3 days ago
“ታሪክ በትዝታ ላይ የተጫነ ሸክም አይደለም-የነፍስ መገለጥ እንጂ”
ጋዜጠኛ ዮናስ አየለ እንደጻፈው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከአሚኮ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ አዳምጬ እንደጨረስኩ በቃለ ምልልሱ በርዕሰ ጉዳይ ደረጃ ጎልተው ከወጡ ዋና ዋና ጭብጦች መካከል አንዱ ነገረ ታሪክ እንደሆነ ተሰምቶኛል፡፡ ታሪክ-የሀገር ውስጥና የውጭ፤ የሩቅና የቅርብ ዘመን! ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያንጸባረቁትን ሚዛናዊና አምክኖአዊ የታሪክ እይታና ድምዳሜያቸውን አለማድነቅ ንፉግነት ነው፡፡ የአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን እንግሊዛዊ የታሪክ ጸሐፊና ፖለቲከኛ ሎርድ አክተን “History is not a burden on the memory but an illumination of the soul” ብሎ ሲጽፍ “ታሪክ የነፍስ መገለጥ እንጂ በትዝታ ላይ የተጫነ ሸክም አይደለም” ማለቱ ነበር፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያነሷቸው የታሪክ አንኳር ጉዳዮች እስከዛሬ ድረስ በሀገራችን የታሪክ አጻጻፍ(Historiography) እና በሕዝባዊ ትርክቶቻችን(በሚዲያዎችን ጭምር) በሚገባቸው ልክ ያልተወሱ፤ ቢወሱም ፈራ ተባ እየተባሉ የሚጠቀሱ፤ አለፍሲልም ባልተገባ የፖለቲካ እይታ ደንቃራ ተደርገው የተወሰዱ የታሪክ ግርዶሽ(eclipse of the history) ሆነው የኖሩ ስብራቶቻችን ነበሩ፡፡ ከነዚህ ቁልፍ ጉዳዮች መካከል ዋነኛዎቹ አንዱ የሕዝቦች ትስስር እና መስተጋብር ታሪክ ሲሆን ሌላኛው በአገረ መንግስት ምሥረታ ውስጥ የሸዋ ጂኦ-ስትራቴጂካዊ ሚናን የተመለከቱት ናቸው፡፡
በመጀመሪያ የአማራና የኦሮሞ ሕዝቦች በኩታ ገጠም ቀዬዎቻቸው እና የታሪክ እድል በፈጠረላቸው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የባህል አጋጣሚዎች እንደሌሎች ማህበረሰቦች ሁሉ መጋባት መዋለዳቸው፤መተሳሰር መዋሀዳቸው ሀቅ የመሆኑን ያህል የታሪክ ጥናት እና የትርክቶቻችን ማጠንጠኛ አለመሆናቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህ በባሰ ሁኔታ ደግሞ በነገሥታቱ መካከል የነበረው የፖለቲካ ጋብቻና የመሪዎቻችን ማህበራዊ መሠረት ጉዳይ ነውር እስኪመስል በእውነታው ልክ ሳይጠናና፣ሳይነገርለት ዘመናት አልፈዋል ፡፡ በሌላ በኩል በሸዋና አካባቢው ለረዥም ዘመን የኖሩ ሕዝቦች በአገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት የተጫወቱት ሚናና የሚጋሩት ቀደምት የሥልጣኔ ባለቤትነት (ታሪክ ሰሪነት-Agency) ግጥምጥሞሽ በሀገር መሪ ደረጃ መወሳታቸው እጅግ ጉልህ ፋይዳ ያለው ጉዳይ ነው ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያነሷቸው የታሪክ እውነታዎች ያለጥርጥር ታሪካችንንና የታሪክ ምልከታችንን ደጋግመን መመርምር እንዳለብን የሚያስገነዝቡና የወገንተኝነት ጥያቄ በሚነሳባቸው ሃይማኖታዊ የታሪክ ምንጮች እንኳን የተቀመጡ ገሃድ እውነታዎች ናቸው፡፡ መመርመር ለሚፈልግ አጥኚ እነዚህ የታሪክ እውነታዎች በየነገሥታቱ ዜና መዋዕሎች (የዐጼ አምደ ጽዮን፣ ዐጼ ሱስንዮስ፣የዐጼ ገላውዲዮስ፣ የዐጼ ሠርጸ ድንግል ወዘተ)፤ የሃይማኖት ሰነዶች፣ የታሪከ ነገሥት ቅጂዎች፣ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩ አውሮፓውያን ተጓዦችና ጸሐፊያን (ፍራንስስኮ አልቫሬዝ፣ ፔድሮ ፔዝ፣ ማኑኤል አልሜዳ፣ ጄሮኒሞ ሎቦ፣ ጀምስ ብሩስ፣ ኮንቲ ሮሲኒ ወዘተ ) መዝግበው በተውልን ሰነዶች ሰፍረው የምናገኛቸው፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የኖሩ ቱባ መረጃዎች ናቸው፡፡
ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ የተወልን የጽሑፍ ሰነድና ሌሎች ሀገርኛ የቃል መረጃ ምንጮች ዐፄ ልብነድንግል(1498-1532 ዓ.ም.) እንደ መሪ የአማራና የኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ምናልባትም የሌሎች ሕዝቦችም ማህበራዊ ዳራ የነበራቸው ንጉሠ ነገሥት እንደሆኑ የሚያስረዱ ሲሆን አልቫሬዝ የንጉሱ የእናት ወንድም የነበሩት አጎታቸው ዶሪ ባህረ ነጋሽ ኦሮሞ እንደነበሩና ባህረ ነጋሽ ዶሪ ሲሞቱ ሥልጣኑ በቀጥታ ወደልጃቸው ቡሎ መሸጋገሩን ጭምር በአይኑ ያየውን ጽፏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በትኩረት መታየት የሚገባው ጉዳይ ስለዐጼ ልብነ ድንግል የጦር አዛዦች የተነገሩ የቃል መረጃዎች ናቸወ፡፡ ከእነዚህ መካከል የንጉሠ ነገሥቱ ሠራዊት የቦረንትቻ ባሕል ያውቅ እንደነበር በተክለጻዲቅ መኩሪያ መጻፉና ከዐጼ ልብነድንግል የጦር አዛዦች አንዱ የነበረው ቱሉ ደገልሀን በመራው ከኢማም አሕመድ ጋር የተካሄደ ጦርነት የዐጼው ጦር ሲያፈገፍግ ንጉሠ ነገሥቱ “ሁሉም ቢፈራ ቱሉ እንዴት ፈራ? ” ማለታቸው ስለሠራዊታቸው ሥብጥር የሚነግረን ነገር አለ፡፡
ኦቶማን ቱርኮችን እና የዘመኑ ተላላኪዎቻቸውን ለመዋጋት የንጉሠ ነገሥቱ ሠራዊት አንድ አካል ሆነው እስከ ኤርትራ ድረስ ዘምተው ስለነበሩ የኦሮሞ ተዋጊዎች ተጋድሎ የዐጼ ሠርጸድንግል(1542-1590 ዓ.ም.) ዜና መዋእል በግልጽ አስፍሯል፡፡ እነዚህ የኦሮሞና የሌሎች ሕዝቦች ተወላጅ ወታደሮች ትግራይ እንጢጮ አካባቢ ያካሄዱትን አውደ ውጊያ ዜና መዋዕሉ ይተርካል፡፡ ለመንግሥታቸውና ለሀገራቸው እስከባሕር ጠረፍ ድረስ ዘምተው ዋጋ መክፈላቸውም ተመዝግቧል፡፡ የዐጼ ሱስንዮስ(1607-1632 ዓ.ም.) ዜና መዋእል እና በዘመኑ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩ የአውሮፓ(የፖርቱጋል) ተጓዦች የጻፏቸው የመረጃ ምንጮች ንጉሠ ነገሥቱ ግንደበረት፣ሐምቦና አካባቢው ቤታቸው እንደነበር፤ አጎታቸው ለማሞ እንደሚባል፣ ወላጅ እናታቸው(ሐመልማል ወርቅ) የአዛዥ ኩሎ ልጅ የነበረች፤ የዚሁ የሐመልማል ወርቅ ጎሳ ተወላጅ የሆነ ቡኮ የተባለ ኦሮሞና ሠራዊቱ ለአባይ ቅርብ የሆነች ምዕራብ ሸዋ ላይ ዐጼ ሱስንዮስ ሲያገኙት የነበረውን ደስታና የፍቅሩን ጽናት ዜና መዋዕሉ ሳይሰስት ጽፎታል፡፡ ዐጼ ፋሲል(ከ1632 እስከ 1667 ዓ.ም.) አባቱ ሱስንዮስ እናቱ የወሎ ቃሉ ሰው(እቴጌ ሥልጣን ሞገሳ የሚል ስም የተሰጣት) እንደሆነች የታሪክ ምንጮች ያስረዱናል፡፡ በ1620ዎቹ ዓመታት ጀምሮ በኢትዮጵያ ይኖር የነበረው ፖርቱጋላዊ ቄስ ጄሮኒሞ ሎቦ ስለዐጼ ፋሲል እናትና ኦሮሞ ዘመዶቻቸው በአይን ምስክርነት የሚያውቀውን ጽፏል፡፡ የእቴጌ ሥልጣን ሞገሳ አያት ስለብዝሀ ሃይማኖት አስፈላጊነት የነበራቸውን ግልጽ ፖሊሲ ጭምር ሎቦ ዘግቦታል፡፡ የዐጼ በካፋ(1721-1730 ዓ.ም.) እና የዐጼ ኢዮአስ(1747-1761 ዓ.ም.) ጎንደር መቼም ለሕዝቦች ውህደትና ትስስር ጥሩ ማሳያ ነበረች፡፡ የየጁ ኦሮሞ ገዢ የነበረው የአሚቶ ሴት ልጅ ዝነኛዋ ውቢት ልጇ ዐጼ አዮአስ ነበር፡፡ ኢዮአስ ከኦሮሞ አጎቱ ከደጃች ሉቦ ጋር ሥልጣኑን በጎንደር እንዴት እንዳጸና፤ የቤተ መንግሥቱም የሥራ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ እንደነበረ የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕልና በጀምስ ብሩስ ቅጽ ሁለት መጽሀፍ የተመዘገቡ የታሪክ መረጃዎች ያስረዱናል፡፡
መነሻውን ወሎ በማድረግ ጎንደር ጸንቶ የኖረው የየጁ ሥርወ መንግሥት(ወረ ሼኮች) መሥራቾች የመርሳው አባ ጌትዬ፣ የልጃቸው ጓንጉል አባ ሴሩ እንዲሁም የልጅ ልጃቸው የራስ አሊ ጓንጉል(አሊ ትልቁ) ታሪክ በኢዮአስ ዜና መዋዕል፣ በጀምስ ብሩስ መጽሐፍና በሌሎች በርካታ ሰነዶች ታሪካቸው ተዘግቧል፡፡ በኋላ ላይ በሽፈራው በቀለ(ፕሮፌሰር) እና ሞላ ትኩዬ የቀረቡ ጥልቅ ጥናቶች ይህን እውነት በዝርዝር ያስረዱናል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው እንደጠቀሱት የእነዚህ መሪዎች የፖለቲካ ጋብቻ ታሪክ የሚያሳየን በሄዱበት አገር ሁሉ የሕዝቦች ትሥሥር እና የፖለቲካ ጋብቻ የኖረ ታሪካችን እና የጉልበታችን ምንጭ እንደነበረ ነው፡፡ በዳግማዊ ዐጼ ቴዎድሮስ ዘመን የተጻፉ የታሪክ ሰነዶች የወሎዋ ገዢ ወርቂቱ ወዳጆ(የማመዶች ሥርወ መንግሥት መሪ የኢማም አሊ አባ ቡላ ባለቤት) ንጉሥ ምኒልክ ከመቅደላ እስር ቤት እንዲያመልጡ ያደረጉ፤ አጃቢ ሠራዊት አሰማርተው ምኒልክን እስከሸዋ የሸኙ እንደነበሩ በዋናነት ከጸሓፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ ታሪከ ዘመን ዘ ዳግማዊ ምኒልክ ዜና መዋዕል እና በመቅደላ አምባ እስር ላይ የነበሩ አውሮፓውያን ከጻፏቸው መረጃዎች እንረዳለን፡፡
ሥልጣኔዎቻችን ሁሉ ተደምረን ያሳካናቸው እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው አንስተዋል፡፡ የዐድዋ ዘመቻና ድሉ ለዚህ አንዱ ማሳያ እንደሆነ ተጨባጭ የታሪክ ምንጮች ያስረዱናል፡፡ በ1888 ዓ.ም. ለዓድዋ ዘመቻ ከመላው ኢትዮጵያ የተመመው ሠረዊት ወፍላ ላይ የነበረው ሠልፍ የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል እንኳን እንዲህ ይገልጸዋል፡፡ “የመኳንንቱ የጦር መሣሪያ፣ወርቁ፣ ጣፋ፣ ብሩ፣ ሙጣው፣ ጫሜው፣ ሎሚታውና ኩፊታው፣ ከሌቻው፣ ወርቅ ለምዱ እንደጸሐይ ሲያበራ ዋለ፡፡” እንደጸሐይ የበራውን ሕብረ ባሕልና ሕብረ ማንነት ትርክቶቻችን በልኩ አጉልተው ያውቃሉ?
ሸዋና አካባቢው(ወሎን ጨምሮ) እንደ አንድ ጂዞ ስትራቴጂ ሥፍራ የሕዝቦች ውህደትና ትስስር መሠረት ሆኖት የመልክዓ ምድር መገኛው ለግብርና እና ለውጭ ንግድ የተመቸ በመሆኑ በኢትዮጵያ አገረ መንግሥት ግንባታ ታሪክ ውስጥ ቁልፍ ቦታ ይዞ መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው መግቢያ አስታውሰውናል፡፡ ሸዋና አካባቢው ከመንግሥታት ምስረታ ጋር በተገናኘ ከዘጠነኛው አንስቶ እስካሁን ያለው ረዥም የታሪክ ጉዞ በርግጥም ሊነገር፣ ሊተነተን የአደባባይ ትርክት አካል ሊደረግ የሚገባው እውነት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሸዋ ሡልጣኔት ምስረታ( እ.አ..አ.896 ዓ.ም.) እስከ ዓድዋ ድል(1888 ዓ.ም.) ሥላወሷቸው የአርጎባ(የወላስማ/ወሊ አስማ ሥርወ መንግሥት)፣ የአማራ(ሰለሞናዊ ሥርወ መንግሥት)፣ ኦሮሞ(ቱለማው በተለይ)፣ወርጂ፣ ጉራጌ፣ ጋፋት፣ ወዘተ ሕዝቦች ትስስርም ይሁን የፖለቲካ ጋብቻ የተመለከተ ታሪክ ከበቂ በላይ የታሪክ ማስረጃ ምንጮች ቢኖሩንም በታሪክ ግርዶሹ ምክንያት የወል ትርክት አካል መሆን አልቻለም፡፡
ኤንሪኮ ቼሩሊ ከሐረር አግኝቶ ያሳተመው በአረብኛ የተጻፈው የሸዋ ሡልጣኔት ዜና መዋዕል እንደሚያመለክተው ሡልጣኔቱን እ.አ.አ. በ896/7 የመሰረቱት የማህዙሚ ጎሳ አባላት ናቸው፡፡ መንግሥታቸውም ከ9ኛው እስከ 13ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በተከታታይ በገዙ አሥራ አራት ሱልጣኖች እንደጸና የታሪክ መረጃ ምንጮች ያመለክታሉ፡፡ የሸዋ ሙስሊም ሡልጣኔቱ መቀመጫ ከተማ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምሥራቅ 70 ኪሎ ሜትር ላይ የምትገኝ ወለላ የተባለች ሥፍራ እንደነበረች የጆርጅ ደብሊው ቢ ሀንቲንግፎርድ(1989) ጥናት ያመለክታል፡፡ የማህዙሚ ሥርወ መንግሥት ከመጨረሻዎቹ መሪዎች አንዱ የነበረው ሡልጣን ድልመራህ ወርጂዎች የይኖሩበት በነበረው አካባቢ በ1270ዎቹ በነበረ የርስ በርስ ጦርነት ድል ሳይቀናው ሲቀር ሕይወቱን ለማትረፍ ዐጼ(የአማራ ገዥ?) እንደሄደ ይህው የአረብኛ ዜና መዋእል ያስረዳል፡፡ የማህዙሚዎች የሸዋ ሡልጣኔት የተተካው በዋናነት የአርጎባዎች አገር በሆነው ይፋት(ዊፋት) ላይ በወላስማዎች ነበር፡፡ ወላስማዎች ከአጎራባቾቻው ጋር እየተጋቡ፣ እየተስማሙም እየተጋጩም የይፋት ሡልጣኔትን ከ13ኛው እስከ 15ኛው ክፍለ ዘመን ከሸዋ እስከ ምሥራቃዊ የኢትዮጵያ ጠረፍ እንዳስተዳደሩ ስፍር ቁጥር የሌለው የሰነድ( የኢብን ካልዱን ተማሪ የነበረው አል ማቅሪዚ ጽሑፍ- ኪታብ አል ኢልማም)፣ የአርኪዮሎጂና የቃል መረጃ ምንጮች አሉ፡፡
መነሻውን ሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ወሎ ያደረገው የክርስቲያኑ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት በአካባቢው ያሉ ሕዝቦች ተዋህደው ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በጋራ የመሠረቱት እንደሆነ አያጠያይቅም፡፡ አማራዎች፤ አርጎባዎች፣ ወርጂዎች፣ ጋፋቶች፣ ጉራጌዎች እና ኦሮሞዎች፣ አፋሮች፣ ሐረሪዎች ወዘተ በዚህ የሸዋ መንግሥታት የተጽዕኖ ምህዳር(Orbit) ውስጥ እንደሚገኙ ዜና መዋእሎች፣ የሃይማኖት ሰነዶች፣ የአርኪዮሎጂ ማስረጃዎች ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የኖሩ የቃል መረጃ ምንጮች ያመለክታሉ፡፡ ለምሳሌ ታደሠ ታምራት(ፕሮፌሠር) ከ13ኛው እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን የቤተ ክርስቲያንና መንግሥትን ግንኙነት ታሪክ ባጠኑበት መጽሐፋቸው የገላንና ያያ ሰዎች ሸዋ ውስጥ በ13ኛው ክፍለ ዘመን በኦዳ ዛፍ (ኮቢል የሚባል ዋርካ) ሥር ሃይማኖታዊ ሥርዓት ይፈጽሙ እንደነበር ገድለ አቡነ ቀውስጦስን ጠቅሰው ጽፈዋል(ገጽ 184)፡፡ ሸዋ የባለ ብዙ ማንነት ሕዝቦች ሀገር ከመሆኗ ባሻገር በ16ኛው ክፍለ ዘመን የተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች ላይ መረጃ የተወልን መነኩሴው አባ ባህሪይ እንደገለጸው “ሸዋ የመንግሥት ሀገር ነች” (ገጽ 130)፡፡ በየዘመናቱ ከሸዋ የተነሱ የፖለቲካ ኃይሎች፣ ፈረሰኛ ሠራዊታቸውን ይዘው በሰሜን እስከ ኤርትራ(በዐጼ ሠርጸ ድንግል ዘመን- የኤርትራዋ ባሬንቱ የዚህ የታሪክ ሂደት ውርስ አይደለችም ማለት አይቻልም፡፡) በምሥራቅ እስከ ዘይላ(ከዐጼ አምደጽዮን እስከ ገላውዲዮስ ዘመን)፣ በምዕራብ እስከ ሱዳን ፋዞግሊ(ዐጼ ሱስንዮስ ዘመን) በደቡብ እስከ ሞያሌ ተንቀሳቅሰው በአገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ውስጥ ቁልፍ ሚና ተጫተዋል፡፡
እነዚህ የሸዋ እና አካባቢው ሕዝቦችና ገዢዎች ትልቁን ንቅናቄያቸውን ያደረጉት ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ዐጼ ምኒልክና ራስ ጎበና ዳጬ የቱለማ ኦሮሞ፤ የሸዋ አማራ እና የሌሎችም ውህድ የሆነ ጦራቸውን አዝምተው ወሎ ወግተው ወረኢሉን የመንሥታቸው መቀመጫ ያደረጉት አርሲ፣ወለጋ፣ከሐረር ከመዝመታቸው በፊት ነበር፡፡ የመጫ ኦሮሞ ተወላጁን የጎጃሙን ንጉስ ተክለሃይማኖት(አዳል ተሰማ) በቱለማው መሪ ራስ ጎበና ዳጪ እምባቦ ላይ ያስገበሩት የጂኦ ፖለቲካዊ እና የሕዝቦች ትስስር እድሎች ጉልበት ፈጥሮላቸው፤ ኃይል አጎናጽፏቸው እንጂ በአጋጣሚ አይደለም፡፡ በርግጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፖለቲካችን ደንቃራነት የፈጠረውን የታሪክ ግርዶሽ ያሸነፉ ፋና ወጊ ጥናቾች መውጣት ጀምረዋል፡፡ አንዱ “Invisible Actors: The Oromo and the Creation of Modern Ethiopia(1855-1913)” በሚል ርዕስ በብሪያን ጀምስ ዬትስ(2002) በኤሊኖይስ ዩኒቨርሲቲ ከተጠናው እጅግ ጠቃሚ የዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ጥናት ሲሆን ሌላው የደቻሳ አበበ(ዶ/ር) ጎበና ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሕይወት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው የዘመናዊት ኢትዮጵያን እውን መሆን ያለ ምኒልክና ያለ ጎበና እንደማይታሰብ ሲጠቅሱ ይህንን እውነታ ማጉላታቸው ይመስለኛል፡፡
የሕዝቦች ትስስርና የፖለቲካ ጋብቻ በአማራና በኦሮሞ ሕዝብ መስተጋብር ብቻ የታጠረ አልነበረም-ሊሆንም አይችልም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባህልና ሥልጣኔ መጋመዱ ረቂቅ ነው፡፡ ከጥንታዊ አክሱም ዘመን ጀምሮ በዝነኞቹ የአክሱም መቃብር ሀውልቶች እና በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ላይ ከምናገኛቸው የኪነ ሕንጻ ትእምርቶች(Symbols) መካከል የውሸት በሮች (False Doors) እና የውሸት መስኮቶች(False windows) የሙታን መንፈስ(ኤከራ) መመላለሻ እንደሆኑ በጥናት የተረጋገጠ ነው (ቢትራይስ ፕሌይን Annales d'Éthiopie 1965) ፡፡ ይህ የኤከራዎች መመላለስና የመነጋገር ባህል እና እምነት ከደቡባዊ ግብጽ አንስቶ እስከ ሰሜን ኬንያ ድረስ በሚኖሩ የኩሽ ሕዝቦች በሰፊው የሚታወቅ ረዥም ዘመን ያስቆጠረ ልምምድ ነው፡፡
ሌላው በልኩ ያልተጠና እና በትርክቶቻችን ውስጥ ትኩረት ያልተሰጠው በሕዝቦች መካከል ያለ ሥልጣኔ ትስስር ታሪክ የእያንዳዱን የዛግዌ ነገሥታት የሥልጣን ዘመናትን የተመለከተ ነው፡፡ ከታሪክ ነገሥት፣ ከልዩ ልዩ ዜና መዋዕሎች፣ ከፖርቱጋል ተጓዦች(ፓኤዝና አልሜዳ) ከብሪቲሽ ሙዝየም እንዲሁም ከኮንቲ ሮሲኒ የተገኙት ምንጮች የሚረጋግጡት የሁሉም የዛግዌ ዐጼዎች( ከአንድ ሁለቱ በስተቀር) የሥልጣን ዘመን 40፤40 ዓመታት ነበር፡፡ ይህ ጉዳይ በኦሮሞ የገዳ ሥርዓት የአንድ ትውልድ የሥልጣን ዑደት ጋር አንድ አይነት የሆነው በአጋጣሚ ነው ወይስ ዛግዌዎች እና ኦሮሞዎች የኩሽ ሕዝቦች በመሆናቸው ቀዳሚ ከሆነው የጋራ ሥልጣኔያቸው የሚቀዳ የአስተዳደር ሥርዓት ነው? እነዚህስ ሀቆች የወል ትርክቶቻችን መመሆን አለመቻላቸው በፖለቲካ ደንቃራነት የተፈጠረ የታሪክ ግርዶሽ(eclipse of history) እንጂ ሌላ ምን ሊባል ይችላል? በላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትና እና በሸዋ በሚገኘው የአዳዲ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ኪነሕንጻ መካከል ያለው ፍጹም ተመሳሳይነት ምንጩ ምንድነው? ሊጠና፣ ሊነገር ልንማርበት ይገባል፡፡
በርግጥም ታሪካችን ትዝታችን ላይ የተጫነ ሸክም ሳይሆን የነፍስ መገለጥ ነው የሚያሰኘው የሕዝቦች ትሥሥር፣ ውህደት የሥልጣኔ መጋራትና መወራረስ ታሪክ መታወቁ መንፈስን ሃርነት ማውጣቱ ይመስለኛል፡፡

