(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የሀገሪቱን የትውልድ ዜግነት መብት ለመገደብ ያለመ አዲስ ነገር ግን ጠበብ ያለ ማዕቀፍ ያላቸውን ሁለት አስፈጻሚ ትዕዛዞች ሐሙስ ዕለት ፈርመዋል። ይህ አዲስ እርምጃ፣ ፕሬዝዳንቱ ቀደም ሲል ያወጡት ተመሳሳይ ትዕዛዝ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ መደረጉን ተከትሎ፣ የአሜሪካን ህገ-መንግስት ድንጋጌ ዳግም ለመሞገት የተደረገ ሙከራ ነው።
በትራምፕ የሪፐብሊካን አስተዳደር የጸረ-ስደተኞች ፖሊሲ ውስጥ የትውልድ ዜግነትን መገደብ ቀዳሚው አጀንዳ ሆኖ ቆይቷል። በተለይም ነፍሰጡር የውጭ ዜጎች ልጆቻቸውን በአሜሪካ ምድር በመውለድ ዜግነት ለማግኘት የሚያደርጉትን ጉዞ ወይም ዋይት ሀውስ "የወሊድ ቱሪዝም" በማለት የሚጠራውን አሰራር ዋነኛ ኢላማው አድርጓል።
ባለፈው ሰኔ 30 ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የትራምፕን የመጀመሪያ ትዕዛዝ "ከህገ-መንግስቱ ጋር የሚጻረር ነው" በማለት ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ፣ ፕሬዝዳንቱ ኮንግረሱ ህግ እንዲያወጣ ጥሪ አቅርበው ነበር። ሆኖም ሐሙስ ዕለት ፖሊሲን የሚያወጡ ነገር ግን የህግ አስገዳጅነት የሌላቸውን አስፈጻሚ ትዕዛዞችን መፈረምን መርጠዋል። የትራምፕ አስተዳደር እንደሚለው፣ እነዚህ አዳዲስ መመሪያዎች ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ካስቀመጣቸው ገደቦች ውጪ የሆኑ ናቸው። ይህም የወሊድ ቱሪዝምን ጨምሮ የትውልድ ዜግነት መብት የማይገባቸውን ሰዎች ምድብ ለማስፋት ያስችለዋል ብሏል። በትራምፕ ትዕዛዝ መሰረት፣ እነዚህ ምድቦች "ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ካወጀው የትውልድ ዜግነት ደንብ ስር አይወድቁም።"
በዋይት ሀውስ የፕሬዝዳንቱ ረዳት የሆኑት ስቴፈን ሚለር በትዕዛዙ የፊርማ ስነ-ስርዓት ላይ፣ "ይህ ትዕዛዝ ከተፈረመበት ጊዜ ጀምሮ የወሊድ ቱሪዝም ልምምድ ሙሉ በሙሉ ታግዷል። ይህ ማለት ማንም ሰው ለዚህ አታላይ ዓላማ ቪዛ ማግኘት አይፈቀድለትም" ሲሉ ተናግረዋል።
አዳዲሶቹ ትዕዛዞች ከወሊድ ቱሪዝም ባሻገር፣ በአሜሪካ ለሚገኙ የውጭ መንግስታት ሰራተኞች እና እንደ 'ጠላት' (Alien Enemies) ለተፈረጁ የውጭ ዜጎች የሚወለዱ ልጆችን የዜግነት መብት ይገድባሉ። ከዚህም በተጨማሪ ኮንግረሱ አዲስ ህግ ካጸደቀ፣ በአሜሪካ ግዛቶች (Territories) ውስጥ የሚወለዱ ሰዎች አውቶማቲክ ዜግነት እንዳያገኙ ሊያደርግ እንደሚችል ተጠቁሟል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የተሰጠውን የ6 ለ 3 የድምጽ ውሳኔ አጥብቀው ተችተዋል። "በትውልድ ዜግነት ላይ ከጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እጅግ አሳዛኝ ውሳኔ አጋጥሞናል... በጣም ተቀራራቢ ድምጽ ቢሆንም፣ እጅግ አሳዛኝ ውሳኔ ነው" ብለዋል። አክለውም፣ "ሰዎች ዜግነትን ማግኛ መንገድ አድርገው ንግድ እየገነቡበት ነው። አሰራሩ እንደዚህ መሆን አልነበረበትም፤ ይህ አሳፋሪ ነው። ዜግነትን በገንዘብ እየገዙ ነው፣ እኛ ደግሞ ይህ እንዲሆን አንፈቅድም" ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
የአሜሪካ ህገ-መንግስት 14ኛው ማሻሻያ ከውጭ ዲፕሎማቶች ወይም ወራሪ የጠላት ኃይል አባላት ልጆች ውጪ፣ በአሜሪካ ምድር ለሚወለዱ ህጻናት በሙሉ የዜግነት መብትን እንደሚያረጋግጥ በህግ ሲተረጎም ቆይቷል። ትራምፕ ግን ይህ ህግ የወጣው ከእርስ በርስ ጦርነቱ በኋላ ለባሮች ልጆች ዜግነት ለመስጠት መሆኑን በመጥቀስ፣ የአሁኑ አሰራር የህጉን መንፈስ የሳተ ነው ብለዋል።
በሌላ በኩል የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዋና ዳኛ ጆን ሮበርትስ በውሳኔያቸው ላይ፣ የ14ኛው ማሻሻያ አርቃቂዎች ይህንን ቃል ኪዳን በሀገሪቱ ውስጥ ለተወለደ እያንዳንዱ ነጻ ሰው እንዳሰፉት አስታውሰው፣ "ዜግነት በዚያን ጊዜም ሆነ አሁን መብቶችን የማግኘት እና በፖለቲካዊ ማህበረሰባችን ውስጥ በነጻነት የመሳተፍ መብት ነው። ይህንን ቃል ኪዳን ዛሬም እንጠብቃለን" በማለት የህገ-መንግስቱን ሰፊ ትርጉም አጽንኦት ሰጥተውበታል።
በ2020 የትራምፕ የመጀመሪያ የስልጣን ዘመን አዲስ የተወለደ ልጅ የአሜሪካ ዜግነት እንዲያገኝ በሚል ዓላማ የቱሪስት እና የንግድ ቪዛዎችን መጠቀምን የሚከለክል የፌዴራል ደንብ ወጥቶ የነበረ ቢሆንም፣ የወሊድ ቱሪዝምን ሙሉ በሙሉ የሚከለክል ግልጽ ህግ በአሜሪካ የለም። ይህን መሰል ማጭበርበር ላይ የሚሳተፉ ሰዎች በህግ ሊጠየቁ ቢችሉም፣ የትራምፕ አዳዲስ አስፈጻሚ ትዕዛዞች በፍርድ ቤቶች በኩል ጠንካራ የህግ ተግዳሮት እንደሚገጥማቸው በሰፊው ይጠበቃል።

6 hours ago