3 hours ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የሶማሊያ መንግስት በአማራ ክልል የሰዎችን ህይወት በቀጠፈው እና ከባድ ውድመት ባስከተለው አሳዛኝ የመሬት መንሸራተት አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ፣ በዚህ የሀዘን ጊዜ ከጎረቤት ሀገር ኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆም አስታውቋል።
የሶማሊያ መንግስት ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ "የሶማሊያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ በአማራ ክልል በደረሰው አውዳሚ የመሬት መንሸራተት ምክንያት ለኢትዮጵያ ጥልቅ ሀዘኗን ትገልፃለች" ብሏል። አክሎም "በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጎን ትቆማለች፤ ሀሳባችንም ከአደጋው ተጎጂዎች ጋር ነው" ሲል አጋርነቱን አሳይቷል።
ይህ የመሬት መንሸራተት አደጋ የተከሰተው፣ ኢትዮጵያ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከባድ ዝናብ እና ጎርፍን ጨምሮ ተደጋጋሚ የአየር ንብረት ነክ አደጋዎች እያጋጠሟት ባለበት ወቅት መሆኑ ተገልጿል።
ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የዲፕሎማሲ እና የፀጥታ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፣ ሁለቱ ሀገራት በቀጣናው መረጋጋት እንዲሰፍን እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ቡድኖችን ለመዋጋት በጋራ በመስራት ላይ እንደሚገኙ ዘገባው አስታውሷል።

11 hours ago
ሶማሊያ በአማራ ክልል በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለኢትዮጵያ ማጽናኛ እና ሐዘኗን ገለጸች
#fastmereja I የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በአማራ ክልል በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ።
የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ አገሪቱ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆም አስታውቃለች። ሚኒስቴሩ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦች እና ወዳጆች መጽናናትን የተመኘ ሲሆን፣ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ደግሞ በፍጥነት እንዲያገግሙ መልካም ምኞቱን አስተላልፏል።
በተጨማሪም በአደጋው አካባቢ የተጎዱትን ለመታደግ እና የጎደሉትን ለመፈለግ እየተደረገ ያለውን የእርዳታና የመፈለግ ስራ ያደነቀው የሶማሊያ መንግሥት፣ በጸሎት እና በሐሳብ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እንደሚገኝ አረጋግጧል።

2 days ago
ግብፅ፣ ሱዳን፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ በሳዑዲ አረቢያ የሚመራውን ስምንት አገራትን ያካተተ የቀይ ባህርና የኤደን ባህረ ሰላጤ አዲስ የደህንነት ጥምረት ተቀላቀሉ፡፡
