33 mins. ago
ሀሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም ፓስፖርት ለማውጣት የሞከረው ኤርትራዊ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ እንደገለፀው ግለሰቡ ሀሰተኛ ሰነዶችን ተጠቅሞ ፓስፖርት ለማውጣት ሲሞክር መያዙን አስታውቋል።
ግለሰቡ ዳዊት ጎይቶም የተባለ ሲሆን በኦንላይን ያመለከተውን የፓስፖርት ጥያቄ ለማስፈጸም ሀሰተኛ ሰነዶችን በመያዝ ወደ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በመጣበት ወቅት በተፈጠረ ጥርጣሬ እና በተሰጠ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ውሏል።
የዞኑ ፖሊስ ባደረገው ማጣራት ተጠርጣሪው ከአዲስ አበባ የተሰጠ ሀሰተኛ የፋይዳ መታወቂያ፣ ከትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ የተሰጠ የ8ኛ ክፍል የትምህርት ሰነድ ኮፒ እንዲሁም ከአርባምንጭ ከተማ የተሰጡ ሀሰተኛ የቀበሌ መታወቂያና የወሳኝ ኩነት ሰነዶችን አዘጋጅቶ ሲጠቀም ተገኝቷል።
በተደረገው የማጣራት ስራ ግለሰቡ የቀድሞ የኤርትራ ባሕር ኃይል አባል እንደነበርና ከሠራዊቱ በመኮብለል በትግራይ ክልል በኩል ወደ አዲስ አበባ ገብቶ ይኖር እንደነበር ተረጋግጧል።በዚህም ፖሊስ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አውሎ የክስ መዝገቡን በማጣራት ላይ እንደሚገኝ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነትና ገፅታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥቆማ በመስጠትና በማስፈጸም ረገድ ላደረጉት ከፍተኛ ትብብር ለኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አመራሮችና ሠራተኞች ምስጋና አቅርቧል።
በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል

2 hours ago
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
በዛሬው እለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእጩነት የቀረቡትን የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላትን አጽድቋል።
ሹመት የምንዝናናበት ሳይሆን የምንፈጋበት፣ የምንሰራበት፣ ኢትዮጵያን ለማጽናት፣ ኢትዮጵያን ለማበልጸግ፣ ኢትዮጵያን ወደ ስልጣኔ ጉዞ ለማስኬድ ከፍተኛ ጥረት የሚደረግበት መስክና የሀገር ትልቅ አደራ ነው።
በሚቀጥሉት ዓመታት ኢትዮጵያ በውሳኔዋ ሉዓላዊ፣ በልዩነት ውስጥ የተሳሰረች፣ እሴት በመፍጠርና ጠብቆ በማቆየት ረገድ ምርታማ፣ ቀጣናዊና አህጉራዊ መልህቅ በመሆን የምትመራ፣ እንዲሁም ለቀጣዩ ትውልድ በምታሸጋግራቸው አቅሞች ጸንታ እንድትቀጥል ሰፊ ስራ ይጠበቃል።
የመደመር መንግሥት ይህንን እውን ለማድረግ ቁርጠኛ ነው!

ሁሉም ሚኒስትሮችና ሚኒስትር ዲኤታዎች ለአንድ አመት ያክል ከፍተኛ ሚስጥራዊ ክትትል ሲደረግባቸው እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ፡፡
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በዛሬው እለት ሹመታቸው የፀደቀላቸውን የሚኒስትሮች መመዘኛ አስመልክቶ ለምክርቤት አባላት ባደረጉት ንግግር ሁሉም ሚኒስትሮችና ሚኒስትር ዲኤታዎች ቢያንስ ላለፉት አንድ አመታት ከፍተኛ ሚስጥራዊ ክትትል ሲደረግባቸው እንደነበር አስታውቀዋል።
ሚኒስትሮች በሌብነት የተሳተፉ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረጉን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲደረግባቸው የቆየው ክትትልም በሀገር ውስጥና በውጪ ያላቸውን እንቅስቃሴ ያጠቃለለ ሲሆን ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ ከሚያገኙቸው ሀብታሞች ጋር በሙሉ የመረጃ ክትትል ይደረግ ነበር ብለዋል፡፡
በዚህም መሰረት በልዩ ትኩረት ግምገማዎች መደረጉን ገልፀው ሹም ሽር የተካሄደው ያለምክንያት እንዳልሆነም ጠቅሰዋል፡፡
ነገርግን አንድ ሚኒስትር ራሱ ሌባ ላይሆን ይችላል ሲሉ ገልፀው በከባቢው ያለውን ሌብነት የመቆጣጠርና ጥቆማ ሲሰጠው እንደ ግብዓት ወስዶ የመፈተሽ አንዱ ለተሿሚዎች መመዘኛ እንደነበር አንስተዋል።
ክትትል ብቻም ሳይሆን እያንዳንዱ ግለሰብ በሚጠረጠርበት ጉዳይ ለራሱ እንዲከላከል መገምገሙን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህም አንዳንዱ ወቀሳ ብቻ እና አንዳንዱ ደግሞ በቂ መረጃ ያልተገኘባቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ አንስተዋል።
ምንም አይነት የጥርጣሬ ዝንባሌ ያለባቸውን ግን የካቢኔ አባላት አላደረግናቸውም ሲሉ ተናግረዋል። በዚህ አግባብ ግምገማቸው ካለፈ በኋላም እስከ አንድ ወር ከሁለት ሳምንት ድረስ ስልጠና እና ተደጋጋሚ ፈተና እንደነበር ገልፀዋል።
በስፍራሽ ደመላሽ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

4 hours ago
አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ስንት ያገኛሉ ?
አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአርሰናል ቤት ለተጨማሪ አምስት አመታት ለመቆየት ውላቸውን አራዝመዋል።
ሚኬል አርቴታ በአርሰናል የሚያገኙት አመታዊ ክፍያ 29.5 ሚልዮን ዩሮ ሊደርስ እንደሚችል ተገልጿል።
አሰልጣኙ የጉርሻ ክፍያን ጨምሮ በወር 2.5 ሚልዮን ዩሮ እንደሚያገኙ ታይምስ ስፖርት ዘግቧል።
አርቴታ የሚያገኙት አመታዊ ክፍያ ፔፕ ጋርዲዮላ በማንችስተር ሲቲ ካገኙት 24.4 ሚልዮን ዩሮ የበለጠ ሆኗል።
ክፍያው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታን በአለም ከፍተኛ ክፍያ ከሚያገኙ አሰልጣኞች አንዱ አድርጓቸዋል።
@tikvahethsport kidusyoftahe በአርሰናል መቀጠሌ ክብር ነው “ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የዋና አሰልጣኛቸውን ሚኬል አርቴታ ውል ለቀጣዮቹ አምስት አመታት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል። “ በክለቡ በቀጣይ መቆየት መቻሌ ክብር ነው “ ሲሉ ከውል ማደሱ በኃላ የገለፁት አርቴታ “ ለአርሰናል ጥሩ ነገር ከሚፈለጉ ግለሰቦች ጋር በመቀጠሌ ክብር ይሰማኛል “ ብለዋል። አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ “ ይህ ሁነት ለኔ እና ለመላው ቤተሰብ…

Sponsored by
Surafel
4 hours ago
ተጨማሪ ሹመቶሽ ተሰጡ።
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የተለያዩ ተጨማሪ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡
በዚህም መሰረት ፡-
1) አቶ አደም ፋራህ በም/ጠ/ሚ ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ አስተባባሪ
2) አምባሳደር በትረ መንግስቱ የጠ/ሚ ፅ/ቤት ሃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር
3) ወ/ሮ እናትአለም መለሰ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር
4) አቶ ፍቃዱ ተሰማ የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia

6 hours ago
ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በድጋሜ የትምህርት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀረቡ ዕጩ ሚኒስትሮችን በዛሬው ዕለት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
በዚህም የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በኃላፊነታቸው ቀጥለዋል፡፡
ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከመስከረም 26 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የትምህርት ሚኒስትር በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
@tikvahuniversity

