8 hours ago
መዝሙረ ሄላም ላይ የተደረገ አጭር ኂሳዊ ንባብ
ከቢኒያም አቡራ
#ethiopia | አዳም ረታ ታሪክን ከነገሥታት፣ ከመሪዎች፣ ማኅበረሰቡ ባበጀው ድልድል ውስጥ ‹ላዕላይ› ከሚባሉት ደረጃዎች አንጻር አያስመለክተንም። ታሪካዊ ከሚባሉ አጋጣሚዎች ውስጥ የተዘነጉትን ጥቃቅን የታሪክ ኹነተ-ደቂቅ (micro-events) ይመርጣል። ይወስዳል መንገድ ላይ … “ቀዳዳ” በተሰኘው ታሪክ ላይ ፍንዳታውን ከሚሞት ዘመድ፣ ከሚደነግጥ ለማኝ፣ ከሚሰነጠቅ የወፍ እንቁላል፣ ከሚፈስ የእናት ወተት ጋር Micro-Macro Connection በመፍጠር የትልቁ ቀዳዳ መፈጠርን ከሚጢጢዬ ሽንቁሮች ጋር ያስተሳስርልናል። እንዲህ ያሉ የኒው ሂስቶሪሲዝም ባሕሪያትን ከዚህ ቀደም ባሳተማቸው መጻሕፍቱ ውስጥ በተለያየ መጠን እናገኛለን።
Adam Reta አዳም ረታ "መዝሙረ ሄላም" በተሰኘው በዐዲሱ መጽሐፉ ላይም በኢትዮጵያ ታሪካዊ-ፖለቲካዊ አጋጣሚ ውስጥ እንደ ዐውራ የሚታዩትን የእድገት በኅብረት ዘመቻን እንደነ-አሮን፣ እንደነቃል … ባሉ ገጸባሕርያት በኩል፣ የሰባ ሰባቱን ድርቅ በሄላም ጡት በኩል፣ “ጥላሁን ለምን ለምን ሞተ” እየተባለ ኢዮቤልዩ ቤተመንግሥት ጋር የተደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ በሡልጣን በኩል፣ የከተማ መሬት ዐዋጅን በተለያዩ ግለሰቦች በኩል … እናያለን። በዚህም የታሪክን ትልቅ ካርታ ለመረዳት የተረሱና የጠለሉ ታሪኮችን ይመረምራል። ስለዚህ ነቁጣዊ ማኅበራዊ ክስተቶችን ወደ ታሪክ ምኩራብ በማምጣት ከትልቁ የታሪክ ምሥል ጎን ያስተያያል። ይህ ደግሞ የኒው ሂስቶሪሲዝም ኹነኛ ማጠንጠኛ ነው።
ልክ “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ …” በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ ባለው “የመንግሥቱ ጊዜ” በሚለው ድርሰት ውስጥ፣ ትልቁን “የታኅሣሥ ግርግር”ን እንደ መቼት አምጥቶ የተጻፈውና የተተኮረው ግን ኹነተ-ደቂቅ (micro-events) ላይ ነው። ስለግርማሜ ንዋይ፣ ስለኮሌኔል ወርቅነህ ገበየሁ፣ ሰለጄነራል ሙልጌታ ቡሊ አይደለም የሚያትተው። ስለአንድ ብላቴና ከእንቅልፍ መነሳት፣ ስለገበጣ ጨዋታ፣ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሕፃናትን አሰብስቦ ‹ኪራላይሶን› የሚያስብል ካሕን፣ ስለመንደር ውስጥ ሐሜቶች፣ ስለግለሰቦች ፍርሃት፣ በአጋጣሚ ስላየው አስደናቂ አሞራ … ያወጋል። የታሪክ አጋጣሚ አምጥቶ በታሪክ ውስጥ ግለሰቦች ላይ ስለሚረብበው የታሪክ መንፈስ ያትታል። ልክ እንደዚሁ መዝሙረ ሄላም ላይም ጽሑፉ ታሪክን አያብራራም፤ ነገር ግን ታሪክ እንዴት በሰው ልብ ውስጥ እንደሚኖር ያሳያል። በዚህ ኹነተ-ደቂቅ (micro-event) ምክንያት በዘመኑ ላይ ያገነገነውን ባሕላዊ እምነትን፣ የሥልጣን መዋቅርን፣ የወል ግንዛቤን አጨንቁረን እንድንመለከት ያስችለናል።
ከመንግሥት ሼልፍ ላይ ሳይኾን ከግለሰብ ጀርባ ላይ የተወሰደው የአዳም የአጻጻፍ መንገድ ከኒው ሂስቶሪስዝም ጽንሰ-ሐሳቦች ጋር በአንድ መም ላይ የሚሄዱ ናቸው። መዝሙረ ሄላም የተሰኘው ዐዲሱ የአዳም ረታ መጽሐፍ የኒው ሂስቶሪሲዝም ባሕርያትን ይጋራል። አንዳንድ ነገሮችን በዓይን መመልከት ባይቻልም በግብሩ (ቁስ ላይ በሚያደርገው ግፊት) ግን ይታወቃል። በመዝሙረ ሄላም መጽሐፍ ውስጥም አንዳንድ ነገሮችን በቀጥታ ማየት ባንችልም ቅሉ እነርሱን የሚያሳይልንን ነገሮች ግን እንቃኛለን። ዘማች ወጣት ተማሪዎችን እናያለን፤ መንግሥትን፣ ሕግንና ኃይልን ግን በቀጥታ አንመለከትም። የተማከለ ኃይል አናይም ግን የገጸባሕርያቱ የፍርሃት ምንጭ ከተማከለ ኃይል ጋር የተያያዘ ቀጭን መስመር መኖሩን እናያለን። መንግሥትም ቢኾን በቀጥታ አይገባም፤ ነገር ግን ፍርሃት እንደ ሥርዓት ዘዋሪ (system driver) ይኾናል። እንደ ሚሸል ፉኮ አገላለጽ ኃይል ከተማከለ ሥርዓት የሚመነጭ ሳይኾን በየትኛውም ቦታና ጊዜ በፍርሃት፣ በልማድ፣ በንግግር … ሊከሰት የሚችል ሂደት አይደል?
መዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክ እንደ “circulation of social energy” ቀርቧል። መዝሙረ ሄላም ላይ መረጃ ከመንግሥት አይመጣም፤ ከግለሰብ እንጂ። የከተማ መሬት ዐዋጅም ኾነ የተማሪዎች ዘመቻ በገጸባሕርያቱ ወሬ ውስጥ ነው የሚንቀረቀበው። ይህ የመረጃ ሥርዓት ኃይል ማን እንዳለው ማን እንደሌለው ያሳያል። እንግዲህ ይህ በፉኮኛ micro-power መኾኑ ነው። በመዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክ እንደ ወሬ እንጂ እንደ ሰነድ አይቀርብም።
ወሬ የፍርሃት ቤንዚን ነው … ፍርሃት ደግሞ በዝምታ መሸበብን ይፈጥራል … የዝምታ አፈ-ሙቅ ደግሞ ኃይለኛው እንዳይታይ ያደርጋል … የተደራጀው ኃይል ጥፋትን ሊያደርስ ባሰበ ቁጥር የወሬ ቤንዚን ይጨምራል። ሰዎች በዕቅብተ-ንግግር ራሳቸውን ሲሸብቡ ደርዝ ያለው ሙግት ይኮሰምናል፣ ንግግር ሲጠፋ ያልታወቀ አደጋ ይከሰታል፣ ፍርሃትም ይጨምራል። ያልታወቀ አደጋ ደግሞ ከታወቀ አካል ይመጣል። ስለዚህ ጥንስሱ የሚጀምረው ከወሬ እንደኾነ ያስመለክተናል። አዳም በመዝሙረ ሄላም ላይ ታሪክን እንደ “circulation of social energy” ሲያቀርብ ፕሬዝዳንት፣ ጀነራል፣ ፕሮፌሰር የኾኑ ታሪክ ከላዕላይ ያስቀመጣቸው ሰዎች አያስፈልጉትም። በአንጻሩ ሄላም ለማን እንደሳመችው ተደርጎ ብርሃኔ ያስወራው ወሬ፣ የሄላም አባት ወታደር በመኾኑ ምክንያት በካሱ፣ በሄኖክ እናት የተነዛው ወሬ እና ሄላም ከሄኖክ ጋር የተቆራረጠችበት መንገድ እንዲሁም የሄላምን የጡት ወተት በተመለከተ የተነዛው ወሬን ይጠቀማል።
መዝሙረ ሄላምን ከድኅረ-ቅኝ-አገዛዝ የኂስ መንገድ አንጻር እንመልከተው።
እውን ቅኝ-ግዛት ተረት ኾኖ ቀርቷል? በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በሥነልቦና ረገድ የቅኝ አገዛዝ ዳናው ሙሉ ለሙሉ ጠፍቷል? አዳም በመዝሙረ ሄላም ጽሑፍ ውስጥ ከቅኝ-ግዛት በተወረሰ መዋቅር ምክንያት የተሰናከለን ሕይወት ሊያስመለክተን ይኾን?
“ከተሞች ከቅኝ ግዛት በኋላ ሁለት ዓይነት መልክ ይኖራቸዋል፤ ለጥቂቱ የተድላ፣ ለተቀረው ደግሞ የአሳር መንደር ይኾናሉ” ይላል ፍራንዝ ፋኖን። በመዝሙረ ሄላም ላይ እና “የቢሾፍቱ ልጆች ጥላሞት” የተሰኘው ድርሰት ላይም ይህንን ነው የምንመለከተው። “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ …” በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ ካሉ ጽሑፎች መካከል “የቢሾፍቱ ልጆች ጥላ ሞት” አንዱ ነው። የቢሾፍቱ ልጆች ሆቴሉን ያዩታል፤ ግን አይገቡበትም። ሆቴሉ የሀገራቸው መሬት ላይ ነው፤ እነርሱ ግን ከሆቴሉ ውጭ ናቸው። መናፈሻው ውስጥ አንዲት የፈረንጅ ልጅ ጠግባ ለልጆቹ እንደ ውሻ ዳቦ ትወረውርላቸዋለች። አፈር ላይ የወደቀን ዳቦ አራግፈው ይመገባሉ። በገዛ ሐይቃቸው ዳር ላይ ናቸው፤ ሌሎች ግን በጀልባ እየተንሸራሸሩ ይንፈላሰሳሉ። ለፈረንጆቹ ያደረው ሞገስ የላንድሮቨር ተፈናጣጭ ኾኗል። ሌሎቹ ግን ከመኪናው ውጪ ናቸው። ሞገስ እንደ እነርሱ ሕጻን ቢኾንም ለፈረንጅ በማሸርገዱ የትምህርት ቤቱ ባለቤት ሲመስል ሌሎች ልጆች ግን በገዛ መምህራቸው ይብጠለጠላሉ። የቢሾፍቱ ልጆች፣ ነጻ በተባለች ሀገር እየኖሩ በቅኝ ግዛት ጥላ ይተዳደራሉ። የቢሾፍቱ ልጆች በገዛ መንደራቸው አካሉ በማይታይ የቅኝ ግዛት እጅ ይገፋሉ። ሞገስ አይናገርም፤ የሚናገርለት አለ። ልክ የቢሾፍቱ ልጆች ላይ በአንድ ከተማ ውስጥ ሁለት የከተማ ምሥል እንደምናገኘው ሁሉ “የስንብት ቀለማት” ላይም በአዲስ አበባ ውስጥ ሁለት የከተማ ምሥል እንመለከታለን። እንደ ዘድሬክ፣ ሳተርን፣ ከተስፋዬ ወደ አሸናፊ የተቀየሩ የድሎት ምሥሎች እና የእነምትክ ጉልት፣ የእትየ እልልታ የጉርሻ መሸጫ መስኮት ያሉ የእጦት ሥዕል እናገኛለን። መዝሙረ ሄላም ላይም እንዲህ ያለ በአንድ ከተማ ላይ የሁለት ምሥሎች አደባባይ እጀግ ብዙ ቦታ ይገኛል።
በሌላኛው የድኅረ-ቅኝ-ግዛት ኂስ (postcolonial criticism) መዝሙረ ሄላምን ስንመለከት መጀመሪያ ላይ “ፈረንጅ ሲያደንቀኝና ሲገረምብኝ የሰሙ የአገሬ ደነዞች በየተራ “ካላስ የኔ ጎሳ ናት” … እያሉ መሻማት ጀመሩ ትላለች - ሄላም። በኋላ ደግሞ በተነዛባት አጓጉል ወሬ … የሄላምን ጡት ንቀው፣ አንጓጥጠው፣ አባረዋት ሲያበቁ የፈረንጅ የዱቄት ወተትን ይመርጣሉ። ይህ በባሕላዊ ማንነትና በዘመናዊነት መካከል የሚዋልል ማኅበረሰብን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ የድኅረ-ቅኝ-ግዛት አካል ነው። በሌሎቹ የአዳም ሥራዎች ውስጥ ድኅረ-ቅኝ-ግዛት አተያይ በቋንቋና በኪነ-ጥበብ ምርጫ ውስጥ እንዴት እንደሚንፀባረቅ ያሳያል። በመዝሙረ ሄላም ላይ ደግሞ ምዕራባዊው ዓለም ለአገር በቀል መፍትኼ-ሥራይ የሚሰጠው ዋጋ ዝቅተኛ መኾኑንና የኢኮኖሚ ብዝበዛው አሁንም በረቂቅ መንገድ መቀጠሉን ያሳያል። እዚህ ላይ ሥዕለማርያም የተባለችዋን ገጸባሕርይ እና በውጭ ሀገራት የተነዙ ወሬዎችን ስንጨማምር ደግሞ የበለጠ ብዙ ለማለት ያስችላል።
መዝሙረ ሄላም ላይ እጅግ ብዙ ማኅበረሰባዊ ኂስ እናገኛለን። ለአብነት ያህል አንድ ሁለቱን እንቃኝ።
“መዝሙረ ሄላም” ላይ ማኅበረሰቡ በችላ-ባይነት አልያም በኾን ተብሎነት ልጆቹን ምን ያህል ተጠቂ እንዳደረጋቸው የሚያሳይ መልክ ተንጸባርቆበታል ማለት ይቻላል። ጋሽ ክብካብና ዘመናይ ኾን ብለው ቴዲና ሄላም ላይ የሚያደርሱትን፣ ተክለማርያም የወላጁን(የዘሪቱን) ችላ-ባይነት ለአብነት ማቅረብ ይቻላል። ማኅበረሰቡ ልጆችን “የነገ ተስፋዎች” ይላል፤ ነገር ግን ዛሬያቸው ላይ አይሠራም።
ማኅበረሰብ የመማጸኛ ከተማዎችን ወደ ተጨማሪ ግፍ መሥሪያ ቦታዎች እንደሚቀይር በአዳም መጻሕፍት ላይ በብዛት እንመለከታለን። “ይወስዳል መንገድ …” ላይ … “ቀዳዳ” በተሰኘው ታሪክ ላይ ማርታ ለደበበ በምትሰጠው ፍቅር ሳቢያ የሚሠራበትን ግፍ የምታስረሳ ብትኾንም ማኅበረሰቡ ግን ተጨማሪ ግፍ የሚሠራበት መሣሪያ ኾናለች። የስንብት ቀለማት ላይ ምኒልክ ከዚያ ሁሉ እስርና እንግልት በኋላ፣ “በፊያሜታ አርፋለሁ” ብሎ ቤቷ ሲሄድ ተጨማሪ ሕመም በጆሮው በኩል ጭንቅላቱ ላይ ይሻጥበታል። መዝሙረ ሄላም ላይም፣ ሄላም “ሙዚቃዬን ከሕዝብ ጆሮ ያደርስልኛል … ያሳርፈኛል …” ብላ የተመካችበት ምናሴ እንጦሮጦስ ይጨምራታል። ማኅበረሰባችን የመስቀል ተ ሠላጢን ግብር እንዳለው፣ ከላይ አሳልሞ ከታች በአንካሴው ጉድጓድ እንደሚምስ ያሳያል። ይህም የመልእክትን ወጭት ሰብሮ የወጣ ጥበባዊ አጻጻፍ ነው። በፈጣጣው የቀረበ የትችት ኮሶ አይደለም። ድንቅ ነው!
መዝሙረ ሄላም ላይ ከምናገኛቸው ዋና ዋና ገጸባሕርያት የተወሰኑት (አሮን፣ ቃል፣ ምናሴ፣ ሄላም) ላይ መጠነኛ ቅኝት እናድርግ።
auto-fiction ዓይነት አጻጻፍ ባለው የአሮን አተራረክ ውስጥ አሮን “system observer” መኾኑን እንገነዘባለን። ሥርዓቱን ያያል፣ ዘማቹን ያስተውላል፣ ቃለጉባኤ ይይዛል፣ ችግሩን ይመለከታል፣ ይጽፋል። አሮን የተገፋ ታሪክ ድምፅ ነው፤ ንቃት አለው፣ ግን የታሪክ ሂደትን የሚቀይር ኃይል የለውም፤ ስለዚህም ያ ሁሉ የጻፈውን ጽሑፍን ያጣል። የንቃት ችግር የለበትም፤ የማኅበራዊ ንቃት ድምፅነቱን ከዘመነ አባት ጋር ባደረገው ውይይት ውስጥ ተመልክተናል። ግን ደግሞ ይህ ብቻውን የቆመ ነጠላ ነገር ነው፤ ምክንያቱም ማኅበራዊ ተሳትፎ የለበትም። ቃል የተሰኘችው ገጸባሕርይም እንደ አሮን ናት፤ ንቃት ያላት፣ system observer ናት። ማኅበራዊ ንቃት ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ካላገዘው ግንጥል ጌጥ ነው። ቃልና አሮን ንቃት አላቸው፤ ግን ንቃታቸውን ተግባር አላገዘውም፤ ንቃቱን የሚተገብር አደረጃጀት የላቸውም። ስለዚህ ዕጣ-ፈንታቸው ውድቀት ይኾናል። በኢትዮጵያ ውስጥ የተንሰራፋውን ይህን የድግግሞሽ አዙሪት መዝሙረ ሄላም ላይ ደራሲ አዳም ረታ በሰላ ብዕር አስቀምጧል።
የደራሲና የአርታኢ ትስስር በተንጸባረቀበት በሄላም አተራረክ ውስጥ ምናሴ የተሰኘ ገጸባሕርይ እናገኛለን። ምናሴ የ-false collective consciousness ትእምርት ነው። ምናሴዎች ለሥልጣን ይሠራሉ፣ ራሳቸውን እንደ ነጻ ያስባሉ፤ ነገር ግን የሥርዓቱ የመጠቀሚያ መሣሪያ (system functionary) ናቸው። ምናሴዎች የኦልቪቴዎች ጥይት ናቸው። ምናሴዎች የሔላምዎች ስኬት ሳይኾን የገዛ ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙ የማኅበረሰቡ አካል ናቸው። ምናሴ በሌላ መነጽር ብናየው የመንግሥት ቢሮክራት የመካከለኛው መደብ ውክል ነው። ሀገሩ ከንጉሣዊ ሥርዓት ወደ ወታደራዊ ሥርዓት ቢቀየርም፤ ከወታደራዊ ሥርዓት ወደ ሌላ ሥርዓት ቢለወጥም ምናሴያውያን ግን አይቀየሩም። ሥርዓት ይቀየራል - ምናሴያውያን አይቀየሩም፣ ትእዛዝ ይፈጽማሉ፣ ይከድራሉ። ይህ በኢትዮጵያ ፖለቲካል-ታሪክ ውስጥ የተደጋገመ፣ ግን ደግሞ ያልተስተዋለ እውነት ነው።
ሄላም የወታደር ልጅ ናት፤ እንዲያሳድጋት በአደራ የተሰጠው ቤተሰብ የሚበድላት። የሷ ዓይነት ዕጣ ከደረሰው እንደ ወንድሟ ከምታየው ቴዲ ከሚባል ልጅ ጋር ታድጋለች። መጀመሪያ የሚልዮን፣ የኋላ ኋላ የምናሴ ፍቅረኛ የምትኾን ድምፀ-መረዋ ሴት ናት። ሁሉ ነገሯን ባጣችበት ወቅት ጡቷ ተአምር ያመርታል።
በመዝሙረ ሄላም ላይ የሄላም የጡት ወተት የአንዳች ነገር ውክል ይመስለኛል። ሻዕቢያ ለታጋይ ወጣቶች ማሳደጊያ ፈልጓት ሊሰርቃት መፈለጉ በቀላሉ የሚዘለል ነገር ነው? ወተት እና ጡት በመጀመሪያ እይታ የሕፃናት ትዝታ፣ የእናትነት ምሥል፣ የእምነት እና የጾታ መነሳሳት የተዋሃዱበትም አይደል? ወተት ሕይወት ነው? የመጀመሪያ ምግብ፣ ከእናት ወደ ልጅ የሚፈስም አይደል? በክርስቲያናዊ ምልክት ንጹሕነትን አይወክልም? ወተት ከ“ቅዱስ” ወደ “ሥጋዊ” የሚያስተላልፍ ድልድይ ነው ማለት እንችል ይኾን? የሄላምን ጡት የጠባ ታማሚ ልጅ እንዴት ጤናማ ሊኾን ቻለ? የምን ትእምርት ነው? ሄላም ከብዙ ወንድ ጋር የወጣች እንደመኾኗ ለዚህ ሰናይ ግብር ለምን የሷ ጡት ተመረጠ?
ሌላው፣ መዝሙረ ሄላም ላይ ኦልቬቲን እናገኛታለን። ኦልቬቲ የግራጫ ቃጭልዋ። መዝገቡ ንፋስ መውጫ ሳለ፣ ባልንጀራው ኤልያስ የብልግና ሀሁ ሊያስተምረው እፊቱ ያቆማት ቀይ ሰሌዳ ነበረች ኦልቬቲ። መዝሙረ ሄላም ላይ ምናሴን እና ቤተሰቡን የምታሾር ዐውራ ገጸባሕርይ ኾና ትከሰታለች። መዝሙረ ሄላም እና ግራጫ ቃጭሎች በጋለሞታይቱ በኦልቬቲ ብቻ ሳይኾን በዘመነ እንድርያስ እና በመዝገቡ ዱባለም ይገናኛሉ። ነጋ ዳቦ ጋጋሪውም በ-typological space መዝሙረ ሄላም ላይ እናገኘዋለን።
መዝሙረ ሄላምን ከህላዌነት (Existentialism) አንጻር እንመልከተው። ሄላም ትርጉም በማይሰጥ ዓለም ውስጥ እንዴት እንደምትኖር እናነባለን። የሀገሯ ዳር ድንበር እንዳይነካ አባት ብታዋጣም አሳዳጊዎቿ ግን የወላጅን ፍቅር አዋጥተው አይለግሷትም። ወርቅ አበድራ ጠጠር ትነፈጋለች። ዕቃ ለማገዝ ቤቷ ድረስ ለመጣው ሚልዮን ልቧን ትሰጣለች። ሀና የሸነቆረችውን ክፍተት ለሞላችበት ውለታዋ ክፍያ ይኾን ዘንድ ሚልዮን ለሄላም የወለፈንዴ ቡጢ ያሳርፍባታል። ለሕይወት ትርጉም ለመስጠት ባስ ውስጥ ካገኘችው ሄኖክ ጋር ብትሞክርም የበለጠ የሕይወት ትርጉም ይዛባባታል። የወታደር ልጅ መኾኗ ሄላምነቷን በዜሮ ያባዘዋል። የመጨረሻው ስንብትም ከሄኖክ ጓደኛ አፎት በሚወጣ ሰይፍ መቀላት ይኾናል። ከሄኖክ ጓደኛ ጀርባ የሚውለበለበው ባንዲራ ደግሞ የሄኖክ ሸሚዝ መኾኑ ደግሞ ቁስሉን እንደ አቡሰዲቅ ያደርገዋል። ለሕይወቷ ትልቅ ትርጉም ያለውን የሙዚቃ ሥራዋን፣ “ትርጉም ወዳለው
ነገር ይቀይርልኛል” ብላ በምትተማመንበት በምናሴ ትነጠቃለች። ተአምር በሚያስብለው በጡት ወተት ምክንያት ለሕይወቷ ትርጉም ለመስጠት ትታትራለች። የጡት ወተቷን ምርምር በማድረግ ለትልቅ ዓለምአቀፍ በጎ ተፅዕኖ ታደርጋለች ተብላ የተቆጠረችው ሥዕለማርያም የዓለም አቀፍ መሳለቂያና ትችት ምንጭ ትኾንባታለች። ይህ ሁሉ ትርጉም የሌለው ድግግሞሽ ነው። ይህ ደግሞ በሳርተር የተገለጸውን “existence without essence”-ን ያሳያል።
የህላዌነት መሠረታዊ ሐሳብ ነጻነት ነው፤ ግን ነጻነት ፍርሃትን ይወልዳል። ሄላም ለአሮን ፍቅሯን መናገር ትችላለች፤ ነገር ግን ዝምታን መርጣለች። የግራጫው መዝገቡ፣ የእንጀራ እናቱ የምታደርስበትን በደል እንደሚያውቀው ሁሉ ሄላምም ክብካብና ዘበናይ የሚያደርሱባትን አድሎ ታውቃለች፤ ግን ለረዥም ጊዜ ዝም ብላለች። ሄላም፣ ሙዚቃዋን ካጣች በኋላ ወደ ባንዱ ሄዳ መጋፈጥ ትችላለች፤ ነገር ግን አትሄድም … ይህ በሳርተርኛ bad faith ነው።
የሄላም ምርጫ ዝምታ ኾነ እንጂ ደካማ ናት ማለት አይደለም። “አልተናገርኩም ማለት አላውቀውም ማለት አይደለም” የሚል ዝምታ ነው ያላት። በሌላ ጎኑ ደግሞ ዝምታዋ፣ የለመደችውን ግፍ ከማታውቀው ዐዲስ ግፍ የመምረጥ ኹኔታ ነው። ዐዳዲስ ግፎችን ለመሸሽ በዝምታ አላዋቂነት ዛጎል ውስጥ የመደበቅ ብቃት ነው። የለመደችውን ግፍ የመከላከል አቅም ስላላት ባለመደችው ግፍ እንዳያጠፏት ሠግታ በውስጣዊ ንቃተ ሕሊና የዘየደችው ብልሃት ሊኾን ይችላል። ዝምታዋ የመቆየቷ ምሥጢር ነው። ደበበ ቀዝቃዛ ገለልተኛ ነኝ የሚለው ሰው ለመኖር ሲል ሳይታወቀው ስሜቱን የሚቆጣጠርበት መንገድን ለማስታወስ ነው።
“የስንብት ቀለማት” ገጸባሕርይ የኾነው ዮሴፍም ብዙ ነገር ያውቃል፤ ግን ዝም ይላል … ፊያሜታ ቂል መስሏት ትዘባርቃለች … እሱ ግን “አልተናገርኩም ማለት አላውቀውም ማለት አይደለም” የሚል የዝምታ መልስ ይመልስላታል። እሷ ግን ዝምታው አይገባትም። የ“ቀዳዳ”ው ደበበ እና “የስንብት …” ዮሴፍ ቀዳዳውን አይሞሉትም፤ እያዩት ይኖራሉ። ዶነሮች ጥሩ ፈንድ ሲለቁ ፊያሜታ ፕሮጀክቱን ለአሳምነው ትሰጠውና ዮሴፍን “ምን ዶነሮች እኮ ጠፉ ትለዋለች” … ዝም ይላል፤ ይታዘባል።
ቃል መሣሪያ ነበር፤ በዘመነ ደበበ፣ በዘመነ ዮሴፍ፣ በዘመነ ሄላም እና በዘመነ መዝገቡ ዱባለ ግን ቃል አደገኛ ኾኗል፤ ዝምታ ኹነኛ መጠጊያ ነው … ይህ ከደርግ በኋላ የተፈጠረ “traumatized literary silence” ማሳያ ነው። ስለኾነም ተራኪዎቹ (ደበበ፣ መዝገቡ፣ ዮሴፍ እና ሄላም) ለምን ዝም አሉ ሳይኾን "ዝምታን የሚያመነጭ ሥርዓት ምን ይኾን?" ብለን እንድንጠይቅ ያደርጋል። ግለሰብ ዝም ሲል፤ ሕዝብ በጸጥታ ይዋጣል፤ የዚያኔ የተማከለው ኃይል አፍ ያወጣል።
የአዳምን ዐዲሱን መጽሐፍ "በንባብ ይለቅ" ብለን መርቀናል።
ቢኒያም አቡራ
ሐምሌ 25 / 2018 ዓ.ም