ሳዑዲ አረቢያ ስምንት በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ የሚገኙ ሀገራትን በማስተባበር አዲስ ተጨማሪ የባህር ላይ የደህንነት ጥምረት አዋቅራለች።
ከእነዚህ ስምንት ሀገራት መካከል አምስቱ ሀገራት ግብፅ፣ ሱዳን፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ ናቸው።
የታቀደው ህብረት ሳዑዲ አረቢያን፣ ዮርዳኖስን፣ የመንን እና አምስቱን የአፍሪካ ሀገራት ያካተተ ነው።
የሳዑዲ አረቢያ የመከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ጥምረቱ ዓላማው በቀይ ባህር ላይ በሚያዋስኑ ሀገራት መካከል ያለውን ቅንጅት ማጠናከር እና ዓለም አቀፍ የባህር ላይ መስመሮችን፣ የንግድና የኃይል ማጓጓዣ መንገዶችን እንዲሁም የጋራ የባህር ላይ ጥቅሞችን መጠበቅ መሆኑን አስታውቋል።
ጥምረቱ የተመሰረተው በቀጠናው ውጥረቶች እና በንግድ መርከቦች ላይ የሚደርሱ መስተጓጎሎች እየጨመሩ የመጡበት ወቅት ላይ ነው።
Seledadotio

3 days ago
የአረንጓዴ ዐሻራ የሰባት ዓመታት ሰባት አንኳር ስኬቶች
*************
አረንጓዴ ዐሻራ በኢትዮጵያ ምድር ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ባለፉት ሰባት ዓመታት፣ ሀገራችንን ከአፈር መሸርሸር እና ከበረሃማነት የመታደግ ሀገራዊ ራዕይ ብቻ ሳይሆን፤ የምድርን ሕይወት የሚያድስ፣ የዜጎችን ሥነ-ልቦናዊ አስተሳሰብ የሚቀርጽ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም የሚገነባ ታላቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ ሆኖ ዘልቋል።
ይህ ሀገራዊ የሕልውና ጥረት ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስትራቴጂዎች ጋር ተናብቦ ባለፉት ሰባት ዓመታት ያስመዘገባቸው ሰባት ዋና ዋና ተጨባጭ ስኬቶች እንደሚከተለው ተተንትነዋል።
1. የችግኝ ብዛትን ከጽድቀት ምጣኔ ጋር ያጣመረ አዲስ ታሪካዊ ሽግግር
ባለፉት ሰባት ዓመታት በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞች መተከላቸው ብቻ ሳይሆን፣ የተከላው ዋና ትኩረት ወደ ጥራት እና ድኅረ-ተከላ እንክብካቤ በማደጉ የችግኞች ጽድቀት ምጣኔ ከ80 በመቶ በላይ ማደግ ችሏል።
ይህም ቀደም ሲል የነበረውን "መተከል እንጂ አለመጽደቅ" የሚል የብክነት ታሪክን በመቀየር በቆላ እና በደጋ አካባቢዎች የተጎዱ መሬቶች በፍጥነት አረንጓዴ እንዲለብሱ እና ሥነ-ምኅዳራዊ ሚዛን እንዲጠበቅ አድርጓል።
2. ከአካባቢ ጥበቃ ወደ የምግብ ዋስትና የተደረገ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግር
አረንጓዴ ዐሻራ ከተፈጥሮ የደን ዛፎች ባሻገር እንደ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ አፕል እና ቡና ያሉ ፍሬያማ ተክሎችን በስፋት አካትቷል።
ይህ ስትራቴጂያዊ እርምጃ ፕሮጀክቱን ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ የቤተሰብ የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጥ እና አባወራዎችን የገበያ ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ ብሎም የሀገራችን የግብርና ምርት የወጪ ንግድ የሚያሳድግ የኢኮኖሚ ሞተር አድርጎታል።