የሚኒስትሮች ሹመት ፀደቀ።
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቧቸው ዕጩ ሚኒስትሮች በሙሉ ድምጽ ፀድቀዋል።
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቧቸው ዕጩ ሚኒስትሮች በሙሉ ድምጽ ፀድቀዋል።
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
6 hours ago
የሚኒስትሮች ሹመት ፀደቀ።
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህ/ ተ/ም/ቤት ያቀረቧቸው ዕጩ ሚኒስትሮች በሙሉ ድምጽ ፀድቀዋል።
በዚህም መሰረት፦
1. አቶ ተመስገን ጥሩነህ - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
2. ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
3. አቶ አዲሱ አረጋ (ዶ/ር) - የግብርና ሚኒስትር
4. ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) - የገንዘብ ሚኒስትር
5. አቶ መሃመድ እድሪስ - የመከላከያ ሚኒስትር
6. ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) - የትምህርት ሚኒስትር
7. ወ/ሮ ሃና አርአያሥላሴ - የፍትሕ ሚኒስትር
8. ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
9. ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር) - የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
10. ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) - የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር
11. መቅደስ ዳባ (ዶ/ር) - የጤና ሚኒስትር
12. አቶ አወሉ አብዲ- የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
13. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ - የገቢዎች ሚኒስትር
14. አቶ በረከት ፍስሃጽዮን - የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር
15. ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ- የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር
16. ወ/ሮ ዓለምጸሃይ ጳውሎስ - የማዕድን ሚኒስትር
17. አቶ ሳዳት ነሻ - የሎጂስቲክስ ሚኒስትር
18. ወ/ሮ ሻዊት ሻንካ - የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
19. አቶ ሙሳ አደም - የሰላም ሚኒስትር
20. ወ/ሮ ፍሬሕይወት ታምሩ - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
21. መሃመድ አብዱራሃማን (ኢ/ር) - የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር
22. ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) - የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር
23. አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) - የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።

ላሊጋ የካርቫልን ዝውውር አስቁሟል !
ሄታፌ ስፔናዊውን የቀኝ መስመር ተሰላፊ ዳኒ ካርቫል ለማስፈረም መስማማታቸው ተገልፆ ነበር።
ይሁን እንጂ የክለቡ ፕሬዝዳንት የተጨዋቹ ዝውውር መቋረጡን በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።
ሄታፌ ለማስመዝገብ ያቀረበው የዳኒ ካርቫል ደሞዝ በፋይናንስ ኮሚቴው አመኔታ እንዳላገኘ ተነግሯል።
ክለቡ ለዳኒ ካርቫል አመታዊ 400ሺህ ዩሮ ደሞዝ ለማስመዝገብ መጠየቁ ተገልጿል።
ዳኒ ካርቫል በሪያል ማድሪድ ቤት 10 ሚልዮን አመታዊ ክፍያ ያገኝ የነበረ በመሆኑ ላሊጋው ሀሰተኛ ነው በሚል ውድቅ አድርጓል።
@tikvahethsport kidusyoftahe ዳኒ ካርቫል ወደ ሄታፌ ? ስፔናዊው የመስመር ተጨዋች ዳኒ ካርቫል ሄታፌን ለመቀላቀል በንግግር ላይ መሆኑ ተገልጿል። የላሊጋው ክለብ ሄታፌ ዳኒ ካርቫልን በነፃ ዝውውር ለማስፈረም እየሰራ መሆኑን አረጋግጧል። በሁለቱ ወገኖች መካከል ከስምምነት ባይደረስም ንግግሮች የተሻለ ደረጃ ላይ መሆናቸው ተዘግቧል። ዳኒ ካርቫል በዚህ ክረምት ሪያል ማድሪድን ከሀያ ሶስት አመታት በኋላ መልቀቁ አይዘነጋም።…

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ተካሂዷል
ለሚንስትርነት ስፍራው እጩዎች በጠ/ሚ አማካኝነት አቀርበዋል
👉አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
👉ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
👉ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) የገንዘብ ሚኒስትር
👉 ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በድጋሚ የትምህርት ሚኒስትር
👉 ወ/ሮ ሀና አርያስላሴ የፍትህ ሚኒስትር
👉አቶ መሀመድ እድሪስ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር
👉 አቶ አዲሱ አረጋ የግብርና ሚኒስትር
👉 ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር
👉 ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
👉 ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር
👉 ወ/ሮ ያስሚን ወሀብረቢ የንግድና ቀጠናዊ ስትትር ሚኒስትር
👉 ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ለባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር
👉 አቶ አወሉ አብዲ የስራና ክህሎት ሚኒስትር
👉 አቶ በረከት ፍስሃፅዮን የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር
👉 አቶ ሳዳት ነሻ የሎጅስቲክስ ሚኒስትር
👉 ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
👉 አቶ ሙሳ አደም የሰላም ሚኒስትር
👉 ፍሬህይወት ታምሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
👉ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ የገቢዎች ሚኒስትር ሆነው እንዲሾሙ በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል።

7 hours ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግሥት ካቢኔያቸውን በዛሬው ዕለት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባሉ ‼️
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስፈጻሚ አካላትን ስያሜ፣ አደረጃጀት፣ ሥልጣን እና ተግባር ለመወሰን የቀረበውን ረቂቅ አዋጅን በትናንትናው ዕለት በሙሉ ድምፅ ማፅደቁ ይታወሳል።
ረቂቅ አዋጁም አዋጅ ቁጥር 1440/2019 ዓ.ም ሆኖ ጸድቋል።
የማሻሻያው ዋና ዓላማ ተቋማት ሥራቸውን በግልጽ እንዲያውቁ፣ የጋራ እና የተናጠል ኃላፊነቶች እንዲለዩ እና የመንግሥት አፈጻጸም የበለጠ ቀልጣፋ እንዲሆን ነው።
ይህም በተቋማት መካከል የሚፈጠርን የሥራ መደራረብ በመቀነስ፣ ኃላፊነትን በመለየት እና ተጠያቂነትን በማጠናከር የመንግሥትን የማስፈጸም አቅም ያሳድጋል። የዚህ ለውጥ ዋና ተጠቃሚው ደግሞ ዜጎች ናቸው።
የተደራጀ ተቋም ማለት የተሻለ አገልግሎት፣ የተገለጸ ኃላፊነት ማለት የበለጠ ተጠያቂነት፣ በተሻለ ሁኔታ የሚመራ የሕዝብ ሀብት ማለት ደግሞ የበለጠ ውጤት ማለት ነው።
ማሻሻያው ባለፉት አምስት ዓመታት በአስፈጻሚ ተቋማት የታዩ ውስንነቶችን ለመቅረፍ ጠንካራ መሠረት እንደሚፈጥር ተገልጿል።
በአዋጁ መሠረት ከቁጥር አንፃር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች በነበሩበት 22 ሆነው መቀጠላቸው እና በሁለት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ላይ የስያሜ ለውጥ ሲደረግ፣ ሁለት ሚኒስቴሮች አንደ አዲስ ተቋቁመዋል።
Seledadotio

በብልሽት ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት መኖሩ ተገለፀ
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በአዲስ ዌስት ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ የትራንስፎርመር ብልሽት ምክንያት ዛሬ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም የኃይል አቅርቦት የተቋረጠባቸው እና የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፡፡
ከጠዋት 12፡00 - ቀኑ 8፡00
👉እህል በረንዳ፣ አማኑኤል ቤ/ክ ፊትለፊት፣ ሻንቅላ ወንዝ፣18 ማደያው ጋር፣ ፈጥኖ ደራሽ፣ ኮልፌ ኮምርሄንሲቭ ት/ቤት እና አካባቢው
👉 አማኑኤል ሆስፒታል ፊት ለፊት፣ ሰባተኛ፣ ድሬ ህንጻ ፊት ለፊት፣ ኮልፌ 18 ጤና ጣቢያ፣ ኮልፌ 18 ድልድዩ ድረስ፣ አውጉስታ፣ ወይራ ሰፈር፣ ወይራ ኮንዶሚኒየም፣ ሞቢል፣ ራሺያ ካምፕ የነበረው፣ ተዘንአ ሆስፒታል፣ ሙስና ሰፈር፣ ጦር ኃይሎች ጎልፍ ክለብና አካባቢው፣ እና አካባቢው
ከቀኑ 8፡00 - ምሽት 4፡00
👉አዲስ ዌስት ሰብስቴሽን፣ ኮልፌ መናፈሻ፣ ፊሊጶስ፣ ኮልፌ ጤና ጣቢያ በከፊል፣ ቀራንዮ መድኃኒዓለም ቤ/ክ፣ ቤተል ሆስፒታል፣ ቤተል ቢጫ ፎቅ፣ መስኪድ፣ ቤተል ፓስታ ቤት አካባቢ፣ ኮልፌ ወ.8 ፅህፈት ቤት እና አካባቢው፣

ከምሽት 4፡00 - ጠዋት 12፡00

ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ እስኪመለስ ድረስ በትእግስት እንድትጠብቁ በአክብሮት እናሳውቃለን።
የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ Photo