1 day ago
ተንቀሳቃሽ ቤተ-መጽሐፍት፡ ስልክ ላይ የማቀርቀርን አዚም የሰበረው ባለታክሲ
********************
በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የሚንቀሳቀሱ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች አብዛኛውን ጊዜ በሙዚቃ ጩኸት፣ በትራፊክ ጫጫታና በጉዞ ድካም አዙሪት ውስጥ በመቆየት ይታወቃሉ።
ተሳፋሪውም ታክሲ ውስጥ እንደገባ አንገቱን ደፍቶ በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ መንሸራሸር የዘመናችን የተለመደ እውነታ ሆኗል። ወጣት ሰሎሞን አማረ ግን፣ የራሱን ሜትር ታክሲ ከዚህ አሰልቺ እና የተለመደ ምህዋር በማውጣት በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ወደ የሚሽከረከር "ተንቀሳቃሽ ቤተ-መጽሐፍት" ቀይሮታል።
በንግድና በጥድፊያ በሚታወቀው የመርካቶ ሰባተኛ ሰፈር ተወልዶ ያደገው ሰሎሞን፣ ከቅድስተ ማርያም ዩኒቨርሲቲ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል። ከዲጂታል ሚዲያው መስፋፋት ጋር ተያይዞ ህብረተሰቡ፣ በተለይም ወጣቱ፣ ከመጽሐፍት እየራቀ መምጣቱ በእጅጉ አሳስቦታል። በዚህም የተነሳ፣ ላለፉት ጥቂት ወራት ታክሲውን የዕውቀት ማዕከል በማድረግ ልዩ ልዩ የአማርኛና የእንግሊዝኛ መጻሕፍትን ለተሳፋሪዎቹ እንደ አዲስ አማራጭ ማቅረብ ጀምሯል።
ሁሉም ሰው ስልኩ ላይ ባቀረቀረበት በዚህ ዘመን፣ ሰሎሞን የታክሲው ውስጥ መደርደሪያዎች ላይ መጽሐፍትን በማስቀመጥ የሰዎችን ትኩረት ወደ ንባብ ለመመለስ የራሱን የትግል ስልት ነድፏል።
ሰለሞን ወደ ታክሲው ለሚገቡ መንገደኞች የሚያቀርበው ሞቅ ያለ ፈገግታና ሰላምታን ብቻ አይደለም፤ በስርዓት የተደረደሩ የዕውቀት ማህደሮችንም ጭምር እንጂ። የትራፊክ መጨናነቅን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም፣ ተሳፋሪዎች በጉዞ ወቅት መጽሐፍትን እንዲያነቡ ይጋብዛል።
የጀመሩት መጽሐፍ ልባቸውን ከሰረቀው ደግሞ፣ እዚያው ታክሲ ውስጥ ገዝተውት መንገዳቸውን ያለመሰልቸት በዕውቀት ታጅበው ያጠናቅቃሉ። ይህ አሰራር ከማህበራዊ ሚዲያ ጩኸት ለተወሰኑ ደቂቃዎችም ቢሆን አእምሮን የሚያሳርፉበት ልዩ የጉዞ ተሞክሮ ሆኗል።
የሰሎሞን አካሄድ የንባብ ባህልን ከማበረታታት ባለፈ፣ የገበያ ጥናትን (Marketing Management) ከተግባር ጋር ያዋሃደ አዲስ የስራ ፈጠራ ነው።
ጊዜን ወደ እሴት መቀየር፡ የታክሲ ተሳፋሪን የትራፊክ ውስጥ የባከነ ጊዜ ወደ ምርታማ የገበያ ሰዓት ቀይሮታል።
ድርብ ገቢ፡ ከትራንስፖርት አገልግሎቱ ባሻገር፣ መጽሐፍትን በመሸጥ የራሱን የገቢ ምንጭ አሳድጓል።
ማህበራዊ ካፒታል፡ "ተሳፋሪዎች የሚሰጡት አዎንታዊ ምላሽና አስደናቂ ስሜት ለስራዬ ትልቅ መነቃቃት ይፈጥርልኛል" የሚለው ሰሎሞን፣ በየቀኑ ከሚያገኛቸው አዳዲስ ሰዎች ጋር የሚያደርገው ገንቢ ውይይት ከገንዘብ በላይ የሆነ ትልቅ የህይወት ስንቅ እንደሆነለት ይናገራል።
የሰሎሞን አስገራሚው ጎን የዲጂታል ዓለሙን ሙሉ በሙሉ መሸሹ ሳይሆን፣ ቴክኖሎጂውን ለራሱ ዓላማ ማዋሉ ነው። "Sol Books" በሚል ስያሜ በቲክቶክና በሌሎች ማኅበራዊ ገጾች መጻሕፍትን በማስተዋወቅ፣ ዲጂታል ትውልዱን በዲጂታል መድረክ እየቀሰቀሰ ይገኛል።
የዚህ አብዮተኛ ወጣት መልዕክት አጭር እና ግልጽ ነው፦ የተለመደውን አሰራር በመስበር ሌሎች የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችም ይህን መሰል በጎ ተግባር ቢያራምዱ፣ ታክሲዎቻችንን ከትራፊክ ጫና ማምለጫነት አልፈው የዕውቀት፣ የሰላምና የፈጠራ ማዕከል ማድረግ ይቻላል።
በሊያ ተስፋዬ
Ethiopian Broadcasting Corporation FM Addis 97.1 /ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬዲዮ/ #መጽሀፍ #ንባብ

