(ዘ-ሐበሻ ዜና) በለንደን ኢትዮጵያዊው ላይ የግድያ ክስ ተመሰረተበት፡፡ ስካይ ኒውስ እንደዘገበው የ60 አመቱ እንግሊዛዊ ሚክላስ ኪራኩ በለንደን ጎዳና ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው ሀሙስ ሜይ 14 ቀን ነበር፡፡ ፖሊሶች በስፍራው ደርሰው እኚህን ግለሰብ በአምቡላንስ ወደሆስፒታል ከወሰዷቸው በኋላ የህክምና ክትትል ማድረግ ይጀምራሉ፡፡
ፖሊሶችም በእኚህ ግለሰብ ላይ አደጋውን ማን እንዳደረሰው የማጣራት ስራቸውን ይቀጥሉና እሁድ እለት የ36 አመቱ ኢትዮጵያዊ ቢንያም ተወልደ ነጋሽ በጉዳዩ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ይውላል፡፡ በቢንያም ላይ የመግደል ሙከራ ክስ ተመስርቶበት ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ ቀጠሮ ተሰጥቶት አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኝ ዘገባው አስረድቷል፡፡
ይሁን እንጂ የለንደን ሜትሮፖሊቲያን ፖሊስ እንደገለፀው በሆስፒታል ህክምናቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ተጎጂው ከ8 ቀናት በኋላ ትላንት አርብ ህይወታቸው አልፏል፡፡ በመሆኑም በእስር ላይ የሚገኘው ቢንያም ላይ በግድያ ሙከራ የሚለው ክስ ሰው መግደል ወደሚል መቀየሩን ፖሊስ አስታውቆ በመጪው ሰኞ በአዲሱ ክስ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ አስረድቷል፡፡

3 months ago