ይህም የአካባቢ ጥበቃን ከዜጎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ማሻሻል ግብ ጋር በማስተሳሰር ዘላቂነቱ የተረጋገጠ የልማት ምሰሶ እንዲሆን አስችሎታል።
3. የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ እና የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ
በመላ ሀገራችን የተቋቋሙት በዐሥር ሺዎች የሚቆጠሩ የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች ለብዙ ዜጎች፣ በተለይም ለወጣቶች እና ለሴቶች አዲስ እና ዘላቂ የገቢ ምንጭ ሆነዋል።
ችግኝ ማፍላት፣ መንከባከብ እና ለገበያ ማቅረብ በራሱ አዲስ የኢንቨስትመንት ዘርፍ እና የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የሀገራችንን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ጅማሮ በጠንካራ መሠረት ላይ አኑሮታል።
ችግኞች ከተተከሉ በኋላ የሚደረገው ጥበቃ እና ክብካቤም በርካታ ወጣቶችን ተጠቃሚ ያደረገ ቋሚ የሥራ ዘርፍ መሆን ችሏል።
4. የውኃ ሀብት እና የታላላቅ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶች ዋስትና
በስፋት የተከናወነው የደን ልማት እና የአፈር ጥበቃ ሥራ የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ፣ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ሀገራዊ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫዎች በደለል እንዳይሞሉ የመከላከል ታሪካዊ ሚና ተጫውቷል።
በተጨማሪም የከርሰ ምድር ውኃ መጠን እንዲያገግም እና የደረቁ የምንጭ ውኃዎች መልሰው እንዲፈልቁ በማድረግ አስተማማኝ የውኃ ዋስትናን እያረጋገጠ ይገኛል።
ይህ ታላላቅ መሠረተ ልማቶችን የመጠበቅ አቅም ለኢትዮጵያ ብልጽግና ብቻ ሳይሆን፣ ሀገራችን የውኃ ምንጭ ለሆነችላቸው የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጭምር ትልቅ ትሩፋት ነው።
5. አረንጓዴ ዲፕሎማሲ እና የቀጣናዊ ትሥሥር ማጠናከሪያ
ኢትዮጵያ ያዘጋጀቻቸውን ችግኞች እንደ ጂቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኬንያ ላሉት ጎረቤት ሀገራት በማጋራት፣ የምሥራቅ አፍሪካን እና የአፍሪካ ቀንድን የቀጣና አየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮት በጋራ የመከላከል መሪነት ሚናዋን በተግባር አሳይታለች።
ይህም አረንጓዴ ዐሻራን የድንበር ተሻጋሪ ዲፕሎማሲ፣ የቀጠናው ሰላም እና የጋራ ልማት መሣሪያ አድርጎታል።
በርካታ የአፍሪካ ሀገራትም የኢትዮጵያን ፈለግ በመከተል የአረንጓዴ ልማትን በሀገሮቻቸው እያስፋፉ ይገኛሉ።
ከዚህ ባሻገር፣ ኢትዮጵያ ባመጣቻቸው ተጨባጭ ስኬቶች “ዘላቂ የደን ልማት አያያዝ እና አጠቃቀም” በሚል ዘርፍ ከዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት (FAO) ከፍተኛ እውቅናን አግኝታለች።
6. የከተሞች ሥነ-ምኅዳር መታደስ እና የኮሪደር ልማት ውበት
አረንጓዴ ዐሻራ በገጠር ተራራዎች ብቻ ተወስኖ ሳይቀር ወደ ከተሞች በመግባት የዘመናዊ ፓርኮች ግንባታ፣ የከተማ አረንጓዴ ልማት እና አሁን ላይ በስፋት እየተተገበረ ላለው የኮሪደር ልማት ዋነኛ አካል ሆኗል።