3 days ago
ብዕሩም እንደ አንደበቱ የሰላ ነው
#ethiopia | የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በተለየ የጽሁፍ ዘይቤአቸው እና ጥልቅ በሆነ ሃሳባቸው ይታወቃሉ።
ከጻፏቸው መጻሕፍት መካከል በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ አድናቆት ያገኙት እና ከፍተኛ ተነባቢ ከሚባሉት መካከል እነዚህ ተጠቃሽ ናቸው።
በፈረንጆቹ 2020 ላይ ተፅፎ ለንባብ የበቃው A promised Land ወይም የተስፋይቱ ምድር የተሰኘው መፅሐፋቸው እጅግ ተነባቢ ከሆኑት መካከል ይጠቀሳል።
ይህ መጽሐፍ የአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት ትዝታዎች የመጀመሪያ ክፍል ሲሆን የኦባማ በጣም ታዋቂው እና በስፋት የተነበበው ሥራ ነው።
መፅሐፉ ከለጋ የፖለቲካ ህይወቱ ጀምሮ በ2008 የነበረውን ታሪካዊ የምርጫ ድል እና የመጀመሪያውን የስልጣን ዘመን እስከ ኦሳማ ቢን ላደን መገደል ይተርካል።
በተጨማሪም ከዋና ዋና ታሪካዊ ውሳኔዎች ጀርባ የነበረውን ውስጣዊ ስሜት የፖለቲካ ውጥረቶች እና የስልጣን ፈተናዎችን ግልጽ በሆነ መንገድ ያቀርባል።
ሌላው ኦባማ ወደ ፖለቲካው ዓለም ከመግባታቸው በፊት የጻፉት እና የብዙዎችን ትኩረት የሳበ ግላዊ ታሪካቸው የሆነው መፅፍ ደግሞ "Dreams from my Father"ይሰኛል።
መፅሐፉ በዋናነት ማንነትን ፍለጋ ስለ ዘር ሐረጋቸው እና ስለ አባታቸው ታሪክ ለመረዳት ያደረጉትን ጉዞ ያብራራል።
ስሜት ቀስቃሽ እና ፍልስፍናዊ በሆነ የጽሁፍ ውበት የተዋቀረ በመሆኑ በብዙዎች ዘንድ ከምርጥ ግላዊ ታሪክ መጻሕፍት መካከል ተመራጭ አድርጎታል።
ሶስተኛው የኦባማ ተመራጭ መፅሐፍ
The Audacity of Hope ይሰኛል።
ይህ መጽሐፋቸው የአሜሪካ ፖለቲካዊ ክፍፍል እንዴት ማስተካከል እንደሚቻል የፖለቲካ እሴቶች እና ለወደፊት አሜሪካ ያለውን ተስፋና ራዕይ ያቀርባል።
የኦባማን የፖለቲካ ፍልስፍና እና የኋለኛውን የፕሬዝዳንትነት ዘመናቸው መሪ ሃሳብ በጥሩ ሁኔታ የሚያሳይ መፅሐፍ ነው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #barackobama #apromisedland #theaudacityofhope #dreamsfrommyfather

5 days ago
ነገ ሁለቱ ተጓዦች ይመጣሉ!”
ለጥበብ እና ለጉዞ ወዳጆች -ታላቅ የምስራች!
በዓመታዊው የንባብ ለሕይወት የመጻሕፍት አውደርዕይ ላይ፣ መድረኩን ለየት ባለ ጥበባዊ ድምቀት ሊያነዝሩት የተዘጋጁ ሁለት ታላላቅ ስሞች በአንድ መድረክ ይከሰታሉ!
የሀገራችንን ውበት በቃላትና በምስል እየቀመረ የጉዞን ጥበብ ያስተማረን ሄኖክ ስዩም...ከአንደበተ ርቱዑ እና ተወዳጁ የይዘት አዘጋጅ አቤል ብርሃኑ (የወይኗ ልጅ) ጋር በመሆን “ንባብና ቱሪዝም”ን በጥበብ መነጽር ያሳዩናል።እነዚህ ሁለቱ ተጓዦች ነገ ምን ይዘውልን ይከሰቱ ይሆን?በንባብ ዓለም ውስጥ የሚደረግ ረጅም ጉዞ፣የኢትዮጵያን ውበት በጥበብ የመቃኘት ጥልቅ እይታ፣የአእምሮ ስንቅ እና የማይረሱ ውብ ትዝታዎች!ነገ ቅዳሜ ሐምሌ 25/2018፣ የዕውቀት እና የጥበብ ማዕድ ተካፋይ ለመሆን ቀጠሮዎን ከእኛ ጋር ያድርጉ። ይህ ድንቅ አጋጣሚ እንዳያመልጥዎ!
ቦታው ኤግዚቢሽን ማዕከል
ቅዳሜ ሐምሌ 25/2018

🎤ድምፃዊ ፀሐዬ በፀሐይ ተሸለመ!
📚ንባብ ለሕይወት በድምቀት ተከፍቷል
ሐሙስ ሐምሌ 23/2018 በኤግዚቢሽን ማዕከል ጥቁር እንግዳ መድረኩን ተቆጣጠረው።
ተወዳጅ ድምፃዊ ፀሐዬ ዮሐንስ በንባብ ለሕይወት የመጻሕፍት አውደርዕይ ላይ ተገኝቶ ዘመን ተሻጋሪ ሙዚቃውን "ማንበብና መጻፍ"ን በልዩ ብቃት በመጫወት ታዳሚዎችን በደስታ ብዛት ከመቀመጫቸው አስነስቷል። ልጆችም አብረውት አዚመዋል።
በኢትዮጵያ ሴት ደራሲያን ታሪክ በረዥም ልቦለድ ዘርፍ ፋና ወጊ የሆነችው "ፀሐይ መላኩ" ለአርቲስቱ የምስጋና ሰርተፊኬት በክብር አብርክታለች።
ንባብ ለሕይወት እስከ ሐምሌ 26/2018 በኤግዚቢሽን ማዕከል ይቀጥላል።

Sponsored by
Surafel
5 days ago
🎤ድምፃዊ ፀሐዬ በፀሐይ ተሸለመ!
📚ንባብ ለሕይወት በድምቀት ተከፍቷል
ሐሙስ ሐምሌ 23/2018 በኤግዚቢሽን ማዕከል ጥቁር እንግዳ መድረኩን ተቆጣጠረው።
ተወዳጅ ድምፃዊ ፀሐዬ ዮሐንስ በንባብ ለሕይወት የመጻሕፍት አውደርዕይ ላይ ተገኝቶ ዘመን ተሻጋሪ ሙዚቃውን "ማንበብና መጻፍ"ን በልዩ ብቃት በመጫወት ታዳሚዎችን በደስታ ብዛት ከመቀመጫቸው አስነስቷል።
ልጆችም አብረውት አዚመዋል።

8 days ago
አንጋፋው ደራሲ አዲስ መጽሐፍ ይዞ መጣ
#ethiopia | የተወዳጁ ደራሲ ፍቅረማርቆስ ደስታ አዲስ መጽሐፍ «የአምባው ላይ ልዑላን ዩንቨርሲቲ» ለንባብ መብቃቱ ተገለጸ።
በአሁኑ ወቅት አዲሱ መጽሐፍ በሁሉም የመጽሐፍ መደብሮች ውስጥ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡
አንጋፋው ደራሲ ይህንን አዲስ ሥራውን ለአንባቢያን ሲያደርስ፣ በኪነ-ጥበብ ጉዞው በርካታ አጓጊ እና ተወዳጅ መጻሕፍትን ለአገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ገበያ አበርክቷል።
ደራሲ ፍቅረማርቆስ ደስታ ከዚህ ቀደም በሐመር ሕዝብ ባህልና አኗኗር ላይ ያተኮሩትን እንደ «ከቡስካ በስተጀርባ» (የበኩር ድርሰቱ)፣ «ኢቫንጋዲ» እና «የዘርሲዎች ፍቅር» የመሳሰሉ እጅግ ተወዳጅ ኤትኖግራፊክ ልብወለዶችን ለአንባቢያን አድርሷል።
ከዚህም በተጨማሪ «አቻሜ»፣ «የንሥር ዐይን»፣ እንዲሁም የጀግናውን የአርበኛ ጃገማ ኬሎን ታሪክ የሚያወሳው «ጃገማ ኬሎ – የበጋው መብረቅ» እና «የሚሳም ተራራ» የተሰኙ ድንቅ መጻሕፍቱ ይታወሳሉ።
አሁን ደግሞ ይህንን አዲስ «የአምባው ላይ ልዑላን ዩንቨርሲቲ» የተሰኘ መጽሐፉን በመጨመር የንባብ ማዕዶቱን አስፍቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#newbook #amharicbook #fikremarkosdesta

እኔ ምሕረት ደግፍ በቅርቡ ለንባብ ያበቃሁት "የውቦች ንግሥት" የተሰኘ መጽሐፌን ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም፤ እናንተ ወዳጆቼ ፣ አጋር የኪነጥበብ ሰዎች እና የጥበብ አፍቃሪያን በተገኙበት የማስመርቅ ይሆናል።
በዕለቱ እርሶ የክብር እንግዳዬ በመሆን ደስታዬን ይካፈሉ ዘንድ ከታላቅ አክብሮት ጋር ጋብዤዎታለሁ።
ቀን:- ሐምሌ 25 ቅዳሜ ከቀኑ 11:00 ሰዓት
ቦታ:- የኢትዮጵያ ቤተመጻሕፍት እና ቤተመዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር)

11 days ago
የባሕር በር…የታሪክ እና የተፈጥሮ ጥሪ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት የብሔራዊ ጥቅም ጥያቄ ብቻ ሳይሆን በታሪክ የግዛቷ አካል የነበረውን እና በሴራ ያጣቸውን የባሕር በር መልሶ የማግኘት የታሪክ እና የተፈጥሮ ጥሪ ነው፡፡
ታሪክ እንደሚያስረዳው በአክሱም ሥልጣኔ ዘመን የአዱሊስ ወደብ የዓለም አቀፍ ንግድ ማዕከል የነበረ ሲሆን ፥ በቀጣዮቹ ዘመናትም ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነቷ በምጽዋና አሰብ ወደቦች መዝለቅ ችሎ ነበር።
በቀጣናው የባሕር በር ባለቤት የነበረችው ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር አካባቢ እጅግ ጥንታዊ የታሪክና የስልጣኔ አሻራ አኑራለች፡፡ ሆኖም በታሪክ አጋጣሚ በተወሰነ የፖለቲካ ውሳኔና የጠላቶች ሴራ ምክንያት ከታሪካዊና ሕጋዊ በሯ ከተነጠለች ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የባሕር በር ያጣችበት መንገድ በጣም የሚያስቆጭ ፤ ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን ለፍትሕ የቆመ ማንኛውም ሰው ይህንን ሀሳብ የሚጋራው ነው፡፡
ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ወደብ አልባ ከሆነችበት ጊዜ አንስቶ ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረው ይህ እውነታ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት እና በትውልዱ ስነ-ልቦና ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ይገኛል።
ከዚህ በፊት የነበረው መንግሥት ይህን ጫና ለመከላከል እና የባሕር በር ለማግኘት ያደረገው ሙከራ ካለመኖሩ በተጨማሪ ትውልዱ ኢትዮጵያ ያጣቸችውን የባሕር በር በተመለከተ ግንዛቤ እንዳይኖረው አድርጎ አልፏል፡፡
በተለይ ከ1980ዎቹ ጀምሮ የመጣው ትውልድ በልዩ ሁኔታ በራስ ጥረትና ንባብ ከተረዳው ውጪ አብዛኛው ወደብ የባሕር በር፣የባሕር ሃይል እንዲሁም ባሕር ላይ ስላለ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ግንዛቤ የለውም፤ እንዲያውቅም አልተደረገም፡፡
በዚህም ትውልዱ የወደብ አልባነት ትርክት ሰለባ ሆኖ ቆይቷል፡፡
ይሁን አንጂ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የባህር ጉዳይን ፊት ለፊት እንነጋገርበት ብለው በአደባባይ ይፋ ካደረጉ በኋላ ኢትዮጵያ የባሕር በር አልባ በመሆኗ የሚቆረቆር ትውልድ እንዲፈጠር አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ጥያቄ የራሴ ሉዓላዊ የባሕር በር ይኑረኝ ፤ ወደብና የመተላለፊያ ኮሪደር በሰላማዊ መንገድና በስምምነት ለማግኘት በሚደረግ ጥረት እንጂ የአንድን ሉዓላዊ ሀገር ግዛት ባለቤትነት የመጠየቅ ጉዳይ አይደለም።
በሰጥቶ መቀበል፣ መሬት ወይም ሌላ ሀብት በመለዋወጥ የባሕር በር ያገኙ ሀገራት እንዳሉ ሁሉ በቅን ልቦና እና በትብብር መንፈስ ለሚረዳ ማንኛውም ወገን የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ምንም ዓይነት የፖለቲካ ሸፍጥ እንደሌለበት መገንዘብ ቀላል ነው፡፡
የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የታሪክ ብቻ ሳይሆን የነባራዊ እውነታ፣የህጋዊ ባለቤትነት እና የሕልውና ጉዳይ ሲሆን÷ ከ130 ሚሊየን በላይ ሕዝብ ላላት ኢትዮጵያ፣ የባሕር በር ተደራሽነት የቀን ፖለቲካ ክርክር ሳይሆን የረጅም ጊዜ የልማት ስትራቴጂ እቅድ አካል ሊሆን ይገባዋል።
በመሆኑም ጥያቄው መልስ እንዲያገኝ ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ አማራጮችን በመከተልና ልዩነትን ወደ ጎን በመተው ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ፤ ኢትዮጵያውያንን እንደ ሕዝብ አንድ የሚያደርግ አጀንዳ አድርጎ አጠናክሮ መቀጠል ይገባል፡፡
በትዕግስት ግዛቸው

