Logo
SeledaPost
ቤተሰብ ለመጠየቅ የሄደችውን ባለትዳር  አስገድዶ መድፈር የፈፀመው አጓቷ እና ሌላኛው ተከሳሽ በእስራት ተቀጡ

በካምባ ዙሪያ ወረዳ ኦቶሎ ቀበሌ ከርሼ በተባለ አካባቢ ነው የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው።

ፖሊስ እንዳታወቀው ተበዳይ 22 ዓመቷ ሲሆ   ባለትዳር ናት  ቤተሰቦቿን ለመጠየቅ በመንገድ  ላይ እየተጓዘች ባለችበት ወቅት ተከሳሾቹ እንዳገኟት ተገልጿል።

በዚህም ከተከሳሾቹ መካከል አንደኛው የተበዳይዋ አጎት ሲሆን ይህንን የቤተሰብ ቅርበት በመጠቀም ተበዳይዋ ሌሊቱን በሌላኛው ተከሳሽ ቤት አድራ በማግስቱ እንድትጓዝ በማሳመን ይዟት ይሄዳል።

ሆኖም በጫካ ውስጥ ከደረሱ በኋላ ተከሳሾቹ ተበዳይዋን በዱላ በመምታት ራሷን መከላከል እንዳትችል ካደረጉ በኋላ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈፀማቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በደረሰው ወንጀል ተበዳይዋ ያቀረበችውን አቤቱታ ተከትሎ ፖሊስ ምርመራ በማካሄድ  የተበዳይዋን ቃል ጨምሮ በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች የተደገፈ መሆኑን በመግለጽ የምርመራ መዝገቡ ለዐቃቤ ህግ ይልካል።

ዐቃቤ ህግም ክስ መስርቶ ጉዳዩን ለካምባ ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤት ያቀርባል።ፍርድ ቤቱም በጉዳዩ ላይ የቀረቡትን ማስረጃዎችና የተከራካሪ ወገኖችን አቋም ከመረመረ በኋላ፣ የዋና ወንጀል አድራጊው ከተበዳይዋ ጋር የቅርብ የስጋ ዝምድና ያለው በመሆኑ  ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት 1ኛ ተከሳሽ አየለ ባርጋደ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት፣ 2ኛ ተከሳሽ  ጹንዖ ገርሻ ደግሞ በ13 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

Seledadotio
Seledadotio
20 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.