Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) እስራኤል አዞዎችን ከዱር አራዊትነት ዝርዝር አወጣች፡፡ የእስራኤል አካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ኢዲት ሲልማን አዞዎች ከዱር አራዊትነት ዝርዝር ውስጥ መውጣታቸውንና በእንስሳት ማቆያ ውስጥ ተዳቅለው ያደጉ የዱር እንስሳት በሚል ውስጥ መካተታቸውን አስታወቁ፡፡ እንደኤኤፍፒ ዘገባ ይህ ውሳኔ እነዚህን ተሳቢ እንስሳት ከእስር ቤት የማምለጥ ሙከራን ጨምሮ ለተለያዩ የደህንነት ስራዎች ለማዋል መንገድ የሚጠርግ ነው፡፡

ውሳኔውን የእስራኤል ብሄራዊ ደህንነት ሚኒስትር የሆኑት ኢታማር ቤን ጂቨር በደስታ መቀበላቸውን ገልፀዋል፡፡ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገፃቸው ላይ በኤአይ የተቀናበረ ራሳቸውን ከአዞ ጋር ተቃቅፈው የሚያሳይ ምስል ለጥፈው ‹‹ከእስር ቤት ማምለጥ የሚፈልግ ደግሞ ያስብበት›› የሚል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ እኚህ ሚኒስትር በዲሴምበር ወር በፍሎሪዳ የሚገኘውን ‹‹አሊጌተር አልካታራዝ›› የኢሚግሬሽን ማቆያ እንደምሳሌ ጠቅሰው በአገራቸው የሚገኙ የፍሊስጤም እስረኞች በአዞ እንዲከበቡ ምክረ ሀሳብ አቅርበው ነበር፡፡

ቻናል 13 የተሰኘው የእስራኤል ቴሌቪዥን እንደዘገበው ሚኒስትሩ ይህንን ሀሳብ ባቀረቡበት ወቅት በርካታ ባለስልጣናት እንደፌዝ ቆጥረውት ነበር፡፡ ሀሳቡን የእስራኤል የተፈጥሮ ፓርኮች ባለስልጣንም አጥብቆ መቃወሙን አውስቷል፡፡ ይሁንና አሁን አዞዎች ከዱር አራዊትነት መውጣታቸው እነዚህን እንስሳት ለ‹‹ደህንነት አገልግሎት›› መጠቀምን ይፈቅዳል፡፡

17 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.