ጽናት
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ታሪካዊ የለውጥ ጉዞ
1947-2017
#ethiopia | የዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን Asrat Atsedeweyn መጽሐፍ በጎንደር ከተማ እየተመረቀ ነው።
ይህ መጽሐፍ መታሰቢያነቱ ስጎንደር ዩኒቨርሲቲ ርስታቸወነ ስሰጡ 59 የጎንደር አርሶ አደሮች፧ እንዲሁም በተለያዩ ዘመናት በአመራርነት፤ በባለሙያነት፤ በሠራተኛነትና በአጋርነት አገልግለው ተቋሙን አሁን ላስበት ታላቅ ደረጃ ኣደረሱ ሞስንነ ባለውለታዎች በሙሉ ይሁን፡፡
***
ከመጽሐፉ ጀርባ (blurb)
ጎንደር የኒቨርሲቲ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ዩኒቨርሲቲዎች በአንጋፋነት ተርታ የሚመደብ ነው:: በቅርቡም ሰባኛ ዓመቱንና የዩኒቨርሲቲው አስኳል የሆነውን ሆስፒታሉን መቶኛ ዓመት በደማቅ ሁኔታ መዘከሩ ይታወሳል። በዚህ የታሪክ አጋጣሚ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት የሆነው ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን እነሆ የዩኒቨርሲቲውን ታሪካዊ ጉዞ እርሱ ራሱ በተለያዩ የኃላፊነት እርከኖች ካከናወናቸው ተግባራት ጋር አዛምዶ የሚዘግብ፣ በጠንካራ መረጃ ላይ የተዋቀረ መጽሐፍ አቅርቦልናል።
በዚህም የዩኒቨርሲቲ ቆይታቸውን ከግለ ታሪካቸው ጋር አሰናስለው ለንባብ ያበቁትን የቀደምት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንቶችን ፈለግ ተከትሏል ማለት ይቻላል። የተቋሙ ታሪካዊ ጉዞ በስኬት የታጀበውን ያህል አያሌ ፈተዎችና ተግዳሮቶችም የተጋረጡበት ነበር። የመጽሐፉ ትልቁ ፋይዳም እነዚህን ስኬቶችና ተግዳሮቶች ነቅሶ በማውጣት ሰፊ ግንዛቤ መስጠቱ ላይ ነው:: በተለይም በደራሲው አመራር የተከናወኑትን P70/100 ዝክረ በዓል ዘርፈ ብዙ ዝግጅቶችና ክንዋኔዎች በዝርዝር ያትታል፤ ዘላቂ እርባናቸውንም ይጠቁማል። በመጨረሻም ከዩኒቨርሲቲ አመራር ተሞክሮው የቀሰማቸውን ትምህርቶች በተመሳሳይ ተቋም ግንባታ ላይ ላሉ ያካፍላል።
ባሕሩ ዘውዴ፣ የታሪክ ኤሜሪተስ ፕሮፌሰር አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
***
የስኬታማ ተቋማትና የአገር ግንባታ በትውልዶች ቅብብሎሽ፣ በቁርጠኝነትና በመሪዎች እቅድ ላይይመረኮዛል። ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን በዚህ መጽሐፋቸው የጎንደር ዩኒቨርሲቲን የ7ዐ ዓመታት ጉዞ፣ በየዘመናቱ የነበሩ መሪዎችንና ባለድርሻ አካላትን አበርክቶ፣ እንዲሁም የራሳቸውን የኃላፊነት ዘመን ፈተናና ስኬት በጥልቀት አቅርበዋል። በከፍተኛ ትምህርት አመራርነት በነበረኝ የረጅም ጊዜ ኃላፊነት ተቋሙንም ሆነ ደራሲውን በቅርብ እንደማወቄ መጠን፤ ይህ መጽሐፍ ከተጨባጩ ዓለም የተገኘ ጥልቅ እውቀት የሚሰጥ፣ ለመሰል ተቋማት መሪዎችና ተመራማሪዎች ታላቅ ማስተማሪያና ማጣቀሻ እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለኝ።
ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዚደንት
***
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በፈተናዎች ውስጥ ያለፈ ታላቅ ዓለም አቀፍ ተቋም ቢሆንም፣ የነበረው የታሪክ ምዝገባ ግን በቂ አልነበረም:: የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን “ጽናት” በተሰኘው መጽሐፋቸው ይህንን የታሪክ ክፍተት ለመሙላት ሞክረዋል። መጽሐፉ፣ ተቋሙ በፈተናዎች ውስጥ አልፎ ለዛሬው ስኬት እንዲበቃ አሻራቸውን ያሳረፉ የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮችን እውቅና ይሰጣል። በተጨማሪም፣ ዶ/ር አሥራት ላለፉት ስምንት ዓመታት በኘሬዚዳንትነት ሲያገለግሉ ያጋጠሟቸውን ከባድ ፈተናዎች እንዴት በብቃት እንደተወጧቸውና የዩኒቨርሲቲውን ስኬት እንዴት ማስቀጠል እንደቻሉ ያሳያል። ይህም ለተቋሙ ቀጣይ ጤናማ የአመራር ሽግግርና ለተተኪ አመራሮች ትልቅ ስንቅ የሚሆን ነው።
ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ፣ በኦሃዮ ስቴት ግሎባል ዋን ሄልዝ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር እና የቀድሞ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት
እንኳን ደስ አለህ!

12 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የካናዳ ፍርድ ቤት በ4 ኤርትራዊያን ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ አሳለፈ፡፡ በካናዳ ካልጋሪ ከተማ የሚገኘው ፍርድ ቤት ዳኛ 4 ኤርትራዊያን በቀረበባቸው የረብሻ፣ ጦር መሳሪያ መያዝና ድብደባ ክስ ጥፋተኞች ሆነው መገኘታቸውን ገለፁ፡፡ ዳኛው ‹‹ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማችን ውስጥ ከተከሰቱት ረብሻዎች በሙሉ ትልቁ›› በሚል የገለፁት ይህ ድርጊት የተፈፀመው እ.ኤ.አ በ2023 ሴፕቴምበር ወር ነበር፡፡ በወቅቱ በፖለቲካ ልዩነት ያላቸው ሁለት የኤርትራዊያን ቡድኖች በፋልኮን ፕላዛ እርስ በእርሳቸው ፀብ ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል፡፡
ይህ ድርጊት ከተፈፀመ ሶስት አመት የሆነው ቢሆንም ዳኛው ግን የተፈጠረው ሁከት እንደሆነና 4ቱ ተከሳሾች ጥፋተኛ መሆናቸውን ማረጋገጥ ከባድ አለመሆኑን በውሳኔያቸው ገልፀዋል፡፡ ዳኛው ሎይድ ሮበርሰን በንባብ ባሰሙት 2 ሰአታትን በፈጀ ውሳኔያቸው የጥፋተኝነት ውሳኔ ያሳለፉባቸው አማኑኤል ክፍለግዚ፣ ያሚን እቁበዮሀንስ፣ ገብኪዳን ሀይለማሪያምና ሙሴ እስጢፋኖስ ናቸው፡፡
ለፍርድ ቤት በቀረበው ሰነድ መሰረት በወቅቱ የነበረው ፀብ 10 ደቂቃ የፈጀ ቢሆንም 97 እንጨትና ቱቦዎች፣ 118 ድንጋዮችና 18 ጠርሙሶች በሁለቱ ቡድኖች እርስ በእርስ ተወርውረዋል፡፡ ፖሊስ ፀቡን ለማብረድ ወደ200 ያህል የፖሊስ አባላትን ከማሰማራቱም በላይ በርካታ የጭስ ጋዝና ከ2000 በላይ የሚያቃጥሉ ድቡልቡል ጥይቶችን እንደተጠቀመም ለፍርድ ቤት የቀረበው ሰነድ ያሳያል፡፡

በሽብር ወንጀል የተከሰሱት እነ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና 52 ተከሳሾች የተከሰሱበትን ክስ ይከላከሉ ወይስ በነጻ ይሰናበቱ የሚለው ጉዳይ ላይ ብይን ሳይሰጥበት በድጋሚ ተራዘመ።
በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ የቀድሞ የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ዮሐንስ ቧያለው እንዲሁም ዶ/ር ካሳ ተሻገር፣ ዶ/ር ጫኔ ከበደን ጨምሮ በድምሩ 52 ተከሳሾች የፍርድ ውሳኔ ሳያገኙ ላለፉት ሦስት ዓመታት ገደማ በእስር ላይ ይገኛሉ።
ክሱ የተመሠረተው መጋቢት 2016 ዓ.ም ሲሆን፣ ጉዳዩ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሕገ መንግሥትና ፀረ-ሽብር ወንጀሎች ችሎት እየታየ ይገኛል።
ተከሳሾቹ በተለያዩ ወቅቶች ካለባቸው የጤና ችግር ጋር በተያያዘ፣ ከቤተሰብ ጥየቃ፣ ከሰብአዊ መብት ሁኔታ፣ እና ሌሎችም ደረሰብን በማለት በሚያቀርቧቸው ቅሬታዎች ዙሪያ ችሎቱ የተለያዩ ቀጠሮዎችን በመስጠት ጉዳያቸውን ሲመለከት የቆየ በመሆኑ የተከሰሱበትን ዋናው የክስ መዝገብን የማየት ሂደት በተለዋጭ ቀጠሮዎች ከ 4 ጊዜ በላይ ሲራዘም ቆይቷል።
በዋናው የሽብር ክስ መዝገብ ላይ ብይን ለመስጠት ቀደም ሲል ለሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም፣ ችሎቱ ጉዳዩን በተጨማሪ ዝግጅት አጠቃሎ ለማቅረብ ለዛሬ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ለተለዋጭ ቀጠሮ አስተላልፎት ነበር።
ችሎቱ ዛሬ የሚሰጠው ብይን ተከሳሾቹ የተከሰሱበትን ክስ ይከላከሉ ወይስ የነጻ ይሰናበቱ የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ እንደሚሆን ቢጠበቅም በድጋሚ በተለዋጭ ቀጠሮ ለ ጥቅምት 6/2019 ዓም በመስጠት ውሳኔውን አራዝሞታል።
ፍርድ ቤቱ ብይኑን ማጠናቀቁን ገልጾ ነበር፤ ይሁን እንጂ የተወሰኑ ተከሳሾች በችሎት ባለመገኘታቸው ብይኑን ለንባብ ማቅረብ እንደማይችል በመግለጽ ንባቡን አላደረገም።
በዛሬው ችሎት ፍርድ ቤቱ ያሰማዋል ተብሎ ሲጠበቅ ከነበረው ብይን በተጨማሪ ከተከሳሾቹ አንዱ ከሆኑት ከዶ/ር ካሳ ተሻገር እና ከጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ስልክ ቁጥር ጋር በተያያዘ ቁጥራቸውን ሌላ ሰው እየተጠቀመበት መሆኑን በመግለጽ ከእዚህ ቀደም በችሎቱ ያቀረቡትን ቅሬታ በተመለከተ ኢትዮ ቴሌኮም ለችሎቱ ይሰጠዋል ተብሎ የሚጠበቀውን ምላሽ የመስማት ጉዳይ ነበር።
ከዶ/ር ካሳ ተሻገር እና ከጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ስልክ ቁጥሮች ጋር በተያያዘ ኢትዮ ቴሌኮም የላከውን ምላሽ ችሎቱ በንባብ አሰምቶታል።
በምላሹ መሠረት፣ የሁለቱ ተከሳሾች ስልክ ቁጥሮች ለረዥም ጊዜ ከአገልግሎት ውጭ በመቆየታቸው በኩባንያው አሠራር መሠረት ጊዜው አልፎበት (expire አድርጎ) ለሌሎች አዳዲስ ተጠቃሚዎች መዘዋወራቸውን ኢትዮ ቴሌኮም አረጋግጧል።
በዋናው ጉዳይ ላይ የሚጠበቀው ብይን ተከሳሾቹ አቃቤ ሕግ ባቀረበባቸው ማስረጃ ላይ ተመስርተው ክሱን ሊከላከሉ ይገባል ወይስ አቃቤ ሕግ ክሱን በበቂ ማስረጃ ስላላስረዳ በነጻ ሊሰናበቱ ይገባል የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ ነው።
የተከሳሾች ጠበቃ የሆኑት አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል "ተከሳሾቹ ከእዚህ ቀደም በችሎት ውሎዎች ላይ አቃቤ ሕግ ካቀረባቸው የድምጽ፣ የጽሑፍ እና የፎረንሲክ ማስረጃዎች ጋር በተያያዘ አስተያየታቸውን ማቅረባቸውን"ገልጸዋል።
ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን ይህን አስተያየት እና አቃቤ ሕግ ያቀረበውን ማስረጃ መርምሮ፣ ማስረጃው ክሱን በበቂ ሁኔታ የሚያስረዳ ሆኖ ካገኘው ተከሳሾቹ እንዲከላከሉ፣ ካላገኘውም ተከሳሾቹ ያለ ተጨማሪ ክርክር በነጻ እንዲሰናበቱ ብይን የሚሰጥበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቅ ነበር ብለውናል።
ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን ሙሉ ተገኝነት መሠረት በማድረግ ብይኑን ወደ ጥቅምት 6 ቀን 2019 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ችሎቱን ዘግቷል።
የበጀት ዓመቱ መጠናቀቁን ተከትሎ የዳኝነት አገልግሎት ክብደትና ውስብስብነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የፌዴራል የመጀመሪያ፣ ከፍተኛና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች በየአመቱ ከነሐሴ 1 እስከ መስከረም 30 ለ2 ወራት በከፊል ዝግ ሆነው የሚቆዩ መሆኑ ይታወቃል።
tikvahethiopia

19 days ago
የመጽሐፍት አውደ ርዕይና ሽያጭ በታሪካዊው ራስ ሆቴል ግቢ ውስጥ ተጀመረ
በዋና ከተማችን የአንባቢነትንና የንባብ ባህልን አዲስ ትንፋሽ ለመዝራት ያለመ፣ እጅግ ማራኪ የመጽሐፍት ኤግዚቢሽንና ሽያጭ በዛሬው ዕለት በራስ ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ በድምቀት ተጀምሯል።
የዝግጅቱ አስተባባሪዎች እንደገለጹት፣ በአውደ ርዕዩ ላይ ከገበያ የጠፉና ለማግኘት አስቸጋሪ የሆኑ ብርቅዬ የጥበብ ስራዎችን ጨምሮ፣ በሺዎች የሚቆጠሩና ልዩ ልዩ የርዕስ ጉዳዮችን የዳሰሱ መጽሐፍት ለአንባብያን ያቀርበዋል ብለዋል። ይህ ለየት ያለ መድረክ የሶስት ቀናት ቆይታ የሚኖረው ሲሆን ከዛሬ አርብ ጀምሮ እሁድ እንደሚጠናቀቅ አዘጋጆቹ ገልፀዋል።
አዘጋጆቹ እንዳሉት"የዕውቀት ጥማትዎን የሚያረኩ የትም ተፈልገው ያወጧቸውን መፃህፍት እኛ ጋር ያገኛሉ ''ብለዋል። በተጨማሪም አንባቢዎች የሚፈልጓቸውን መጽሐፍት በቀላሉ እንዲያገኙና ወቅታዊ መረጃዎችን እንዲከታተሉ፣ በቴሌግራም፣ በቲክቶክ እና በሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች አማካኝነት የማስተዋወቅ ስራው በስፋት እየተሰራ ይገኛል።
ዛሬ በኤግዚቢሽኑ ላይ ያልተካተቱ በርካታ አዳዲስ መጽሐፍት ነገ በልዩ ሁኔታ ተጨምረው ለሽያጭና ለንባብ እንደሚቀርቡ አስተባባሪዎቹ በምስራችነት ገልጸዋል።
ይህ የዕውቀትና የጥበብ ድግስ እንዳያመልጥዎ! መጽሐፍ ወዳውያን በሙሉ በአካል በመገኘት የልባቸውን መጽሐፍ እንዲመርጡና ከዚህ ታላቅ የዕውቀት ማዕድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አዘጋጆቹ የከበረ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