8 hours ago
«በደቡብ ጎንደር አምስት ሰዎች በፌዴራል ፖሊስ አባላት ተኩስ ቆሰሉ፤ የአንድ ታዳጊ ሕይወት አለፈ»
በደቡብ ጎንደር ዞን በእስቴ ወረዳ ጉቢቻ ቀበሌ የጉምሩክ ጥበቃ የሚያደርጉ የፌዴራል ፖሊስ አባላት በከፈቱት ተኩስ ንጹሃን ሰዎች መመታታቸው ተገለጸ።
የፌዴራል ፖሊስ አባላቱ «ኮንትሮባንድ እቃ ይዛለች» ባሏት አንድ ባጃጅ ላይ በከፈቱት ተኩስ ጥቃቱ መከሰሱ ተገልጿል።
በተከፈተው ተኩስ ወደ ስፖርት በመሄድ ላይ የነበረ አንድ ታዳጊ ወጣት ሕይወቱ ሲያልፍ፣ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት በማድረስ ላይ የነበሩ የእድሜ ባለጸጋን ጨምሮ አምስት ሰዎች በጽኑ ቆስለዋል።
ተጎጂዎቹ ምንም የማያውቁ ንጹሃን መሆናቸውንና በባጃጇ ተጭኖ የነበረውም እቃ ኮንትሮባንድ ሊባል የማይችል እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
@Yenetube Fikerassefa

9 hours ago
ወንድሜ ሞተብኝ
የእናቴ ልጅ ገና በወጣትነቱ ሞተብኝ
ወንድሜ ብርሃንዬ ምንም ሳይሆን ማታ ላይ ፀሎት ወደሚያደርግበት ክፍል ለፀሎት ገብቶ በዛው ሞተብን 🥹💔
በልጅነቱ ከተወለደ ጀምሮ ለደብረሊባኖስ ገዳም ተሰቶ በዛው ተምሮ ተምሮ በዛው አድጎ በዛው ሞተብኝ
ያለፉት 9 ቀኖች ለቤተሰባችን በጣም ከባድ ሀዘን ነበር .. እንደአይን ብሌናችን የምንሳሳለት ወንድማችን , ለሰው እንኳን ወንድማችን ነው ብለን ለማውራት የምንፈራለት የምንሳሳለት ወንድማችን አጣነው....
የደብረሊባኖስ ገዳም እና የእኛ ቤተሰብ ታሪክ የሚጀምረው እንደዚህ ነው ... አያቴ እናቴን በወለደች በ 20 ቀኗ ባለቤቷ ድንገት ሲሞትባት እናቴ ሶስት ወር ሲሆናት ለአያቷ ሰታት እሷ በ 17 አመቷ ወደ ደብረሊባኖስ ገዳም ሂዳ ምንና መንኩሳ ከ 60 አመት በላይ በቆብ ( በምንኩስና) ገዳሙን በፈታይነት እንዲሁም ሌሎች በገዳሙ ሴቶች ሊሰሩት የሚችሉትን እየሰራች እና ገዳሙን እያገለገለች ኑራ ነበር ... አባቴ ደሞ በደርግ ጊዜ በስራ ምክንያት የተለዩ ክፍለሀገራት ይሄድ ነበር እናቴንም ልጆቹንም ይዞ ነው ስሄድ እና እየሰራ ሲኖር የነበረው የኔ ታላላቆች የተለያየ ቦታ ነው የተወለዱት ይህ ወንድሜ በሰሜን ሸዋ ፍቼ ነው የተወለደው ከዛ በኃላ አባቴ ከልጆቹ አንድ ሰው ቤቤተክርስትያን እንዲያድግ ምኞቱ ስለነበረ ሁላችን ወደ ደብረሊባኖስ ገዳም አያቴ ጋር እየሄድን እና እየተቀመጥን ፊደል ቆጥረናል እኔም በዜማ መምህር በነበሩት በየንታ መርአዊ ወንበር ስር ተቀምጬ እስከ መዝሙረ ዳዊት ድረስ በግዕዝ ተምሬጨርሼ ነው ከዛ ወደዘመናዊ ትምህርት የገባሁት ...ወንድሜ ብርሃኑ ግን ከ አራት አመቱ ጀምሮ በገዳም ሊማር እንድሄደ በዛው እየቀጠለ እየቀጠለ እድሜውን ሙሉ ተምሯል , ከዚህ በታች ያለውን ስርአተ ፍትሀቱ ላይ አባቶች ካነበቡለት ከመሰከሩለት ከህይወት ታሪኩ ላይ ነው የወሰድኩትኝ ...
እድሜያቸው ለትምህርት በደረሰ ጊዜ ወደዚህ ታላቁ ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም መጥተው በመጀመሪያ ደረጃ የንባብ ትምህርታቸውን
ከመምህር አባ ኢያሱ አሰፋ ጉባኤ ቤት በመግባት በልዩ ኹኔታ መዝሙረ ዳዊቱን በቃል ጭምር አጠናቀው ተምረዋል፡፡
በመቀጠልም በዚሁ ገዳም ውስጥ ስመጥርና አንጋፋ ከኾኑት ከአለቃ መርዓዊ ሣህለ ሚካኤል ጉባኤ ቤት በመግባት ከውዳሴ ማርያም ዜማ ጀምረው ጾመ ድጓ እና ድጓ አጠናቀው
በሚገባ ተምረዋል፡፡ ከዚህም በኋላ ከታላቁ ሊቅ የተክሌ አቋቋም መምህር ከኾኑት ከየኔታ በትረ ማርያም ገ/መድኅን የተክሌ አቋቋምን በመምህርነት ደረጃ በሚገባ አጠናቀው ተምረዋል፤ የቅኔ ሰዋስው ትምህርትንም ከመምህራን ቀጽለዋል፡፡
ክቡር አጋፋሪ ብርሃኑ እነዚህን ሁሉ ትምህርቶች ተምረው ለዚህ ሁሉ ሊቅነት ምሁርነትና ተጠያቂነት ያበቃቸው የእናታቸው የወይዘሮ ፍሬሕይወት ታፈሰ በጎ ምኞት ቅን አመለካከትና
የከፈሉት ታላቅ የእናት መሥዋዕትነት የአያታቸው የእማሆይ ብዙነሽ ታሃለው ጥብቅ ክትትል፣ ጥረትና ጸሎት ሲኾን ክቡር አጋፋሪ ብርሃኑ የዜማ ትምህርታቸውን ተምረው ገብተው
በልጅነት ጎናቸው አርፋለሁ ሲሉ አያታቸው እማሆይ ብዙነሽ የመጣኸው ለትምህርት እንጅ ለመኝታ መች መጣህ? እያሉ ከገድል ቤቱ በንባብ ከቅኔ ማሕሌቱ አገልግሎት እንዳይለዩ
አድርገው ተከታትለው ስላስተማሯቸው ነው፡፡
በዚህ መልኩ በመንፈሳዊ አገልግሎት በክርስትና ሕይወት አምረውና አሸብርቀው ከአደጉ በኋላ በተለያዩ የሥራ ቦታዎች ላይ ተመድበው አገልግለዋል፡፡
ከሁለት ሺሕ እስከ ሁለት ሺሕ ዐሥር ዓመተ ምሕረት በቅኔ ማሕሌቱ በኩል በአጋፋሪነት ማዕርግ ተመድበው የቦታውን ይትበሃል ከታላላቆች የቦታው ሊቃውንት ከአለቃ መርዓዊ
ሣህለ ሚካኤል እና ከየኔታ በትረ ማርያም ገ/መድኅን በማጥናት ብሎም በእጃቸው ጭምር በመጻፍ ለቦታው የይትበሃሉ ተጠያቂ የሥርዐተ ማሕሌቱ መሪ በመኾን
ሥርዐቱን በመጠበቅና በማስጠበቅ ከሊቃውንቱ ጋር በመከባበርና በመፈቃቀር ረጅሙን ዓመት በሚገባ
· አገልግለዋል፡፡
ክቡር አጋፋሪ ብርሃኑ ከዐሥር ዓመት የአጋፋሪነት ማዕርግ አገልግሎት በኋላ በሌሎች ልዩ ልዩ ሥራዎች ላይ እያገለገሉ በቅኔ ማሕሌቱ በኩልም የማሕሌቱ ኮከብ የሊቃውንቱ ጌጥ
የዝማሜው ውበት ነበሩ ከዚህ የተነሳ ሊቃውንቱም አጋፋሪ ይዝመመው አጋፋሪ ይወርበው፣አጋፋሪ ያንብበው ይሏቸዋል፣ እርሳቸውም ቢቃኙ፤ቢዘሙ፤ቢወርቡ ቢያነብቡ የማይሰለቹ
አንደበተ ርቱዕ አንደበተ ቀልጣፋ ድንቅ፣ ታላቅ፣ ሊቅና ምሁር ነበሩ፡፡
ከሁሉ የበለጠ ጸጋና ስጦታም አላቸው ለተራበ የሚያበሉ ለተጠማ የሚያጠጡ ለታረዘ የሚያለብሱ ካዘነው ጋር አዝነው የሚያረጋጉ ከተደሰተውም ጋር የሚደሰቱ ርኅሩኅ ታማኝ ሰው ወዳጅ ወንድም ነበሩ፡፡ " ....
ወንድሜ ገና ልጅ ነው እድሜው ከ 39 ወደአርባ እየሄደ ነበር ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ወቶ እዚህ አዲስ አበባ የተለያዩ አድባራት እንዲሁ በአሜሪካ ያሉ አድባራት ላይ እንዲያገለግል የተለያዩ እድሎች መተውለት ቢጠየቅም በተደጋጋሚ አልፈልግም ገዳሙን ትቼ አልወጣም በማለት ኑሯል እኛ ፕሮግራም እንኳን ኑሮን አዲስ አበባ ከመጣ አንድ ቀን ብቻ አድሮ ነው የሚሄደው ከገዳሙ መለየት በፍፁም አይፈልግም ነበር .. ወንድሜ በድንግልና የኖረ መናኝ ነበር በሚቀጥሉት አመታቶች ላይ መንኩሶ ዻዻስ የሚሆን እና እረጅም አመት ኑሮ እኛን እህት እና ወንድሞቹን ሁሉ ቀብራችንን አሳምሮ ከዛ በኃላ ይሞታል ብዬ የማስበው ወንድሜ ሰስቼው ለሰው የማላወራው ወንድሜ አንደተለመደው የቀን ውሎውን በሰላም ውሎ ሁሌ ከመተኛቱ በፊት እንደሚያደርገው ሊፀልይ ወደ ፀሎት ክፍሉ እንደገባ ሞተብኝ 💔 ሳላስታምመው ምንህን ነው ወንድሜ ሳልለው በቃ እንዲሁ ቀረብኝ 🥹💔
በጣም እረጅሙ ቆንጆው ባለግርማ ሞገሱ የእግዚአብሔር አገልጋይ የእግዚአብሔር ባሪያ .. ያ እኔ እንዲሆንልኝ እንዲሳካልኝ የሚፀልይልኝ ወንድሜን ጨክኜ ቀብርኩት

