(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአሜሪካ 16 ወታደራዊ ጦር ሰፈሮች ላይ ጉዳት መድረሱ ተዘገበ፡፡ ሲኤንኤን ቴሌቪዥን ባቀረበው ዘገባ ፌብሩዋሪ 28 በተጀመረው እስራኤልና አሜሪካ በኢራን ላይ በከፈቱት ጦርነት ቢያንስ 16 የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጿል፡፡ ይህንን ጉዳት ያደረሱት ኢራንና አጋሮቿ መሆናቸውንና ጉዳቱም በ8 በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ የጦር ሰፈሮች ላይ ያጋጠመ መሆኑን አስረድቷል፡፡ ቅርበት ያላቸውን ምንጮቹን የጠቀሰው ዘገባው ጉዳቱ ካጋጠማቸው ጦር ሰፈሮች ውስጥ አንዳንዶቹ ጥቅም መስጠት በማይችሉበት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡
አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያለው የኮንግረስ ምንጭ ለሲኤንኤን ሲናገር ‹‹በደረሰው ጉዳት ላይ የተለያዩ ግምገማዎች ተደርገዋል፡፡ ግምገማዎቹ መላው በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች በመውደማቸው ሊዘጉ ይገባል ከሚለው አንስቶ ከሚሰጡት ጥቅም አኳያ መጠገን ይኖርባቸዋል እስከሚለው የመሪዎች ሀሳብ ድረስ ናቸው›› ብለዋል፡፡ ዘገባው የሳተላይት ምስሎችን ጠቅሶ እንደገለፀው የቴሄራን መንግስት ዋና ኢላማዎች የነበሩት የአሜሪካ ዘመናዊ የራዳር ስርአቶች፣ የመገናኛ ሲስተሞችና አውሮፕላኖች ሲሆኑ አብዛኛዎቹ ውድና ለመተካት አስቸጋሪ ናቸው፡፡
ምንጩ ጨምረው እንዳሉት በመካከለኛው ምስራቅ አሜሪካ የነበራት የራዳር ስርአት እጅግ ውድ ከመሆኑም በላይ በጣም ውስን ከሚባሉት ሀብቶች መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡ እኚህ ምንጭ እንደምሳሌም በባህሬን የሚገኘው የአሜሪካ ፊፍዝ ፍሊት ባህር ሀይል ላይ የደረሰውን ጉዳት አንስተዋል፡፡ ይህንን የባህር ሀይል ሰፈር ለመጠገን 200 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡

1 month ago