ይህም የከተሞችን የአየር ጥራት በከፍተኛ ደረጃ ከመጨመሩም በላይ፣ የሥነ-ሕይወት ስብጥርን ወደ ነበረበት በመመለስ እና ለዜጎች ምቹ የመዝናኛ እና የኑሮ አካባቢን በመፍጠር የከተሞቻችንን ገጽታ ሙሉ በሙሉ በመለወጥ ላይ ይገኛል።
7. ሕዝባዊ ንቅናቄ እና የዜግነት አገልግሎት ባህል ግንባታ
በአንድ ጀምበር በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በነቂስ ወጥተው ችግኝ የመተከል ልምዳቸው፣ የአካባቢ ጥበቃን ከዘመቻነት አውጥቶ የባህል እና የዜግነት ግዴታ አካል አድርጎታል።
ይህም የሕዝባዊ ወንድማማችነትን ያጠናከረ እና የአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤን በማሳደግ ለቀጣዩ ትውልድ የሚሻገር እጅግ ግዙፍ ማኅበራዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ስኬት ነው።
በአጠቃላይ አረንጓዴ ዐሻራ ባለፉት ሰባት ዓመታት የተፈጥሮ ሀብታችንን ከመመለስ አልፎ ሀገራዊ አንድነትን ያጠናከረ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ አቅማችንን የገነባ እና ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ለአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ አቅራቢ ሀገር ያደረገ አንጸባራቂ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ነው።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #greenlegacy #climateaction #greendiplomacy #greeneconomy

Sponsored by
Surafel
3 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና ዳሰሳ) የሶማሌላንድ የሀገርነት ጥያቄ እና አለም አቀፍ እውቅና የማግኘት ፍላጎት በዋናነት የተመሰረተው በቅኝ ግዛት ወቅት በነበራት ግልጽ ድንበር፣ እ.ኤ.አ. በ1960 ለተወሰኑ ቀናት አግኝታው በነበረው ነጻነት እና በ1991 ያወጀችው ነጻነት አዲስ የመገንጠል ጥያቄ ሳይሆን የነበረን ሉዓላዊነት የመመለስ እርምጃ ነው በሚለው መከራከሪያ ላይ ነው። እንግሊዝ ከ1884 እስከ 1886 በሰሜን ሶማሊያ ከሚገኙ የጎሳ መሪዎች ጋር ባደረገችው የስምምነት ውል መሰረት የሶማሌላንድን ግዛት የመሰረተች ሲሆን፣ የውጭ ድንበሮቿም ከፈረንሳይ፣ ጣሊያን እና ኢትዮጵያ ጋር በተደረጉ አለም አቀፍ ስምምነቶች የተከለሉ ነበሩ። ሰኔ 26 ቀን 1960 ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነጻነቷን የተቀዳጀችው ሶማሌላንድ፣ ከአምስት ቀናት በኋላ በፈቃደኝነት ከጣሊያን ሶማሊያ ጋር በመዋሃድ የሶማሊያ ሪፐብሊክን መስርታለች። ይሁን እንጂ የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግስት በ1991 መውደቁን ተከትሎ፣ ሶማሌላንድ ከውህደቱ በፊት ወደ ነበራት ነጻነት መመለሷን በማወጅ የ1960ዋን ግዛቷን ይዛለች።