11 hours ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የሊቢያ ቤንጋዚ አስተዳደር 100 ኢትዮጵያዊያንን ከአገር ማባረሩን አስታወቀ፡፡ የምስራቃዊ ሊቢያ ቤንጋዚ ባለስልጣናት በትላንትናው እለት 100 ያህል ኢትዮጵያዊያንን ማባረራቸውን አስታወቁ፡፡ የአገሪቱ ህገ ወጥ ስደትን የመከላከል ዳይሬክተር የታላቋ ቤንጋዚ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያዊያኑ የተባረሩት አስፈላጊውን ህጋዊ ሂደት ካጠናቀቁ በኋላ መሆኑን አስረድቷል፡፡
ይህ እርምጃ የተወሰደውም የዳይሬክሩ ሀላፊ ሜጀር ጄኔራል ሳላህ መሀመድ አል ካፊፊ ባወጡት መመሪያ መሰረት በሊቢያ የባህር ጠረፍ በኩል የሚደረገውን ህገ ወጥ ስደት ለመከላከል እንደሆነ አስታውቋል፡፡ በቀጣይነትም በቤንጋዚ ውስጥ ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውን ስደተኞች የመለየት ስራው እንደሚቀጥልና ሰነድ የሌላቸውን የማሰርና ከአገር የማባረር ዘመቻው እንደሚቀጥልም አስረድቷል፡፡
መግለጫው እነዚህን 100 ኢትዮጵያዊያን ከአገር ለማባረር የተጠቀመበትን መንገድ ወይንም መዳረሻቸው የት እንደሆነ ያለው ነገር የለም፡፡ ይህ መግለጫ የተሰጠው የምስራቃዊ ሊቢያ መንግስት የተለያዩ አገራት ዜጎች የሆኑ 258 ህገ ወጥ ስደተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ካስታወቀ ከቀናት በኋላ ነው፡፡

16 hours ago
በዩኒቨርሲቲዎች ስር ለሚተዳደሩ ማስተማሪያ ሆስፒታሎች የሚመደበው የሕክምና አገልግሎት በጀት ከመደበኛው የትምህርት በጀት ስሌት ቀመር ውጪ በተናጠል ተጣርቶ የበጀት ድጋፍ እንዲቀርበለት የሚያዘው ደንብ በስራ ላይ ውሏል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ከመንግሥት የሚሰጠውን የብሎክ ግራንት የበጀት አፈጻጸም ለመደንገግ ያወጣው ደንብ ቁጥር 594/2018 በስራ ላይ ውሏል።
ደንቡ ተቋማቱ በፋይናንስ ራሳቸውን እስኪችሉ ድረስ በሂደት እየቀነሰ የሚሄድ ዓመታዊ የበጀት ድጋፍ የሚመደብበትን ሥርዓት ያካተተ ሲሆን፣ ዩኒቨርሲቲዎቹ ከተጨባጭ ነባራዊ ሁኔታዎቻቸውና ስትራቴጂካዊ ዕቅዶቻቸው በመነሳት በበጀታቸው በነፃነት እንዲጠቀሙና ተልዕኳቸውን በጥራት እንዲወጡ ማስቻልን ዓላማ ያደረገ መሆኑን ያስረዳል።
ደንቡ ለራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደበው ዓመታዊ የብሎክ ግራንት እንደ አግባብነቱ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሲባል፣ የመግቢያ መስፈርቱን አሟልተው ነገር ግን የትምህርት ወጪያቸውን መሸፈን ለማይችሉ ተማሪዎች የሚደረግ የበጀት ድጋፍ ሊያካትት እንደሚችል ያስረዳል።
በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲዎች በሚያስተዳድሯቸው ማስተማሪያ ሆስፒታሎች አማካኝነት፣ በሕግ አግባብ በነፃ ሊሰጡ ለሚገባቸው የሕክምና አገልግሎቶች እና በነፃ ማግኘት ለሚገባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚውል የበጀት ድጋፍ እንዲያገኙ ለማስቻልም ሊመደብ እንዲሚችል ይገልጻል።
እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎች የሚያከናውኗቸውን የምርምርና ጥናት፣ የማኅበረሰብ ጉድኝት አገልግሎት እንዲሁም ብቁ ተቋማዊ አቅምን ለመገንባት የሚያስፈልግ የፋይናንስ ድጋፍ ሊመደብ እንደሚችል ተደንግጓል።
በዚህ ደንብ መሠረት አጠቃላይ የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የበጀት ድልድል የግብዓት፣ የውጤትና የፍትሐዊነት መስፍርቶችን መሰረት የሚያደርግ ሲሆን ይህም
• የመማር-ማስተማር ሂደቱን መደበኛ ተማሪዎች ቁጥር፣
• የሳይንሳዊ ምርምር ውጤትና ተፅዕኖን፣
• የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎችን እንዲሁም
• ልዩ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎችን እና የተቋማቱን መልክዓ-ምድራዊ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ታሳቢ ያደርጋል።
ይህ የበጀት ማከፋፈያ ቀመር እንደ አስፈላጊነቱ በገንዘብ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር ትብብር የሚዘጋጅ ሲሆን፣ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ለማጣጣም በየሁለት ዓመቱ ክለሳ ይደረግበታል።
በተለየ መልኩ፣ በዩኒቨርሲቲዎች ስር ለሚተዳደሩ ማስተማሪያ ሆስፒታሎች የሚመደበው የሕክምና አገልግሎት በጀት ከመደበኛው የትምህርት በጀት ስሌት ቀመር ውጪ በተናጠል ተጣርቶ የበጀት ድጋፍ እንደሚደረግለት ተደንግጓል።
ይህ ድጋፍ ሆስፒታሎቹ በሕግ አግባብ በነፃ ሊሰጡ ለሚገባቸው የሕክምና አገልግሎቶችና ተጠቃሚ ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚውል ሲሆን፤ ድልድሉም በሆስፒታሉ አገልግሎት ያገኙ ታካሚዎች ብዛት፣ የህክምና አልጋዎች ቁጥር፣ የአገልግሎቶቹ ውስብስብነት እንዲሁም ለመድኃኒትና ለአላቂ የሕክምና ቁሳቁሶች የሚወጣውን ወጪ መሠረት በማድረግ ይወሰናል።
በዚህም ማንኛውም ራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ የሚያገኘው ዓመታዊ ድጋፍ አጠቃላይ የመማር-ማስተማርና የምርምር በጀቱን እንዲሁም ለማስተማሪያ ሆስፒታሎች በጥናት ላይ ተመስርቶ የሚመደበውን ልዩ በጀት በአንድ ላይ ያካተተ የተቀናጀ የብሎክ ግራንት ሆኖ ይቀርባል።
የበጀት ጥያቄ አቀራረብና አስተዳደርን በተመለከተ፣ ማንኛውም ራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ የበጀት ጥያቄውን በየዓመቱ እስከ የካቲት ወር መጨረሻ ድረስ ለገንዘብ ሚኒስቴር ማቅረብ እንዳለበት እና የተፈቀደው በጀትም በቀጥታ ወደ ተቋማቱ ፈሰስ እንደሚደረግ ተመላክቷል።
የቁጥጥር ሥርዓቱን ለማጠናከርም ትምህርት ሚኒስቴር በቁልፍ ውጤት አመላካቾች ላይ የተመሠረተ የአፈጻጸም ውል በመፈራረም በዓመት ሁለት ጊዜ ሁለንተናዊ ግምገማ እንደሚያካሂድ ተደንግጓል።
በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲዎቹ የብሎክ ግራንት ሒሳብ በፌደራል ዋና ኦዲተር እንደሚመረመርና የሒሳብ ሰነዶችም ቢያንስ ለአስር ዓመታት ተጠብቀው እንዲቆዩ በማድረግ ተጠያቂነትና ግልጽነት እንዲሰፍን ይደረጋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም

