Logo
SeledaPost
በአርባምንጭ ከተማ የኮሪደር ልማት የመብራት ምሰሶ ላይ ጉዳት ያደረሰው አሽከርካሪ 1 ሚሊዮን ብር ተቀጣ

በአርባምንጭ ከተማ በኮሪደር ልማት ሥራ የተተከለ ዘመናዊ የመንገድ ዳር መብራት ምሰሶ (ፖል) በመግጨት ውድመት ያደረሰ አሽከርካሪ በቁጥጥር ሥር ውሎ 1 ሚሊዮን ብር እንዲቀጣና የወደመውን ሀብት በራሱ ወጪ ወደ ነበረበት እንዲመልስ ተወሰነ።

በከተማዋ ሲቀላ ክፍለ ከተማ አሽከርካሪው ተሽከርካሪ ለማንቀሳቀስ ባልተፈቀደ ቦታ ላይ በማሽከርከር በከፍተኛ ወጪ የተተከለውን ስማርት የመብራት ምሰሶ በመግጨት ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።

ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ የአርባምንጭ ከተማ ደንብ አስከባሪ ጽሕፈት ቤት ከከተማው ትራፊክ ፖሊስ ጋር ባደረጉት የተቀናጀ ክትትል ጥፋተኛውን አሽከርካሪ በቁጥጥር ሥር ማዋል ተችሏል።

የከተማው ደንብ አስከባሪ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰራዊት ገዛኸኝ እንዳስታወቁት፣ በቸልተኝነት በሚፈጸሙ ጥፋቶች የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት እንዳይባክን እና አስተማሪ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ሲባል የተሰበረውንና የወደመውን ስማርት የመብራት ምሰሶ በራሱ ወጪ ወደ ነበረበት እንዲመልስ።

ጥፋተኛውን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ከነዋሪዎች የተገኘው የጥቆማ ትብብር ከፍተኛ ሚና እንደነበረው የገለጹት አቶ ሰራዊት፣ ለኅብረተሰቡ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ኃላፊው አክለውም ለከተማዋ እድገትና ለነዋሪዎች ምቾት በከፍተኛ ወጪ የተገነቡ የኮሪደር ልማት ሥራዎችንና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን በሚያበላሹ ወይም ሕግ በሚተላለፉ አካላት ላይ የሚወሰደው ሕጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳስበዋል።

Seledadotio
Seledadotio
2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.