የሶማሌላንድ ዋነኛ የህግ መከራከሪያ አዲስ ነጻ የሚወጡ ሀገራት በቅኝ ግዛት ወቅት የነበራቸውን ድንበር ጠብቀው ሊቀጥሉ ይገባል የሚለው መርህ ነው። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በ1964ቱ የካይሮ ውሳኔው እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት የመመስረቻ ሰነዱ ላይ አባል ሀገራት በነጻነት ጊዜ የነበራቸውን ድንበር ሊያከብሩ እንደሚገባ አስፍረዋል። በመሆኑም ሶማሌላንድ አለም አቀፍ እውቅና ማግኘቷ የቅኝ ግዛት ድንበርን ከመጠበቅ ባለፈ አዲስ ድንበር የማካለል ስራ አይደለም በማለት ትከራከራለች። አቋሟም ከዚህ ቀደም ሉዓላዊ ሀገር እንደነበረች፣ የ1960ውን ውህደት በራሷ ፈቃድ እንደፈጸመች እና የ1991ዱ እርምጃዋም የከሸፈን ውህደት ማፍረስ እንጂ አዲስ ግዛትን ከሶማሊያ መገንጠል አይደለም በሚሉ ሶስት ምሶሶዎች ላይ የቆመ ነው። ይህ አቀራረብ ሶማሌላንድን ምንም አይነት የቅኝ ግዛት ወይም አለም አቀፍ ድንበር መሰረት ከሌላቸው የመገንጠል ጥያቄዎች የተለየች ያደርጋታል።
የሶማሌላንድን ሁኔታ ከኤርትራ ጋር ማነጻጸር የጉዳዩን የዲፕሎማሲ ውስብስብነት በደንብ ያሳያል። ሁለቱም ግዛቶች የተለየ የቅኝ ግዛት ታሪክ፣ ከማዕከላዊ መንግስት ጋር የተደረገ የትጥቅ ትግል እና ከ1991 በኋላ ውጤታማ የሆነ ራስን በራስ የማስተዳደር ልምድ አላቸው። ይሁን እንጂ የኤርትራ የነጻነት ጥያቄ የኢትዮጵያን የሽግግር መንግስት ፈቃድ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህዝበ ውሳኔ ታዛቢነትን በማግኘቱ ፈጣን አለም አቀፍ እውቅናን ሊያጎናጽፋት ችሏል። በሶማሌላንድ በኩል ግን ጠንካራ ተቋማትን መገንባት እና ህዝበ ውሳኔ ማካሄድ ብትችልም፣ ከሶማሊያ መንግስት የተገኘ ስምምነትም ሆነ እንደ ኤርትራው አይነት አለም አቀፍ ድጋፍ ባለማግኘቷ የዲፕሎማሲ እውቅናው ሊዘገይባት ችሏል። ይህ የሚያሳየው ውጤታማ አስተዳደር እና ታሪካዊ ድንበር መኖር ብቻውን በቂ እንዳልሆነ እና እውቅና ማግኘት በስምምነት፣ በቀጠናዊ ፖለቲካ እና በዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ላይ በእጅጉ የተመሰረተ መሆኑን ነው።
የአፍሪካ ህብረት በ2005 ወደ አካባቢው አጣሪ ቡድን ልኮ የሶማሌላንድ ጥያቄ በቅኝ ግዛት ድንበር እና በቀድሞ ነጻነቷ ላይ የተመሰረተ ታሪካዊ መነሻ እንዳለው ቢገነዘብም፣ አሁንም ድረስ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ቅድሚያ መስጠትን መርጧል። በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ሶማሌላንድን እውቅና መስጠት በሌሎች አካባቢዎች የመገንጠል ጥያቄዎችን ሊያነሳሳ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። ሶማሌላንድ በበኩሏ የድሮውን ድንበር መመለስ እንጂ አዲስ ድንበር መፍጠር አይደለም ስትል ምላሽ ትሰጣለች።
ሶማሌላንድ በቅኝ ግዛት ድንበር እና በቀድሞ ነጻነት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ የህግ መከራከሪያ ብታቀርብም፣ የኤርትራን ተሞክሮ ስንመለከት የህግ ትንታኔ ብቻውን እውቅናን እንደማያመጣ መገንዘብ ይቻላል። ሶማሌላንድ ከሶማሊያ ጋር የደረሰችበት ምንም አይነት ስምምነት ባለመኖሩ፣ የእውቅና ጉዳይ አሁንም ድረስ አለም አቀፍ ተቋማት የድሮዋን ሉዓላዊ ሀገር ዳግም መመለስ አድርገው ይቀበሉታል ወይስ የሶማሊያን የግዛት አንድነት የሚፈታተን ድርጊት አድርገው ይቆጥሩታል የሚለው ጉዳይ የፈተና መድረክ ሆኖ ቀጥሏል።