“የባሕር በር ጉዳይ ብሔራዊ አጀንዳችን ነው” - የምክር ቤት አባላት
*******************
የባሕር በር ጉዳይ የግለሰብ ወይም የፓርቲ አጀንዳ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሀገራዊ አጀንዳ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገለጹ።
ጉዳዩ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ እንዲሁም የሀገራችንን ልማትና ሥልጣኔ ከማስቀጠል ጋር በቀጥታ የተያያዘ መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
በሰጥቶ መቀበል መርህ በሰላማዊ መንገድ የባሕር በር ለማግኘት እየተሠራ መሆኑን ጠቁመው፣ ይህ ብሔራዊ አጀንዳ እንዲሳካ ኢትዮጵያውያን ሁላችንም በአንድነት መቆም አለብን ብለዋል።
ብሔራዊ ጥቅምን ማስቀደም፣ አንድነትን ማጠናከርና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መቆም ወቅቱ የሚጠይቀው ዋነኛ ሀገራዊ ኃላፊነት መሆኑንም አባላቱ ገልጸዋል።
የፖለቲካ ፉክክርና አብሮ መሥራት ሚዛኑን ጠብቆ ለሀገር ጥቅም እንዲውል ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባም ጠቁመዋል።
“ሁላችንም ሀገራችንን ማስቀደም መቻል አለብን” ያሉት አባላቱ፣ የተጀመረው አዲስ የፖለቲካ ባህል ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና አብሮ መሥራት እንደሚገባ አመላክተዋል።
በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ልዩነት ካለም በግጭት ሳይሆን በምክክር መፍታት እንደሚገባ የገለጹት አባላቱ፣ የሕዝብን ሰላም ማረጋገጥ ለሀገር ልማትና ዕድገት መሠረት መሆኑን አክለዋል።
በተጨማሪም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ጨምሮ የዲጂታላይዜሽን ሪፎርሞች አገልግሎት አሰጣጥን ከማሳለጥ ባለፈ ብልሹ አሠራርና ሌብነትን ለመቀነስ የሚያግዙ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የተጠያቂነት ሥርዓትን ማስፈን፣ መንግሥታዊ አገልግሎትን ከብልሹ አሠራር ማጽዳትና መልካም አስተዳደርን በአስተሳሰብ እና በተግባር ጭምር ማስረጽ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ሀገራዊ አንድነት፣ ሰላም፣ ምርታማነትና ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ በጋራ መሥራትን የሚጠይቁ ዋነኛ ሀገራዊ አጀንዳዎች መሆናቸውን በማንሳት፣ የባሕር በር አጀንዳም በዚሁ አግባብ በትብብር ሊሠራበት የሚገባ የሁሉም ዜጎች የጋራ አጀንዳ መሆኑን ገልጸዋል።
በኢንቲሃድ አብራር
#ethiopia #seaaccess #nationalinterest #nationalunity #peace #accountability #ebc

17 hours ago
የ2026 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ (2026 African Impact Award)
የክብር ምሽትን አብረው ለማሳለፍ ይፈልጋሉ?
በዝግጅቱ ላይ የእራት ግብዣ፣ የሙዚቃ ዝግጅት፣ የክብር ዘበኞች ትርኢት እና የዋናው ዝግጅት ተሻጋሪ ለውጥ ያመጡና ተፅዕኖ የፈጠሩ ተሸላሚዎች ዕውቅና አሰጣጥ ይከናወናል።
የተዘጋጁት የትኬት ቁጥሮች ውስን ሲሆኑ፤ ከሽያጩ የሚገኘው ገቢ በሙሉ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ድጋፍ ይውላል።
የ2026 የሽልማቱ ተቀባዮች፦
ፕሮፌሰር ዶናልድ ጆሃንሰን (Prof. Donald Johanson) — ታዋቂው የፓሊዮአንትሮፖሎጂስት እና የ"ሉሲ" (ድንቅነሽ) ግኝት ባለቤት
ፖል ቴርጋት (Paul Tergat) — የረጅም ርቀት ሩጫ አትሌት እና የቀድሞ የዓለም ማራቶን ሪኮርድ ባለቤት
እዮብ "ጆ" ማሞ (Eyob "Joe" Mamo) — ስኬታማ የንግድ ባለቤት እና ሥራ ፈጣሪ
አለምፀሐይ ወዳጆ (Alemtsehay Wedajo) — በኪነ-ጥበብ፣ ባህል እና በበጎ አድራጎት ዘርፍ የጎላ አስተዋጽኦ ያበረከቱ
ማክዳ አሰፋ (Makda Assefa) — የፈር ቀዳጅ ሚዲያ መሪ
ቀን፦ እሁድ፣ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም (October 11, 2026)
ሰዓት፦ ከምሽቱ 11:30 (5:30 PM)
ቦታ፦ ሜትሮ ፖይንትስ ሆቴል (Metro Points Hotel)፣ ሜሪላንድ - 8500 Annapolis Road, New Carrollton, MD 20784.
For tickets, Google: 2026 African Impact Award

18 hours ago
የአቦቦ ወረዳ ፖሊስ በአደረገው ክትትል የጂን አልኮል መጠጦች ተያዘ
በጋምቤላ ክልል በአኙዋሃ ብሔረሰብ ዞን በአቦቦ ወረዳ የተከለከለ የአልኮል መጠጥ ይዘው የሚዘዋወሩ ግለሰቦችን ለመቆጣጠር የወረዳው ፖሊስ በአደረገው ክትትል 180 የጂን አልኮል መጠጦች ተይዘው እንዲወገዱ ተደርጓል።
የአልኮል መጠጦችን በሚያዘዋዉሩ ግለሠቦች ላይ ወረዳው ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርግና እርምጃ እንደሚወስድ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ኡሞድ ኡጌራ ገልፀዋል።
የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ኡሞድ ኡጌራ በተጨማሪ እንደገለጹት አልኮል ለጤና ጠንቅ በመሆኑ ህብረተሠቡ ይሄን የአልኮል ዝውውር ተግባር የሚያከናውኑ ግለሰቦች ሲያጋጥሟቸው ለወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