የአርታኢው ማስታወሻ
#ethiopia | የአርማጌዶን በር የትውልድ ማንቂያ ደውል ነው፤ በግለስብደረጃም ሆነ እንደ ሀገር ከተጠመድንበት የአዙሪት ልክፍት የሚያድን የሀሳብ ፀበል። የዘወትር ትንቅንቃችን ከውጤቱ
ጋር መሆኑ ከመፍትሔ ይልቅ ድካም ብቻ ያተረፈልን ከንቱ
ሩጫ እንደሆነ ገብቶታል፤ ደራሲው።
ይዞንም ወደ ምንጩ ይዘልቃል። የሩቅ ዓለማቱን ልሣን ሳይቀር አንብቦና ተርጉሞ ከሚስጢራቱ ባህር ያጠልቀናል። የተፃፈልንን
እያነበነብን፣ በተነገረን እየፎከርን፤ ያረጀ ያፈጀውን እየመዘዝን ስንራኮት የድራማው ፀሀፊዎች ከዳር ቆመው ሲስቁብን የታዘበውን ሊያሳየን የሞከረበት መንገድም እጅጉን ይደንቃል።
የጦርነት ሜዳውም ሆነ ስልቱ የሚለዋወጥበት ፍጥነት
ለግምት ይከብዳል። በጦርና ጋሻ የጠበቅነው ጠላት
እንዳሞራ በአየር መርዝ ታጥቆ ይመጣል።
ጦርና ጋሻውን ጥለን አዲሱን መሳሪያ ታጥቀን ስንጠብቀው አዲስ መንገድ አበጅቶ በስልካችን በኩል ይመጣና በስውር ጥበቡ ልባችንን ሰውሮ ኃይላችንን በመስለብ ሳንገጥመው በሽንፈት እጅ
ያሰጠናል። ማርኮም በባርነት ይገዛናል።
ሁሌም እንግዶች ነን። አንዱን የቤት ሥራ ሳንጨርስ ሌላ
አዲስ የቤት ሥራ ይጠብቀናል። እረፍት አልባ በሆነ
አዙሪት ውስጥ ተጠምደን ስንኳትን አዲስ የነበረው አርጅቶ
ደሞ ሌላ አዲስ ወይም እራሱ መልኩን አድሶ ይወለዳል።
እኛ ያንኳኳነው የስልጣኔ በር፣ እነሱ የሚከፍቱልን የስይጣኔ
በር፤ ታዲያ ከዚህ በላይ አዙሪት ከወዴት ይገኛል። 10
በጥቅሉ በዚህ መጽሐፍ የአርማጌዶን በር ሲነቀነቅ
የሚያስተጋባውን ስውር ድምፅ በቃላት ተስሎ ታደምጡታላችሁ። ድምፁ ግን ለፍርኃት አሳልፎ የሚሰጥ የጥፋት አዋጅ ሳይሆን የማንቂያ ደውል ነውና ተሸብራችሁ አትበረግጉም። ግን ትደነግጣላችሁ። በመጨረሻም ድንጋጤአችሁ ሰልፋችሁን እንድትለዩ የሚያነቃ የትንሳኤ ዋዜማ ሆኖ ነፃ ያወጣችኋል።
የአርማጌዶን በር፤ በእያንዳንዳችን እጅ ላይ ነው።
መልካም ንባብ!
ተስፋዬ አየለ (ዶ/ር)

21 days ago
የ"ሸገሩ"፣ "የእነሆ መቆያው" እሸቴ አሰፋ!
#ethiopia | ባለፈው ሳምንት "እነሆ መቆያ" የተሰኘ መጽሐፉን ለንባብ ያበቃው፣ አንጋፋውና ስመ-ጥሩ ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ (እሸቴ ከጃንሜዳ) ሐምሌ 19 ቀን 1953 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ መንዝና ግሼ አውራጃ ተወለደ።
የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በተወለደበት አካባቢ ራቤል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ያጠናቀቀ ሲሆን፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በመሐል ሜዳ፣ በሆለታና በአቃቂ ተማሪ ቤቶች ተከታትሏል።
ገና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለ በሚኒ-ሚዲያ በመሳተፍ የጋዜጠኝነት ፍቅሩን ያሳየው እሸቴ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቋንቋና ሥነ-ጽሑፍ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል።
ለመጀመሪያ ጊዜ ጽሑፉ የታተመለት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ "አድማስ" አምድ ላይ ነበር ይላል - ለዚህ ጽሑፍ ዋነኛ ምንጭ አድርገን የተጠቀምነው የ"ተወዳጅ ሚዲያ" መረጃ።
በተለይም "የካቲት" መጽሔት ላይ እንደ ጳውሎስ ኞኞ፣ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር፣ ብርሃኑ ዘርይሁን፣ ወጋየሁ ንጋቱ፣ ይድነቃቸው ተሰማና ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ያሉ ታላላቅ ሰዎችን ታሪክ በጥናት አስደግፎ በማቅረብ የአንባቢን ልብ መግዛት ችሏል።
በተለያዩ ዘርፎች ብዙ ውለታ የዋሉ ታላላቅ የሀገራችንን ሰብዕናዎችንም 'ቃለ-መጠይቅ' (Interview) አድርጓል።
በዚህ የጋዜጠኝነት ጉዞው ውስጥ የአጻጻፍና የጋዜጠኝነት ሙያዊ ዕውቀት የሰጡትንና እንደ መምህር የሚያያቸውን የመጽሔቷን ዋና አዘጋጅ አቶ ጸጋዬ ኃይሉ ተፈራን ምንጊዜም በታላቅ አክብሮት ያስታውሳል።
በአንድ ጊዜ በበርካታ ሚዲያዎች ላይ የመሥራት ልዩ ታታሪነት የነበረው እሸቴ፣ ከ1978 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ዓመታት ያህል በለገዳዲ ሬዲዮ "የእሁድ ለአንዳፍታ" ፕሮግራም ላይ "እሸቴ ከጃንሜዳ" በሚል ስያሜ የገጠሪቱን ኢትዮጵያ ባህልና ውሎ የሚያሳዩ ማራኪ የሥነ-ቃል ስብስቦችን በራሱ አንደበት እያነበበ ለአድማጭ ያቀርብ ነበር።
በተያያዥነትም ከ1979 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በፍሪላንስ ጋዜጠኛነት በመቀጠር፣ በተለይ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ አካባቢዎች ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ባለ አንድ ሰዓት ዘጋቢ ፊልሞችን (ዶክመንተሪዎችን) አዘጋጅቷል።
ከእነዚህም መካከል ስለ ጣና ሐይቅ አድባራት የሠራውና አዲስ አበባ 100ኛ ዓመቷን ስታከብር ያቀረበው ባለ አንድ ሰዓት ተኩል ልዩ ፕሮግራም ተጠቃሽ ናቸው።
በ1987 ዓ.ም "ሪፖርተር" ጋዜጣ ሲመሠረት ከዋና መሥራቾቹ አንዱ የነበረ ሲሆን፣ ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የ"ሪፖርተር" ጋዜጣና መጽሔት ምክትል ዋና አዘጋጅና ዋና አዘጋጅ በመሆን ሙያዊና እውነተኛ መረጃ ላይ የተመሠረተ ጋዜጠኝነት እንዲሰፍን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት ደግሞ በሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ሬዲዮ በቅዳሜው "እነሆ መቆያ" መሰናዶው የዓለም መሪዎችን፣ ታዋቂ ሰዎችንና ታላላቅ የስለላ ተቋማትን፣ ታሪካዊ ክስተቶችን እና ሌሎችንም ጉዳዮች በበቂ ንባብና ማስረጃ አደራጅቶ በማቅረብ ከፍተኛ ተወዳጅነትን አትርፏል።
በአሁኑ ወቅትም በሸገር fm 102.1 ሬዲዮ ጣቢያ በዋና አዘጋጅነት እያገለገለ ይገኛል። ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነው።
ስለራሱ በአንደበቱ ከማውራት ይልቅ በሥራው መናገርን የሚመርጠው ይህ በሳል ጋዜጠኛ፣ ባለፉት ሠላሳ ዓመታት በሀገሪቱ ሚዲያ ታሪክ ውስጥ የራሱን የማይረሳ ደማቅ አሻራ አስቀምጧል። እናመሰግናለን፤ እሼ!
#ወይ_አዲስ_አበባ_on_Sheger_fm_102 .1 #sheger_fm_102 .1 #zefenenazemen #jafarbooks #radio #አዲስ_አበባ

24 days ago
“የንባብ ከተማ” የተሰኘ የህጻናት ቲያትር በድምቀት ተመረቀ
#ethiopia | የህፃናትን የንባብ ባህል ለማዳበር ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀው “የንባብ ከተማ” የተሰኘው አዲስ የህፃናት ቴአትር ዛሬ ረፋድ ላይ ለእይታ በቃ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቲያትር ቤቶች አስተዳደር፣ የህጻናትን እና የወጣቶችን ጥበባዊ ተሰጥኦ ለማሳደግና ታሪክን ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማሸጋገር ዘመናዊ የቲያትር መድረኮችን በስፋት እየተጠቀመ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ቲያትር ቤቶች አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተስፋገኘው ለገሠ እንደገለጹት፣ ከተማዋ ዘመናዊ የንባብና የመዝናኛ ቦታዎችን በመገንባት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሰራች ነው።
በዚህም መሰረት በቅርቡ ተመርቆ አገልግሎት እየሰጠ በሚገኘው እና ፍላሚንጎ አካባቢ በሚገኘው የህጻናት እና ወጣቶች ቲያትር ቤት ለህጻናት የተዘጋጀ አዲስ ቲያትር በይፋ መመረቁን ጠቅሰው፣ ይህንን መድረክ ለታለመለት አላማ ሙሉ ለሙሉ ለመጠቀም እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
“የንባብ ከተማ” ቴአትር ከሚቀጥለው እሁድ ጀምሮ በቋሚነት ዘወትር እሁድ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ለታዳሚዎች እንደሚቀርብ ተገልጿል።
ለህፃናትና ለወላጆች ምቹ በሆነው በዚህ አዳራሽ፣ ከቴአትር በተጨማሪ ማራኪ ሙዚቃዎችና አስተማሪ የታሪክ መርሐግብሮች እንደሚኖሩት ተጠቁሟል።
ጌትነት ተመስገን
📷ከበደ መክብብ
#addisababa #theaterlife #culturalheritage #ethiopianarts #kidstheater #citydevelopment #performingarts #communityengagement

“የንባብ ከተማ" የህፃናት ቴአትር ዛሬ በታላቅ ድምቀት ለእይታ በቃ!
#fastmereja I የህፃናትን የንባብ ባህል ማዳበር ላይ ትኩረቱን ያደረገው “የንባብ ከተማ" የተሰኘው አዲስ የህፃናት ቴአትር፣ ዛሬ ሐምሌ 12 ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ፍላሚንጎ ፊትለፊት በሚገኘው አዲሱ የህፃናትና ወጣቶች ቴአትር አዳራሽ ለታዳሚዎች ቀርቧል።
ቴአትሩ በዛሬው ዕለት መታየት የጀመረ ሲሆን በዋናነትም በሰላም፣ በአንድነት፣ በመዋደድ፣ በፍቅር እና በጋራ የመስራት እሴቶች ላይ ያተኮረ ነው።
ቴአትሩ በዓለም አቀፍ የትያትር አዘገጃጀት ስልት “ፋንታሲ” (Fantasy) በሚባለው ዘውግ የተዘጋጀ በመሆኑ፣ ዛሬ መድረክ ላይ የቀረቡት እንስሳትና ድንጋዮች ህይወት አግኝተው ሲናገሩና ሲተገብሩ ታይተዋል።
ይህ አቀራረብ በዕለቱ የተገኙ ህፃናትን ትኩረት በእጅጉ የሳበና ታሪኩን በቀላሉ እንዲረዱት ያደረገ ነበር ተብሏል።
በአዘጋጅ ደምሴ በየነ የተመራውና ስምንት አንጋፋና ወጣት ተዋናዮች የተሳተፉበት ይህ ቴአትር፣ ከተለመደው ትወና በተጨማሪ ማራኪ ሙዚቃዎች፣ ተረቶችና አስተማሪ የታሪክ መርሐግብሮችን አካቶ ቀርቧል።
ዛሬ ቴአትሩ ለእይታ የበቃበት ፍላሚንጎ ፊትለፊት የሚገኘው አዲሱ አዳራሽ፣ ለታዳሚ ህፃናትና ወላጆች እጅግ ምቹና ሰፊ ሁኔታን ይዞ መምጣቱ በዕለቱ በተጨባጭ ታይቷል።
“የንባብ ከተማ” ቴአትር ከዛሬው የመክፈቻ ዕይታ በኋላ፣ ከሚቀጥለው እሁድ ጀምሮ ዘወትር እሁድ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ለታዳሚዎች መቅረቡን እንደሚቀጥል ተገልጿል።
#ኪነ_ጥበብ

25 days ago
በዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ የተጻፉ ሁለት አዳዲስ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መጽሐፍት ተመረቁ
#ethiopia | የቀድሞው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታ እና የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ አዴ፣ የወደፊቱን ዓለም በሳይንስና በቴክኖሎጂ የሚመለከቱ ሁለት አዳዲስ መጽሐፍትን ለንባብ አበቁ።
«Architecting the Future: A Blueprint for the Next Human Civilization» እና «Introduction to Astronautics: A Beginner's Guide» በሚል ርዕስ የቀረቡት መጽሐፍት፣ የወደፊቱን የሰው ልጅ ሥልጣኔ፣ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ሚና፣ እንዲሁም የጠፈር ሳይንስ እድሎችን በሰፊው የሚዳስሱ መሆናቸው ተገልጿል።
በመጽሐፍቱ ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ዶ/ር ይሹሩን እንዳስታወቁት፣ «Architecting the Future» የሰው ልጅ ሕይወትን በፍጥነት እየቀየሩ ባሉ ቴክኖሎጂዎች መካከል የወደፊቱን ዓለም በሰብዓዊ እሴቶች፣ በዘላቂነትና በራዕይ መገንባት ላይ ያተኩራል።
ሁለተኛው መጽሐፍ «Introduction to Astronautics» ደግሞ የጠፈር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለዕለት ተዕለት ኑሮ፣ ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለብሔራዊ ደህንነት ያለውን ፋይዳ በቀላል አቀራረብ በማስረዳት፣ በተለይም አፍሪካውያን ወጣቶች በጠፈር ኢኮኖሚ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያበረታታል።
ደራሲው እንደገለጹት፣ ሁለቱ መጽሐፍት አንዱ የወደፊት ራዕይን ሲያስቀምጥ፣ ሌላው ደግሞ ያንን ራዕይ ለማሳካት የሚያስፈልጉ ሳይንሳዊና ቴክኖሎጂያዊ መሠረቶችን ያቀርባል።
መጽሐፍቱ ወጣቶችን ወደ STEM (ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስናና ሂሳብ) ዘርፎች ለመሳብ፣ በኢትዮጵያ የምርምርና የፈጠራ ባህልን ለማጠናከር እንዲሁም ፖሊሲ አውጪዎች የረጅም ጊዜ ስትራቴጂያዊ እይታ እንዲኖራቸው በማገዝ ረገድ አስተዋፅኦ እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል።
ጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ መክብብ
#ethiopia #science #technology #innovation #spacescience #stem #booklaunch #getutemesgen #ጌጡተመስገን

በዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ የተሰናዱ ሁለት የሳይንስና የወደፊት ራዕይ መጻሕፍት ተመረቁ!
#fastmereja :- በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ እና በሰው ልጅ ቀጣይ ስልጣኔ ላይ የሚያተኩሩ ሁለት አዳዲስ መጻሕፍት በዛሬዉ እለት በልዩ ስነ-ስርዓት ተመረቁ።
የቴክኖሎጂ ባለሙያውና ተመራማሪው ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ ያዘጋጇቸዉ «Architecting the Future: A Blueprint for the Next Human Civilization>> እና «Introduction to Astronautics: A Beginner's Guide» የተሰኙት መጻሕፍት፤ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የአካዳሚክ ማህበረሰብ፣ ዲፕሎማቶችና የቴክኖሎጂ ዘርፍ አጋሮች በተገኙበት ነው ለንባብ የበቁት።
በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት ደራሲው ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ፣ መጻሕፍቱ የተዘጋጁት መረጃ ለመስጠት ብቻ ሳይሆን አገር በቀል እውቀትን በማሳደግ የወደፊቱን ትውልድ ለታላቅ ስኬት ለማነሳሳት መሆኑን ገልጸዋል።
"ሀገራት የሚለወጡትና ከፍ የሚሉት በእውቀት፣ በፈጠራ፣ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ራዕይ ብቻ ነው" ያሉት ደራሲው፣ ሁለቱ መጽሐፍት በይዘታቸው የተለያዩ ቢመስሉም የሚያስተላልፉት መልዕክት ግን በአንድ ማዕቀፍ ውስጥ የሚቀመር መሆኑን አስገንዝበዋል።
የመጀመሪያው መጽሐፍ-«Architecting the Future» -አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)፣ ሮቦቲክስ፣ ኳንተም ኮምፒውቲንግ፣ ባዮቴክኖሎጂ እና የዲጂታል ኢኮኖሚ የሰው ልጅን ህይወት በከፍተኛ ፍጥነት እየቀየሩት ባሉበት በዚህ ወቅት፣ የወደፊቱን ዓለም በሥነ-ምግባር፣ በሰብዓዊ እሴቶችና በፍትሐዊነት እንዴት መምራት እንደሚቻል ስልታዊ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል። መጽሐፉ ለመንግሥታት የፖሊሲ አቅጣጫን፣ ለዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ የምርምር ራዕይን ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
በሌላ በኩል «Introduction to Astronautics>> የተሰኘው ሁለተኛው መጽሐፍ የጠፈር ቴክኖሎጂን በቀላል ቋንቋ የሚያስተምር ሲሆን፤ የሮኬት ሳይንስ፣ ሳተላይቶች፣ የጠፈር ህግና ዲፕሎማሲ እንዲሁም የጠፈር ኢኮኖሚ በተግባራዊ መልኩ የቀረቡበት ነው። በተለይም ኢትዮጵያና አጠቃላይ አፍሪካ በአዲሱ የጠፈር ኢኮኖሚ ውስጥ ተገብሮ ተመልካች ሳይሆኑ፣ ንቁ ተሳታፊ መሆን እንዳለባቸው መጽሐፉ በግልጽ እኖደሚያሳይ ተገልጿል።
ዶ/ር ይሹሩን የሁለቱን መጻሕፍት ትስስር ሲያስረዱም፦

26 days ago
በመጋቢት ኑኑ ገዛኸኝ የተዘጋጀው "የእናትነት ዋጋዉ ስንት ነው?" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ለአንባቢያን በቃ!
#fastmereja I በማኅበረሰቡ ውስጥ የእናቶችን ክብር የሚነኩ አጉል ባህሎችን ለመለወጥና ሥነ-ምግባር የሰፈነበት የመግባቢያ ባህልን ለመገንባት ያለመ "የእናትነት ዋጋዉ ስንት ነው?" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ተመረቀ።
በቤተሰብ እና በቅድመ-ጋብቻ ምክር ላይ ትኩረቱን አድርጎ በሚንቀሳቀሰው “አልባስጥሮስ” የቤተሰብና የሴቶች አገልግሎት ተቋም ዋና ሥራ አስኪያጅ በመጋቢት ኑኑ ገዛኸኝ የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ፤ ተቋሙ ከተመሰረተበት የአንድ ዓመት ጊዜ ወዲህ ለንባብ ያበቃው ሁለተኛው መጽሐፍ መሆኑ ታዉቋል።
የመጽሐፉ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በድምቀት የተከናወነ ሲሆን፣ ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ውስጥ የእናቶችን ክብር የሚነኩ፣ የሚያዋርዱ እና የሚያንቋሽሹ አነጋገሮችን ለማስቀረት ለሚደረጉ የሕዝብ ግንዛቤ ማሳደጊያ እና የአድቮኬሲ (የጥብቅና) ሥራዎች የሚውል መሆኑ ተገልጿል።
የተቋሙ ተወካይ በምረቃው ወቅት እንደገለጹት፤ የመጽሐፉ ርዕስ እና የድርጅቱ ስም "አልባስጥሮስ" (ትርጉሙም መልካም እና ውድ ሽቶ የሚቀመጥበት ዕቃ) መሆኑ ከእናቶች ክብርና እንክብካቤ ጋር የተያያዘ መሆኑ ነዉ የተገለፀዉ።
ይህ መፅሀፍ በህብረተሰቡ ዘንድ እናትን የመውደድ ስሜት ቢኖርም፣ በተግባር ግን እናትን የማይመጥኑ አጉል ባህሎችና ስድቦች በመኖራቸው፣ ይህንን የተበላሸ የመግባቢያ ባህል ለመለወጥ መጽሐፉ የበኩሉን አስተዋፅኦ ያበረክታል ብለዋል።
ኤልባስጥሮስ የቤተሰብና የሴቶች አገልግሎት ተቋም ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ከጋብቻ በፊትና በኋላ ባሉ የሕይወት ምዕራፎች ዙሪያ 12 የሚጠጉ ተግባራዊ ሥልጠናዎችን መስጠቱ ተገልጿል።
በአሁኑ ወቅት የበርካታ ጥንዶች ትዳር በጥንቃቄ ባለመጀመሩ ምክንያት እየፈረሰ መሆኑን የጠቀሱት ተወካይዋ፣ ተቋማቸው በዋናነት ትኩረት አድርጎ እየሰራ ያለው ጋብቻ ከመመስረቱ በፊት ባለው "ቅድመ-ጋብቻ" የወጣቶች ዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቀዋል።
በስነ-መለኮት (Theology) እና በሶሺዮሎጂ (Sociology) የትምህርት ዘርፍ በሰለጠኑ ባለሙያዎች የሚመሩት እነዚህ ሥልጠናዎች፤ ተቋሙ መንፈሳዊ ይዘት ያለው ቢሆንም ኦርቶዶክስ፣ እስልምና እና ሌሎችንም እምነቶች ጨምሮ "ሰው ለተባለ ሁሉ'' እና ትዳርን ለሚያስብ ማንኛውም ዜጋ ክፍት መሆናቸው ተገልጿል።

ወላጆች የልጆችዎ የክረምት እረፍትን ትርጉም ባለው መልኩ እንዲያልፍ ያድርጉ!!!
👉 በአይነቱ የተለየ የሕፃናትና ታዳጊዎች ሁለንተናዊ የብቃት ካምፕ ከዮቶጵያ፤
💡የልጅዎን አእምሮ፣ አካል እና መንፈስ የሚገነባ ድንቅ መርሃ-ግብር አዘጋጅተናል፤
🏢 ልጆችዎን እኛ ካምፕ ሲገቡና ሲቆዩ👇
🧠 በአእምሮ ምህንድስና ክፍለ ጊዜ
ራስን ማወቅ (SWOT)፣ የመጽሐፍ ንባብ ልምድ (Atomic Habits)፣ Active Recall እና Mind Mapping ይማራሉ፤
🏃♂️ በአካል ብቃትና መዝናኛ ሰዓታቸው
እግር ኳስ፣ ባስኬት ቦል፣ ኤሮቢክስ እና ጅይምናስቲክ እንዲሁም ተጨማሪ surprising ጌሞች ተዘጋጅቶላቸዋል፤
⛪️🕌 በመንፈሳዊ ትምህርት ሰዓታቸው
በየእምነታቸው መስመር (ኦርቶዶክስ፣ ፕሮቴስታንት እና እስላማዊ) ስነ-ምግባር እና ሃይማኖታዊ እውቀት በብቁ መምህራን ያገኛሉ።
🏥 ለደህንነታቸው እንዳይጨነቁ
የ24/7 ጥበቃና ነርስ በቦታው ከመኖሩም በላይ በየሳምንቱ የልጅዎን እድገት መከታተል ይችላሉ!፤
🎁 ከ2 በላይ ልጆች ለሚያስመዘግቡ የ10% ቅናሽ ይደረግላቸዋል፤ ያሉት ቦታዎች ውስን በመሆናቸው ልጅዎንቀድመው ያስመዝግቡ!
📍 የስልጠና ቦታዎች -
ቁጥር 1 - ብስራተ ገብርኤል
ቁጥር 2 - አያት አደባባይ ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ
📱ለምዝገባ
በ0963999966 / 0963999977 ስልክ ቁጥሮች ይደውሉ።
📚 ዮቶጵያ (Utopia) የሕጻናትና ታደጊዎች ሁለንተናዊ ብቃት ካምፕ

27 days ago
💎 ጠቃሚ መረጃ ለወላጆች!!!
👉 ክረምቱን ለልጅዎ ትልቅ መሠረት የሚጥሉበት ወርቃማ ጊዜ ያድርጉት!
💡ዮቶጵያ (Utopia) የሕጻናትና ታደጊዎች ሁለንተናዊ ብቃት ካምፕ
🗓 ከሃምሌ ወር አጋማሽ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ልጆች አእምሯቸውን፣ አካላቸውንና መንፈሳቸውን በአንድነት የሚገነቡበት ልዩ ዝግጅት! ✨
📚 በካምፓችን ምን አዘጋጅተናል?
🧠 የአእምሮ ምህንድስና፦
ራስን ማወቅ (SWOT)፣ የመጽሐፍ ንባብ ልምድ (Atomic Habits)፣ Active Recall እና Mind Mapping፤
🏃♂️ አካል ብቃትና መዝናኛ፦
እግር ኳስ፣ ባስኬት ቦል፣ ኤሮቢክስ እና ጅይምናስቲክ፤ እንዲሁም ተጨማሪ surprising ጌሞችን ጨምሮ፤
⛪️🕌 መንፈሳዊ ትምህርት፦ በየእምነታቸው መስመር (ኦርቶዶክስ፣ ፕሮቴስታንት እና እስላማዊ) ስነ-ምግባር እና ሃይማኖታዊ እውቀት።
🏥 የደህንነት ዋስትና፦
የ24/7 ጥበቃና ነርስ በቦታው ከመኖሩም በላይ በየሳምንቱ የልጅዎን እድገት መከታተል ይችላሉ!፤
🎁 ከ2 በላይ ልጆች ለሚያስመዘግቡ የ10% ቅናሽ ይደረግላቸዋል፤ ያሉት ቦታዎች ውስን በመሆናቸው ልጅዎን ቀድመው ያስመዝግቡ!

የሕፃናትን ምናብ ለማሳደግ የተዘጋጀው አዲስ የሕፃናት ትያትር ለታዳሚ ሊበቃ ነው!
#fastmereja :-የሕፃናትንና የወጣቶችን አእምሮአዊ፣ ሥነ-ልቦናዊና ማኅበራዊ ዕድገት የሚያግዙ በርካታ ትምህርታዊና አዝናኝ ሥራዎችን ሲያቀርብ የቆየው የሕፃናትና ወጣቶች ትያትር ቤት፤ “የንባብ ከተማ” (በሌላ መጠሪያው “የፊደል ከተማ”) የተሰኘ አዲስና ድንቅ የሕፃናት ትያትር ዝግጅቱን አጠናቆ ለምረቃ ማብቃቱን አስታወቀ።
የሕፃናትን ረቂቅ ምናብ (Imagination) እና የፈጠራ ክህሎት ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀው ይህ ትያትር፤ በዓለም አቀፍ የትያትር አዘገጃጀት ስልት በፋንታሲ (Fantasy) ዘውግ የተቃኘ ሲሆን በትያትሩ ውስጥ ሕፃናትን ይበልጥ ለመሳብና ታሪኩን በቀላሉ እንዲረዱት ለማድረግ ሲባል፣ እንስሳትና ድንጋዮች ሕይወት አግኝተው እንዲናገሩና እንዲተገብሩ ተደርጎ በልዩ ጥበብ ተቀርጿል።
የትያትሩ ዋና አብይ ጭብጥ በትውልዱ ዘንድ የጠፋውንና እጅግ የሚፈለገውን የንባብ ባህል ማሳደግ ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ ጎን ለጎን የሚሄደው ንዑስ ጭብጡ ደግሞ ሰላም፣ አንድነት፣ መዋደድና ፍቅርን ለሕፃናቱ በአንደበታቸውና በምስል በሚገባቸው መልኩ የሚያስተምር ስለመሆኑም ነዉ የተገለፀዉ።
የሕፃናት ትያትር እንደ አዋቂዎች ትያትር ሳይሆን ከፍተኛ ድካምና ጥንቃቄ የሚጠይቅ መሆኑን የገለጹት የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎቹ፤ ተዋንያኑ መድረክ ላይ ከሚገኙት ሕፃናት ጋር ቀጥተኛ፣ ሕያውና ንቁ ተሳትፎ (Active participation) እንዲያደርጉ የሚያስገድድ በመሆኑ ሥራውን ፈታኝና ማራኪ ያደርገዋል ብለዋል።
ይህንን ፈታኝ ጥበብ በብቃት ለመወጣትም ከተቋሙ የተገኙ 5 ወጣቶችና አንጋፋ ተዋንያንን ጨምሮ፣ ከተለያዩ ታዋቂ የጥበብ ተቋማት (ከማዘጋጃ ቤት ባህል አዳራሽ እና ከሀገር ፍቅር ትያትር) የመጡት እንደ ሚሊዮን ብርሃኔ እና ዮዲት አሰፋ ያሉ 2 አንጋፋ ባለሙያዎች በአጠቃላይ 8 ተዋንያን በትያትሩ ላይ ተሳትፈዋል። ትያትሩ ጥራት ባላቸው ዘመናዊ መብራቶችና ማራኪ ሙዚቃዎች የታጀበ በመሆኑ ለሕፃናቱ እጅግ ማራኪና ቀልብ ሳቢ ሆኖ መዘጋጀቱ ተገልጿል።
ይህ ቀደም ሲል በአራት ኪሎ በነበረው ጠባብ አዳራሽ ውስጥ ለሕፃናት ድራማ የማይመች፣ የመጫወቻ ቦታ የሌለውና ወንበሮቹ ሕፃናትን ለውድቀት የሚዳርጉ እንደነበሩ አስታውሶ፤ አሁን ግን ይህ ችግር ተቀርፎ ሕፃናት በነፃነት የሚጫወቱበትና ቢወድቁ እንኳ በምቾት ምክንያት እንቅልፍ አሸንፏቸው እንጂ በጉዳት ስጋት እንዳይሆን ተደርጎ የተሠራ አዲስ አዳራሽ ማግኘታቸውን ገልጿል።
ይህ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው “የንባብ ከተማ” ትያትር ከሚቀጥለው እሁድ ጀምሮ በይፋ የሚከፈት ሲሆን፣ ዘወትር እሁድ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ለታዳሚዎች የሚቀርብ ሲሆን ከተለመደው ትያትር በተጨማሪ ሙዚቃ፣ ተረት እና ሕፃናትን የሚያዝናኑና የሚያስተምሩ የታሪክመርሐግብሮች በፓኬጅ መልክ መካተታቸው ታውቋል።
ትያትሩ ተማሪዎችና ሕፃናት ለክረምት ዕረፍት በሚወጡበት በዚህ ወቅት መዘጋጀቱ ለወላጆችና ለልጆች ትልቅ መልካም አጋጣሚ መሆኑ ተገልጿል።
እንዲሁም ወላጆች ያለምንም ስጋት ልጆቻቸውን ይዘው በመምጣት እንዲያዝናኑ፣ የንባብ ባህላቸውን እንዲያሳድጉና ልጆቻቸውን በዚህ አዲስ ተቋም በተለያዩ የጥበብ ዘርፎች በማሰልጠን ለነገ ትላልቅ ባለሙያዎች የሚሆኑበትን መሠረት እንዲጥሉ ጥሪ ቀርቧል።

