ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አድናቂዎቹን አመስግኗል
#ethiopia | የኢትዮጵያ ሙዚቃ ንጉሥ በመባል የሚታወቀው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)፣ በሙዚቃው ዓለም የቆየባቸውን 25 ዓመታት አስመልክቶ ለደጋፊዎቹ የምስጋና መልእክት አስተላለፈ።
ድምጻዊው ዛሬ ባሰራጨው የጽሑፍ መልእክት የሙዚቃ ጉዞው የጀመረበትን 25ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ፣ ላለፉት ዓመታት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የሚገኙ አድናቂዎቹ ላሳዩት የማይቀንስ ፍቅርና ድጋፍ በልዑል እግዚአብሔር ስም ምስጋናውን አቅርቧል።
ቴዲ አፍሮ በመልእክቱ እንዳስታወሰው፣ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ከግማሽ በላይ በሙዚቃ ህይወቱ ውስጥ በነበሩት ውጣ ውረዶች፣ ስኬቶች እና ተግዳሮቶች ጊዜ ሁሉ አድናቂዎቹ ለእርሱ የነበራቸው ጽኑ ወዳጅነትና የማይጠፋ ፍቅር ትልቅ ጉልበት እንደሆነው ገልጿል።
የሙዚቃው ዓለም እውቅና ያተረፈለትና በርካታ ተወዳጅ አልበሞችን ለአድማጭ ያደረሰው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን፣ አድናቂዎቹ ላሳዩት ቀጣይነት ያለው ፍቅር ያለውን አክብሮት በመግለጽ ለወደፊቱም ሙዚቃዊ ስራዎቹን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክቷል።
"ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! ፍቅር ያሸንፋል!" በሚል መፈክር መልእክቱን የቋጨው ድምጻዊው፣ በአድናቂዎቹ ዘንድ ያለውን ትልቅ አክብሮት በምስጋና አረጋግጧል።
#ethiopia #getutemesgen #getunews #ethiopiamusic #ድምጻዊቴዎድሮስካሳሁን

23 days ago