የኢትዮጵያ የክተት ጥሪ!
*************
የዘመን ማህደርን ገልጠን ወደ ኋላ ስንመለከት፣ ልክ ከ130 ዓመታት በፊት በ1888 ዓ.ም የኢትዮጵያ ተራሮች በታላቅ የክተት አዋጅ እና በነጋሪት ድምጽ ተንቀጥቅጠው ነበር። ወራሪው የፋሺስት ጦር ሉዓላዊ ድንበራችንን ጥሶ ክብራችንን ሊገፍና ነፃነታችንን ሊቀማ በዘመተ ጊዜ፣ የወቅቱ ንጉሥ አፄ ምኒልክ ያንን ታሪካዊ የክተት ጥሪ አሰሙ።
"ጉልበት ያለህ በጉልበትህ፣ ጉልበት የሌለህ በጸሎትህ እርዳኝ፤ ሀገር የሚያጠፋ ጠላት መጥቷልና ተነስ! ይህን ሳታደርግ ቀርተህ ሀገርህ ስትደፈር ዝም ብትል ግን ማርያምን እጣላሃለሁ!" የሚለው የንጉሡ ጥሪ ኢትዮጵያን ከዳር እስከ ዳር አነቃነቃት።
ያኔ ጥሪው የኅልውና ነበር፤ ሀገር የማዳን፣ ድንበር የተጋፋውን የፋሽስት ወራሪ ኃይል በጀግንነት የመመከት ጥሪ ነበር። በዚህ ብሔራዊ ጥሪ የተንቀሳቀሰው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ እንደ ማዕበል ተምሞ በዓድዋ ተራሮች ላይ በደሙ የነፃነት ታሪክ ጻፈ። ኢትዮጵያም በልጆቿ አንድነት ዳነች።
ዛሬ ደግሞ ዘመን ተቀይሯል። የትናንቱ ጠላት በጀግኖች አባቶቻችን ተሸንፎ ታሪክ ሆኗል። ነገር ግን ዛሬም በድጋሚ ኢትዮጵያ እየተጣራች ነው።
የዛሬዋ ኢትዮጵያ ጥሪ ግን፣ እንደ ትናንቱ የጦርነት የጠላት ወረራ ክተት አይደለም። የዛሬው ጥሪ ምድሪቱን የማከም፣ እናት ሀገርን አረንጓዴ ካባ የማልበስ እና ልምላሜዋን የመመለስ የብልጽግና ጥሪ ነው። ይህ ጥሪ አባቶቻችን በደም እና በአጥንታቸው ያስከበሯትን ውድ ሀገር፣ እኛ በአረንጓዴ ዐሻራችን አድሰን፣ በላባችን አልብሰን ልዕልናዋን በተግባር የምናረጋግጥበት ታሪካዊ አዋጅ ነው።
ኢትዮጵያን በአረንጓዴ ዐሻራ ወደ ከፍታ ማማ የማሸጋገር እና የጀመረችውን የተስፋ ጉዞ የማስቀጠል ተከታታይ እና ያልተቋረጠ የክተት ጥሪ ነው።
እነሆ የዘንድሮው የኢትዮጵያ የክተት ጥሪ ደግሞ ታሪክን በአዲስ መልክ ሊያድስ፣ ተደጋጋሚ ድሎችን ሊያስመዘግብ እና የዓለምን ክብረ ወሰን በድጋሚ ሊሰብር ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም የጋራ ሀገራዊ ቀጠሮ ይዟል።
በዚህ ታሪካዊ ዕለት፣ አዲሱ የመደመር ትውልድ 800 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር ለመትከል ሀገራዊ የክተት አዋጅ ታውጆለታል።
ከማለዳው የንጋት ጮራ ጀምሮ ጀንበር እስክትጠልቅ ድረስ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እጆች፣ የነገዋን ሀገር በምናብ እያዩ በአንድ ልብ ይሰባሰባሉ። በእነዚህ ጥቂት የብርሃን ሰዓታት ውስጥ 800 ሚሊዮን የተስፋ ዘሮችን በኢትዮጵያ ማህፀን ውስጥ ያኖራሉ።
ይህ የሐምሌ 27ቱ ክተት ከዛፍ ተከላ የዘለለ እጅግ ጥልቅ የሆነ ሀገራዊ ትርጉም አለው። ይህ ድንቅ የአንድ ጀንበር ተአምር፣ የተረሱና የተራቆቱ ተራሮቻችን ዳግም ህይወት የሚዘሩበት፣ የነገው ትውልድ ንጹህ አየር የሚተነፍስበት እና የኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ በጽኑ መሰረት ላይ የሚገነባበት ህያው ታሪክ ነው።
ትናንት አባቶቻችን በነጋሪት ድምጽ ጥሪዋን ሰምተው ሀገር እንዳዳኑ ሁሉ፣ ዛሬም እኛ ልጆቿ ይህንን የአረንጓዴ ዐሻራ ጥሪ ሰምተን በጋራ ስንሰለፍ ኢትዮጵያ በልጆቿ እጅ ትንቆጠቆጣለች፣ ውበቷ ይደምቃል፣ ሉዓላዊነቷም በምጣኔ ሀብት ይረጋገጣል።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ፍቅር ተጣርታለች፤ ምድሪቱን ለማልበስ፣ 800 ሚሊዮን ዐሻራዎችን በአንድ ቀን ለማሳረፍ፣ ክተት ለሐምሌ 27!
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
#ethiopia #ebc #greenlegacy #800milliontrees #ethiopiarising #environmentalprotection #ebcdotstream

5 days ago