ታይዋን ለሞሮኮ ዜጎች የምትሰጠውን የቪዛ አገልግሎት አገደች
#ethiopia | ታይዋን ለሞሮኮ ዜጎች የምትሰጠውን የቪዛ አገልግሎት ማገዷን ይፋ አድርጋለች።
ሞሮኮ "አንድ ቻይና" ("One-China") ፖሊሲ ጋር የተያያዘውን የቤጂንግ አቋም የምትደግፍ በመሆኗ ከታይዋን ጋር ያለው የንግድና የጉዞ ግንኙነት እንቅፋት ገጥሞታል።
ውሳኔው የተሰማው ሞሮኮ በንጉሥ ሞሃመድ 6ኛ አመራር ስር ያስመዘገበችውን የ27 ዓመታት የኢኮኖሚና የማህበራዊ እድገት በታላቅ ድምቀት በማከበር ላይ በምትገኝበት ወቅት ነው።
የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እገዳውን የጣለው ሞሮኮ ቀደም ሲል ለታይዋን ዜጎች ትሰጥ የነበረውን የመግቢያ ፈቃድ በማቋረጧ ምክንያት እንደሆነ አስታውቋል።
የሞሮኮ ንጉሥ ሞሃመድ 6ኛ ስልጣን ከተረከቡበት ጊዜ ጀምሮ ሞሮኮ በሰሜን አፍሪካ የኢንዱስትሪና የንግድ ማዕከል ለመሆን ያደረገችው ጉዞ ስኬት አምጥቶላታል።
የሁለቱ ሀገራት የቪዛ ውሳኔ በዜጎች እንቅስቃሴ እና በንግድ ልውውጥ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ የማይቀር ነው ተብሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #taiwan #visas #moroccans #onechinapolicy

5 days ago
እንኳን ለቅዱስ መርቆርዮስ ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤አደረሰን🙏
የመጀመሪያ ስሙ ፒሉ-ፓዴር ሲሆን ቤተሰቦቹ አረማውያን ሲሆኑ ከአምልኮተ ጣኦት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር የተመለሱ ናቸው፡፡ ፊታቸው የውሻ የሆነ፣ የአውሬነት ጸባይ ያላቸው በእግዚአብሔር ኃይል የሚታዘዙት ሁለት አገልጋዮች የነበሩት አባቱ ወደ መርዶሳውያን ሀገር ተማርኮ ቢሔድም ጸጋ እግዚአብሔር በዝቶለት በዚያ ሹመት አጊቷል፡፡ ልጃቸው ቅዱስ መርቆርዮስን የወለዱት ግን በሮም ነው፡፡ ወላጆቹ ሲያርፉም የአባቱን ስልጣን ተረክቧል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ በክርስቲያኖች ሁሉ ዘንድ እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ታሪካቸው ከሚነገርላቸው ሰማዕታት አንዱ ሲሆን በሀገራችን በኢትዮጵያም በአማላጅነቱ የሚታወቀው ታላቁ ሰማዕት ነው፡፡ መርቆሬዎስ ማለት የአብ ወዳጅ ማለት ነው። በሁለተኛ ትርጉሙ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው። በሀገራችን በኢትዮጵያም በበርካቶች ዘንድ በፈጣን ተራዲኢነቱ ይታወቃል፡፡
የዓለም ክብራቸውን ስለ ክርስቶስ ፍቅር ከጣሉና በተጋድሏቸው ከሚታወቁ ሰማዕታትም አንዱ ነው፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስ የአባቱን ስልጣን ወርሶ በንጉሱ ስር በመርዶሳውያን አገር ላይ ተሾመ፡፡ መርቆሬዎስ በመኰንንነት በተሾመም ጊዜ የውሻ ፊት ያላቸው የአባቱ አገልጋዮች አብረውት ነበሩ፤ ለመዋጋትም ሲወጣም እግዚአብሔር የአውሬነት ተፈጥሯቸውን ይመልስለት ስለነበር ማንም አይቋቋመውም ነበር፡፡ የድል አድራጊነት ኃይሉ ዜናም በሁሉም ሀገሮች ተሰማ፡፡ በሮሜ ሀገር ጣዖትን የሚያመልከው ዳኬዎስ የተባለውም ንጉሥ የበርበር ሰዎች ጋር ጦርነት ሊገጥም በወጣ ጊዜ እጅግ ሲበዙበት ፈራ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን በጦሩ መካከል የተሳለ ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ ስላየ “እግዚአብሔር ያጠፋቸዋልና አትፍራ” አለው፤ ከዚያም ሰይፉን ለቅዱስ መርቆሬዎስ ሰጠውና “ጦርነቱን ድል ባደረግህ ጊዜ እግዚአብሔርን አስበው” አለው፡፡
ቅዱስ መርቆሬዎስ በድሉ ውስጥ ትልቅ ድርሻ በወሰደበት ውጊያም ጦርነቱ በንጉሱ ዳኪዮስ ወገን አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ መርቆሬዎስም ድል አድርጎ ሲጨርስም መልአኩ ድጋሚ ተገልጦለት “ለምን የፈጣሪህን ስም መጥራት ረሳህ” አለው፡፡ ንጉሡ ግን ከጦርነቱም በኋላ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን አደረገ፡፡ በዚህ ያዘነው ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን አልተገኘም፡፡ ንጉሡም መልእክተኞችን ልኮ አስመጣውና “ከእኔ ጋር ለምን አታጥንም?” አለው፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስ ትጥቁንና ልብሱን አውልቆ ከወረወረለት በኋላ “ክብር ይግባውና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን ፈጽሞ አልክደውም፤ ለረከሱ ጣዖቶችህም አልሰግድም” አለው፡፡ ከዚህ በኋላ ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ በክርስትናው ተፈተነ፤ ውለታው ተረስቶ ንጉሡ በልዩ ልዩ ሥቃዮችም እጅግ አሠቃየው፡፡ ይሁንና ስለ መርቆሬዎስ ብለው የሀገሩ ሰዎች እንዳይነሡበት ፈርቶ በብረት ችንካር ቸንክሮ የቀጵዶቅያና የእስያ ክፍል ወደ ሆነች ወደ ቂሳርያ ከደብዳቤ ጋር ላከው፡፡
በዚያም እጅግ ካሠቃዩት በኋላ በንጉሥ ዳኬዎስ ትዕዛዝ ኅዳር 25 ቀን አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት ተጋድሎውን ፈጸመ፤ በየወሩ በ25ኛው ቀንም መታሰቢያው ነው፡፡ የሕይወትንም አክሊል ተቀዳጀ፤ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ታነጹለት፡፡ ዛሬም የገዳማውያንን ጸሎት ይሰማል፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

7 days ago
የቀድሞው የኡጋንዳ አምባገነን መሪ ኢዲ አሚን የልጅ ልጅ የስኮትላንድ ንጉሥ ለመሆን እየሰራ ነው
#ethiopia | የቀድሞው የኡጋንዳ አምባገነን መሪ ኢዲ አሚን የልጅ ልጅ የሆነው የ25 ዓመቱ አዚዝ አብዱል በግላስጎው እየተካሄደ በሚገኘው የኮመንዌልዝ ጨዋታዎች በሱፐር ሄቪዌይት ቦክስ ውድድር የሀገሩን ስም ለማስጠራት እየተፋለመ ይገኛል።
ኢዲ አሚን ስድስት ጊዜ ያገባ ሲሆን በይፋ አምኖ የተቀበላቸውን ጨምሮ ወደ 60 የሚጠጉ ልጆችን ወልዷል። አዚዝ አብዱልም ከእነዚህ በርካታ የዘር ሐረጎች መካከል አንዱ ነው።
"ሪንጎ" በሚለው የቅጽል ስሙ የሚታወቀው አዚዝ ከ90 ኪሎግራም በላይ የክብደት ክፍል ሩብ ፍጻሜ ውድድር እንግሊዛዊውን ዳማር ቶማስን ማሸነፍ ከቻለ የነሐስ ሜዳሊያ ማገኘቱን የሚያረጋግጥ ሲሆን ይህም ከእ.ኤ.አ 1990 ወዲህ ለኡጋንዳ የመጀመሪያውን የኮመንዌልዝ የቦክስ ሜዳሊያ የሚያስገኝላት ይሆናል።
ይህ አጋጣሚ በግላስጎው መከሰቱ ለውድድሩ ልዩ ትርጉም ሰጥቶታል ምክንያቱም አያቱ ኢዲ አሚን በሕይወት በነበሩበት ወቅት ለስኮትላንድ ልዩ ፍቅር የነበራቸው ሲሆን በ1976 እራሳቸውን "የስኮትላንድ ንጉሥ" ብለው እስከመሰየም ደርሰው ነበር።
አዚዝም ልክ እንደ አያቱ '' ምናልባት አዲሱ የስኮትላንድ ንጉሥ እኔ እሆን ይሆናል ፤ እዚህ እንደደረስኩ ሰንደቅ ዓላማውን ሰቅያለሁ፤ ምክንያቱም ስኮትላንድን እጅግ በጣም እወዳታለሁ። ሀገሬ እንድታውቀኝና እውቅና እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ።” ብሏል
እራሳቸው ኢዲ አሚንም በወጣትነታቸው የኡጋንዳ የላይት ሄቪዌይት ቦክስ ሻምፒዮን እንደነበሩ የሚታወስ ሲሆን የልጅ ልጃቸው አዚዝ ግን የአያቱን አምባገነናዊና አወዛጋቢ ታሪክ ወደ ጎን በማለት በራሱ ስፖርታዊ ስኬት አዲስ ታሪክ ለመጻፍና እየሰራ ይገኛል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

