Logo
Getu Temesgen
“የንባብ ከተማ” የተሰኘ የህጻናት ቲያትር በድምቀት ተመረቀ

‎​#ethiopia | የህፃናትን የንባብ ባህል ለማዳበር ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀው “የንባብ ከተማ” የተሰኘው አዲስ የህፃናት ቴአትር ዛሬ ረፋድ ላይ ለእይታ በቃ።

‎​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቲያትር ቤቶች አስተዳደር፣ የህጻናትን እና የወጣቶችን ጥበባዊ ተሰጥኦ ለማሳደግና ታሪክን ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማሸጋገር ዘመናዊ የቲያትር መድረኮችን በስፋት እየተጠቀመ ይገኛል።

‎የአዲስ አበባ ቲያትር ቤቶች አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተስፋገኘው ለገሠ እንደገለጹት፣ ከተማዋ ዘመናዊ የንባብና የመዝናኛ ቦታዎችን በመገንባት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሰራች ነው።

‎በዚህም መሰረት በቅርቡ ተመርቆ አገልግሎት እየሰጠ በሚገኘው እና ፍላሚንጎ አካባቢ በሚገኘው የህጻናት እና ወጣቶች ቲያትር ቤት ለህጻናት የተዘጋጀ አዲስ ቲያትር በይፋ መመረቁን ጠቅሰው፣ ይህንን መድረክ ለታለመለት አላማ ሙሉ ለሙሉ ለመጠቀም እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

‎​“የንባብ ከተማ” ቴአትር ከሚቀጥለው እሁድ ጀምሮ በቋሚነት ዘወትር እሁድ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ለታዳሚዎች እንደሚቀርብ ተገልጿል።

‎ለህፃናትና ለወላጆች ምቹ በሆነው በዚህ አዳራሽ፣ ከቴአትር በተጨማሪ ማራኪ ሙዚቃዎችና አስተማሪ የታሪክ መርሐግብሮች እንደሚኖሩት ተጠቁሟል።

‎ጌትነት ተመስገን
‎📷ከበደ መክብብ

‎#addisababa #theaterlife #culturalheritage #ethiopianarts #kidstheater #citydevelopment #performingarts #communityengagement

24 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.