4 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የሳኡዲ አረቢያ መንግስት የቀይ ባህርንና የባብኤል መንደብን ሰርጥ ደህንነት ለማስጠበቅ በሚል በ14 አገራት አማካኝነት ጥምር ሀይል መመስቷ ይታወቃል፡፡ ይህ ጥምር ሀይል ዋና መቀመጫው በሪያድ እንደሚሆን የተገለፀ ሲሆን ዋነኛ አላማውም የየመን ሀውቲ ታጣቂዎች በቀጠናው ውስጥ የፈጠሩትን ስጋት መቀነስ ነው፡፡
በጥምረቱ ውስጥ ከቀጠናው አገራት ኩዌት፣ ባህሬን፣ ኳታር፣ ዮርዳኖስ፣ ግብፅ፣ ሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ የየመን ህጋዊ መንግስትና ኮሞሮስ ሲካተቱ ከአለም አቀፍ አጋሮች ቱርክ፣ ፓኪስታን፣ ባንግላዲሽና ናይጄሪያ ይገኙበታል፡፡ ይሁንና በቀይ ባህር ላይ ከ1700 ኪሎ ሜትር በላይ ጠረፍ ያላት ኤርትራ የዚህ ጥምረት አልሆነችም፡፡ ይህ ጉዳይ መነጋገሪያ በሆነበት በዚህ ወቅት ኤሪትሪያን ፖስት ዛሬ ባሰራጨው ዘገባ ኤርትራ ጥምረቱ ውስጥ እንድትሳተፍ ጥሪ ቀርቦላት እንዳልተቀበለችው አስታውቋል፡፡
በዘገባው አገሪቱ ይህንን እርምጃ የወሰደችው ከውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ አኳያ መሆኑን ጠቅሶ ይህም ገለልተኛ አቋም መያዝ እንደሆነ ገልጿል፡፡ ኤርትራ ከሳኡዲ አረቢያና ከግብፅ ጋር የጠበቀ የትብብር ግንኙነት እንዳላት የጠቀሰው ዘገባው በሌላ በኩል ከኢራን ጋር መልካም ግንኙነቷን ማስጠበቅ እንደምትፈልግ አስታውቋል፡፡
በውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ የራሷ ሉአላዊነት ሲነካ ብቻ ምላሽ እንደምትሰጥ በማስቀመጧ የተነሳ የሀውቲ ታጣቂዎች በኤርትራ የውሀ ግዛት ውስጥ ስጋት ካልፈጠሩ በስተቀር ወታደራዊው ጥምረት ውስጥ ላለመግባት መወሰኗን አስረድቷል፡፡ ይህ ውሳኔዋም ብሄራዊ ጥቅሟን እያስጠበቀች በቀጠናው ካለው የሀይል ፉክክርና መጠላለፍ እንድትጠነቀቅ ያደርጋታል ሲልም ገልጿል፡፡

5 days ago
📞✨ዲያስፖራው ባለበት ሁሉ ኢትዮ-ኮል እየመጣ ነው!
ማንኛውንም የሞባይል ወይም የመደበኛ ስልክ ላይ በታላቅ ቅናሽ መደወል ያስችላል።
🇺🇸 አሜሪካ 🇮🇱 እስራኤል
🇨🇦 ካናዳ 🇾🇪 የመን
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ 🇰🇪 ኬንያ
🇮🇹 ጣሊያን 🇩🇪 ጀርመን
🇮🇳 ሕንድ 🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
🇷🇼 ሩዋንዳ 🇸🇴 ሶማሊያ
መተግበሪያውን ያውርዱ: https://onelink.to/ethioca...
ወደ አገርቤት በቅናሽ ይደውሉ፤ በገዙት ጥቅል ደዋዮች ሳይቆጥርባቸው በነፃ ይቀበሉ!
#ethiocall #ethiotelecom #telebirr #telebirrsuperapp #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia

6 days ago
ቬንዙዌላ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የወንጀል መጠን የሚፈጸምባት ሀገር ተባለች።
#ethiopia | የረቀቁና የተደራጁ ወንጀሎች በብዛት ከሚፈጸምባቸው ሀገራት ቬንዙዌላ አንዷ ስትሆን በትጥቅ የተደገፈ ዝርፊያ ግድያ እና እገታ በብዛት ይበዛበታል ተብሏል።
መረጃው እንደጠቆመው ከፍተኛ የወንጀል መጠን የሚመዘገብባቸው አገራት በዋናነት በኢኮኖሚ አለመረጋጋት በፖለቲካዊ ውጥረት እና በቡድን ሁከቶች የሚታወቁ ናቸው።