Sponsored by
Surafel
7 days ago
የኢትዮጵያ የክተት ጥሪ!
*************
የዘመን ማህደርን ገልጠን ወደ ኋላ ስንመለከት፣ ልክ ከ130 ዓመታት በፊት በ1888 ዓ.ም የኢትዮጵያ ተራሮች በታላቅ የክተት አዋጅ እና በነጋሪት ድምጽ ተንቀጥቅጠው ነበር። ወራሪው የፋሺስት ጦር ሉዓላዊ ድንበራችንን ጥሶ ክብራችንን ሊገፍና ነፃነታችንን ሊቀማ በዘመተ ጊዜ፣ የወቅቱ ንጉሥ አፄ ምኒልክ ያንን ታሪካዊ የክተት ጥሪ አሰሙ።
"ጉልበት ያለህ በጉልበትህ፣ ጉልበት የሌለህ በጸሎትህ እርዳኝ፤ ሀገር የሚያጠፋ ጠላት መጥቷልና ተነስ! ይህን ሳታደርግ ቀርተህ ሀገርህ ስትደፈር ዝም ብትል ግን ማርያምን እጣላሃለሁ!" የሚለው የንጉሡ ጥሪ ኢትዮጵያን ከዳር እስከ ዳር አነቃነቃት።
ያኔ ጥሪው የኅልውና ነበር፤ ሀገር የማዳን፣ ድንበር የተጋፋውን የፋሽስት ወራሪ ኃይል በጀግንነት የመመከት ጥሪ ነበር። በዚህ ብሔራዊ ጥሪ የተንቀሳቀሰው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ እንደ ማዕበል ተምሞ በዓድዋ ተራሮች ላይ በደሙ የነፃነት ታሪክ ጻፈ። ኢትዮጵያም በልጆቿ አንድነት ዳነች።
ዛሬ ደግሞ ዘመን ተቀይሯል። የትናንቱ ጠላት በጀግኖች አባቶቻችን ተሸንፎ ታሪክ ሆኗል። ነገር ግን ዛሬም በድጋሚ ኢትዮጵያ እየተጣራች ነው።
የዛሬዋ ኢትዮጵያ ጥሪ ግን፣ እንደ ትናንቱ የጦርነት የጠላት ወረራ ክተት አይደለም። የዛሬው ጥሪ ምድሪቱን የማከም፣ እናት ሀገርን አረንጓዴ ካባ የማልበስ እና ልምላሜዋን የመመለስ የብልጽግና ጥሪ ነው። ይህ ጥሪ አባቶቻችን በደም እና በአጥንታቸው ያስከበሯትን ውድ ሀገር፣ እኛ በአረንጓዴ ዐሻራችን አድሰን፣ በላባችን አልብሰን ልዕልናዋን በተግባር የምናረጋግጥበት ታሪካዊ አዋጅ ነው።
ኢትዮጵያን በአረንጓዴ ዐሻራ ወደ ከፍታ ማማ የማሸጋገር እና የጀመረችውን የተስፋ ጉዞ የማስቀጠል ተከታታይ እና ያልተቋረጠ የክተት ጥሪ ነው።
እነሆ የዘንድሮው የኢትዮጵያ የክተት ጥሪ ደግሞ ታሪክን በአዲስ መልክ ሊያድስ፣ ተደጋጋሚ ድሎችን ሊያስመዘግብ እና የዓለምን ክብረ ወሰን በድጋሚ ሊሰብር ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም የጋራ ሀገራዊ ቀጠሮ ይዟል።
በዚህ ታሪካዊ ዕለት፣ አዲሱ የመደመር ትውልድ 800 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር ለመትከል ሀገራዊ የክተት አዋጅ ታውጆለታል።
ከማለዳው የንጋት ጮራ ጀምሮ ጀንበር እስክትጠልቅ ድረስ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እጆች፣ የነገዋን ሀገር በምናብ እያዩ በአንድ ልብ ይሰባሰባሉ። በእነዚህ ጥቂት የብርሃን ሰዓታት ውስጥ 800 ሚሊዮን የተስፋ ዘሮችን በኢትዮጵያ ማህፀን ውስጥ ያኖራሉ።
ይህ የሐምሌ 27ቱ ክተት ከዛፍ ተከላ የዘለለ እጅግ ጥልቅ የሆነ ሀገራዊ ትርጉም አለው። ይህ ድንቅ የአንድ ጀንበር ተአምር፣ የተረሱና የተራቆቱ ተራሮቻችን ዳግም ህይወት የሚዘሩበት፣ የነገው ትውልድ ንጹህ አየር የሚተነፍስበት እና የኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ በጽኑ መሰረት ላይ የሚገነባበት ህያው ታሪክ ነው።
ትናንት አባቶቻችን በነጋሪት ድምጽ ጥሪዋን ሰምተው ሀገር እንዳዳኑ ሁሉ፣ ዛሬም እኛ ልጆቿ ይህንን የአረንጓዴ ዐሻራ ጥሪ ሰምተን በጋራ ስንሰለፍ ኢትዮጵያ በልጆቿ እጅ ትንቆጠቆጣለች፣ ውበቷ ይደምቃል፣ ሉዓላዊነቷም በምጣኔ ሀብት ይረጋገጣል።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ፍቅር ተጣርታለች፤ ምድሪቱን ለማልበስ፣ 800 ሚሊዮን ዐሻራዎችን በአንድ ቀን ለማሳረፍ፣ ክተት ለሐምሌ 27!
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
#ethiopia #ebc #greenlegacy #800milliontrees #ethiopiarising #environmentalprotection #ebcdotstream

የኢትዮጵያ ክተት ጥሪ ለአረንጓዴ ዐሻራ!

11 days ago
እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏
ቅዱስ ገብርኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ!!!
ነቢዩ ዳንኤል የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ “ዐይኖቼንም አነሣሁ “እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡ ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኀይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኀይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡ በዳንኤል 10÷5-9 የተገለጸው የዚህ መልአክ ግርማ የአምላክን ግርማ ይመስላል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ “አምላክ ወሰብእ” ሰውና አምላክ ማለት ሲሆን ከዋነኞቹ የመላዕክት አለቆች አንዱ ነው፡፡
ነቢዩ ኢሳይያስ በምዕራፍ 14÷16 በሰማያት የሳጥናኤል ትዕቢትና ውድቀት ምን እንደሚመስል ሲጽፍልን “አንተ በንጋት የሚወጣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! ወደ አሕዛብ መልእክትን የላክ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ! አንተም በልብህ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደረጋለሁ፤ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወድቃለህ፤ ወደ ምደር ጥልቅም ትወርዳለህ” ይለናል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በቅድስና ሕይወት ለተጋውና በገዢዎች ዘንድ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ያደረበት ሰው ተብሎ ለተመሰገነው ለነቢዩ ዳንኤል ማስተዋልንና ጥበብን የሰጠ፣ እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጆችን ከሰይጣንና ከሞት ባርነት ነጻ ሊያወጣቸው ሰው እንደሚሆንና ሰማይንና ምድርን አሳልፎ በቅዱሳን ላይ ነግሦ እንደሚኖር በምሳሌ ገልጾ ያስተማረው መልአክ ነው፡፡
ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳንን ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት ከአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው መልአክም ነው፡፡ ሦስቱ ሕጻናት አናንያ አዛርያና ሚሳኤል ለጣኦት አንሰግድም ባሉ ጊዜ በንጉሥ ናብከደነፆር ወደ እቶን እሳት ሲጣሉ እስራታቸውን ፈቶ፣ እሳቱን እንደ ውኃ አቀዝቅዞ ያዳናቸው ቅዱስ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣንም ከእሳት ያወጣ እርሱ ነው፡፡ የቅዱስ ገብርኤል ምልጃና ጸሎት ይጠብቀን፡፡ ዛሬም ይህን አማላጅነቱንና ፈጣን ተራዳኢነቱን ያመኑ ገዳማውያ አባቶች በጸሎታቸው ይጠሩታል እርሱም ይራዳቸዋል፡፡ እኛም ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

13 days ago
ዛሬ የኢትዮጵያ የመጨረሻው ንጉሥ የልደት ቀን ነው
#ethiopia | ቁመታቸው ከ1 ሜትር ከ 60 ሴንቲ ሜትር አይበልጥም፣ክብደታቸውም ከ50 ኪግ የሚዘል አይደለም፡፡በጣም አጭር እና ቀጭን ነበሩ፡፡
ግን ግርማ ሞገሳቸው ልዮ ነው፡፡ ቤተሰቦቻቸው 8 ጊዜ ወልደው ከእርሳቸው በስተቀር አላደገላቸውም፡፡በእርግጥ እናታቸው ወይዘሮ የሺእመቤትም በልጅነታቸው ስለሞቱባቸው ያለ እናት፣በአባት ብቻ አድገዋል፡፡
አባታቸው ራስ መኮንን በባዶ እግራቸው በሮም አደባባይ ኢትዮጵያን ብሎም አፍሪካን የሸመገሉ መሪ ነበሩ።ግርማዊነታቸው ከአባታቸው ዲፕሎማሲን ተምረዋል፡፡በዓለም ላይ ከ 160 በላይ ሀገራትን የጎበኙ እሳቸው ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡የሁለተኛው የዓለም ጦርነት በአሜሪካ አሸናፊነት ሲያከተም፣የሂትለር ባድማ ጀርመን ዓለም ፊቱን አዞረባት፡፡ጀርመን እንደ ሲኦል መንደር ተቆጠረች፡፡ጃንሆይ ግን የተዘጋ በር ከፍተው ጀርመንን ጎብኝተዋል፡፡አስታርቀዋል፡፡አሜሪካ ከጆርጅ ዋሽንግተን እስከ ትራምፕ ድረስ 45 ፕሬዝዳንቶችን ሹማለች፡፡
እነዚህ ፕሬዝዳንቶች በሙሉ አየር ማረፊያ ድረስ ሂደው የሀገር መሪ አይቀበሉም፡፡ጃንሆይን ግን ፕሬዝዳንት ኬኔዲ መንገድ ወጥተው ተቀብለዋቸዋል፡፡ለጥቁር የነፃነት አውጭ ናቸው፡፡
ኤርትራን ከኢትዮጵያ አዋህደዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ከግብፅ ጣልቃገብነት ነፃ አውጥተዋል፡፡የፊውዳሊዝም ሥርዓትን አሻሽለዋል፡፡ስነፁሁፍ እንዲያድግ ነፃነትን ሰጥተዋል፡፡1960 ዎቹ ወርቃማው የስነፁሁፍ ዘመን ነበር፡።
የተፃፈ ህግን፣ ህገመንግስትን ጨምሮ አሰንደዋል፡፡ ከአፍሪካ ህብረት እስከ ተመድ ድረስ እንዲመሰረት ዋና ተዋናይ ነበሩ፡፡
የኒወክርክ ታይምስ ጋዜጣ ጃንሆይን የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ንጉስ አድርጎ ከማውጣቱም ባለፈ፣የኖቤል ሽልማት ሊሸለሙ እያለ በ 1953 ዓም በተነሳው አለመረጋጋት ምክንያት ሽልማቱ አልፏቸዋል ፡፡
የአፍሪካ መስራች ቢሆኑም፣ሀውልት ለጃንሆይ ሳይገነባ ለጋናዊው ክዋሜ ንኩርማህ ብቻ ተገንብቶ ቆይተዋል፡፡በሗላ ከመሸምቢሆን የአፍሪካ ህብረት የጃን ሀውልት በግቢው አቁሟል።
ለነባር ዕውቀት ዕድገት ተግተዋል፡፡
ጃንሆይ ለፈረንጅ የማያጎበድዱ ይልቁንም ጃንሆይ ና ህዝቦቻቸው ለነጭ ንቀት ያላቸው ብቸኛ የዓለማችን ሰዎች ናቸው ይላሉ ፈረንጀች፡፡እንዳውም ፈረንጆች አማርኛ ቋንቋ እንዲናገሩ ይገደዳሉ፡፡የኢትዮጲያን ባህል እንዲላበሱ ይወተወታሉ።
በእርግጥም ጃንሆይ፣ሀገር በቀል እውቀት እንዲለማ ከጣና ገዳማት እስከ አክሱም ፅዮን ያሉ አብያተክርስቲያናት እንዲታደሱ እና ለታሪክ ምርምር እንዲውሉ አድርገዋል፡፡
የዓለም ስልጣኔ መነሻው ውሃ እንደሆነ በመረዳት አባይን ከመገደብ ጀምረው ጣናን እስከ ማልማት እንቅስቃሴ ጀምረው ነበር፡፡ግን በነሩሲያ የፖለቲካ ጫና እና በነጣሊያን ውስጣዊ ሴራ መክኗል፡፡
ለሙስሊም ህብረተሰብ የሀይማኖቱን ምሁራንን ከየአካባቢው በመሰብሰብ ቁርዐንን ከአረብኛ ወደ አማርኛ እንዲተረጉሙ ታላቅ ድጋፍ እና አስተዋፅዎ አድርገዋል።
ጃንሆይ ሀምሌ 16 ቀን 1884 ዓም በሀረርጌ ኤጀርሳ ጎሮ ተወለዱ፡፡ ሐምሌ 16 የመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉስ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የልደት በዓላቸው ነው፡፡ራስታዎችም( ጃይማካዎች) የጃንን ልደት ይዘክራሉ።
ደጋፊና ነቃፊዎቻቸው መሳ ለመሳ ቢሄዱም ሟች አይወቀስምና ምንዳው ምንዳው ብቻ ተጻፈ
📸 ተስፋዬ ወልደሚካሄል

16 days ago
የአቡነ አረጋዊ ረድኤት እና ምልጃቸው አይለየን 🙏
አባታቸው ይስሃቅ የሮም ነገሥታት ወገን ስለሆኑ ከነገሥታት ወገን የምትሆን ሚስት ቢትታጭላቸውም እምቢ ብለው ወደ አባ ጳኩሚስ ገዳም ገቡ፡፡ በምንኩስና ስማቸው ዘሚካኤል ተብለው የሚጠሩትና ከተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አቡነ አረጋዊ፡፡ ገና በትንሽ እድሜያቸው መመንኮስ ቢፈልጉም የንጉሥ ልጅ ስለነበሩ የአባታቸውን ንግስና ወራሽ ይሆናሉ ተብለው በመታሰባቸው፣ ዓለምን ንቀውና ቆርጠው ገዳም መግባታቸውን በተለያዩ ፈተናዎች ካረጋገጡ በኋላ በ14 ዓመታቸው ምንኩስና ሰጧቸው፡፡ ዘሚካኤልም ከእንጦንስና ከመቃርስ ከጳኩሚስም የምንኩስና መንፈሳዊ ሐረግ 4ኛ ትውልድ ሆኑ፡፡ የአባ ዘሚካኤል እናት ንግሥት ዕድናም የልጃቸውን ዜና ሰምተው መንኩሰው የሴቶች ገዳም ገብተዋል፡፡ ተስዓቱ ቅዱሳን በአልአሜዳ ዘመነ መንግሥት በዘሚካኤል መሪነት በ460 ዓ.ም አክሱም ከተማ ሲገቡ እናታቸው ቅድስት ዕድናም ልጃቸውን ተከትለው መጥተዋል፡፡
ከሰንበት በስተቀር እህል የማይቀምሱት እነዚህ ቅዱሳን አባ ዘሚካኤልን የበላይ አድርገው ሾሙትና ስሙንም አረጋዊ አሉት፡፡ ተስዓቱ ቅዱሳን ኢትዮጵያን በኪደተ እግራቸው ባርከዋታል፣ በትምህርታቸው የእምነቷን መሠረት አጽንተውታል፡፡ ለ12 ዓመታትም በፍጹም አንድነት በጸሎት እየተጉ አብረው ከተቀመጡ በኋላ ተለያዩ፡፡ አቡነ አረጋዊ ከሩቅ ሆነው የዳሞን ተራራ ባዩት ጊዜ እጅግ ወደውት ሲጠጉት ረጅሙን ገደል ጫፉ ላይ ለመድረስ መውጫ ቢያጡ ሌሊቱና ቀኑን ሁሉ በጸሎት አሳለፉ፡፡ ከሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት በኋላ ቅዱስ ሚካኤል “እግዚአብሔር ወደ ተራራው ጫፍ የምትወጣበትን ነገር እስኪያዘጋጅልህ ጥቂት ታገስ” ብሏቸው ሁለት ሱባኤ በዚያ ቆዩ፡፡ ከዚያም ቁመቱ ስድሳ ክንድ የሆነ ዘንዶ በቅዱስ ሚካኤል ጥበቃ አስወንጭፏቸው ደብረ ዳሞ ላይ ሲወጡ መስቀላቸውና መጎናጸፊያቸው ያረፈበትና ቅርጽ ዛሬም ድረስ በጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ምልክቱ በግልጽ ይታያል፡፡
ጌታችን ለአቡነ አረጋዊ ተገልጦ ቃልኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡ ድንገተኛም የሰውና የእንስሳ ሞት አይደርስበትም፣ የእህል ችግርም አይኖርበትም፡፡ በልባዊ ጥሞና የገድልህን መጽሐፍ የሰማ ያለስንፍና በፍጹም መታመን የንባቡን ኃይለ ቃል ያሰማ እኔ ለችግሩ ሁሉ ፈጥኜ እደርስለታለሁ፣ አንተም የሞት ጥላ አያርፍብህም፣ እንደ ነቢያቶቼ ኤልያስና ሄኖክ ትሰወራለህ እንጂ” ካላቸው በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ አቡነ አረጋዊም ደቀ መዝሙራቸው ማትያስን ጠርተው ጌታችን የሰጣቸውን ቃልኪዳን ከገድላቸው ጋር ተጽፎ ለልጅ ልጅ መታሰቢያ እንዲሆን አዘዙት፡፡ ጌታችን እንደነገራቸውም በጥቅምት 14 ቀን ተሰውረዋል፡፡ ቅዱሳን ገዳማውያን ገድልና ትጋታቸው የዘለዓለሙን መንግስት በመናፈቅ ነውና ዘወትር በጸሎት ይተጋሉ፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና በረከታቸው ያድርብናል፡፡