19 hours ago
#ችሎት
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በማጽናት በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የኢህአፓ አባላት የዋስትና መብት እንዲከበር ብያኔ ሰጠ።
በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የኢህአፓ አባላት የዋስትና ጉዳይ በዳኞች ፈረቃ መቀያየርና መዝገብ ባለመቅረቡ ምክንያት በተደጋጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሲሰጥበት መቆየቱ ይታወሳል።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት የዋስትና ውሳኔ ሊጸና ይገባል ወይስ አይገባም፤ እንዲሁም ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም የሚለውን ለመመርመር የፌደራል ፖሊስ ያደራጀውን የምርመራ መዝገብ አስቀርቦ ሲመለከት ቆይቷል።
ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት፣ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ አጽንቷል።
በዚህም መሠረት በሽብር ተግባር ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ይስሓቅ ወልዳይ፣ አቶ አበበ አካሉ እና ጠበቃ አቶ አበራ ንጉሥ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከእስር እንዲፈቱ ብያኔ መሰጠቱን ጠበቃቸው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት፣ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት፣ ፖሊስ የፎረንሲክ ውጤቶችን ለመጠበቅና ተጨማሪ ምስክሮችን ለመስማት በሚል የጠየቀውን የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ውድቅ በማድረግ ተጠርጣሪዎቹ እያንዳንዳቸው በ50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ውሳኔ መስጠቱ ይታወሳል።
የፌዴራል ፖሊስ የተሰጠውን የፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ማለቱን ተከትሎ ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸውን እስከዛሬ መስከረም 27/2019 ዓም ድረስ በእስር ላይ ሆነው ሲከታተሉ ቆይተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #ችሎት በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የኢሕአፓ አባላት የዋስትና ጉዳይ ዛሬም ውሳኔ ሳያገኝ ለአርብ ተቀጠረ። የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት የሰጠው የዋስትና ውሳኔ ሊጸና ይገባል ወይስ አይገባም? እንዲሁም ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም? የሚሉትን ነጥቦች ለመመልከት የፌደራል ፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንዲቀርብለት ማዘዙ ይታወሳል። ይሁን…

20 hours ago
ጃፓን ለየመን እና ለጅቡቲ የ10 ሚሊዮን ዶላር የድንገተኛ ጊዜ እርዳታ ለመስጠት ወሰነች
የጦርነቱ ተፅዕኖ ወደ ጎረቤት ሀገራት መዛመቱን እና በየመን እየከፋ የመጣውን የሰብአዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ጃፓን ለየመን እና ለጅቡቲ የ10 ሚሊዮን ዶላር የድንገተኛ ጊዜ እርዳታ እንደምትሰጥ አስታውቃለች።
የጃፓን መንግስት እርዳታውን ማክሰኞ ዕለት ማጽደቁን የሀገሪቱ ኤምባሲ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልጿል።እርዳታው የባብ አል-መንደብ ወሽመጥ ዙሪያን ጨምሮ በመካከለኛው ምስራቅ ሰላምና መረጋጋትን ለመደገፍ አልሞ የተዘጋጀ መሆኑም ተነግሯል።
የጃፓን መንግስት ይህ የባህር ወሽመጥ በኢነርጂ ደህንነት ረገድ ለጃፓንም ሆነ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ “እጅግ ከፍተኛ አስፈላጊነት” ያለው መሆኑን ገልጿል።
በዚህም መሰረት የመን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም ፣ በዓለም አቀፉ የሬድ ክሮስ ኮሚቴ እና በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በኩል 8 ሚሊዮን ዶላር የምታገኝ ሲሆን፣ ጅቡቲ ደግሞ በተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ በኩል 2 ሚሊዮን ዶላር ይደርሳታል ተብሏል ።
በሚኪያስ ጸሐዬ

የአፍሪካ ዋንጫ ውዝግብ፡ ሴኔጋል ይግባኙን ነገ በCAS ታቀርባለች
#ethiopia | የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ዋንጫ የማን ነው? የሚለው ክርክር ነገ ወደ ዓለም አቀፉ የስፖርት ዳኝነት ፍርድ ቤት (CAS) ይመራል።
የሴኔጋል እና የሞሮኮ የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ ያስከተለው ውዝግብ እስካሁን መፍትሄ አላገኘም። ሴኔጋል በጨዋታ ሜዳ 1ለ0 አሸንፋ ዋንጫውን ከፍ ካደረገች በኋላ፣ ካፍ በኋላ የወሰደው ውሳኔ ውጤቱን ቀይሮ ሞሮኮን 3ለ0 አሸናፊ እንድትሆን አድርጓል።
ክርክሩ እንዴት ተጀመረ?
በጥር 18 ቀን 2026 በራባት በሚገኘው ፕሪንስ ሙላይ አብደላ ስታዲየም የተደረገው ፍጻሜ ለ90 ደቂቃዎች 0ለ0 ተጠናቀቀ። በመደበኛ የጨዋታ ጊዜ መጨረሻ ላይ ለሞሮኮ የተሰጠውን የፍጹም ቅጣት ምት በመቃወም የሴኔጋል ተጫዋቾች ሜዳውን ለቀው ወጥተው ጨዋታው ለተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ ነበር። ተጫዋቾቹ ወደ ሜዳ ከተመለሱ በኋላ ጨዋታው ቀጥሎ የተሰጠው የፍጹም ቅጣት ምት በኤድዋርድ ሜንዲ ተመናፍሷል።
በተጨማሪ ጊዜ ላይ የሴኔጋሉ አማካይ ፓፔ ጉዬ ያስቆጠራት ጎል ሴኔጋልን 1ለ0 አሸናፊ አድርጋ፣ አገሪቱም ለሁለተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን እንድታሸንፍ አድርጓታል።
ካፍ በኋላ የወሰደው ውሳኔ
ከጨዋታው በኋላ ሞሮኮ ቅሬታ አቀረበች። በመጋቢት 17 ቀን 2026 የCAF Appeal Board የሴኔጋል ቡድን በጨዋታው የመልቀቅ ድርጊት የAFCON ደንቦችን እንደጣሰ በመወሰን ሴኔጋል ጨዋታውን በፎርፌ እንደተሸነፈች አውጇል። በዚህም ውጤቱ 3ለ0 ለሞሮኮ እንዲመዘገብ ወስኗል።
ይህ ውሳኔ ሴኔጋል በሜዳ ላይ በ1ለ0 ያሸነፈችውን ጨዋታ በማስቀረት ሞሮኮን የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ አድርጓታል።
ሴኔጋል ጉዳዩን ወደ CAS ወሰደች
የሴኔጋል የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የካፍን ውሳኔ በመቃወም ወደ Court of Arbitration for Sport (CAS) ይግባኝ አቀረበች። CAS ይግባኙን በመጋቢት 25 ቀን 2026 መመዝገቡን አረጋግጧል። ሴኔጋል የካፍን ውሳኔ እንዲሻር እና የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ እንደሆነች እንዲወሰን ጠይቃለች።
የCAS ችሎት ነገ
CAS የሴኔጋልን ይግባኝ ሐሙስ፣ ጥቅምት 8 ቀን 2026 በላውዛን፣ ስዊዘርላንድ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ ያዳምጣል። ችሎቱ ከጠዋቱ 9፡30 ላይ እንደሚጀምር እና ከሰዓት በኋላ ሊቀጥል እንደሚችል ተገልጿል። ችሎቱም በዝግ ይካሄዳል፤ ሚዲያዎች በችሎቱ ውስጥ እንዲገኙ አይፈቀድላቸውም።
በጉዳዩ ላይ የሚወስነው የCAS ፓነል በፕሮፌሰር Gérald Simon የሚመራ ሲሆን፣ ፕሮፌሰር Luigi Fumagalli እና ፕሮፌሰር ዶ/ር Ulrich Haas አባላት ናቸው። የሂደቱ ቋንቋም ፈረንሳይኛ እንዲሆን ተስማምተዋል።
ውሳኔው ነገ ይፋ ይሆናል?
አይሆንም። CAS በግልጽ እንዳስታወቀው ችሎቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የዳኞች ውይይት ይጀምራል፤ ነገር ግን የመጨረሻ ውሳኔ በጥቅምት 8 ቀን እንደማይሰጥ ተገልጿል። የውሳኔው ቀንም እስካሁን አልተወሰነም።
በመሆኑም የነገው ችሎት የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ዋንጫ በሴኔጋል ወይስ በሞሮኮ እንደሚቀር ለመወሰን ወደ መጨረሻው የሚያቀርብ ወሳኝ ሕጋዊ ሂደት ነው።
አንተነህ ብርሃኔ

