የአቡነ አረጋዊ ረድኤት እና ምልጃቸው አይለየን 🙏
አባታቸው ይስሃቅ የሮም ነገሥታት ወገን ስለሆኑ ከነገሥታት ወገን የምትሆን ሚስት ቢትታጭላቸውም እምቢ ብለው ወደ አባ ጳኩሚስ ገዳም ገቡ፡፡ በምንኩስና ስማቸው ዘሚካኤል ተብለው የሚጠሩትና ከተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አቡነ አረጋዊ፡፡ ገና በትንሽ እድሜያቸው መመንኮስ ቢፈልጉም የንጉሥ ልጅ ስለነበሩ የአባታቸውን ንግስና ወራሽ ይሆናሉ ተብለው በመታሰባቸው፣ ዓለምን ንቀውና ቆርጠው ገዳም መግባታቸውን በተለያዩ ፈተናዎች ካረጋገጡ በኋላ በ14 ዓመታቸው ምንኩስና ሰጧቸው፡፡ ዘሚካኤልም ከእንጦንስና ከመቃርስ ከጳኩሚስም የምንኩስና መንፈሳዊ ሐረግ 4ኛ ትውልድ ሆኑ፡፡ የአባ ዘሚካኤል እናት ንግሥት ዕድናም የልጃቸውን ዜና ሰምተው መንኩሰው የሴቶች ገዳም ገብተዋል፡፡ ተስዓቱ ቅዱሳን በአልአሜዳ ዘመነ መንግሥት በዘሚካኤል መሪነት በ460 ዓ.ም አክሱም ከተማ ሲገቡ እናታቸው ቅድስት ዕድናም ልጃቸውን ተከትለው መጥተዋል፡፡
ከሰንበት በስተቀር እህል የማይቀምሱት እነዚህ ቅዱሳን አባ ዘሚካኤልን የበላይ አድርገው ሾሙትና ስሙንም አረጋዊ አሉት፡፡ ተስዓቱ ቅዱሳን ኢትዮጵያን በኪደተ እግራቸው ባርከዋታል፣ በትምህርታቸው የእምነቷን መሠረት አጽንተውታል፡፡ ለ12 ዓመታትም በፍጹም አንድነት በጸሎት እየተጉ አብረው ከተቀመጡ በኋላ ተለያዩ፡፡ አቡነ አረጋዊ ከሩቅ ሆነው የዳሞን ተራራ ባዩት ጊዜ እጅግ ወደውት ሲጠጉት ረጅሙን ገደል ጫፉ ላይ ለመድረስ መውጫ ቢያጡ ሌሊቱና ቀኑን ሁሉ በጸሎት አሳለፉ፡፡ ከሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት በኋላ ቅዱስ ሚካኤል “እግዚአብሔር ወደ ተራራው ጫፍ የምትወጣበትን ነገር እስኪያዘጋጅልህ ጥቂት ታገስ” ብሏቸው ሁለት ሱባኤ በዚያ ቆዩ፡፡ ከዚያም ቁመቱ ስድሳ ክንድ የሆነ ዘንዶ በቅዱስ ሚካኤል ጥበቃ አስወንጭፏቸው ደብረ ዳሞ ላይ ሲወጡ መስቀላቸውና መጎናጸፊያቸው ያረፈበትና ቅርጽ ዛሬም ድረስ በጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ምልክቱ በግልጽ ይታያል፡፡
ጌታችን ለአቡነ አረጋዊ ተገልጦ ቃልኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡ ድንገተኛም የሰውና የእንስሳ ሞት አይደርስበትም፣ የእህል ችግርም አይኖርበትም፡፡ በልባዊ ጥሞና የገድልህን መጽሐፍ የሰማ ያለስንፍና በፍጹም መታመን የንባቡን ኃይለ ቃል ያሰማ እኔ ለችግሩ ሁሉ ፈጥኜ እደርስለታለሁ፣ አንተም የሞት ጥላ አያርፍብህም፣ እንደ ነቢያቶቼ ኤልያስና ሄኖክ ትሰወራለህ እንጂ” ካላቸው በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ አቡነ አረጋዊም ደቀ መዝሙራቸው ማትያስን ጠርተው ጌታችን የሰጣቸውን ቃልኪዳን ከገድላቸው ጋር ተጽፎ ለልጅ ልጅ መታሰቢያ እንዲሆን አዘዙት፡፡ ጌታችን እንደነገራቸውም በጥቅምት 14 ቀን ተሰውረዋል፡፡ ቅዱሳን ገዳማውያን ገድልና ትጋታቸው የዘለዓለሙን መንግስት በመናፈቅ ነውና ዘወትር በጸሎት ይተጋሉ፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና በረከታቸው ያድርብናል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

3 months ago