Logo
FastMereja
ሊዮኔል ሜሲ የዓለም ዋንጫ ታሪክ አዲስ ንጉሥ

​የአርጀንቲናው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በዓለም ዋንጫ ታሪክ ብዙ ግቦችን ያስቆጠረ ተጫዋች በመሆን አዲስ ክብረ ወሰን አስመዘገበ። ሜሲ ይህንን ታሪካዊ ድል ያሳካው አሁን በአርጀንቲና እና በኦስትሪያ መካከል እየተካሄደ ባለው የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ላይ ባስቆጠረው ግብ ነው።

​በጨዋታው 38ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ግብ የሜሲን የዓለም ዋንጫ የግብ መጠን ወደ 17 ከፍ በማድረግ፣ የጀርመኑን አጥቂ ሚሮስላቭ ክሎዜ የነበረውን የ16 ግቦች ክብረ ወሰን በይፋ እንዲያፈርስ አስችሎታል።

​በጨዋታው 10ኛው ደቂቃ ላይ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት መቶ ሳይጠቀምበት ቀርቶ የነበረ ቢሆንም፣ በመቀጠል ባሳየው ብቃት ኳሷን መረብ ላይ በማሳረፍ አዲስ ታሪክ መጻፍ ችሏል። ይህ ድል ሜሲ በ6ኛው ተከታታይ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎው ያመዘገበው ሲሆን፣ የዘንድሮውን የዓለም ዋንጫ ድንቅ አጀማመር በይበልጥ ደምቆ እንዲታይ አድርጎታል።

​ሜሲ ከዚህ ቀደም የነበረውን የክሎዜን ክብረ ወሰን ለመጀመሪያ ጊዜ እኩል ያደረገው በአልጄሪያ ላይ በነበረው የምድብ ጨዋታ ላይ ነበር። አሁን ግን ይህንን ክብረ ወሰን ብቻውን በመቆጣጠር የእግር ኳስ ዓለሙን የ"GOAT" ደረጃውን በይበልጥ አጠናክሯል።

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.