''ስጦታውን ሳይሆን የሰጠንን እንውደደው''
ከዶ/ር ማሙሻ ፈንታ ትምህርቶች
#ethiopia | በአንድ ወቅት በአንድ ታዋቂ ባህር ዳርቻ ላይ በየቀኑ ትኩስ አሳ እያጠመደ፣ እየጠበሰ የሚሸጥ አንድ ወጣት ነበር።
ሰዎች እየመጡ በእሱ አሳ ይዝናናሉ። አንድ ቀን አንድ ሚሊየነር ሰውዬ ወደዚያ ባህር ዳርቻ መጥቶ ወጣቱን ሲያየው ሊመክረው ፈለገና እንዲህ አለው "ለመሆኑ ሕይወትህ ይሄው ነው? ለምን አትማርም?" አለው
ወጣቱም፡ "ለመሆኑ ለምን እማራለሁ?" አለው
ሚሊየነሩም፡ "ተምረህ ትምህርትህን ስትጨርስ ትልቅ ሰው ትሆናለህ፤ እንደ እኔ ትልቅ ካምፓኒ ይኖርሃል" አለው።
ወጣቱም፡ "ከዛስ?" ሲል ጠየቀ።
"ከዛማ ብዙ ገንዘብ ታገኛለህ!"
"ከዛስ?"
"ከዛማ በቃ እንደ ልብህ እያረፍክ፣ ልክ እንደዚህ ባለ ቦታ እየመጣህ ትዝናናለህ!"
ወጣቱ ፈገግ ብሎ ሚሊየነሩን አየውና፡
"ታዲያ አሁንስ እያደረግኩ ያለሁት እሱን አይደል?" አለው።
የዚህ ዓለም ነገር መጨረሻው ወደ ነበረበት መመለስ ነው። እኛ የምንለፋ፣ የምንበላው
፣ የምንጠጣ፣ ቤት የምንሠራ... ከዛስ? ከዚህ ሁሉ በኋላ በሕይወታችን ውስጥ የተጨበጠ ነገር ያስፈልገናል።
በዕድሜያችን መጨረሻ ላይ ተጸጽተን፣ እንደ ንጉሥ ሰሎሞን በመክብብ መጽሐፍ ላይ "ሁሉ ከንቱ ነው፤ የከንቱ ከንቱ ፤ ነፋስንም የመከተል ያህል ነው" እንዳንል ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል።
የሰሎሞን የሕይወት ፍጻሜ ያሳዝናል፤ ምክንያቱም ሁሉን አግኝቶ መጨረሻው ባዶ ነበር።
የሰሎሞን ጸሎት፡ ሰሎሞን እግዚአብሔርን ጥበብ ለመነ፤ እግዚአብሔርም ጥበብን፣ ማስተዋልንና ባለጠግነትን ሰጠው። ነገር ግን ዋናውና ከሁሉ የሚበልጠው ነገር እሱ አልነበረም።
ሙሴ እግዚአብሔርን ሲጠይቅ የፈለገው ስጦታውን ሳይሆን ራሱን እግዚአብሔርን ነበር፤ "አንተን!" ነው ያለው። እግዚአብሔር ብቻ ነው ዘላለማዊና የተጨበጠው ነገር!
በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ የጨዋታ ተመልካች አትሁኑ!
ዛሬ በመንፈስ ቅዱስ ስም የምነግራችሁ ታላቅ እውነት አለ፤ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ የጨዋታ ተመልካች አትሁኑ። በዕድሜያችሁ መጨረሻ ላይ ተጸጽታችሁ እንዳታለቅሱ፣ አሁን በጉልምስናችሁና በወጣትነታችሁ ዘመን እግዚአብሔርን በቅንነት አገልግሉ።
ለመሆኑ እናንተ በዘመናችሁ እያደረጋችሁት ያለው ትርጉም ያለው ነገር ምንድር ነው?
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

21 days ago