17 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ማጠቃለያ ላይ ስፔን አርጀንቲናን 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፋ ዋንጫዋን በተረከበችበት የሽልማት ስነ-ስርዓት ወቅት፣ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና የፊፋው ፕሬዝደንት ጃኒ ኢንፋንቲኖ ወደ ሜዳ ሲገቡ በስታዲየሙ በነበሩ ደጋፊዎች ዘንድ ከፍተኛ የቅሬታ ጩኸትና ተቃውሞ አስተናግደዋል።
ፕሬዝደንት ትራምፕ ከጨዋታው መጀመር 45 ደቂቃ ያህል ቀደም ብሎ “ማሪን ዋን” በተሰኘችው የፕሬዝደንቱ ሄሊኮፕተር ስታዲየሙን ከበው በመብረር ነበር የደረሱት። በጨዋታው ወቅትም ከፊፋው ፕሬዝደንት ጃኒ ኢንፋንቲኖ ጋር በመሆን በመስተዋት በተከለለ የክብር እንግዶች ወንበር ላይ ተቀምጠው ጨዋታውን ተከታትለዋል። በአቅራቢያቸውም የስፔኑ ንጉሥ ፊሊፔ ስድስተኛ፣ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ እና የሜክሲኮዋ ፕሬዝደንት ክላውዲያ ሼይንባውምን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የቀድሞ ታዋቂ ተጫዋቾች ተገኝተው ነበር።
የአሜሪካ ብሔራዊ መዝሙር ከተዘመረ በኋላ የፕሬዝደንት ትራምፕ ምስል በስታዲየሙ ትላልቅ የቪዲዮ ስክሪኖች ላይ ለጥቂት ጊዜ ታይቶ የነበረ ሲሆን፣ በወቅቱ ከታዳሚዎች ዘንድ መጠነኛ የተቃውሞ ድምፅ ቢሰማም፣ በፕሬዝደንትነት ዘመናቸው በሌሎች የስፖርት መድረኮች ላይ እንደገጠማቸው ዓይነት የከረረ ጠላትነት የተሞላበት አቀባበል አልነበረም።
ነገር ግን ስፔን ድሏን ካረጋገጠች በኋላ፣ የአሜሪካው ፕሬዝደንት እና ኢንፋንቲኖ ለሽልማት ስነ-ስርዓቱ ወደ ሜዳ ሲዘልቁ በስታዲየሙ ዙሪያ ከፍተኛ የተቃውሞ ጩኸት አስተጋብቷል። የዋይት ሃውስ (የነጭ ማሊያ) የጋዜጠኞች ቡድን ሪፖርት እንዳመለከተው፣ ሁለቱ ግለሰቦች ወደ ሜዳ ከመግባታቸው በፊት በስታዲየሙ የነበረው የተለመደው የሕዝብ ድምፅ ጩኸት 78 ዴሲበል ገደማ የነበረ ሲሆን፣ ትራምፕ ሜዳውን ሲረግጡ ግን ደጋፊው ባሰማው ከፍተኛ የተቃውሞ ጩኸት ምክንያት ድምፁ ወደ 84 ዴሲበል ከፍ ሊል ችሏል።
ከዚህም በላይ ፕሬዝደንት ትራምፕ የሜዳውን መድረክ ተቀላቅለው ዋንጫው በሚነሳበት ወቅት በምስል ዕይታ ውስጥ በመግባት፣ የስፔንን ብሔራዊ ቡድን ታሪካዊ የድል አከባበር ድግስ (Victory party) በጋራ ለመጋራት እና ለመቀላቀል ጥረት ማድረጋቸው በሰፊው ተስተውሏል።

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የአንድን ቡድን ድል “የእግር ኳስ ውበት ድል” ብሎ መግለጽ ምናልባትም የተለመደና ሰልችቶን የነበረ አገላለጽ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን በ2026ቱ የኒው ጀርሲ የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ መድረክ ላይ ስፔን አርጀንቲናን ጥልቃ ስታሸንፍ፣ ማንኛውም ገለልተኛ የእግር ኳስ አፍቃሪ በዚህ አገላለጽ ላይ ቅሬታ ይኖረዋል ተብሎ አይታሰብም።
በጭማሪ ሰዓት ላይ ፌራን ቶሬስ ያንን ወርቃማ ግብ የአርጀንቲና መረብ ላይ ሲያሳርፈውና ሮድሪ ዋንጫውን ወደ ኒው ጀርሲ ሰማይ ከፍ አድርጎ ሲያነሳው፣ ለአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ያዘነ ወይም ያነባ አንድም እውነተኛ የስፖርት አፍቃሪ አልነበረም። ስፔን የተጫዋቾችንም ሆነ የተመልካቾችን ትዕግሥት የፈተነውን ያንን አሰልቺ የአርጀንቲናውያንን የብረት መከላከያ ሰብራ በመውጣት፣ በታሪኳ ሁለተኛውን የዓለም ዋንጫ በደመቀ ሁኔታ አሳክታለች። በሁሉም የእግር ኳስ መለኪያዎች—አንዳንዶች እንደሚሉት ደግሞ በስፖርታዊ የሞራል ልዕልናም ጭምር - ይህ ፍፁም ትክክለኛና የሚገባ ውጤት ነበር።
የቀድሞው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ አላን ሽረር ላይ እንደተናገረው “ትክክለኛው ቡድን እንዳሸነፈ ምንም ጥርጥር የለውም። ከጅምሩ እስከ ፍፃሜው ስፔን የኳስ ቁጥጥር የበላይነቱን ወስዳለች። እግር ኳስ ለመጫወት፣ ዕድሎችን ለመፍጠርና ከተከላካይ ጀርባ ለመውጣት የሚጥሩት እነሱ ብቻ ነበሩ። ይህ ውጤት በተጫወቱበት ማራኪ መንገድ ምክንያት ለእግር ኳስ የተገኘ ትልቅ ድል ነው፤ ስፔን በእውነት ይገባታል።”
አኃዞቹ ራሳቸው እውነታውን በግልፅ ይመሰክራሉ። ስፔን 65% የኳስ ቁጥጥር፣ 1.94 የሚጠበቅ የግብ መጠን (xG) እና 20 ወደ ግብ የተደረጉ ሙከራዎችን (11ዱ ኢላማቸውን የጠበቁ) አስመዝግባለች። በአንፃሩ በሌላኛው የሜዳ ክፍል ግብ ጠባቂው ኡናይ ሲሞን በ8 ጨዋታዎች 7ኛውን ግቡን ሳያስደፍር በመውጣት የውድድሩ ምርጥ ግብ ጠባቂ በመሆን የጎልደን ግላቭ ሽልማትን አጋብሷል። ስፔን በጠቅላላው ውድድር ያስተናገደችው 1 ግብ ብቻ ሲሆን፣ ይህም በዓለም ዋንጫ ታሪክ አንድ ሻምፒዮን ቡድን ያስተናገደው አነስተኛው የግብ መጠን ሆኖ ተመዝግቧል።
የዓለም እግር ኳስን በአሁኑ ሰዓት በበላይነት እየመራ ያለው አንድ ኃይል ቢኖር እርሱም ስፔን ነው። በአሁኑ ወቅት የዓለም፣ የኦሊምፒክ እና የአውሮፓ ሻምፒዮን ናቸው - የሴቶች ቡድናቸው የዓለም ሻምፒዮን መሆኑ ሳይረሳ! የወንዶች ቡድናቸው በአሁኑ ወቅት ባደረጋቸው ያለፉት 38 ጨዋታዎች በሁሉም ውድድሮች ላይ ሽንፈት አላስተናገደም፤ ይህም በታሪክ የማንኛውም አውሮፓ ሀገር ረጅሙ ባለመሸነፍ ጉዞ ነው።
ምንም እንኳን በዚህ ውድድር መጀመሪያ ላይ ከኬፕ ቨርዴ ጋር 0ለ0 በሆነ አሰልቺ ውጤት በመጀመር አድናቂዎቻቸውን ቢያስደነግጡም፣ ልክ እንደ 2010ቱ የደቡብ አፍሪካ ዓለም ዋንጫ (በመጀመሪያው ጨዋታ በስዊዘርላንድ 1ለ0 ተሸንፈው እንደነበረው) የመክፈቻ ጨዋታቸውን ሳይያሸንፉ ቀርተው ዋንጫውን ማንሳት የቻሉበትን አስገራሚ አጋጣሚ በድጋሚ ደግመውታል።
በዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ታሪክ ውስጥ አንድ ተጫዋች 100 እና ከዚያ በላይ ኳሶችን አቀብሎ ያጠናቀቀባቸው ሦስት አጋጣሚዎች ብቻ ሲሆኑ፣ ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ የተመዘገቡት በዚህ ምሽት በስፔን ተጫዋቾች ነው - ሮድሪ 101 ቅብብሎችን ሲያደርግ፣ የ19 ዓመቱ ታምረኛ ተከላካይ ፓው ኩባርሲ ደግሞ 121 ስኬታማ ቅብብሎችን አድርጓል።
ለዚህ ወጣት ቡድን ይህ ገና ጅምር ነው! ኩባርሲ የውድድሩ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ሲባል፣ የባርሴሎና የቡድን አጋሩ ላሚን ያማል ደግሞ ገና ወደፊት ብዙ የሚያሳያቸው ወርቃማ ዓመታት ከፊቱ ይጠብቁታል። በ19 ዓመት ከ6 ቀን ዕድሜው ላሚን ያማል ከፔሌ (1958) እና ከጁሴፔ ቤርጎሚ (1982) በመቀጠል በዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ላይ የተጫወተ ሦስተኛው ታናሽ ተጫዋች እና ሦስተኛው ታናሽ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ መሆን ችሏል።
አርጀንቲናዎች በዓለም እግር ኳስ መድረክ ላይ ብዙ ጊዜ “ጨካኝና ተንኮለኛ” ተደርገው ይሳላሉ - በተለይም በእንግሊዝ ደጋፊዎች ዘንድ። በግማሽ ፍፃሜው ላይ በእንግሊዝ ላይ እንዳደረጉት ሁሉ፣ በዚህም ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ላይ እግር ኳስ ለመጫወት ሳይሆን፣ የሜዳውን ውበትና የስፔንን እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ ብቻ ትኩረት አድርገው ነበር የገቡት። ሊአንድሮ ፓሬዴስ ዋነኛው የጨዋታ አበላሺ ሲሆን፣ ኤንዞ ፈርናንዴዝ ደግሞ የእሱ ምክትል ረዳት ነበር። ምንም እንኳን አራት የአርጀንቲና ተጫዋቾች ቢጫ ካርድ ቢመለከቱም፣ ብዙዎች ግን ዳኞች ለአርጀንቲና አሁንም ቢሆን ርኅራኄ አሳይተዋል የሚል እምነት አላቸው።
አርጀንቲናዎች በጨዋታው በድምሩ 464 ቅብብሎችን ብቻ ሲያደርጉ፣ ስፔን ግን 852 ቅብብሎችን አድርጋለች። ነገር ግን እንደ እንግሊዝ ሳይሆን፣ ስፔን በሁለተኛው አጋማሽ አልዛለችም፤ አልፈራችምም። ጨዋታው ቶሬስ በ106ኛው ደቂቃ ላይ ግብ ሳያስቆጥር ከብዙ ጊዜ በፊት በስፔን የበላይነት መጠናቀቅ ነበረበት። የአርጀንቲናው ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ 11 ኳሶችን ለማዳን (Saves) የተገደደ ሲሆን፣ ይህም በዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ታሪክ አንድ ግብ ጠባቂ ካደረጋቸው ማዳኖች ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።
በተቃራኒው ደግሞ የወቅቱ ሻምፒዮናዎች የነበሩት አርጀንቲናዎች በዓለም ዋንጫ ታሪክ በመደበኛው የ90 ደቂቃ ጨዋታ ውስጥ ወደ ግብ አንድም ሙከራ ሳያደርጉ የወጡ የመጀመሪያው ቡድን በመሆን አሳፋሪ ታሪክ አስመዝግበዋል። የመጀመሪያው ሙከራቸው የመጣው በ117ኛው ደቂቃ ላይ በሊዮኔል ሜሲ አማካኝነት ነበር። አርጀንቲና የዓለም ዋንጫ አክሊሏን ብቻ ሳይሆን፣ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ያሳየችው ባህሪ ክብሯንም ጭምር ያስገፈፋት ነበር።
ኤንዞ ፈርናንዴዝ በመጀመሪያ ለዳኛ ባለመታዘዝ ቢጫ ካርድ ከተመለከተ በኋላ፣ በፓው ኩባርሲ ላይ በሰራው እጅግ አደገኛና ዘግይቶ የመጣ ጥፋት (ታክል) በሁለተኛ ቢጫ ካርድ በካርድ ተባሯል። ጨዋታው ሲጠናቀቅ ደግሞ ሜዳው ወደ ቦክስ ስታዲየምነት ተቀይሮ ነበር! ፓሬዴስ ከሮድሪ፣ ጋቪ እና ቦርጃ ኢግሌሲያስ ጋር ወደ ግጭት ሲያመራ፣ ናሁኤል ሞሊና ደግሞ በዚያ ለሚያልፍ የስፔን ተጫዋች በቦክስ ሲሰነዝር ታይቷል።
ተንታኙ ዌይን ሩኒ ይህንን ክስተት ሲያወግዝ “ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ እንዲህ ዓይነቱን ነገር ማየት ፍጹም የሚያሳፍር ነው። አንድ ቡድን የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን ሆኖ ዘላለማዊ ክብሩን እያከበረ ባለበት ሰዓት እንዲህ ዓይነት ሁከት መፍጠር በጭራሽ ተቀባይነት የለውም። ፓሬዴስ ከዚህ የተሻለ ስብዕና ሊኖረው ይገባ ነበር፤ እሱ ግን ማቆም አልቻለም፤ አሁንም መጋፋቱን ቀጥሏል” ብሏል።
የአርጀንቲናው አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በዕንባ እየታጠቡ የቡድናቸውን እንቅስቃሴ ለመከላከል ቢሞክሩም፣ በመጨረሻ ግን ትክክለኛውና የተሻለው ቡድን ማሸነፉን አምነዋል። “ምንም እንኳን እስከ 85ኛው ደቂቃ ድረስ የበላይነታቸውን ቢያሳዩንም፣ ሜዳ ላይ 11 ተጫዋቾችን ይዘን ብንቆይ ኖሮ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማወቅ እፈልግ ነበር” ብለዋል ስለ ኤንዞ መባረር ሲናገሩ። አክለውም “ጨዋታው ክፍት በነበረበት ሰዓት እስከ መጨረሻው ለመጓዝ ሞክረን ነበር፣ ግን አልተሳካም። እነሱ ድሉ ይገባቸዋል፣ እውነታው ይህ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
አርጀንቲና ጨዋታውን ወደ ጭማሪ ሰዓት መውሰድ ብትችልም - ይህም ባለፉት ስድስት የዓለም ዋንጫዎች ውስጥ አምስቱ ጨዋታዎች ወደ ጭማሪ ሰዓት የሄዱበትን አጋጣሚ የደገመ ቢሆንም - ይህ ግን ሜዳ ላይ የነበራቸውን ፍጹም የበታችነት ሊሸፍንላቸው አልቻለም።
የቀድሞው የእንግሊዝ ግብ ጠባቂ ጆ ሃርት በበኩሉ “አርጀንቲናዎች ስለተፈጠረው ነገር ምንም ዓይነት ቅሬታ ሊኖራቸው አይገባም። ፍጹም አስጸያፊ ባህሪ ነው ያሳዩት። ሮድሪ ወደ እነሱ ፊት ሄዶ መጨቃጨቅ አልነበረበትም፤ ነገር ግን ለ120 ደቂቃዎች ሙሉ ስሜትህ ሲነካካና ዳኛው በአንተ ላይ ጫና ሲያደርግ ከቆየ በኋላ ድል ስታደርግ የሚሰማህን ስሜት መረዳት ይቻላል” ሲል ምሽቱን ቋጭቶታል።
በመጨረሻም ጥበብ አሸንፋለች፤ እግር ኳስም ነፃነቷን አውጃለች! ስፔን የዓለም አዲስ ንጉሥ ናት! 🇪🇸🏆