ፓፓዋ ጊኒ ከፍተኛ የወንጀል መጠን ከሚፈፀምባቸው ሀገራት መካከል በሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን ከከተሜነት መስፋፋት እና ሥራ አጥነት ባስከተለው ማኅበራዊ ውጥረት ምክንያት ከፍተኛ የወንጀል መጠን የሚመዘገብባት ሀገር ሆናለች።
ደቡብ አፍሪካ ከአለም ሶስተኛ ከአፍሪካ በቀዳሚነት ከፍተኛ የወንጀል መጠን የሚፈጸምባት ሀገር ተብላለች።
በጥናቱ መሠረት በሀገሪቱ የጦር መሣሪያ በቀላሉ መገኘቱ የኢኮኖሚ አለመመጣጠን እና የጎዳና ላይ ጥቃቶች መስፋፋታቸው ለወንጀሉ መጨመር በምክንያትነት ተጠቅሰዋል።
ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠል ናይጄርያ በህገ-ወጥ እገታዎችና በሳይበር ወንጀሎች ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
እንዲሁም ሶማሊያ እና ሊቢያ በፖለቲካዊ አለመረጋጋትና በታጠቁ ቡድኖች እንቅስቃሴ ምክንያት ከአህጉሩ ከፍተኛ የወንጀል ስጋት ካለባቸው ሀገራት መካከል ሶስተኛና አረተኛ ደረጃን ይዘዋል።።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #reviewindex #venezuela #southafrica

8 days ago
ሻዕቢያ ሕዝቡን ለእንግልትና ለስደት ዳርጓል፤ ኢትዮጵያ ከ400 ሺህ በላይ ኤርትራውያንን ተቀብላ አስጠልላለች
ሻዕቢያ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ከ30 ዓመታት በላይ በኤርትራ ሕዝብ ላይ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውሶችን አስከትሏል፡፡
የኤርትራ ሕዝብ ከሰላሳ ዓመታት በላይ በተደረገ የትጥቅ ትግል ነጻነት ተጎናጸፍኩ ቢልም፣ የነጻነት ትግሉን የመራው የሻዕቢያ መንግሥት፣ ሀገሪቱን በብቸኝነት እያስተዳደረ ይገኛል።
ይህ አካሄድም ኤርትራን ወደ ተወሳሰበ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ የከተታት መሆኑን ወደ ኢትዮጵያ ተሰደው የመጡ ኤርትራውያን፣ በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማትና የፖለቲካ ተንታኞች ይስማማሉ።
በኤርትራ የሚታየው ዋነኛው ቀውስ ከፖለቲካዊ መዋቅሩ ጋር የተያያዘ ነው። በፈረንጆቹ 1997 የሀገሪቱ ብሔራዊ ምክር ቤት ያጸደቀውና በርካታ የሲቪል መብቶችን የያዘው ህገ-መንግሥት እስካሁን ድረስ ተግባራዊ አልተደረገም፡፡
በሀገሪቱ ውስጥ የአንድ ፓርቲ አምባገነንነት ነው ያለው፡፡ ከሻዕቢያ ውጭ ሌላ ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ እንዳይቋቋም በህግ የተከለከለ ሲሆን፣ ሀገራዊ ምርጫም ተካሂዶ አያውቅም።
ከፈረንጆቹ 2001 ጀምሮ የግል መገናኛ ብዙሃን ሙሉ በሙሉ የተዘጉ ሲሆን÷ መንግሥትን የተቹ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ጋዜጠኞችና የሃይማኖት መሪዎች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በእስር ላይ ይገኛሉ። ለሥርዓቱ ታግለው በእስር ላይ ሕይወታቸውን ያጡም በርካቶች ናቸው፡፡
ህግ አውጪ፣ ህግ ተርጓሚና ህግ አስፈጻሚው አካል በአንድ ግለሰብ ማለትም በኢሳያስ አፈወርቂ ቁጥጥር ሥር መውደቃቸው የፍትህ ሥርዓቱን አዳክሞታል።
የኤርትራ መንግሥት ራስን መርህ ያደረገ የኢኮኖሚ ፖሊሲ እከተላለሁ ቢልም በተግባር ግን ኢኮኖሚው እንዲዳከምና የሕዝቡ የመግዛት አቅም እንዲደቅ አድርጓል።
