቶ አዲስ ገሰሰ በሙዚቃው ኢንደስትሪ ውስጥ ጉልህ አሻራ ያሳረፉ፣ የብዙዎችን ህይወት የቀየሩ እና የኢትዮጵያን ስም በዓለም አደባባይ ከፍ አድርገው ያቆሙ ታላቅ ሰው ነበሩ። እኚህ የሙዚቃ ማኔጅመንት ባለሙያ፣ ዓለም አቀፍ ዝና ያተረፉትን የሬጌው ንጉስ የቦብ ማርሊ ቤተሰቦችን ጨምሮ የበርካታ ታዋቂ ሙዚቀኞች የጀርባ አጥንት በመሆን አገልግለዋል። የእሳቸው የህይወት ጉዞ ከኢትዮጵያ ጀምሮ፣ በቺካጎ፣ ጃማይካ፣ ኒው ዮርክ እና በመጨረሻም ኒው ጀርሲን ያዳረሰ ረዥም እና አስደናቂ መንገድ ነበር።
አቶ አዲስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተመረቁ በኋላ፣ ከ30 ዓመታት በፊት ወደ አሜሪካ አቅንተው ማኔጅመንት አጠኑ። ከዚያም ወንድሞቻቸው ሲከተሏቸው፣ ህይወታቸውን ሙሉ ለሙሉ ለወንድሞቻቸው የሙዚቃ ስኬት አዋሉ። ወንድሞቻቸውና ጓደኞቻቸው የመሰረቱት "ዳሎል" የተሰኘው ባንድ፣ ከኢትዮጵያዊ ሙዚቃ ወደ ሬጌ በማዘንበል፣ በአቶ አዲስ አመራር ስር በቺካጎ ስሙን ማግነን ጀመረ።
በ1982 የቦብ ማርሊ ባለቤት ሪታ ማርሊ ባቀረበችላቸው ጥሪ መሰረት፣ ዳሎል ባንድ በጃማይካ ኪንግስተን በተካሄደው የመጀመሪያው የቦብ ማርሊ መታሰቢያ ላይ ለመጫወት በቅቷል። አቶ አዲስ ሪታ ማርሊ በባለቤቷ ሞት እያዘነች በነበረችበት ወቅት የሰጧት ድጋፍ፣ ጠንካራ ወዳጅነትን ፈጠረ። ይህ ግንኙነት ዳሎል ባንድ ከ1988 እስከ 1991 ድረስ የዚጊ ማርሊ ይፋዊ ባንድ እንዲሆን አስችሎታል። ዳሎል ባንድ በ "Conscious Party" አልበም ፕላቲነም፣ እና በ "One Bright Day" አልበም ጎልድ ደረጃ በመድረስ፣ ይህን ታሪካዊ ስኬት ያገኘ የመጀመሪያው የኢትዮጵያውያን ባንድ ለመሆን በቅቷል።
አቶ አዲስ ከሪታ ማርሊ ጋር በመሆን የቦብ ማርሊን 'Legend' አልበም ዓለም አቀፍ ጉብኝት አደራጅተዋል። ከሁሉም በላይ ግን፣ አቶ አዲስ በ2005 በአዲስ አበባ የተካሄደውንና ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህዝብ የታደመበትን ታሪካዊውን "Africa Unite" ኮንሰርት በዋናነት የጠነሰሱት እሳቸው ነበሩ። ይህ ኮንሰርት የቦብ ማርሊን 60ኛ የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ፣ የቦብ ማርሊ ቤተሰብ፣ አንጀሊክ ኪጆን ጨምሮ በርካታ ከዋክብትን በአዲስ አበባ ያሰባሰበና ስለ ኢትዮጵያ አዎንታዊ ገጽታ ለዓለም ያሳየ ታላቅ ኩነት ነበር።
አቶ አዲስ የዓለም አቀፍ ከዋክብትን ከማስተዳደር ባሻገር፣ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ወደ ዓለም መድረክ ለማሸጋገር ትልቅ ህልም ነበራቸው። ለዚህም ነው "አዲስ ማኔጅመንት" የተሰኘውን ድርጅታቸውን መስርተው በርካታ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶችን የደገፉት።
ታዋቂውን ድምጻዊ ቴዲ አፍሮን በማግኘትና ለረጅም ጊዜ ማኔጀሩ በመሆን አገልግለዋል። እንዲሁም፣ ታዋቂዋን ድምጻዊት ጂጂን በአጋጣሚ ቤታቸው ውስጥ ካገኟት በኋላ፣ ችሎታዋን አይተው፣ ኒው ዮርክ እንድትመጣ በመምከር፣ ከታዋቂው የአይላንድ ሪከርድስ መስራች ክሪስ ብላክዌል ጋር አስተዋውቀዋት፣ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ውል እንድትፈራረም አድርገዋል።
አቶ አዲስ ዓለም አቀፍ ኔትዎርክ ያላቸውና ስኬታማ ቢሆኑም፣ እንደቅርብ ወዳጆቻቸው ምስክርነት እጅግ ትሁት ነበሩ። ኒው ጀርሲ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው፣ ሹራብና አጭር ሱሪ ለብሰው ከሶስት ዓመት ልጃቸው ሀና ጋር ጊዜ ማሳለፍን የሚወዱ አባት ነበሩ። ከሙዚቃ ስራቸው በተጨማሪ በቺካጎ የሬጌ ክለብ፣ በኢትዮጵያ የእርሻ ስራ እና በ "One Love Africa Foundation" አማካኝነት በኢትዮጵያ ገጠራማ ክፍሎች ትምህርት ቤቶችን የመገንባት ሰፊ ራዕይ ነበራቸው።
አቶ አዲስ ገሰሰ ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ በክብር ያስጠሩ፣ የሙዚቃውን ኢንደስትሪ ያሳደጉ እና ለብዙዎች መነሻ የሆኑ ታላቅ ሰው ናቸው። በድንገተኛ ህልፈታቸው የሙዚቃው ዓለም፣ ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጆቻቸው፣ እንዲሁም አድናቂዎቻቸው ጥልቅ ሀዘን ላይ ይገኛሉ።
ነፍስ ይማር! አቶ አዲስ ገሰሰ፣ ስራዎ እና አሻራዎ ለዘለዓለም ሲታወስ ይኖራል።

7 hours ago