ስፔን ~ "የአዲሱ ትውልድ ንጉሥ"
Ethiopia | በኒው ጀርሲ የሚገኘው ሜትላይፍ ስታዲየም የ2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ ፍጻሜን በማስተናገድ የእግር ኳስ ታሪክ አዲስ ገጽ ጻፈ።
ስፔን አርጀንቲናን 1ለ0 ከተጨማሪ ሰዓት በኋላ በማሸነፍ ሁለተኛዋን የዓለም ዋንጫ አነሳች። የድሉን ግብ ፌራን ቶሬስ በ106ኛው ደቂቃ አስቆጠረ።
ይህ ፍጻሜ የተገለጸው "የታክቲክ፣ የፍጥነት እና የጥራት ውጊያ" በሚል ነበር። ስፔን በኳስ ቁጥጥር፣ በአማካይ ክፍል ብልጫ እና በፈጣን የጎን ጥቃት ጨዋታውን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረች፤ አርጀንቲና ደግሞ በጠንካራ መከላከል እና በኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ ድንቅ ብቃት ረጅም ጊዜ ጨዋታውን አቆየች።
የስፔን የበላይነት
ስፔን በኳስ ቁጥጥር፣ በትክክለኛ ቅብብሎች እና በማያቋርጥ ግፊት ጨዋታውን አስተዳደረች። የሮድሪ የመሀል ሜዳ ብቃት፣ የላሚን ያማል ፈጣን እንቅስቃሴ፣ የፓው ኩባርሲ መከላከል እና የኡናይ ሲሞን የግብ ጥበቃ ስፔንን ወደ ክብሩ አድርሰዋል።
በአንጻሩ አርጀንቲና በሊዮኔል ሜሲ እና ባልደረቦቹ ጥረት ብትታገልም የስፔንን ግፊት መቋቋም አልቻለችም። የኤንዞ ፈርናንዴዝ ቀይ ካርድ ደግሞ የቡድኑን ተስፋ አዳከመ።
የ2026 የዓለም ዋንጫ የውድድሩ ኮከቦች
የፊፋ የውድድሩ ሽልማቶች እንዲህ ተሰጥተዋል፦
🏆 የውድድሩ ምርጥ ተጫዋች (Golden Ball): ሮድሪ (ስፔን)
🧤 የውድድሩ ምርጥ ግብ ጠባቂ (Golden Glove): ኡናይ ሲሞን (ስፔን)
⭐ የውድድሩ ምርጥ ወጣት ተጫዋች: ፓው ኩባርሲ (ስፔን)
⚽ የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አግቢ (Golden Boot): ኪሊያን ምባፔ (ፈረንሳይ)
የዓለም ሚዲያዎች ምን አሉ?
ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ስፔንን እንደ "የአዲሱ ትውልድ ንጉሥ" ገልጸዋታል። በተለይ የመሀል ሜዳ ቁጥጥር፣ የቡድን ቅንጅት እና የወጣት ተጫዋቾቿ ጥራት የድሉ ቁልፍ መሆናቸው ተወድሷል። አርጀንቲና በመከላከል ብትታገልም የስፔንን ግፊት መቋቋም አልቻለችም ብለዋል።
የ2026 የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ እግር ኳስ የታክቲክ፣ የቴክኒክ እና የአዲስ ትውልድ ብልጫ የተንጸባረቀበት ታሪካዊ ምሽት ሆኖ በዓለም የእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ይታወሳል።
አለባቸው ደሳለኝ ( ከኢትዮጵያ )

19 days ago
የስፔን ንጉሥ ፊሊፔ 6ኛ የዓለም ዋንጫ ፍጻሜን በአካል ይከታተላሉ
#ethiopia | የስፔን ብሔራዊ ቡድን እሁድ በ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ከአርጀንቲና ጋር በኒውዮርክ ኒውጀርሲ ስታዲየም በሚያደርገው ጨዋታ፣ የስፔን ንጉሥ ፊሊፔ 6ኛ በአካል እንደሚገኙ ዓለም አቀፍ የዜና ተቋማት ዘግበዋል።
በሪፖርቶቹ መሠረት፣ ንጉሥ ፊሊፔ 6ኛ ብቻቸውን ሳይሆን ንግሥት ሌቲዚያ፣ ልዕልት ሌዮኖር እና ልዕልት ሶፊያ ጋር በመሆን የስፔንን ብሔራዊ ቡድን ከመድረኩ ላይ ያበረታታሉ።
ስፔን በግማሽ ፍጻሜ ፈረንሳይን 2ለ0 አሸንፋ ወደ ፍጻሜ ካለፈች በኋላ፣ የንጉሣዊው ቤተሰብ የስፔንን ማልያ ለብሶ ጨዋታውን ሲከታተል የታየ ሲሆን፣ የስፔን ብሔራዊ ቡድንን በማመስገን የድጋፍ መልዕክትም አስተላልፏል።
ንጉሡ ከድሉ በኋላ ለብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላ ፉንቴ በስልክ ደውለው እንኳን ደስ አለዎት ማለታቸውም ተነግሯል።
በእሁዱ ፍጻሜ ላይ የስፔን ንጉሥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ በስፔን ወገን ከፍተኛ የመንግሥት ውክልናን እንደሚያደርጉ ሲገለጽ፣ በአርጀንቲና በኩል ፕሬዚዳንት ሃቪዬር ሚሌይ በእምነታዊ ልማዳቸው (superstition) ምክንያት ጨዋታውን በአካል እንደማይከታተሉ ተገልጿል።

''ስጦታውን ሳይሆን የሰጠንን እንውደደው''
ከዶ/ር ማሙሻ ፈንታ ትምህርቶች
#ethiopia | በአንድ ወቅት በአንድ ታዋቂ ባህር ዳርቻ ላይ በየቀኑ ትኩስ አሳ እያጠመደ፣ እየጠበሰ የሚሸጥ አንድ ወጣት ነበር።
ሰዎች እየመጡ በእሱ አሳ ይዝናናሉ። አንድ ቀን አንድ ሚሊየነር ሰውዬ ወደዚያ ባህር ዳርቻ መጥቶ ወጣቱን ሲያየው ሊመክረው ፈለገና እንዲህ አለው "ለመሆኑ ሕይወትህ ይሄው ነው? ለምን አትማርም?" አለው
ወጣቱም፡ "ለመሆኑ ለምን እማራለሁ?" አለው
ሚሊየነሩም፡ "ተምረህ ትምህርትህን ስትጨርስ ትልቅ ሰው ትሆናለህ፤ እንደ እኔ ትልቅ ካምፓኒ ይኖርሃል" አለው።
ወጣቱም፡ "ከዛስ?" ሲል ጠየቀ።
"ከዛማ ብዙ ገንዘብ ታገኛለህ!"
"ከዛስ?"
"ከዛማ በቃ እንደ ልብህ እያረፍክ፣ ልክ እንደዚህ ባለ ቦታ እየመጣህ ትዝናናለህ!"
ወጣቱ ፈገግ ብሎ ሚሊየነሩን አየውና፡
"ታዲያ አሁንስ እያደረግኩ ያለሁት እሱን አይደል?" አለው።
የዚህ ዓለም ነገር መጨረሻው ወደ ነበረበት መመለስ ነው። እኛ የምንለፋ፣ የምንበላው
፣ የምንጠጣ፣ ቤት የምንሠራ... ከዛስ? ከዚህ ሁሉ በኋላ በሕይወታችን ውስጥ የተጨበጠ ነገር ያስፈልገናል።
በዕድሜያችን መጨረሻ ላይ ተጸጽተን፣ እንደ ንጉሥ ሰሎሞን በመክብብ መጽሐፍ ላይ "ሁሉ ከንቱ ነው፤ የከንቱ ከንቱ ፤ ነፋስንም የመከተል ያህል ነው" እንዳንል ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል።
የሰሎሞን የሕይወት ፍጻሜ ያሳዝናል፤ ምክንያቱም ሁሉን አግኝቶ መጨረሻው ባዶ ነበር።
የሰሎሞን ጸሎት፡ ሰሎሞን እግዚአብሔርን ጥበብ ለመነ፤ እግዚአብሔርም ጥበብን፣ ማስተዋልንና ባለጠግነትን ሰጠው። ነገር ግን ዋናውና ከሁሉ የሚበልጠው ነገር እሱ አልነበረም።
ሙሴ እግዚአብሔርን ሲጠይቅ የፈለገው ስጦታውን ሳይሆን ራሱን እግዚአብሔርን ነበር፤ "አንተን!" ነው ያለው። እግዚአብሔር ብቻ ነው ዘላለማዊና የተጨበጠው ነገር!
በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ የጨዋታ ተመልካች አትሁኑ!
ዛሬ በመንፈስ ቅዱስ ስም የምነግራችሁ ታላቅ እውነት አለ፤ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ የጨዋታ ተመልካች አትሁኑ። በዕድሜያችሁ መጨረሻ ላይ ተጸጽታችሁ እንዳታለቅሱ፣ አሁን በጉልምስናችሁና በወጣትነታችሁ ዘመን እግዚአብሔርን በቅንነት አገልግሉ።
ለመሆኑ እናንተ በዘመናችሁ እያደረጋችሁት ያለው ትርጉም ያለው ነገር ምንድር ነው?

21 days ago
የቅዱስ ገብርኤል ምልጃ እና ረድኤት አይለየን፤ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን🙏
“እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” 🙏
ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል በሉቃስ 1÷19 “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” ብሎ መገኛ ስፍራውንና እግዚአብሔር የሰጠውን ክብር በይፋ ያወጀ መልአክ ነው፡፡ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔር ኃይል ነው ማለት ነው። ቅዱስ ገብርኤል ድንቅ መልእክቶችን በማድረስና የተረበሹትን በማረጋጋት ይታወቃል፡፡ ነገደ መላክት በሰማይ አምላካቸው ተሰውሮባቸው ማን ፈጠረን ብለው በተጨነቁ ጊዜ ያረጋጋቸው እርሱ ነው፡፡ በክብሩ ከፍ ብሎ በመፈጠሩ መላዕክትን እኔ ነኝ የፈጠርኳችሁ ብሎ ሊያስት የሞከረውን የሀሰት አባት የያኔው (ሳጥናኤል) ጠላት ዲያብሎስ ተከራክሮ የረታው እርሱ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡
መላእክት የሰው ልጆች አፍቃሪና ወዳጅ ናቸው፡፡ ከእነዚህ አንዱ የአምላክና የሰው ልጆች ወዳጅ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ይህንም ህጻኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ከእሳት ሲያድን አይተነዋል፡፡ ዳግመኛም የፋርስ ንጉሥ የነበረው ናቡከደነፆር እግዚአብሔር አምላክ ምድሪቱንና ሕዝቡን እንዲያስተዳድር ቢፈቅድለት በትዕቢት ተሞላ፡፡ በዳንኤል 3፥1 እንደተጻፈው “ሁሉን በኃይሌ አደርጋለሁ፣ በማስተዋል ጥበቤም የአሕዛብን ድንበሮች አርቃለሁ፣ ሀብታቸውንም እዘርፋለሁ፣ የሚቀመጡባቸውንም ከተሞች አናውጣለሁ፣ በእጄም ዓለምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰበስባለሁ፣ እንደ ተተወ እንቁላልም እወስዳቸዋለሁ፤ ከእኔም የሚያመልጥ የለም፤ የሚቃወመኝም የለም” በሚል ትዕቢት ቁመቱ ስድሳ ክንድ፣ ወርዱም ስድስት ክንድ የወርቅ ጣዖትን አሠርቶ በባቢሎን አውራጃ በዱራ ሜዳ ላይ አቁሞ ያልሰገደለት እንዲገደል አዋጅ አስነገረ፡፡
አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል የተባሉ ሦስት ሕጻናት በንጉሡ ፊት ቆመው “ንጉሥ ሆይ እኛ የምናመልከው አምላክ በሰማይ አለ፡፡ ከሚነድደው ከእቶኑ እሳት ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ንጉሥ ሆይ! ይህም ባይሆን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድ ዕወቅ” ባሉ ጊዜ ወደ እቶን እሳት ሲጣሉ ደርሶ ያዳናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ናቡከደነጾርም ተገርሞ እነሆ ሰሦስት ሰዎ በእሳቱ ላይ ጥለን ነበር እኔ ግን አራት ሰዎች አያለሁ፣ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን መልክ ይመስላል አለ፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የአምላክ ባለሟል ነው፡፡ ለካሕኑ ለቅዱስ ዘካርያስ እንደነገረው በእግዚአብሔር ፊት መቆሙ ታላቅ ባለሟል መሆኑን የሚያሳይ ነውና፡፡
ገዳማውያን እናቶችና አባቶቻችን ሊቀ መላአኩ በእግዚአብሔር ፊት በቆመ ጊዜ እንዲያማልዳቸው በዘወትር በጸሎታቸው ተግተው ይጠሩታል፡፡ ከበረከታቸው እንድንካፈል ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አድናቂዎቹን አመስግኗል
#ethiopia | የኢትዮጵያ ሙዚቃ ንጉሥ በመባል የሚታወቀው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)፣ በሙዚቃው ዓለም የቆየባቸውን 25 ዓመታት አስመልክቶ ለደጋፊዎቹ የምስጋና መልእክት አስተላለፈ።
ድምጻዊው ዛሬ ባሰራጨው የጽሑፍ መልእክት የሙዚቃ ጉዞው የጀመረበትን 25ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ፣ ላለፉት ዓመታት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የሚገኙ አድናቂዎቹ ላሳዩት የማይቀንስ ፍቅርና ድጋፍ በልዑል እግዚአብሔር ስም ምስጋናውን አቅርቧል።
ቴዲ አፍሮ በመልእክቱ እንዳስታወሰው፣ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ከግማሽ በላይ በሙዚቃ ህይወቱ ውስጥ በነበሩት ውጣ ውረዶች፣ ስኬቶች እና ተግዳሮቶች ጊዜ ሁሉ አድናቂዎቹ ለእርሱ የነበራቸው ጽኑ ወዳጅነትና የማይጠፋ ፍቅር ትልቅ ጉልበት እንደሆነው ገልጿል።
የሙዚቃው ዓለም እውቅና ያተረፈለትና በርካታ ተወዳጅ አልበሞችን ለአድማጭ ያደረሰው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን፣ አድናቂዎቹ ላሳዩት ቀጣይነት ያለው ፍቅር ያለውን አክብሮት በመግለጽ ለወደፊቱም ሙዚቃዊ ስራዎቹን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክቷል።
"ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! ፍቅር ያሸንፋል!" በሚል መፈክር መልእክቱን የቋጨው ድምጻዊው፣ በአድናቂዎቹ ዘንድ ያለውን ትልቅ አክብሮት በምስጋና አረጋግጧል።
#ethiopia #getutemesgen #getunews #ethiopiamusic #ድምጻዊቴዎድሮስካሳሁን