29 days ago
በአዲስ አበባ በኪነ-ጥበብና በሳይንስ ዘርፍ አዲስ ታሪክ የሚሠራ መርሃ-ግብር፤ በዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ አዴ የተዘጋጁ ሁለት አዳዲስ መጻሕፍት ሊመረቁ ነው
#ethiopia | የቀድሞው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታ እና አሁን ላይ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ታዋቂው ተመራማሪና ምሁር ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ አዴ (PhD) ያዘጋጇቸው ሁለት አዳዲስ መጻሕፍት በይፋ ሊመረቁ መሆኑ ተገለጠ።
ይህ በጉጉት የሚጠበቀውና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር (MInT) የሚያስተናግደው ይፋዊ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት፤ ቅዳሜ ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም (July 11, 2026) ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በቦሌ ዩጎ ቸርች አቅራቢያ በሚገኘው "Best Western Plus" ሆቴል እንደሚካሄድ የወጣው መርሃ-ግብር ያሳያል።
ለዕይታና ለንባብ የሚበቁት ሁለቱ መጻሕፍት የሚከተሉት ናቸው፦
Architecting the Future: A Blueprint for the Next Human Civilization
ይህ መጽሐፍ የሰውን ልጅ ማዕከል ያደረገ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈና በዕሴቶች ላይ የተመሠረተ ሥልጣኔን ለመገንባት የሚያስችል አርቆ አሳቢ ዕቅድ (Blueprint) የሚያቀርብ ነው። መጽሐፉ የፈጠራ ሥራዎች፣ ሥነ-ምግባር፣ አመራርና ሥርዓታዊ አስተሳሰቦች ለዛሬው ዓለም አቀፋዊ ፈተናዎች እንዴት መፍትሔ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይተነትናል።
Introduction to Astronautics: A Beginner's Guide
ይህ መጽሐፍ ደግሞ ስለ ስፔስ (ህዋ) እና አስትሮኖቲክስ አስደናቂ ዓለም ቀላልና ማራኪ ማብራሪያ የሚሰጥ ሲሆን፤ ውስብስብ የሆኑ የህዋ ሳይንስ ጽንሰ-ሀሳቦችን፣ የስፔስ ተልዕኮዎችን፣ የሮኬቶችንና የህዋ ምርምር መርሆችን ለጀማሪዎች፣ ለተማሪዎችና ለዘርፉ ፍቅረኞች በሚመጥን መልኩ ያብራራል።
የደራሲው ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ አዴ
አጭር ታሪክና ሙያዊ አስተዋፅኦ
ደራሲው በሜካኒካል፣ ማሪን እና ኤሮስፔስ ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ከፍተኛ ዕውቀት ያላቸው ምሁር ሲሆኑ፤ በኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በብሔራዊ የስፔስ ፕሮግራም ውስጥ ግንባር ቀደም መሪ ናቸው።
በተለይም የኢትዮጵያን የመጀመሪያዋን የርቀት መቅረጫ ሳተላይት (ETRSS-1) እና ሁለተኛዋን (ET-SMART-RSS) ዲዛይን የማውጣት፣ የማልማትና ወደ ህዋ የማስወንጨፍ ሥራዎችን በበላይነት በመምራትና በማስተባበር ረገድ ከፍተኛ ታሪካዊ አሻራ ያኖሩ የዘርፉ ፈር ቀዳጅ ምሁር ናቸው።
የዕለቱ መርሃ-ግብር
በዚህ ታላቅ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ምሁራን፣ የልማት አጋሮች፣ ተማሪዎችና የፈጠራ ባለቤቶች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በዕለቱም፦
* የመጻሕፍቱ ዝርዝር አቀራረብ (Book Presentation)፣
* የክብር እንግዶች ንግግር (Remarks)፣
* በባለሙያዎች የሚመራ የፓናል ውይይት (Panel Discussion) እና
* የጋራ ትውውቅና ግንኙነት (Networking) መርሃ-ግብሮች እንደሚከናወኑ ተገልጿል።
የዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ አዴ - ዝግጅት በተለይም ቀጣዩን ትውልድ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግና ማትስ (STEM) ዘርፍ ለማነቃቃትና የአፍሪካን የስፔስ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለመቅረጽ ትልቅ መሠረት ይጥላል ተብሎ ይታመናል።

1 month ago
አዲስ መጽሐፍ | የአእምሯዊ ንብረት ሕግ
#ethiopia | የሕግ ባለሙያና ደራሲ ዳዊት መ. በዛብህ (Dawit M. Bezabih) የጻፉት "የአእምሯዊ ንብረት ሕግ (Intellectual Property Law)" መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል።
ዳዊት በሕግ ዘርፍ በአማርኛ ቋንቋ እምብዛም ያልተዳሰሱ ወሳኝ ርዕሰ ጉዳዮችን በማቅረብ የሚታወቅ ጸሐፊ ሲሆን፣ በዚህ መጽሐፉም የአእምሯዊ ንብረት ሕግን ከመሠረቱ ጀምሮ በጥልቀት ያብራራል።
በመጽሐፉ ውስጥ፦
✔️ የአእምሯዊ ንብረት ሕግ ምንነት፣ ታሪክና ዓላማ
✔️ የፈጠራ ባለቤትነት (Patent) እና የምዝገባ ሂደት
✔️ የቅጂ (Copyright) እና ተዛማጅ መብቶች
✔️ የንግድ ምልክት (Trademark)
✔️ የንግድ ሚስጥር (Trade Secret)
✔️ የአእምሯዊ ንብረት ሕግ ከሰው ሠራሽ አስተዋይነት (AI) እና ከዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ጋር ያለው ግንኙነት
በግልጽና በቀላል አቀራረብ ተዳስሰዋል።
⚖️ ለሕግ ተማሪዎች፣ ጠበቆች፣ ደራሲያን፣ ፈጠራ ባለቤቶች፣ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እና በዘርፉ ፍላጎት ላላቸው ሁሉ ጠቃሚ የማጣቀሻ መጽሐፍ ነው።
አንብቡት!
በJafer Books ያገኙታል።

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የግዛት ሥልጣን በአዲስአበባ
ሕግ፣ አፈጻጸም፣ ክፍተት እና መፍትሄ
በኢትዮጵያ ህግ ማእቀፍ እና ተጨባጭ የህግ አፈጻጸም
በጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው 0929101037
የዚህ ጽሁፍ መነሻ ሀሳብ
#ethiopia | ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ ወጥነት ያለው የጉዳዮች ክስ አቀራረብ አስመልክቶ አንዳንድ ጉዳይ ጉዳዩ በተከሰተበት ወይም ለጉዳዩ መነሻ በሆነበት ላስቻለው ፍርድ ቤት ሲከፈቱ አንዳንድ ጉዳዮች ደግሞ የጉዳዩ መነሻ ከሆነበት ስፍራ ይልቅ እንደዚህ አይነት ጉዳይ በልዩ ችሎት በዚህ ክፍለከተማ ባለው በተቋቋመው ምድብ ችሎት እንጂ ይህ ፍርድ ቤት ይህንን ጉዳይ ሊመለከት አይችልም ስለዚህ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ በልዩ ሁኔታ በተቋቋመበት ሄደህ መክፈት እንጂ እዚህ ሊከፈት አይችልም በሚል የጉዳዩ መነሻ የተከሰተበት ስፍራ የግዛት ስልጣን ያለው ተመሳሳይ ፍርድ ቤት ማየት አይችልም ተብሎ ለምሳሌ ከፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቃቂ ቃሊቲ ምድብ ችሎት የጉዳዩ መንስኤ የሆነው ጉዳይ የማንንቀሳቀስ ንብረትም ሊሆን ይችላል እዚህ አቃቂ ቃሊቲ ያለው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከህግ አንጻር የማየት ስልጣን እያለው የልደታ ወይም የአራዳ ምድብ ችሎት ነው የሚያየው ተብሎ የፍትህን ተደራሽነትን ዋጋ ሊያሳጣ በሚችል ደረጃ የፍተሀብሔር ስነስረአት ህግ አላማን ወደ ጎን በመተው ላልተፈለገ ወጪ ፣እንግልት ፣ ኪሳራ፣ ለኢፍትሀዊ እና ለዘገየ ፍትህ የምንዳረግ መሆኑን መገንዘቤ የዚህ ጹሁፍ መነሻዬ ነው ሲሆን የሚያጠነጥነው የፍተሀብሔር ጉዳዮችን በተመለከተ ይሆናል።
መግቢያ
የዚህ ጹሁፍ አላማ "በአዲስአበባ ውስጥ የሚገኙ የፌደራል ፍርድ ቤቶች የግዛት ስልጣናቸው የሚወሰነው በፍርድ ቤቶች አመራር፥ ፥ አስተዳደራዊነት ወይንስ በፍተሀብሔር ወይም በወንጀል አግባብ ባለው የህግ ስልጣን መሠረት?" የሚለውን የተዛባ አሰራር ህጋዊ አስተያየት በመስጠት ሊጠራ የሚገባው ጉዳይ በመሆኑ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ ሌላው ሊታወቅ የሚገባው ነገር የፍተሀብሔር እና ወንጀለኛ ስነስረአት አላማው ነው። የእነዚህ ስነስረአት አላማቸው ምንድነው? ተደራሽነት፣ፍትህ፣ወጪ፣ጊዜ፣የተፋጠነ ፍትህ ከመስጠት አንጻር ግባቸው ምንድነው"የሚለው ጉዳይን በማጤን ጭምር በዚህ ጹሁፍ የምንመለከተው ነው። ይህ ጹሁፍ የራሴ የግል ሀሳብ ተደርጎ ቢወሰድም ከዚህ አንጻር ግርታን የሚፈጥሩ ሀሳቦችን በውይይት፣በጥናት የተሻለውን ለመውሰድ መነቃቃትንና አግባብነት አንጻር የራሱ የሆነ ፋይዳ ይኖረዋል ብዬ በማሰብ ይህንን ጹሁፍ ለንባብ አብቅቻለው።
1. የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር አወቃቀር ከፍርድ ቤቶች ተደራሽነት አንጻር....
አዲስአበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ስትሆን በአስራ አንድ ክፍለከተሞች የተከፈለች ናት። ህዝቦቿ በእያንዳንዱ ክ/ከተማ ብዛት ያላቸው፣ ትላልቅ ኃላፊነት የተሰጣቸው የተለያየ የመንግስት አስተዳደር አካላት ፣ የአገልግሎት ተቋማት፣ የንግድ ትስስሮች ያሉባት የፌደራል መንግስት እና የአፍሪካ መዲና መቀመጫ ናት። ይህ እንደ መሆኑ መጠን የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ስልጣንን ፣ የአገልግሎት ኃላፊነትን፣ በህግ የተሰጠ ስልጣን፣መብት፣ግዴታ የአዳስአበባ ከተማ አስተዳደር ለክፍለ ከተሞች የሰጠው የስልጣን ክፍፍል ዘርፈ ብዙ ከመሆኑ ባሻግር በክፍለከተሞች የሚመለከታቸው ቢሮዎች ፣ የንግድ ፣ የማህበራዊና የፖለቲካ ተቋማት ተደራጅተው ይገኛል። ይህ እንደ መሆኑ መጠን ፍርድ ቤቶቻችን ሲደራጁ ሲዋቀሩ ከእነዚህ አስተዳደራዊ መዋቀር ጋር በመናበብ ለዜጎች ተደራሽ ሊሆኑ ያስፈልጋል።
2. የፍርድ ቤት የግዛት ስልጣን በኢትዮጵያ ፍተሀብሔር ስነስረአት ህግ/local jurisdiction/ እና በወንጀል ስነስረአት
የፍርድ ቤት ግዛት ስልጣን አስመልክቶ በፍተሀብሔር ዋናው አላማው በግዛቱ ለሚኖሩ ሰወች በመቅረብ ተደራሽነትን ተግባራዊ ማድረግ ሲሆን ተከራካሪ ወገኖች ያሉበት አከባቢ፣የክርክሩ ምክንያት የሆነው ነገር፣የማይንቀሳቀስ ንብረት ለክርክሩ መነሻ ሲሆን ፣ የክርክሩ መነሻ ውል ሲሆን ፣ ከሳሽ መንግስትን ከሳሽ ሲሆን፣ የተከሳሽ አድራሻ ባለበት ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባው በአጠቃላይ በፍተሀብሔር ስነስረአት ህግ ቁጥር ከ19 እስከ ድረስ ባለው የግዛት ስልጣን አስመልክቶ ተከራካሪው ወይም የክርክሩ መነሻ ባለበት ባለው አቅራቢ ፍርድ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ሊቀርብ እንደሚገባ ይደነግጋል። ለዚህም አላማው ወጪ ለመቆጠብ፣የተከራካሪ ወገኖችን እንግልት ኪሳራ ለማስቀረት፣ጉዳዮቹ ቀልጣፋ በመሆን አጠር ባለ ጊዜ ፍትሀዊ ውሳኔ ለመስጠት ያስችላል። የወንጀል ጉዳይም በተመለከተ ጉዳዩ ለተፈጸመበት ስፍራ ላለው ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ነው።
3. አዲስአበባ ላይ የሚገኙ የፌደራል ፍርድ ቤቶች በተመሳሳይ ስልጣን ላይ የሚገኙ ፍርድ ቤቶች የግዛት ስልጣንን ተግባራዊ ያለማድረግ ችግር....
በየክፍለከተማው ያሉ የፌደራል ፍርድ ቤቶች በፍርድ ቤት አስተዳደር ምክንያት ስልጣናቸው ተመሳሳይ ሲሆን በጉዳዮች አይነት ለተለዩ ክፍለከተማ ፍርድ ቤቶች የተለዩ ጉዳዮችን ተለይቶ የሚሰጥ ሲሆን ይህ የፍትሀብሄር ስነስረአትን ህግ አላማ ከግምት ውስጥ ያላስገባና የህገመንግስትን ፍትህ የማግኘት ፣ ዜጎች
በራሳቸው አስተዳደር መዋቀራዊ መንግስት የዳኝነት አገልግሎት እንዳያገኝ የሚያደረግ ነው። ኢፍትሃዊነቱን ለማንሳት ያህል፣በእኩል የመንግስት አስተዳደራዊ መዋቅር ስር የሚገኙ ህዝቦች ወይም ዜጎችን መሠረታዊና በመንግስት እንኳን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊገደብ የማይችል ህገመንግስታዊ የእኩልነት መብት ጋር የሚቃረን በየክፍለከተማው ተመሳሳይ የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሚያዩበትን የጉዳዮች መጠን በመለያየት የአከባቢው ማህበረሰብ አቅራቢያ በሚገኘው ፍርድ ቤት አገልግሎት እያጡ በሌላ ክፍለከተማ ባሉ ፍርድ ቤቶች አገልግሎት ለማግኘት ሲሄዱ ለተጨማሪ ወጪና ኪሳራ ከመዳረጋቸውም በላይ ዳኞች የሰነድ እና ሌሎች ማስረጃዎችን ከሌላ ክ/ከተማ ለማስመጣት እና ህጎቻቸውን ተፈጻሚ ለማድረግ ተግዳሮት የሚፈጥርና ለዘገየ ፍትህ ምክንያት የሚሆን ነው።
ምሳሌ አንድ :- በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የንግድና ኢንቨስትመንት ችሎት ያለው አንድ ክ/ከተማ ነው። በሌሎች ክፍለ ከተማ እነዚህ የፍርድ ቤት አገልግሎቶች ባለመኖራቸው ባለጉዳዮች ከየትኛውም የአዲስአበባ ቦታ በመመላለስ ለተለያየ እንግልት እና ለዘገየ ፍትህ የሚዳርግ ሲሆን በሌሎች ክ/ከተማ ያሉትን ሰወች የእኩልነት መብት መርህ ጋር የሚጣረስ ነው።
ምሳሌ ሁለት:- የመንግስት አስተዳደር ተከሳሽ በሚሆንበት ጊዜ
ጉዳዩ ልደታ ያለው መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ብቻ እንዲታይ ማደረጉ በተመሳሳይ በህጉ መሠረት ሌሎች ክፍለከተማ ያሉት የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤቶች እንዲያዩ የተሰጣቸውን ስልጣን ያለ ህግ ልደታ የሚገኘው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ብቻ ማድረግ የፍትህ ተደራሽነት እኛ የተቀላጠፈ ፍትህን ከግምት ውስጥ የማያስገባ ለዘገየ ፍትህ በር የሚከፍት ነው።
ምሳሌ:-ሦስት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በየክፍለከተማው ለማድረግ የበጀት ማነስ ወይም ሌላ ምክንያት ቢኖረውም በየክፍለከተማው ያሉት ውስን ፍርድ ቤቶች የሚመጡትን ጉዳዮች ስልጣኑ እስከሆነ ድረስ የግዛት ስልጣን እስካለው ድረስ ፤ በፍርድ ቤት አመራር አቅጣጫ ምክንያት ከህግ የመነጨ የፍርድ ቤት ስልጣንን ወደ ጎን በመተው አቤቱታዎችን ለመቀበል መለያየት ተገቢነት የለሌው ነው። ለዚህም ለመጥቀስ ያህል በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቲ አቃቂ ቃሊቲ ምድብ ችሎት በፍተሀብሔር ቀጥታ ሳይሆን በይግባኝ ብቻ መመልከቱ በቀጥታ ክስ የማየት ስልጣኑን በመከልከል ይግባኝ ጉዳይ ብቻ እንዲመለከት መደረጉ ፍትሀዊ እና የእኩልነት አገልግሎት መርህን ያላከበረ ነው።
4. የጸሃፊው የህግ አስተያየት እና ምክር
ከፍርድ ቤቶች ስልጣን መካከል አንዱ የግዛት ስልጣን መሆኑ ይታወቃል። ይህም የግዛት ስልጣን በፍተሀብሔር ስነስረአት ህግ ላይ ተደንግጎ የተቀመጠን በፍርድ ቤት አመራር አቅጣጫ ወይም መመሪያ ሊቀየር የማይገባ እና የህግ የበላይነትን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው። በመሆኑም በሁሉም ክፍለከተማ ያሉትን ዜጎች ካልተገባ ወጪ ለመታደግ ፣ የዜጎች እኩልነት፣የተፋጠነ አገልግሎትን ለማረጋገጥ እንዲሁም በፍትሃብሔር ስነስርዓት ህጉ ላይ የተቀመጠውን የግዛት ስልጣን በተመለከተ የተደነገጉ ህጎችን ለማረጋገጥ በሁሉም ክፍለከተማ የሚገኙ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የፌደራል መጀመሪያ ፣ ከፍተኛ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ያለቸው እስከሆነ ድረስ ማየት ይገባቸዋል እንጂ የአቃቂ ቃሊቲ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ወይም ከፍተኛ ፍርድ ቤትን ይህን ጉዳይ ለማየት ስልጣን የለውም በማለት የልደታ፣ ወይም የአራዳ ፌደራል መጀመሪያ/ከፍተኛ ደረጃ ምድብ ችሎት ነው ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ያለው በማለት የሚደረገው ጉዳዮችን በክፍለከተሞች በተመሳሳይ ደረጃ የሚገኙ ፍርድ ቤቶችን ያለ ህግ ስልጣናቸውን መለያየት ህገወጥ በመሆኑ ሊስተካከል ያስፈልጋል።
ማጣቀሻዎች/References/
1. የኢትዮጵያ ፍተሀብሔር ስነስረአት ህግ
2. የፌደራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1234/2013
3. የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር
https://t.me/Fantahunlawye...
tiktok.com/fantahun214
https://www.facebook.com/s...