22 hours ago
የፖለቲካ አለመረጋጋትን ተከተሎ ሄይቲ ምርጫዋን አራዘመች
የምርጫ ኮሚሽኑ የዕጩዎች ምዝገባ ጊዜን እስከ ጥቅምት 21 ቀን ድረስ ያራዘመ ሲሆን የተሻሻለ የብሔራዊ ምርጫ መርሃ ግብር በማዘጋጀት ላይ ይገኛል።
በሄይቲ ቀጣይነት ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋት በመከሰቱ ምክኒያት ሀገሪቱ ልታካሂደው ያቀደችውን ምርጫ ማራዘሟን አስታውቃለች።የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን የተሻሻለ ብሔራዊ የምርጫ መርሃ ግብር በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ጊዜያዊ የምርጫ ኮሚሽኑ ሰኞ ዕለት ባወጣው መግለጫ ከፖለቲካ ተዋንያን ጋር ከተደረጉ ውይይቶች በኋላ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰኔ 2 ቀን 2026 የወጣውን የምርጫ አዋጅ ለማሻሻል ጥቅምት 5 ቀን 2026 የፀደቀውን ድንጋጌ በማስመልከት፣ የተወሰኑ የምርጫ ሂደት መርሃ ግብሮች እንዲቀየሩ ተደርጓል ብሏል።
ኮሚሽኑ አክሎም የምርጫ ቅስቀሳው ጊዜ የታገደ መሆኑን ገልጾ ከተፈቀደላቸው የፖለቲካ አካላት ጋር የተሻሻለ የምርጫ ማዕቀፍን አዘጋጅቶ ሲያጠናቅቅ አዳዲስ ቀናትን ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።የፖለቲካ ፓርቲዎችን ለማስተናገድ ሲባል ኮሚሽኑ የዕጩዎች የኦንላይን ምዝገባዎች እንዲቀጥሉ አሳስቧል።
ፕሬዝዳንትን ፣ የምክር ቤት፣ የክፍለ ሀገር እና የከተማ አስተዳደር አባላትን ለመምረጥ ታስቦ የነበረው ጠቅላላ ምርጫ ታህሳስ 13 ይካሄዳል ተብሎ ታቅዶ ነበር። ሀገሪቱ ከ2016 ጀምሮ ምንም አይነት ጠቅላላ ምርጫ ስላላካሄደች በህዝብ የተመረጡ ብሔራዊ ባለስልጣናት የሏትም።
እ.ኤ.አ. ሀምሌ 2021 የፕሬዝዳንት ጆቨኔል ሞይስ መገደልን እና የህግ መውጫ ዘመናት መጠናቀቅን ተከተሎ ሄይቲ ወደ ከፋ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ገብታለች። በአሁኑ ወቅት ይህችን የካሪቢያን ሀገር እ.ኤ.አ. በ2024 የተዋቀረ ጊዜያዊ የፖለቲካ ስርዓት እየመራት ይገኛል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አሬል ሄንሪ በታጣቂዎች ጫና ስልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ የተዋቀረው ጊዜያዊ የፕሬዝዳንት ምክር ቤት፣ በሹመት ወደ ስልጣን በመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር አሊክስ ዲዲየር ፊልስ-አይሜ ከሚመራውና በአዋጅ ከሚያስተዳድረው የካቢኔ አካል ጋር በመሆን ሀገሪቱን እያስተዳደሩ ይገኛሉ።
ስላማዊ ነጋሲ
#ዳጉ_ጆርናል Photo

23 hours ago
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የጥራት ጉድለት በታየባቸው ሰባት የመድኃኒት ምርቶች ላይ ማሳሰቢያ አወጣ
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የጥራት ጉድለት በታየባቸው እና ከገበያ እንዲሰበሰቡ በተወሰነባቸው ሰባት የመድኃኒት አይነቶች ላይ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።
ባለስልጣኑ ይህንን ማስጠንቀቂያ ያወጣው የኬንያ የመድኃኒት ተቆጣጣሪ አካል በሀገሪቱ በገበያ ላይ በተገኙ የተወሰኑ ምርቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን መነሻ በማድረግ ነው።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመድኃኒት ጥራት እና ደህንነት ክትትል ክፍል አማካሪ ዶ/ር ኤልሳቤት ወልደማርያም እንደተናገሩት ኢትዮጵያ እና ኬንያ ሰፊ ድንበር የሚጋሩ በመሆናቸው እነዚህ ምርቶች ወደ ኢትዮጵያ የመግባት ዕድል አላቸው።
በተለያዩ የጥራት እና የደህንነት ጉድለቶች ምክንያት ከገበያ እንዲሰበሰቡ ከተደረጉት ሰባት የመድኃኒት አይነቶች መካከል በህንድ የተለያዩ የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች የተመረቱት
👉ፍላዛርት ሽሮፕ
👉ሄፓካል 25000
👉ቱናክላቭ እና ክላክሲ 1.2 ግራም የተባሉ የመድኃኒት አይነቶች ይገኙበታል።
በተጨማሪም በቻይና ኩባንያ የተመረተው ሜታሚድ መርፌ እና በኬንያ አምራች የተመረተው ክሎክሳም ሽሮፕም ከተሰበሰቡት የመድኃኒት አይነቶች ውስጥ እንደሚገኙበት ተገልጿል።
በዚህም የክልል ተቆጣጣሪ አካላት የእነዚህን ምርቶች ስርጭት እና አጠቃቀም በቅርበት እንዲከታተሉ ያሳሰበው ባለስልጣኑ ህብረተሰቡም ምርቶቹ በእጁ የሚገኙ ከሆነ እንዳይጠቀምባቸው ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
በፋሲል አረጋይ

የኢትዮጵያን የውጪ ግንኙነት ከተቀባይነት ወደ ተጽዕኖ ፈጣሪነት የሚያሻግር እና የደመኝነት እይታ ያላቸውን የሚመክር ስራ እንደሚሰራ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ ተናገሩ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ፕሬዝዳንቱ ይህን የተናገሩት የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት እና የፌዴሬሽን ምክርቤት 7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።
በንግግራቸውም የ2019 ዓ.ምን ዋና ዋና ትኩረቶች የዘረዘሩ ሲሆን በአንደኛነት ሰላም ለኢትዮጵያ እድገትና ግስጋሴ ያለውን ዋጋ ያጠና እና ከማንኛውም ጊዜ በላይ ህብረትን፣ ትብብርንና ኢትዮጵያን የሚያስቀድም ተግባር እንደሚከናወን አስታውቀዋል።
ጥራትን መሰረት ያደረገ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ሽግግርም የሚደረግ ሲሆን ትምህርት፣ ጤናና ማህበራዊ ጥበቃን ከስፋት ወደ ጥራት በማሸጋገር ዜጋን ማእከሉ ያደረገ ልማት እንደሚፋጠንም አረጋግጠዋል።
ለእድገታችን ቁልፍ ፋይዳ ባላቸው የኢንዱስትሪና የግብርና ግብአቶች እንዲሁም ዘመናዊ የመሰረተ ልማት ግንባታ አቅማችን ራሱን እንዲችል ይደረጋል ሲሉም ገልፀዋል።
የፕሮጀክትና የፕሮጀክት ፋይናንስ አፈጻጸም ዘመናዊ፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን መስራትም ሌላኛው የትኩረት አቅጣጫ በመሆኑ የመንግስት ገቢና ወጪን በአግባቡ የመቆጣጠር አቅም ያድጋል ብለዋል።
በፌደራል መንግስትና በክልሎች መካከል ያለው የስራ ቅንጅት እና የአፈጻጸም ኩነት የተባበረ፣ የተደጋገፈ፣ ቀልጣፋና እንከን አልባ እንዲሆን እንደሚደረግም አክለዋል።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያን የውጭ ግንኙነት ከተቀባይነት ወደ ተጽእኖ ፈጣሪነት የሚያሻግር፣ በተለይም ወዳጆችን በማበራከት የሚተጋ፣ የደመኝነት እይታ ያላቸውን ደግሞ የሚመክር፣ ለቀጠናዊ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ምንጊዜም ቅድሚያ የሚሰጥ፣ ተነሳሽነቶች ያሉትና አለም አቀፍ ተቀባይነታችንን የሚያሳድግ ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም እነዚህን ዋና ዋና ትኩረቶች መሰረት በማድረግ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የአገልግሎት ዘርፍ ከፍተኛ ምርታማነት ይመዘገብባቸዋል ተብለው ከሚጠበቁት መካከል የኤሌክትሪክ ተደራሽነት 65 በመቶ እንደሚያድግ ገልፀዋል።
የውሃ ተጠቃሚነትም በስፋት እንዲዳረስ የሚደረግ ሲሆን የጤና መድህን ሽፋን ወደ 85 በመቶ እንዲያድግ እና የደን ሽፋን ደግሞ አሁን ካለበት 26 በመቶ ከፍ እንዲል እንዲሁም የመሶብ አገልግሎት ማእከላት ቁጥር እንዲበራከቱና ከፍ እንዲሉ፣ የተማሪዎች ምገባ ሽፋንም 70 በመቶ እንዲያድግ ይደረጋል ብለዋል።
የሀገራችን የፍትህ ዘርፍ እንዲዘምንና በሀገራዊ ምክክር የቀረቡ ምክረ ሀሳቦች ወደ ተግባር እንዲገቡ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
የ2019 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫዎችንና ያለፉትን የስራ ክንዋኔዎች በሚገባ የተነተነ፣ መልካሙንና ክፍተቶችን የለየ እና የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅሞች ይበልጥ የሚያስከብርና ፈጣን እድገቷን የሚያረጋግጥ እንደሚሆን ገልፀዋል።
እነዚህን እውን ለማድረግም በተያዘው አመት አዳዲስ አሰራሮችንና አደረጃጀቶችን መከተሉ ከማንኛውም ጊዜው በላይ አስፈላጊ መሆኑን ያነሱ ሲሆን የአመቱን እቅድ ለመፈጸም የሚመደቡ አካላት የህዝብን ፍላጎት ያስቀደሙ፣ የዛሬንና የወደፊት ራእያችንን ጭምር የሚያመለከቱ እንዲሁም ዋዛ ፈዛዛ ልምምድን የሚጠየፉ እና ትጋት ያላቸው አገልጋዮች እንዲሆኑ እንደሚጠበቅ ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል።