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ ሙዚቃ ንጉሥ በመባል የሚታወቀው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)፣ በሙዚቃው ዓለም የቆየባቸውን 25 ዓመታት አስመልክቶ ለደጋፊዎቹ የምስጋና መልእክት አስተላለፈ።
ድምጻዊው ዛሬ ባሰራጨው የጽሑፍ መልእክት የሙዚቃ ጉዞው የጀመረበትን 25ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ፣ ላለፉት ዓመታት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የሚገኙ አድናቂዎቹ ላሳዩት የማይቀንስ ፍቅርና ድጋፍ በልዑል እግዚአብሔር ስም ምስጋናውን አቅርቧል። ቴዲ አፍሮ በመልእክቱ እንዳስታወሰው፣ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ከግማሽ በላይ በሙዚቃ ህይወቱ ውስጥ በነበሩት ውጣ ውረዶች፣ ስኬቶች እና ተግዳሮቶች ጊዜ ሁሉ አድናቂዎቹ ለእርሱ የነበራቸው ጽኑ ወዳጅነትና የማይጠፋ ፍቅር ትልቅ ጉልበት እንደሆነው ገልጿል።
የሙዚቃው ዓለም እውቅና ያተረፈለትና በርካታ ተወዳጅ አልበሞችን ለአድማጭ ያደረሰው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን፣ አድናቂዎቹ ላሳዩት ቀጣይነት ያለው ፍቅር ያለውን አክብሮት በመግለጽ ለወደፊቱም ሙዚቃዊ ስራዎቹን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክቷል።
"ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! ፍቅር ያሸንፋል!" በሚል መፈክር መልእክቱን የቋጨው ድምጻዊው፣ በአድናቂዎቹ ዘንድ ያለውን ትልቅ አክብሮት በምስጋና አረጋግጧል።
ድምጻዊው ዛሬ ባሰራጨው የጽሑፍ መልእክት የሙዚቃ ጉዞው የጀመረበትን 25ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ፣ ላለፉት ዓመታት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የሚገኙ አድናቂዎቹ ላሳዩት የማይቀንስ ፍቅርና ድጋፍ በልዑል እግዚአብሔር ስም ምስጋናውን አቅርቧል። ቴዲ አፍሮ በመልእክቱ እንዳስታወሰው፣ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ከግማሽ በላይ በሙዚቃ ህይወቱ ውስጥ በነበሩት ውጣ ውረዶች፣ ስኬቶች እና ተግዳሮቶች ጊዜ ሁሉ አድናቂዎቹ ለእርሱ የነበራቸው ጽኑ ወዳጅነትና የማይጠፋ ፍቅር ትልቅ ጉልበት እንደሆነው ገልጿል።
የሙዚቃው ዓለም እውቅና ያተረፈለትና በርካታ ተወዳጅ አልበሞችን ለአድማጭ ያደረሰው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን፣ አድናቂዎቹ ላሳዩት ቀጣይነት ያለው ፍቅር ያለውን አክብሮት በመግለጽ ለወደፊቱም ሙዚቃዊ ስራዎቹን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክቷል።
"ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! ፍቅር ያሸንፋል!" በሚል መፈክር መልእክቱን የቋጨው ድምጻዊው፣ በአድናቂዎቹ ዘንድ ያለውን ትልቅ አክብሮት በምስጋና አረጋግጧል።
24 days ago
ቅድስት አርሴማ የልባችንን መልካም መሻት ትሙላልን፤ ረድኤቷ እና ምልጃዋ አይለየን🙏
ራሷን ለእርሱ በሙሽርነት አሳልፋ ሰጥታለች
ራሷን የክርስቶስ ሙሽራ አድርጋ የለየች የፊቷ መልክ እጅግ ልዩ፣ ደምግባቷ ያማረ ነበረች እናታችን ቅድስት አርሴማ። የዲዮቅልጥያኖስ ታዛዥ የሆነው ንጉሥ ድርጣድስ ከሮሜ ሸሽታ በሔደችባት አብረዋት ከነበሩ ገዳማውያን ደናግል ጋራ ካሠራቸው በኋላ እናታችን ቅድስት አርሴማን ሚስቱ እንድትሆን በብዙ ሊያታልላት ሞከረ። እርሷ ግን በመንፈሳዊ ሕይወቷ ፍጹም ራሷን አሳልፋ የሰጠች፣ ራሷንም ለቸሩ አምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽራ ያደረገች ናትና ለሰማያዊ ሙሽርነቷ የታመነች ሆነች። በኋላም እመ ምኔቷን እንድታባብላት ላካት፤ እመ ምኔቷ ግን “አይዞሽ! እንዲህ ላለው ምድራዊ ኃላፊ ነገር እንዳትታለይ፤ ሰማያዊ ሙሽርነትሽንና ንጽሕናሽን አጽኚ” ብላ ይበልጥ አጸናቻት።
ንጉሡም በግድ ይዟት ሊሄድ ቢል ኃይለ መንፈስ ቅዱስ አድሮባት ነበርና ያንን በጦር የጎለመሰ ሰውነት ያለውን ብርቱ ጦረኛ ከመሬት ፈጠፈጠችው። ንጉሡም እጅግም ተቆጥቶ ቅድስት አርሴማን አሠራትና ደናግሉን በፊቷ አንድ በአንድ አንገታቸውን ቀላቸው። እርሷ ግን “አይዟችሁ!” እያለች ታጽናናቸው ነበር። ይልቁንም ትሳቀቃለች ብሎ ባደረገው ነገር ቅዱሳኑ ሰማያዊ አክሊልን ሲቀበሉ ትመለከት ነበር። እርሷንም ሁለቱን ጡቶቿን ቆ ረጠ፤ ቀጥሎም ሁለቱን ዐይኖቿን አወ ጣቸው፤ በብዙ መከራም እጅግ አሠቃያት። ንጽሕት ድንግል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልዩ የብርሃን ዐይኖችን ሰጠቻት።
በመጨረሻም እርሷን ማሠቃየት ሲሰለች ከቀሩት ከሰባ አምስት ወንዶችና ከሃያ ሰባት ደናግል ሴቶች ጋራ መስከረም ሃያ ዘጠኝ ቀን አንገቷን ሰየፋቸውና የሰማዕትነትን የድል አክሊል ተቀዳጁ። ቅድስት አርሴማ በሰማዕትነት ስታርፍ ጌታችን ነፍሷን በክብር ተቀበላት ራሷን ለእርሱ በሙሽርነት አሳልፋ ሰጥታለችና ብዙ ቃል ኪዳንም ሰጣት፡፡
ዓለምን የናቁ ገዳማውያን የሚያገኙት ምድራዊ ክብር አያጓጓቸውም፣ ስጋዊ ድሎትና ምቾት አይማርካቸውም ራሳቸውን ለጌታቸው አሳልፈው ሰጥተዋልና፡፡ እኛም ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና ከበረከታቸው እንሳተፋለን፡፡

በአፍሪካ ቀዳሚው የኢትዮጵያ አቪዬሽን...
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዘርፍ በአፍሪካ ቀዳሚ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ያለ ግዙፍ የኢኮኖሚያዊ ሞተር ሆኗል።
ዘርፉ በሀገሪቱ የቱሪዝም እና የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለሀገር ውስጥ ምርት አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።
አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት ከ165 በላይ እጅግ ዘመናዊና ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ የሆኑ አውሮፕላኖች አሉት።
አማካይ የእድሜ ዘመናቸውም ከ7 ዓመት በታች ነው።
አየር መንገዱ ተጨማሪ 67 አዳዲስ አውሮፕላኖችንም አዝዟል።
በአፍሪካ ውስጥ ካሉ ማናቸውም አየር መንገዶች በላይ ወደ 131 የሚጠጉ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች፤ 63 የአፍሪካ ከተሞችን ጨምሮ መደበኛ የመንገደኞችና የጭነት በረራዎችን ያደርጋል።
በአቪዬሽን ዘርፉ ባሳየው ተከታታይ ስኬት፣ በ2024/2025 ብቻ 7.6 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ በማመንጨት 19 ሚሊዮን መንገደኞችን አጓጉዟል።
በዚህ ዓመት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት የቢሾፍቱው የአቡ ሴራ ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ከተማ ግንባታ በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወነ ይገኛል።
ፕሮጀክቱ 12.5 ቢሊዮን ዶላር የሚፈጅ ሲሆን፣ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በዓመት 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል።
ይህም በአፍሪካ ትልቁ ያደርገዋል።
ፕሮጀክቱ የአሁኑን የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መጨናነቅ በመቀነስ፣ ኢትዮጵያን እንደ ዱባይና ኢስታንቡል የዓለም አቀፍ ትራንዚት ዋና ማዕከል ያደርጋል።
በአሁኑ ወቅት አየር መንገዱ ራዕይ 2035 ስትራቴጂን ቀርጾ በመተግበር የሀገር ውስጥ የበረራ ተደራሽነቱን ወደ 26 አሳድጓል።
በዚህ ስትራቴጂክ ዕቅድ ከ105 በላይ አዳዲስ አውሮፕላኖችን ከቦይንግ እና ኤርባስ ኩባንያዎች ጋር ውል ፈጽሞ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።
ይህም በሚቀጥሉት ዓመታት ጠቅላላ የአውሮፕላኖቹን ቁጥር ከ270 በላይ ለማድረስ ያለመ ነው።
በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ሦስት አዳዲስ ዘመናዊ የክልል አውሮፕላን ማረፊያዎች ተገንብተው ሥራ ጀምረዋል።
እነዚህም ነጌሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ጎሬ መቱ አውሮፕላን ማረፊያና ዛሬ የተመረቀው የደብረ ማርቆስ ንጉሥ ተክለሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያ ናቸው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ትልቁን የጭነት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፣ በዓመት ከ248,400 ቶን በላይ ዕቃዎችን ያጓጉዛል።
ይህም የሀገሪቱን የወጪ ንግድ፣ የአበባ፣ ቡና፣ እና አትክልት በቀጥታ ከዓለም ገበያ ጋር በማስተሳሰር የኢኮኖሚ ዋስትና ሆኗል።
እንደ ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር ሪፖርት፣ በኢትዮጵያ ያለው የአየር ጉዞ ፍላጎት በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ውስጥ በሦስት እጥፍ ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ይህ ዕድገት ከ527,000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቀጥተኛና በተዘዋዋሪ የሥራ ዕድል ፈጥሯል።

25 days ago
u12e8u130eu1303u121d u1218u1293u1308u123bu1363 u12e8u121bu129b u1324u134du1293 u120cu120eu127d u12e8u1230u1265u120d u121du122du1276u127d u121bu12d5u12a8u120du1363 u12e8u1320u1262u1263u1295u1293 u12e8u1300u130du1296u127d u1218u134du1208u1242u12eb u1260u1206u1290u127du12cd u12f0u1265u1228 u121bu122du1246u1235 u12a8u1270u121b u12e8u1270u1308u1290u1263u12cd u12e8u12f0u1265u1228 u121bu122du1246u1235 u1295u1309u1225 u1270u12adu1208 u1203u12edu121bu1296u1275 u12a0u12cdu122eu1355u120bu1295 u121bu1228u134au12ebu1363 u1208u12a0u12ebu120c u12d3u1218u1273u1275 u1270u12f3u134du1296 u12e8u1246u12e8u12cdu1295 u12e8u12a0u12abu1263u1262u12cd u1215u12ddu1265 u12e8u120du121bu1275 u1325u12ebu1244 u1260u1270u130du1263u122d u12e8u1218u1208u1230 u1290u12cdu1362
Ethiopian Broadcasting Corporation","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"User","__isEntity":"User","__isActor":"User","id":"100064325666044","url":"https://www.facebook.com/E... Broadcasting Corporation","work_info":null,"__module_operation_CometTextWithEntitiesRelay_textWithEntities":{"__dr":"ProfileGeminiWeakReferenceLink_user$normalization.graphql
የጎጃም መናገሻ፣ የማኛ ጤፍና ሌሎች የሰብል ምርቶች ማዕከል፣ የጠቢባንና የጀግኖች መፍለቂያ በሆነችው ደብረ ማርቆስ ከተማ የተገነባው የደብረ ማርቆስ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያ፣ ለአያሌ ዓመታት ተዳፍኖ የቆየውን የአካባቢው ሕዝብ የልማት ጥያቄ በተግባር የመለሰ ነው።
Ethiopian Broadcasting Corporation
27 days ago
የፖለቲካ አረዳዴ ያደገው ተንቤን ውስጥ ነው - መሐመድ ንጉሥ ኢብራሂም
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መሐመድ ንጉሥ ኢብራሂም በመቀሌ ከተማ ነው ተወልዶ ያደገው፡፡
በትግራይ ጉዳይ ላይ «ዘይዕገት ማዕበል ወለዶኣዊ ሓርነት» እና «ዘይተነገሩ ሕቅታት ዘይዛሪ ንብዓት» የተሰኙ ሁለት መጻሕፍትን በትግርኛ ቋንቋ አሳትሟል፡፡
ወጣት መሐመድ ንጉሥ የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ በተንቤን በነበረው የሦስት ዓመታት የሥራ ቆይታ የሕወሓትን ጭቆና እና የሕዝቡ አስከፊ የኑሮ ሁኔታ መታዘቡን ይገልጻል።
መሐመድ ንጉሥ ከፋና ፖድካስት ጋር ባደረገው ቆይታ የፖለቲካ አረዳዱ ያደገው ተንቤን ውስጥ መሆኑን ጠቅሶ በትግራይ ጉዳይ ባሳተማቸው መጻሕፍት የሕወሓትን የመሪነት ውድቀት አስቀድሞ እንደጻፈው ተናግሯል፡፡
አሁን ያለው ወጣት ትውልድ ለዘመናት የቆየውን የፍርሃት ሰንሰለት ሰብሮ በመውጣት የሕገ-ወጥ ቡድኑን አፈና በይፋ መጋፈጥ መጀመሩን የሚገልፀው መሀመድ፣ ይህ ንቅናቄ ደግሞ የማይቀለበስ የነፃነት ማዕበል ነው ሲል አንስቷል።
ሙያዊ ብቃትና በራስ መተማመን ያላቸው ዜጎች ተገፍተው፣ አድርባዮች ሲበረታቱ መመልከቱ ነገሮችን በጥሞና እንዲመረምር እንዳደረገው የጠቀሰው መሐመድ፤ ቡድኑ በትግራይም ሆነ በኢትዮጵያ ደረጃ ቀርቶ እንደ ድርጅት እንኳ የሚመጥን ስልታዊ መሪነት የሌለውና ያከተመለት ነው ብሏል።
የጥፋት ቡድኑ አመራር የአንድ ቤተሰብን አገዛዝ ለማስቀጠል ሲል ብቻ የትግራይን ሕዝብ ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለ መሆኑን እና ብዝሃ አስተሳሰብን ባለመቀበል የተለየ ሐሳብ ያላቸውን ዜጎች በጠላትነትና በባንዳነት ሲፈርጅ መቆየቱን ጠቅሷል።
ሕዝቡን በውሸት ሪፖርት የሚያታልለው ይኸው የጥፋት ቡድን፣ የሥርዓቱ ውድቀት የሕዝብን መሠረታዊ ጥያቄዎች ከመመለስ ይልቅ የውሸት ስታቲስቲክስ በማምረት ላይ የተጠመደ መሆኑን ተናግሯል።
በ2002 ዓ.ም የአረና ፓርቲ አባላትን "ባንዳ" በማለት ንብረታቸው የሆኑትን እንስሳቶችን ሳይቀር ውሃና ሳር ከልክሎ ለአንድ ሳምንት በማሰር እንስሳትን የቀጣ አምባገነን መሆኑን በምሬት አስታውሷል።
አሁን ላይ ወጣቱ ትውልድ ከፍርሃት ቆፈን ወጥቶ ሕገ-ወጥ ቡድኑን በግልጽ መቃወም መጀመሩ የለውጥ ጊዜው መድረሱን እንደሚያሳይ የጠቆመው ጸሐፊው፤ መጻሕፍቱ ያልተነገሩ ሐቆችንና የእናቶችን ዕንባ በማሳየት ሕዝቡ ከዚህ ጨቋኝ ሥርዓት ነፃ የሚወጣበትን የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ያመላከተ መሆኑን አረጋግጧል።
ሕገ-ወጥ ቡድኑ ሥልጣን ላይ ለመቆየት ሲል የሰዎችን መብት ብቻ ሳይሆን፣ የተለየ ሐሳብ ያላቸውን ወገኖች እንስሳት ሳይቀሩ በመቅጣት ኢ-ሰብአዊ ድርጊት የሚፈጽም ነው ሲል ወጣት መሀመድ የቡድኑን ጭካኔ አብራርቷል።
በቅድስት ዘውዱ
አቶ መሐመድ ንጉሥ ኢብራሂም ከፋና ፖድካስት ጋር ያደረገውን ቆይታ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ
https://youtube.com/watch?...