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) «መደመር» መጽሐፍ በቻይንኛ ተተርጉሞ ለንባብ ሊበቃ ነው
2018 የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) «መደመር» መጽሐፍ በቻይንኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በቅርቡ ለንባብ ሊበቃ ነው፡፡
በ2010 ዓ.ም የነበረውን ሀገራዊ ለውጥ ተከትሎ የኢትዮጵያ የነገ ጉዞ ፍኖተ ካርታ ሆኖ የተወለደውና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የተጻፈው የ«መደመር» መጽሐፍ የቻይንኛ ቋንቋ ትርጉም ሥራው በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
መደመር ባለፉት አሥርት ዓመታት ከአፍሪካ አህጉር ፈልቀው ወደ ዓለም መድረክ ከተሻገሩ ጥቂት ሀገር በቀል ፍልስፍናዎች መካከል ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ፋና
ቹንጋኦኒ ብለናል ለአብይ
Seledadotio

«የማይናገረው ልዑል» መጽሐፍ በታላቅ ድምቀት ሊመረቅ ነው
• በእናት የተጻፈ በአይነቱ የመጀመሪያው እውነተኛ የህይወት ታሪክ ነው
#ethiopia | አዲስ አበባ — ደራሲ መሠረት ክንፈ ኃይሌ ከኦቲዝም ጋር ከሚኖረው ልጇ ልዑል ጋር ያሳለፈችውን ውጣ ውረድ፣ ጽናት፣ ተስፋ፣ እምነት፣ የእናትነት ፍቅርና ለልጅ የተከፈለ መስዋዕትነት ያጋራችበት «የማይናገረው ልዑል » የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ በመጪው ቅዳሜ ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ይመረቃል።
መጽሃፉ በኦቲዝም ዙሪያ በአንድ ወላጅ እናት ተጽፎ ለንባብ የበቃ በሀገራችን የመጀመሪያው መጽሐፍ ነው።
ይህን ልብ ሰቃይ እውነተኛ የህይወት ታሪክ በከፍተኛ ጥራት ለአንባብያን እንዲመች አድርጎ የአርትኦትና ቅንብር ስራውን የሰራው ታዋቂው ጋዜጠኛና አርታኢ መላኩ ብርሃኑ ነው። ጋዜጠኛ መላኩ ብርሃኑ ከመደበኛ የኮሚዩኒኬሽን ስራው ባሻገር በበጎ ፍቃድ በኦቲዝም ላይ ግንዛቤ በመፍጠር እና ከኦቲዝም ጋር ለሚኖሩ ልጆችና ወላጆቻቸው መብቶች በመታገል የሚታወቅ የኦቲዝም አድቮኬት ነው።ከዚህ ቀደምም ከህጻናት ክህምናና ኦቲዝም ስፔሻሊስት ዶክተር ሃዲያ ይማም ጋር “የኦቲዝም ምስጢሮች” በሚል ርዕስ የተሰናዳ መጽሃፍ በትብብር አዘጋጅቶ ለንባብ ያበቃ ባለሙያም ነው።
“የማይናገረው ልዑል” መጽሃፍ ባለታሪኳና ደራሲዋ መሰረት ክንፈ ሃይሌ ልጇ ልዑል ኦቲዝም እንዳለበት ካወቀችበት ጊዜ ጀምሮ በሃገረ አሜሪካ የልጇን የመማርና በእንክብካቤ የመያዝ መብት ለማስከበር ያደረገችውን እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ፣ እንዲሁም እንደእናት ልጇን ለመርዳት የከፈለችውን መስዋዕትነትና የገጠሟትን ተስፋ አስቆራጭ የህይወት ምስቅልቅሎች የተወጣችበትን ጥንካሬ በልብ አንጠልጣይ ትረካ ያካፈለችበት መጽሃፍ ነው።
ባለፈው ጁን 6 ቀን 20206 በአሜሪካ ሲያትል ከተማ በታላቅ ድምቀት የተመረቀው ይህ መጽሃፍ ብዙዎች እንደመሰከሩት በመላው አለም ላሉና ከኦቲዝም ጋር የሚኖር ልጅ ለሚያሳድጉ ሚሊዮኖች እናቶች የሚያሳልፉትን ውጣውረድ የሞላበት ህይወት የሚያሳይ መስተዋት ነው።
የህ “የማይናገረው ልዑል” መጽሐፍ፤ በቅርቡ በቀረቡ የሚዲያ ዘገባዎች የተነሳ በህብረተሰቡ ውስጥ በኦቲዝምና በወላጅነት ዙሪያ ትልቅ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ሰንብቷል።
በመጪው ቅዳሜ በሚካሄደው በዚህ ልዩ የመጽሃፍ ምረቃ መድረክ ላይ በርካታ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች፣ ታዋቂ የልዩ ፍላጎት ምሁራን፣ ወላጆች፣ በኢትዮጵያ በኦቲዝም ላይ የሚሰሩ ተቋማት መሪዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የጥበብ ሰዎችና ሚዲያዎች እንደሚታደሙበትም ታውቋል ።
በዕለቱ በልዩ ፍላጎትና በኦቲዝም ምልከታዎች፣ በወላጅነት ስነልቡና፣ በመጽሃፉ ፋይዳ፣ በአመለካከት ለውጥ እና ኦቲዝምን በመቀበል በኩል ያሉ ክፍተቶችን ጨምሮ የመጽሐፉን ልብ ሰቃይ አንቀጾችና ዲስኩሮች የማንበብ ስነ-ስርዓት እንዲሁም ጥልቅ የመጽሐፍ ምልከታ (Review) የሚቀርብበት ልዩ መርሃ-ግብር ተዘጋጅቷል።
የዕለቱ የመድረኩ ንጉስ ታዬ ወርቁ መርሃ ግብሩን በሙያዊ ብቃቱ ያሰናስለዋል።
ይህንን መርሃግብር ለመታደም ፍላጎቱ ላለው ማንኛውም ሰው መድረኩ ነጻና ክፍት መሆኑንም ደራሲዋና አርታኢው ተናግረዋል።
ለንባብ በሚጋብዝ ውበት የመጽሃፉን የውስጥ ገጽ አቀማመጥና አጠቃላይ የዲዛይን ስራውን ወጣት ዲዛይነር አክሊሉ ድልነሳ በጥበባዊ ብቃት ሰርቶታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) ሚዲያና ኮሙኒኬሽንስ፣ ድሬ ቲዩብ፣ አርትስ ቲቪ፣ ፋና ቴሌቪዠን፣ አራዳ ኤፍኤም እና በርካታ ሚዲያዎች የመርሃግብሩ የሚዲያ አጋሮች ሲሆኑ የኒያ ፋውንዴሽን ጆይ ኦቲዝም ማዕከል በዚህ መጽሃፍ ምረቃ መርሃግብር ላይ የክብር አባል ሆኖ እንደሚታደምም ታውቋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) «መደመር» መጽሐፍ በቻይንኛ ቋንቋ ሊተረጎም ነው
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) «መደመር» መጽሐፍ በቻይንኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በቅርቡ ለንባብ ሊበቃ ነው፡፡
በ2010 ዓ.ም የነበረውን ሀገራዊ ለውጥ ተከትሎ የኢትዮጵያ የነገ ጉዞ ፍኖተ ካርታ ሆኖ የተወለደውና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የተጻፈው የ«መደመር» መጽሐፍ የቻይንኛ ቋንቋ ትርጉም ሥራው በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
መደመር ባለፉት አሥርት ዓመታት ከአፍሪካ አህጉር ፈልቀው ወደ ዓለም መድረክ ከተሻገሩ ጥቂት ሀገር በቀል ፍልስፍናዎች መካከል ግንባር ቀደሙ ነው፡፡
አሁን ላይ የኢትዮጵያ ሀገር በቀል እሳቤ የሆነውን የመደመር ፍልስፍና በርካቶች በትኩረት የሚመለከቱት አጀንዳ እየሆነ መጥቷል፡፡
ቻይና የትርጉም ሥራውን እያጠናቀቀች ባለችበት በዚህ ወቅት መጽሐፉ ከዚህ ቀደም በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በእንግሊዝኛ ካለው ተደራሽነት በተጨማሪ በቅርቡ በዓረብኛ እና በፓኪስታን የኡርዱ ቋንቋዎች ተተርጉሞ በደማቅ ሁኔታ መመረቁ ይታወሳል።
አሁን ደግሞ በቢሊየኖች የሚነገርለትን የቻይናን መድረክ በይፋ ለመቀላቀል የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው፡፡
ይህ የ«መደመር» መጽሐፍ ወደ ቻይንኛ ቋንቋ መተርጎም እና አሁን ላይ ሀያል ከሆኑ ሀገራት መካከል የምትጠቀሰውን ቻይናን ትኩረት ማግኘቱ ከመጽሐፍ ትርጉም ሥራ ባለፈ በርካታ ስትራቴጂካዊ እና ፖለቲካዊ እንድምታዎችን ይዟል፡፡
እንደ ቻይና ዓይነት እጅግ የዳበረ፣ የረጅም ዘመን የፖለቲካ ፍልስፍና ታሪክ ያላት እና ከማኦ ዜዱንግ እስከ ዴንግ ዚያኦፒንግ አሁን ደግሞ እስከ ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ የዘለቀ የራሷ የርዕዮተ ዓለም መስመር ያላት ሀገር፣ "መደመር"ን ኦፊሴላዊ በሆነ መንገድ ወደ ራሷ ቋንቋ መተርጎሟ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪና ትኩረት ሳቢ ፍልስፍና ማበርከት መቻሏን ማረጋገጫ ነው።
ኢትዮጵያ ባለፉት ዘመናት ከውጭ የሚመጡ ርዕዮተ-ዓለሞችን (ካፒታሊዝም / ሶሻሊዝም) ስታስተናግድ የኖረችበትን የታሪክ ምዕራፍ በመቀየር የራሷን ሀገር በቀል ፍልስፍና ወደ ውጭ የምትልክ ሀገር ለመሆኗ ትልቅ ማሳያ እንደሆነም የብልጽግና ፓርቲ መረጃ አመልክቷል፡፡
መጽሐፉ አፍሪካን፣ መካከለኛው ምስራቅን (በአረብኛ)፣ ደቡብ እስያን (በኡርዱ) እና አሁን ደግሞ ምስራቅ እስያን (በቻይንኛ) ተደራሽ ማድረጉ ፍልስፍናው ከተወለደበት የኢትዮጵያ ምድር ተሻግሮ አህጉራትንና የተለያዩ ባህሎችን የማስተሳሰርና የማቀራረብ ትልቅ የዲፕሎማሲ አቅም እንዳለውም ማሳያ ነው።
FBC

Comments