በጎረቤት ኬንያ የኢቦላ ቫይረስ ታካሚ ሕይወት ማለፉ ተገለጸ
#ethiopia | የኬንያ መንግሥት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ይኖር በነበረ ኬንያዊ ዜጋ ላይ በ«ቡንዲቡግዮ» የቫይረስ ዝርያ የተያዘ የኢቦላ ታካሚ መገኘቱን አስታወቀ።
ግለሰቡ በዲአር ኮንጎ እያለ በበሽታው ተይዞ በተለያዩ ሆስፒታሎች ሕክምና ሲከታተል ከቆየ በኋላ፣ በኡጋንዳ ካምፓላ በኩል ወደ ናይሮቢ ተጓዞ ትናንት ሕይወቱ ማለፉ ተገልጿል።
የዓለም ጤና ድርጅት የበሽታውን ሥርጭት በቁጥጥር ስር ለማዋልና ተጨማሪ የታመሙ ሰዎችን በፍጥነት ለመለየት ከኬንያ፣ ዲአር ኮንጎ እና ኡጋንዳ መንግሥታት ጋር በመተባበር ከታካሚው ጋር የተገናኙ ሰዎችን የመከታተል፣ የምርመራና የቅኝት ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

ኬንያ 109 የተደራጁ ወንጀለኛ ቡድኖችን ዝርዝር ይፋ አደረገች።
የኬንያ መንግሥት በሀገሪቱ 109 የተደራጁ የወንጀል ቡድኖችን ለይቶ ማውጣቱን አስታውቋል። ይህ ቁጥር በ2016 በGazette Notice No. 10427 ህገ-ወጥ ከተባሉ 89 ቡድኖች ጭማሪ ነው።
የተደራጁ የወጣት ቡድኖች ለፖለቲካ ማስፈራራት፣ ጥቃት እና ትንኮሳ ውስጥ መሳተፋቸው በስጋትነት ሲጠቀስ፥ ኬኒያ በ2027 ለምታካሂደው አጠቃላይ ምርጫ ከባድ የደህንነት ፈተና ሊሆን እንደሚችልም ተጠቁሟል።
«ጥቃት፣ ማስፈራራት እና የወንጀል ቡድኖችን ለፖለቲካ ጥቅም መጠቀም በዚህ ሂደት ውስጥ ቦታ የላቸውም» ብለዋል።
መንግሥት ባወጣው መረጃ መሰረት ምዕራብ ኬንያ 38 የሚሆኑ የተደራጁ ወንጀለኛ ቡድኖች የሚገኙባት ግዛት ስትሆን ሪፍት ቫሊ 22፤ እንዲሁም ናይሮቢ 20 የተመዘገቡባቸው ግዛቶች ሆነዋል።
በናይሮቢ የህዝብ ትራንስፖርት እና አነስተኛ ንግድ ላይ የሚደረግ ማስገደድ፣ በባህር ዳርቻ በቢላና በስለት የሚፈጸም ጥቃት፣ በሪፍት ቫሊና በድንበር ደግሞ የመሳሪያ ዝውውርና የከብት ዘረፋ የቆዩ መታወቂያዎች ሲሆኑ፣ እነዚህ ቡድኖች በፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ መጀመራቸው ስጋት ሆኖ ተቀምጧል።
መንግሥት ምርመራውን ከግለሰብ ወንጀለኞች ባሻገር የቡድን መሪዎችን፣ ቅጥረኞችን እና ፋይናንስ አቅራቢዎችን እየተከታተለ መሆኑን ሲገልጽ፣ የተወሰኑ እንቅስቃሴዎች ድንበር ተሻጋሪ በመሆናቸው ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚደረግ ትብብርም እየተጠናከረ ነው ሲል አስታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም
@TikvahethMagazine

1 day ago
ሼር
በኤምሬትስ የ7 ዓመት ህጻን ህይወት
የታደገችው ጀግናዋ ኢትዮጵያዊት!
በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፉጃይራህ ግዛት ውስጥ አንዲት የ25 ዓመት ወጣት ኢትዮጵያዊት የቤት ሠራተኛ የሰራችው አስደናቂ የጀግንነት ስራ ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል። ወጣቷ በምትሰራበት ቤት ጀርባ የነበረ ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ክዳን በድንገት ሲሰበር፣ እርሷ እና የ7 ዓመት ታዳጊ ህጻን አብረው ወደ ጉድጓዱ ውስጥ ወድቀዋል።
በወደቀችበት ቅጽበት የአንደኛ እግሯ አጥንት ቢሰበርም የራሷን ህመም ወደ ጎን በመተው የብረት መዋቅር ተደግፋ ህጻኑን አጥብቃ በመያዝ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እስኪደርሱ ድረስ ሳትለቅ አቆይታዋለች። የፖሊስ እና የሲቪል ዲፌንስ ቡድኖች ደርሰው የማውጣት ስራ ሲጀምሩም ጀግናዋ ወጣት እሷ ከመውጣቷ በፊት ህጻኑ ቅድሚያ ተሰጥቶት ህይወቱ እንዲተርፍ አድርጋለች። ታዳጊው በሆስፒታል ታክሞ በጤንነት ሲመለስ፣ ወጣቷ በደረሰባት የእግር ጉዳት በፉጃይራህ ሆስፒታል በህክምና ላይ ትገኛለች።
ታዳጊው በሆስፒታል ታክሞ በጤንነት ወደ ቤተሰቡ ሲመለስ፣ ጀግናዋ ወጣት ግን በደረሰባት ከባድ የእግር ጉዳት በሆስፒታል በህክምና ላይ ትገኛለች። የፉጃይራህ ሲቪል ዲፌንስ ምክትል ዳይሬክተር በሆስፒታል ተገኝተው ወጣቷን የጎበኙ ሲሆን፣ ገልፍ ኒውስ እንደዘገበው፤ ወጣቷ ላሳየችው የላቀ መስዋዕትነትና ጀብዱ ከፍተኛ እውቅና እና ምስጋና ተሰጥቷታል።

መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የጥራት ጉድለት በታየባቸው እና ከገበያ እንዲሰበሰቡ በተወሰነባቸው ሰባት የመድኃኒት አይነቶች ላይ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።
ባለስልጣኑ ይህንን ማስጠንቀቂያ ያወጣው የኬንያ የመድኃኒት ተቆጣጣሪ አካል በሀገሪቱ በገበያ ላይ በተገኙ የተወሰኑ ምርቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን መነሻ በማድረግ ነው።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመድኃኒት ጥራት እና ደህንነት ክትትል ክፍል አማካሪ ዶ/ር ኤልሳቤት ወልደማርያም ለአሐዱ ሬዲዮ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ እና ኬንያ ሰፊ ድንበር የሚጋሩ በመሆናቸው እነዚህ ምርቶች ወደ ኢትዮጵያ የመግባት ዕድል አላቸው።
በተለያዩ የጥራት እና የደህንነት ጉድለቶች ምክንያት ከገበያ እንዲሰበሰቡ ከተደረጉት ሰባት የመድኃኒት አይነቶች መካከል በህንድ የተለያዩ የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች የተመረቱት ፍላዛርት ሽሮፕ ፣ ሄፓካል 25000 ፣ ቱናክላቭ እና ክላክሲ 1.2 ግራም የተባሉ የመድኃኒት አይነቶች ይገኙበታል።

Comments