1 month ago
ማይክል ካሪክ - የኦልድ ትራፎርድ የልብ ትርታ፣ በታላላቅ ኮከቦች ጥላ ስር ተደብቆ የኖረ ድንቅ ጥበበኛ
***********************
ስለ እርሱ ሲታሰብ አምስት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችና የሻምፒዮንስ ሊጉ ድል ትዝ ሊሉን ይችላሉ። ነገር ግን እውነተኛው ማይክል ካሪክ የተገነባው በብዙዎች ዘንድ በማይታወቁ፣ ልብ በሚነኩና አስገራሚ በሆኑ ድብቅ ታሪኮች ውስጥ ነው።
ዛሬ የምናውቀው ካሪክ በኳስ ቁጥጥሩና አርቆ አሳቢነቱ የሚታወቅ የአማካይ ስፍራ ኮከብ ነው። ነገር ግን ወደ ዌስትሃም አካዳሚ በ15 ዓመቱ ሲቀላቀል ሕልሙ ሌላ ነበር፤ ያኔ የፊት መስመር አጥቂ ነበር።
ካሪክ ያደገው እንደ አላን ሺረር እና ፒተር ቤርድስሌይ ያሉ ታላላቅ ሰዎችን ባፈራው ታዋቂው የዎልሰንድ ቦይስ አካዳሚ ውስጥ ነው። የኒውካስል ዩናይትድ ደጋፊ የነበረ ቢሆንም፣ በ15 ዓመቱ ኒውካስልን ትቶ ወደ ዌስትሃም ዩናይትድ አቀና።
በ15 ዓመቱ ወደ ዌስትሃም አካዳሚ ሲቀላቀል የመስመር አጥቂ ነበር። በአንድ ጨዋታ ላይ ግን የመሃል አማካይ በመጥፋቱ በአጋጣሚ ቦታው ተቀይሮ የክፍለ ዘመኑ ብልህ አማካይ ሊሆን አጋጣሚው ተፈጠረ።
ካሪክ በቦታው መጀመሪያ ባይደሰትም ያለ እንቢታ ተጫወተ። ይህ አጋጣሚ ግን የእግር ኳስን ታሪኩን ቀየረች፤ አጥቂው ካሪክ ቀርቶ፣ የአውሮፓን መድረክ የሚገዛው ብልሁ አማካይ ተወለደ።
የካሪክ የጉርምስና ዕድሜ ደግሞ ሌላ አስገራሚ ፈተናን ይዞ መጣ። 17 ዓመቱ ላይ በአንድ ጊዜ 8 ኢንች ያህል ቁመት ጨመረ። በወቅቱ የነበረው ቀጭን ሰውነቱ ከቁመቱ ጋር ባለመመጣጠኑ ሜዳ ላይ መሮጥ እስኪያቅተው ተቸግሮ እንደነበር የቀድሞ አሰልጣኙ ሃሪ ሬድናፕ ያስታውሳሉ።
ብዙዎች የወደፊት መንገዱን ተስፋ ሲያጡበት፣ እርሱ ግን በትጋትና በጽናት ሰውነቱን ገነባ፤ በመጨረሻም ከሪዮ ፈርዲናንድ እና ፍራንክ ላምፓርድ ጋር የዌስትሃም ወርቃማ ትውልድ አካል ሆነ።
ካሪክ ገና በወጣትነቱ ጨዋታን የማንበብ ብቃቱ ድንቅ ነበር። ከዌስትሃም፣ ስዊንደን፣ በርሚንግሃም እና ቶተንሃም በኋላ በ2006 ታላቁን ማንችስተር ዩናይትድን ሲቀላቀል፣ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በሮይ ኪን መልቀቅ የዛለውን የመሃል ሜዳ የሚያክምላቸውን የፈጠራ ሰው አገኙ።
በእንግሊዝ እግር ኳስ ታሪክ ስቲቨን ጄራርድ እና ፍራንክ ላምፓርድ በችሎታ እንደማይደረስባቸው የመሀል ሜዳ ጣኦታት ይታዩ ነበር። ነገር ግን ታላቁ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ልብ ውስጥ የነበረው እውነተኛው ንጉሥ ካሪክ ብቻ ነበር።
ፈርጉሰን በግል ማስታወሻቸው ላይ “...ላምፓርድና ጄራርድ ታላላቅ ስብዕና የነበራቸው ተጫዋቾች ናቸው፤ እውነተኛ ምርጥ ተጫዋቾች ግን አልነበሩም ፤ ካሪክ ግን የእግር ኳስ አዕምሮ ነበረው። የእንግሊዝ ሚዲያዎች ስለ እነርሱ አብዝተው በማወደስ ሲጮሁ፣ ካሪክ ግን በትህትናውና በአይናፋርነቱ ምክንያት በነርሱ ጥላ ስር ተደብቆ ተበደለ።” ሲሉ ነበር እንጋፋው አሰልጣኝ በብዕራችው ከትበው ስለካሪክ የመሰከሩት።
ማይክል ካሪክ ዛሬም ቢሆን ያው ነው - ዝምተኛ፣ አስተዋይና ልባም። የዩናይትድን ታላቅ ስም ለመታደግ በዋና አሰልጣኝነት ተሰይሟል። ትናንት በዝምታ ሜዳውን እንደገዛው ሁሉ፣ ዛሬም በዚያው ጥንቁቅ አዕምሮው የታላቁን ክለብ ታሪክ ለመጻፍ እየተዘጋጀ ነው።
ካሪክ እ.አ.አ በ2006 ከቶተንሃም ማንቸስተር ዩናይትድን ከተቀላቀለ በኋላ በ12 ወርቃማ ዓመታት 5 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን፣ የሻምፒዮንስ ሊግን እና የኤፍኤ ካፕን ጨምሮ በርካታ የክብር አክሊሎችን ደፍቷል።
ሆኖም ግን እንደ ፖል ስኮልስ ፣ ጄራርድ እና ላምፓርድ ባሉ ደማቅ ስሞች ጥላ ስር ተደብቆ አሳልፏል። ነገር ግን ሳይታይ የሚደምቅ የቡድኑ የጀርባ አጥንት ነበር።
በኦልድ ትራፎርድ የነበረው ስፍራ ከብዙ ተጫዋቾች የተለየ ነበር። ግቦችን ብዙ አያስቆጥርም፣ አስደናቂ ትርዒቶችንም አያሳይም፤ ነገር ግን ጨዋታው በእርሱ እግር ይጀምር፣ በእርሱም አዕምሮ ይመራ ነበር።
ከተጫዋችነት በኋላ በሞሪንሆ እና ሶልሻየር ስር በረዳትነት የሰራው ካሪክ በ2021 ለአጭር ጊዜ ዩናይትድን በጊዜያዊነት መርቶ ጥሩ ውጤት አሳይቷል።
በመቀጠል ሚድልስብሮን በዋና አሰልጣኝነት ይዞ አስደናቂ ጊዜ ካሳለፈ በኋላ፣ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሩበን አሞሪም ስር የተንኮታኮተውን ማንችስተር ዩናይትድን ለመታደግ በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ኦልትራፎርድ ሲደርስ ብዙዎች እምነት አልጣሉበትም ነበር።
ነገር ግን ዝምተኛው ካሪክ ፤ ትናንት በዝምታ ሜዳውን እንደገዛው ሁሉ፣ ታላቁን ክለብ ከመውረድ ውርደት ታድጎ ለሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ አበቃው።
ማይክል ካሪክ በተጫዋችነት ዘመኑ በማንቸስተር ዩናይትድ የቡድን አጋሮቹ "ሃቮክ" በሚል ቅጽል ስም ይጠሩት ነበር። ይህ ስም የመጣው በወቅቱ ተጫዋቾቹ በፒኤስፒ (PSP) ላይ "SOCOM US Navy SEALs: Fireteam Bravo" የተሰኘውን ታክቲካዊና ስውር የጦርነት ጨዋታ(ኮምፒዩተር ጌም) በጋራ ሲጫወቱ ከነበራቸው ትውስታ ነው።
ዌይን ሩኒ እንደተናገረው ይህ ጨዋታና የካሪክ መሪነት ቡድኑን አንድ ላይ ለማሰባሰብ ትልቅ ሚና ነበረው። ካሪክ በጨዋታው ላይ ብቻ ሳይሆን በሜዳው ላይም ያንን ስውር እና ጥንቁቅ ታክቲክ የሚተገብር መሪ ነበር።
ካሪክ ብዙ ጊዜ በሚያወሩ ኮከቦች መካከል በዝምታ የበራ ኮከብ ነበር። የጨዋታውን ስልተ-ምት በአንድ ንክኪ የሚቀይር፣ የቡድኑን ልብ በጸጥታ የሚያስመታ ረቂቅ የሙዚቃ መሪ።
እሱን የሚለየው ያሸነፋቸው ዋንጫዎች ብቻ አይደሉም፤ ያለ ጩኸት ታሪክ መፍጠር የቻለ ሰው መሆኑ ነው። አንዳንድ ኮከቦች በብርሃን ይደምቃሉ፤ ካሪክ ግን በዝምታው ታላቅ ሆነ።
ለዚህም ነው ዛሬም በኦልድ ትራፎርድ ታሪክ ውስጥ ከማይረሱ ስሞች አንዱ ሆኖ የሚጠራው፤ እየመጡ ያሉትን ብሩህ የአሰልጣኝነት ዘመናቱንም ያስናፈቀው።
በአዲስ የሺዋስ
Ethiopian Broadcasting Corporation EBC-መዝናኛ EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት #football

የመደመር መንግሥት ስንል?
********
ታሪክን ወደ ኋላ መለስ ብለን ስንቃኝ፣ ኢትዮጵያ የነፃነት ተምሳሌት፣ የጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤት፣ እና የብዙ ፀጋዎች ማህደር ሆና እናገኛታለን።
አባቶቻችን በደማቸው አቅንተውና ጠብቀው ያቆዩልንን ይህች ምድር፣ ሀብቷ ሳይደመርና አ ቅሟ ሳይቀናጅ ለዘመናት በመቆየቱ ምክንያት፣ በእጦት አዙሪትና በድህነት ማጥ ውስጥ ስትዳክር ኖራለች።
“የኢትዮጵያውያንን ህይወት እንለውጣለን” የሚለው መፈክር በተፈራረቁ መንግስታትና ትውልዶች ዘንድ በተደጋግሚ ቢነገርም፣ በተግባር ግን እንደ ጉም ርቆን፣ እንደ ህልም ተንሳፎ ቆይቷል።
ዘመናት ነጎዱ፣ ትውልዶች ተፈራረቁ፤ እኛ ግን በተረገጥንበት ቦታ መቆማችንን አልተውንም። በዚህ የታሪክ መስቀለኛ መንገድ እና በተከማቸ የቤት ስራ አጣብቂኝ ውስጥ ነው እንግዲህ "የመደመር መንግስት" ብቅ ያለው።
ለመሆኑ የመደመር መንግስት ምንነት ምንድን ነው?
የመደመር መንግስት ማለት መከፋፈልን፣ መነጠልን፣ እና የአንዱን መቃብር የሌላው ዙፋን የሚያደርገውን የዜሮ ድምር ጨዋታ በመፀየፍ፣ ሀገራዊ ፀጋዎችንና አቅሞችን ወደ አንድ የብልፅግና ወንዝ የሚያፈስ ስርዓት ነው። በመደመር ፍልስፍና መነፅር፣ የመንግስት ሚና እንደ ባለፈው ዘመን ሁሉን አድራጊ ፈጣሪ ወይም ጨቋኝ መሆን ሳይሆን፣ የትብብር ሞተር መሆን ነው።
ይህ መንግስት ዜጎችን፣ የግሉን ዘርፍ፣ እና ሀገራዊ አቅሞችን በማስተባበር፤ ትላንት ያመለጠንን የባከነ ጊዜ "በፈጠራ እና በፍጥነት" የሚያካክስ፣ ገቢር ነበብ (Pragmatic) የሆነ የዘመነ መንግስታዊ መዋቅር ነው።
መሰረታዊ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ዲፓርቸሩም ይሄው ነው፡ ትናንትን ከስህተቱ ተምሮ ማረም፣ ዛሬን በትጋት መስራት፣ እና ነገን በምናብ ተልሞ ማለም።
የመደመር መንግሥት ስንል፣ በፍልስፍና መሠረቱ ከታሕታይ መዋቅር (እንደ ኢኮኖሚ እና መሠረተ ልማት) ለውጥ ይልቅ ለላዕላይ መዋቅር (አስተሳሰብ እና ባህል) ለውጥ ቅድሚያ የሚሰጥ ሥርዓት ማለታችን ነው። ይህ መንግሥት የማኅበረሰብን ልዩ ልዩ ጸጋዎች፣ ዕሴቶች፣ እና አቅሞች ማሰባሰብ ለብልጽግና ወሳኝ መሆኑን በፅኑ ያምናል።
የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ኃይሎች በሚፈጥሩት ፍትጊያ ውስጥ ሚዛን (ወርቃማውን አማካይ) በመጠበቅ ሁሉንም አቅፎ የሚጓዝ ነው።
ይህንን እውነት ይበልጥ ለመረዳት የመደመርን መንግሥት መሠረታዊ መለያዎች ካለፉት መንግሥታት ታሪክ ጋር ማነፃፀር ግድ ይላል።
የሀገራችን የፖለቲካ ጉዞ ከውጭ ሀገር (ከምዕራብም ሆነ ከምሥራቅ) የልማት ሞዴሎችን እንዳለ ገልብጦ በማምጣት የኢትዮጵያን ነባራዊ እውነታ ለማሳጣት ሲጥር የኖረ ፤የንጉሡ ሥርዓት "ሰማይ አይታረስ፣ ንጉሥ አይከሰስ" በሚል መርህ አይነኬነትን ያነገሠ፣ ለውጥን የሚጠላና ቆሞ-ቀርነትን ያተረፈ ፊውዳላዊ ሥርዓት ሆና የተካው የደርግ መንግሥት ደግሞ የሶቪየትን ሞዴል በጭፍን በመከተል "ትሻልን ሰድጄ ትብስን አመጣሁ" እንዲሉ፣ በኅብረተሰብአዊነት ስም የግሉን ዘርፍ አቀጭጮ፣ ሀብት ፈጣሪነትን አውግዞ ሀገርን ለከፋ የኢኮኖሚ ቀውስና አዙሪት ዳርጓል።
የኢሕአዴግ መንግሥት በበኩሉ ብሔርን ከአስተዳደራዊ ወሰን ጋር በማስተሳሰሩ ጽንፈኝነትን ያቀጣጠለ፣ ሀገራዊ አንድነትን የሸረሸረ እና በመጨረሻም የሀገር ሀብት በጥቂት የፖለቲካ ልሂቃን እጅ እንዲወድቅ ያደረገ ፣እነዚህ ሁሉ መንግሥታት ከዜሮ ድምር ፖለቲካ፣ ተቀናቃኝን አሳዶ ከማጥፋት፣ እና የሕዝብን እያደገ የሚመጣ ፍላጎት በጊዜው ካለመመለስ አባዜ አልወጡም ነበር።
ከዚህ በተቃራኒ፣ የመደመር መንግሥት የገበያ መር እና የመንግሥት መር ፅንፎችን በማስወገድ "የትብብር ሞዴልን" ገንዘቡ ያደርጋል። የግሉ ዘርፍ ሀብት እንዲፈጥር ሲያበረታታ፣ መንግሥትም ራሱ በኢንተርፕረነርሺፕ (ስራ ፈጣሪነት)ዕሳቤ አዳዲስ ዘርፎችን በመፍጠርና ሀገራዊ ሀብትን በማከማቸት ይተጋል።
የመደመር መንግሥት ሌላው ግዙፍ መለያው "የዔሊ ጉዞን" ሰብሮ በ"ፍጥነት፣ ፈጠራ እና ዝላይ" መገስገሱ ነው። አዳጊ ሀገራት የበለፀጉት ሀገራት የሄዱበትን የክፍለ ዘመናት አዝጋሚ (ደረጃ በደረጃ) ጉዞ መከተል የለባቸውም በማለት፣ ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በቀጥታ በመቀላቀል "የዝላይ መንገድን" (Leapfrogging) በመጠቀም ኢትዮጵያን ተወዳዳሪ ለማድረግ ይሠራል።
ከዚህም ባሻገር፣ የመደመር መንግሥት "ምናባዊ ከፍታን" ተላብሷል። የይድረስ ይድረስ ጊዜያዊ ማስታገሻዎችን ትቶ፣ እንደ አዲስ አበባ ወንዞች ልማት (ገበታ ለሸገር) እና የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሮችን በመሰሉ ሩቅ አላሚ ፕሮጀክቶች ሀሳብን ወደ መሬት በማውረድ "የማድረግ ዐቅሙን" በተግባር አረጋግጧል።
በአጠቃላይ የመደመር መንግሥት የትናንትናውን የተከማቸ ዕዳ በፈጠራ የሚያቃልል፣ ያመለጠንን የኢንዱስትሪ አብዮት ጊዜ የሚያካክስ፣ እና ኢትዮጵያን በጠንካራ ሥርዓታዊ መዋቅርና ትብብር ወደ ብልጽግና ማማ የሚያሸጋግር መሪ ብርሃን ነው።
በአዶኒያስ ወ/አረጋይ
#ethiopianbroadcastingcorporation #medemer #philosophyofmedemer #nationalunity

የአበበ፣ የኃይሌ እና የቀነኒሳ መንፈስ በለንደን ጎዳናዎች!
**************************
የማይቻል የሚመስለውን የቻለ!
የለንደን ጎዳናዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ እግሮችን አስተናግደዋል። በነዚህ ጎዳናዎች ላይ የረገጡ ብዙ እግሮችም የማይዘነጋ ታሪክ ፅፈዋል፤ ጥቂቶች ግን ታሪክን ራሱን መልሰው ቀርፀውታል።
ይህ እሑድ ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በለንደን ጎዳናዎች በኢትዮጵያዊ አትሌት የተፈፀመ የስፖርት ገድል ነው።
ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች ማጠናቀቅ ከዓመታት በፊት ለሰው ልጅ አዕምሮ “የማይታሰብ የቅዠት ድንበር” ነበር። ዮሚፍ ግን ይህንን የዘመናት ገደብ በታላቅ ወዝ፣ በመጀመሪያ የሙከራ ውድድሩ 1 ሰዓት ከ59 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ በመግባት ሰብሮታል።
ኬንያዊው ሴባስቲያን ሳዌ በ1፡59፡30 ቀዳሚ ሆኖ ቢጨርስም፣ የ28 ዓመቱ ቅልጥመ-ረዥሙ ዮሚፍ ያስመዘገበው ውጤት ግን በዓለም አትሌቲክስ ታሪክ ውስጥ እጅግ አስገራሚው እና ተአምረኛው የመጀመሪያ ማራቶን ተብሎ ተመዝግቧል።
ዮሚፍ ቀጀልቻ ለአትሌቲክስ አዲስ አይደለም። የግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረወሰን እስከቅርብ ጊዜ ድረስ የግሉ ነበር። በ1500፣ በ1 ማይል፣ በ5 ሺህ እና በ10 ሺህ ሜትር ፈጣን ሰዓቶችን ያስመዘገበ የረጅም ርቀት ንጉሥ ነው።
ነገር ግን ታሪክን ራሱን ያስገረመው ትልቁ ውሳኔው፣ አብዛኞቹ ሯጮች ለዓመታት የሚለማመዱትንና የሚፈሩትን ማራቶን፣ በ11 ሳምንታት ዝግጅት ብቻ ለመሮጥ መቁረጡ ነበር።
ይህ ውሳኔ ልክ እንደ አበበ ቢቂላ ቆራጥነት፣ እንደ ኃይሌ ገብረሥላሴ እልህ እና እንደ ቀነኒሳ በቀለ አልሸነፍ ባይነት በለንደን ጎዳናዎች ላይ በዚያች የሚያዚያ እሁድ ሲያስተጋባ የዋለበት ሆነ።
ይህ ውጤት ዝም ብሎ የተገኘ አይደለም፤ ከጀርባው በሰከንዶች የታጠረ የሳይንስ እና የፅናት ፍልሚያ ታሪክ አለው።
ዮሚፍ በዝግጅቱ መጀመሪያ ላይ ባጋጠመው ከባድ ጉዳት ምክንያት ልምምድ አቋርጦ ነበር። ነገር ግን ስፔን ድረስ ተጉዞ በከፍተኛ ህክምና ሕመሙን አሸንፎ ነው ወደ ልምምድ የተመለሰው።
በውጤታማው አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ስር በሳምንት ከ120 እስከ 140 ኪሎ ሜትር እየሮጠ፣ በየሦስት ሳምንቱ የደም ምርመራ እየተደረገለት፣ የኃይል መጠኑ ተለክቶና የንፋስ አቅጣጫ ተጠንቶለት ነው ለዚህ ታላቅ ውድድር የበቃው።
ዮሚፍ በታሪክ የመጀመሪያውን ማራቶን የሮጠ አትሌት የገባበትን የፈጠነ ሰዓት በ24 ሰከንዶች ልዩነት በማሻሻል አዲስ የስፖርት ታሪክ ፅፏል።
ይሁን እንጂ 25ኛው እና 35ኛው ኪሎ ሜትር ላይ መውሰድ የነበረበትን የውሃ ማሟያ በስህተት ሳይወስድ መቅረቱ ጥቃቅን የምትመስል፣ ግን ኃይል ያሳጣችው ከባድ ስህተት ነበረች።
በዚህም ምክንያት ውድድሩ ሊያልቅ 41ኛው ኪሎ ሜትር ላይ በሰውነቱ ውስጥ ያለው ኃይል ሙሉ በሙሉ ተሟጠጠ።
ውድድሩን አጠናቆ ከመስመር ሲገባ ለአሰልጣኞቹ የተናገረው የመጀመሪያው ቃል፡“አዝናለሁ፣ ሁለቱን ጠርሙሶች ስቼ ውድድሩን አጣሁት” የሚል ነበር።
እርሱ ውድድሩን ያጣ መስሎት ነበር፤ ነገር ግን ዓለምን ያስደመመ አዲስ ታሪክ መስራቱን በወቅቱ አልተረዳም ነበር።
በአዲዳስ (adidas Adizero Adios Pro Evo 3) ጫማ ታግዞ፣ ያለምንም የረጅም ጊዜ የማራቶን ልምድ እና በኃይል እጥረት ውስጥ ሆኖ 1:59:41 መግባት ተአምር ካልሆነ ምን ሊባል ይችላል?
በውድድሩ ማብቂያ ጉልበቱ አልቆ፣ ድካም እየተጫነው ያሳየው የአጨራረስ ወኔ የኢትዮጵያውያንን የማይበገር፣ ተስፋ ያለመቁረጥ እና የአልሸነፍ ባይነት መንፈስ ለዓለም በድጋሚ ያሳየበት ነበር።
እርሱ ውድድሩን ስላላሸነፈ አዝኖ ሊሆን ይችላል፤ ዓለም ግን በመጀመሪያው ውድድር 1፡59 የገባውን ይህን ጀግና ከማድነቅ አልተመለሰም።
በመጨረሻዎቹ አስጨናቂ ሜትሮች ላይ ፊቱ ላይ ይነበብ የነበረው ቁርጠኝነትና የድል ጥማት፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ምንጊዜም እንደማይተኛ እና ሁልጊዜም አዳዲስ ታሪክ ሰሪዎችን ለዓለም እንደሚያበረክት ያሳየበት ትልቅ ማረጋገጫ ነው።
ለዚህ ጀግና ምን ዓይነት ክብር ይገባዋል?
ለዚህ በሰከንዶች ድንበር ውስጥ ለሰፈረው፣ በዓለም ሁለተኛ፣ በኢትዮጵያ ቀዳሚ የሆነውን ታሪካዊ ሰዓት ላስመዘገበው የሰከንዶች ንጉሥ ዮሚፍ ቀጀልቻ እኛ ኢትዮጵያውያን ምን ዓይነት ክብር እንስጠው?
በአዲስ አበባ ዳርቻዎች ብርድና ቁር ሳይበግረው ለዛሬው ማንነቱ የበቃው ይህ ጀግና የሀገር ባለውለታ ነው። ዮሚፍ የሰከንዶች ንጉሥ ብቻ አይደለም፤ እርሱ ገና ማራቶንን እየለመደው ያለ ነው።
በቀጣይ በበርሊን አሊያም በቺካጎ የራሱን የዓለም ክብረወሰን ለመጻፍ፣ ወይም በ2028 የሎስ አንጀለስ ኦሊምፒክ የወርቅ አክሊል ለመድፋት አልሞ ተነስቷል።
“ይህ ገና ጅምሩ ነው!” .... ይላል ከ2018ም ሆነ ከምንጊዜም የስፖርት ታሪኮችም የአንዱ ባለቤት የሆነው ዮሚፍ።
በአዲስ የሺዋስ
Ethiopian Broadcasting CorporatEBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት #ebc #ethiopia #athletics #london

16 A+ ያስመዘገበው የዓመቱ ኮከብ ተማሪ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
#ethiopia | Ethiopian Civil Service University በዛሬው ዕለት 1,817 ተማሪዎችን በአደዋ ድል መታሰቢያ አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ መካከል በSurvey Engineering የተማረው ዘለቀ መንግስቴ በላቀ አካዳሚያዊ ውጤቱ የዓመቱ ኮከብ ተማሪ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያና ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
ተመራቂው በዩኒቨርሲቲ ቆይታው ከወሰዳቸው 58 ኮርሶች 16 A+ በማስመዝገብ ይህን ክብር ማግኘቱ ተገልጿል። ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት የሆነው ዘለቀ፣ ለስኬቱ የቤተሰቡ፣ በተለይም የባለቤቱ ድጋፍ ትልቅ ሚና እንደነበረው ገልጿል።
ዘለቀ በዩኒቨርሲቲ ቆይታው ከአካዳሚክ ትምህርት ባሻገር ጠቃሚ ልምዶችን እንዳገኘ በመግለጽ፣ ወደፊትም በተማረበት የሙያ ዘርፍ አገሩን በታማኝነት ለማገልገል ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የንጉሥ ታደሰ ተመራቂዎች ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በመጠቀም አገራቸውንና ህዝባቸውን በትጋትና በታማኝነት እንዲያገለግሉ አሳስበዋል።

ቅዱስ ገብርኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፣ የልባችንን መልካም መሻትም ይሙላልን!!!
ነቢዩ ዳንኤል የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ “ዐይኖቼንም አነሣሁ “እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡ ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኀይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኀይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡ በዳንኤል 10÷5-9 የተገለጸው የዚህ መልአክ ግርማ የአምላክን ግርማ ይመስላል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ “አምላክ ወሰብእ” ሰውና አምላክ ማለት ሲሆን ከዋነኞቹ የመላዕክት አለቆች አንዱ ነው፡፡
ነቢዩ ኢሳይያስ በምዕራፍ 14÷16 በሰማያት የሳጥናኤል ትዕቢትና ውድቀት ምን እንደሚመስል ሲጽፍልን “አንተ በንጋት የሚወጣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! ወደ አሕዛብ መልእክትን የላክ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ! አንተም በልብህ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደረጋለሁ፤ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወድቃለህ፤ ወደ ምደር ጥልቅም ትወርዳለህ” ይለናል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በቅድስና ሕይወት ለተጋውና በገዢዎች ዘንድ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ያደረበት ሰው ተብሎ ለተመሰገነው ለነቢዩ ዳንኤል ማስተዋልንና ጥበብን የሰጠ፣ እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጆችን ከሰይጣንና ከሞት ባርነት ነጻ ሊያወጣቸው ሰው እንደሚሆንና ሰማይንና ምድርን አሳልፎ በቅዱሳን ላይ ነግሦ እንደሚኖር በምሳሌ ገልጾ ያስተማረው መልአክ ነው፡፡
ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳንን ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት ከአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው መልአክም ነው፡፡ ሦስቱ ሕጻናት አናንያ አዛርያና ሚሳኤል ለጣኦት አንሰግድም ባሉ ጊዜ በንጉሥ ናብከደነፆር ወደ እቶን እሳት ሲጣሉ እስራታቸውን ፈቶ፣ እሳቱን እንደ ውኃ አቀዝቅዞ ያዳናቸው ቅዱስ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣንም ከእሳት ያወጣ እርሱ ነው፡፡ የቅዱስ ገብርኤል ምልጃና ጸሎት ይጠብቀን፡፡ ዛሬም ይህን አማላጅነቱንና ፈጣን ተራዳኢነቱን ያመኑ ገዳማውያ አባቶች በጸሎታቸው ይጠሩታል እርሱም ይራዳቸዋል፡፡ እኛም ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
ነቢዩ ዳንኤል የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ “ዐይኖቼንም አነሣሁ “እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡ ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኀይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኀይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡ በዳንኤል 10÷5-9 የተገለጸው የዚህ መልአክ ግርማ የአምላክን ግርማ ይመስላል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ “አምላክ ወሰብእ” ሰውና አምላክ ማለት ሲሆን ከዋነኞቹ የመላዕክት አለቆች አንዱ ነው፡፡
ነቢዩ ኢሳይያስ በምዕራፍ 14÷16 በሰማያት የሳጥናኤል ትዕቢትና ውድቀት ምን እንደሚመስል ሲጽፍልን “አንተ በንጋት የሚወጣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! ወደ አሕዛብ መልእክትን የላክ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ! አንተም በልብህ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደረጋለሁ፤ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወድቃለህ፤ ወደ ምደር ጥልቅም ትወርዳለህ” ይለናል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በቅድስና ሕይወት ለተጋውና በገዢዎች ዘንድ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ያደረበት ሰው ተብሎ ለተመሰገነው ለነቢዩ ዳንኤል ማስተዋልንና ጥበብን የሰጠ፣ እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጆችን ከሰይጣንና ከሞት ባርነት ነጻ ሊያወጣቸው ሰው እንደሚሆንና ሰማይንና ምድርን አሳልፎ በቅዱሳን ላይ ነግሦ እንደሚኖር በምሳሌ ገልጾ ያስተማረው መልአክ ነው፡፡
ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳንን ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት ከአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው መልአክም ነው፡፡ ሦስቱ ሕጻናት አናንያ አዛርያና ሚሳኤል ለጣኦት አንሰግድም ባሉ ጊዜ በንጉሥ ናብከደነፆር ወደ እቶን እሳት ሲጣሉ እስራታቸውን ፈቶ፣ እሳቱን እንደ ውኃ አቀዝቅዞ ያዳናቸው ቅዱስ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣንም ከእሳት ያወጣ እርሱ ነው፡፡ የቅዱስ ገብርኤል ምልጃና ጸሎት ይጠብቀን፡፡ ዛሬም ይህን አማላጅነቱንና ፈጣን ተራዳኢነቱን ያመኑ ገዳማውያ አባቶች በጸሎታቸው ይጠሩታል እርሱም ይራዳቸዋል፡፡ እኛም ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
1 month ago
ከደብረማርቆስ ባህርዳር በረራ‼️
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከደብረ ማርቆስ - ባሕር ዳር መደበኛ በረራ ሊጀምር ነው‼️
የደብረ ማርቆስ ከተማና የአካባቢው ማህበረሰብ ለዓመታት ሲጠብቀው የነበረውና የልማት ምዕራፍ ማሳያ የሆነው የደብረ ማርቆስ (ንጉሥ ተክለሃይማኖት) አውሮፕላን ማረፊያ፣ የመጀመሪያውን ታሪካዊ በረራ ካስተናገደ በኋላ አሁን ደግሞ አዲስና ተደራሽ የበረራ መስመር ሊጀምር መሆኑ ታውቋል።
በመሆኑም የበረራ ቀናትን እንደሚከተለዉ አሳውቋል::
1.ከአዲስ አበባ ወደ ደበረ- ማረቆስ ደርሶ መልስ በየቀኑ:
2.ከደብረ ማረቆስ ወደ ባህር ዳር በሳምንት አራት ቀን (4) ሲሆን የበረራ ቀን ሰኞ፣ዕሮብ፣አርብና እሁድ ነው
3.ከባህር ዳር ወደ ደበረ ማረቆስ ደግሞ በሳምንት ሶስት ቀን (3) የበረራ ቀን ማክሰኞ፣ሃሙስና ቅዳሜ መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን ከሚቀጥለው አርብ ማለትም 19/10/2018ዓ/ም ጀምሮ አገልግሎቱ እንደሚጀምር ተገልጿል።
Seledadotio

ሊዮኔል ሜሲ የዓለም ዋንጫ ታሪክ አዲስ ንጉሥ
የአርጀንቲናው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በዓለም ዋንጫ ታሪክ ብዙ ግቦችን ያስቆጠረ ተጫዋች በመሆን አዲስ ክብረ ወሰን አስመዘገበ። ሜሲ ይህንን ታሪካዊ ድል ያሳካው አሁን በአርጀንቲና እና በኦስትሪያ መካከል እየተካሄደ ባለው የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ላይ ባስቆጠረው ግብ ነው።
በጨዋታው 38ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ግብ የሜሲን የዓለም ዋንጫ የግብ መጠን ወደ 17 ከፍ በማድረግ፣ የጀርመኑን አጥቂ ሚሮስላቭ ክሎዜ የነበረውን የ16 ግቦች ክብረ ወሰን በይፋ እንዲያፈርስ አስችሎታል።
በጨዋታው 10ኛው ደቂቃ ላይ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት መቶ ሳይጠቀምበት ቀርቶ የነበረ ቢሆንም፣ በመቀጠል ባሳየው ብቃት ኳሷን መረብ ላይ በማሳረፍ አዲስ ታሪክ መጻፍ ችሏል። ይህ ድል ሜሲ በ6ኛው ተከታታይ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎው ያመዘገበው ሲሆን፣ የዘንድሮውን የዓለም ዋንጫ ድንቅ አጀማመር በይበልጥ ደምቆ እንዲታይ አድርጎታል።
ሜሲ ከዚህ ቀደም የነበረውን የክሎዜን ክብረ ወሰን ለመጀመሪያ ጊዜ እኩል ያደረገው በአልጄሪያ ላይ በነበረው የምድብ ጨዋታ ላይ ነበር። አሁን ግን ይህንን ክብረ ወሰን ብቻውን በመቆጣጠር የእግር ኳስ ዓለሙን የ"GOAT" ደረጃውን በይበልጥ አጠናክሯል።

2 months ago
የንጉሥ ሚካኤል ቤተ መንግስት
በተወዳጇ የደሴ ከተማ ጀሚ ተብሎ በሚጠራ ኮረብታ አናት ላይ የሚገኘው የንጉሥ ሚካኤል ቤተ መንግስት ግዙፉን የአይጠየፍ አዳራሽ፣ የልጅ እያሱ እልፍኝ፣ የራስ እምሩ ችሎት ቤትና የንጉሥ ሚካኤል የፀሎት ቤት አካቶ የያዘ ታሪካዊ ቦታ ነው፡፡ ከእነዚህ ቅርሶች መካከል በ1907 ዓ/ም በመገንባት የደሴ ከተማን ዘመናዊ ታሪክ የሚጋራው የአይጠየፍ አዳራሽ ዝነኛው ነው፡፡ አይጠየፍ ከረጅም ጊዜ ዕደሜ ቆይታው ባሻገር የሀገራችንን የሥነ-ሕንፃ ሥራና ጥበብ ዕድገት ጠቋሚ ከመሆኑ ባሽገር ቀደም ባለው ዘመን የነበረውን የግብር ሥርዓት እና አንድነት የሚዘክር በመሆኑ ታሪካዊ ፋይዳው ጉልህ ነው
Visit Amhara

"ንጉሥ አርማህ"
ሰኞ ሰኔ 15 በልዩ ፕሮግራም
መደበኛ፦ 500 ብር፣
ቪ.አይ.ፒ (VIP)፦ 5,000 ብር፣
ቪ.ቪ.አይ.ፒ (VVIP)፦ 10,000 ብር ፣
ፕሪሚየም። (premium ) :-50,000 ብር
ለተጨማሪ መረጃ እና ትኬት ለማግኘት
በስልክ ቁጥር. 0910195041
.0910316603
1000343965037 CBE
ዳንኤል አሸናፊ
ለተዋናይ ዳንኤል አሸናፊ (ዳኒ ጢሞ)
ላለፉት 30 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ እና በተለያዩ ፊልሞች ላይ ወጣትነቱን እና ሙሉ አቅሙን እየሰጠ ያለው ዳንኤል አሸናፊ (ዳኒ ጢሞ) "ያልተዘመረለት የጥበብ ኮከብ" በሚል ርዕስ አድናቂዎቹ የሙያ አጋሮቹ የጥበብ ቤተሰቦች በተገኙበት በክብር ሊመሰገን ነው።
በዕለቱም ተወዳጁ ንጉሥ አርማህ ቴአትር ለዕይታ ይቀርባል።

Comments