የግሉ ዘርፍ እጅግ የተገደበ ሲሆን÷ አብዛኛው የንግድና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በሻዕቢያ የንግድ ተቋማትና በጦር አዛዦች ቁጥጥር ስር ነው። ይህ የመንግሥት ሞኖፖሊም ጤናማ የገበያ ውድድር እንዳይኖር አድርጓል።
በፖለቲካዊ አለመረጋጋት፣ በሕግ የበላይነት እጥረትና በውጭ ምንዛሪ ቁጥጥር ምክንያት የውጭ ሀገር ኩባንያዎች በሀገሪቱ ኢንቨስት ማድረግ አይፈልጉም።
በሀገሪቱ የተጠናከረ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ባለመኖሩ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የቴሌኮሙኒኬሽንና የትራንስፖርት አገልግሎቶች ደርግ ጥሏቸው እንደሄደ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናው በቀጥታ የኤርትራን ህዝብ ስነ-ልቦናዊና ሥነ-ሕዝባዊ መዋቅር አናግቶታል።
የግጭት ስነልቦና ያልተለየው ሻዕቢያ፣ ወጣቶች በውትድርና እንዲያገለግሉ ግዴታ ይጥላል፡፡ ወጣቶችም በሳዋ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ስልጠናቸውን ከጨረሱ በኋላ ለዓመታት በዝቅተኛ ክፍያ በውትድርናና በግዳጅ ስራ ላይ እንዲሰማሩ ይደረጋል። ይህ አሰራር የወጣቶችን የወደፊት ተስፋ ያጨለመ ሆኗል።
ከዚህ የግዳጅ አገልግሎትና ከኢኮኖሚ ችግር ለማምለጥ በየወሩ በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው ይሰደዳሉ። ይህ ስደት ሀገሪቱን የተማረና አምራች የሰው ኃይል አሳጥቷታል።
አባወራዎች በውትድርና ረጅም ጊዜ ማሳለፋቸውና የወጣቶች በብዛት መሰደድ የኤርትራውያንን ማህበራዊ ትስስርና የቤተሰብ መዋቅር እያፈራረሰው ይገኛል።
ከኤርትራ መገንጠል በኋላ በሀገሪቱ ካለው የፖለቲካና የግዳጅ ውትድርና ሥርዓት ለማምለጥ በ100 ሺህ የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ወደ ኢትዮጵያ ተሰደዋል።
ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ በርካታ ስደተኞችን ከሚያስተናግዱ ግንባር ቀደም ሀገራት አንዷ ስትሆን÷ የኤርትራ ስደተኞች ከደቡብ ሱዳንና ከሶማሊያ ቀጥሎ ሦስተኛውን ትልቅ ስብስብ ይይዛሉ።
የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ ተመሳሳይ የስነ ልቦና ውቅር፣ ታሪክ፣ ባህልና ኃይማኖት የሚጋሩ ህዝቦች በመሆናቸው፣ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከ400 ሺህ በላይ የኤርትራ ስደተኞችን አስጠልላ ትገኛለች፡፡
ይህ ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ዜጎች የምታደርገውን ሰብዓዊ መስተንግዶ የሚያሳይ ሲሆን÷ ኤርትራውያንን ጨምሮ ኢትዮጵያ በአጠቃላይ የ1 ነጥብ 3 ሚሊየን ስደተኞች መጠለያ ናት፡፡
በአጠቃላይ ሻዕቢያ ኤርትራን ወደ ተሻለ የዴሞክራሲና የብልጽግና ምዕራፍ ማሸጋገር አልቻለም። ሻዕቢያ እነዚህን ቀውሶች ከራሱ የፖሊሲ ስህተት ይልቅ ከውጭ ሀገራት ጫና፣ ከድንበር አለመወሰንና ከዓለም አቀፍ ማዕቀቦች ጋር ለማያያዝ ይሞክራል፡፡
በሀገር ውስጥ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ግን የሕዝቡን ህይወት እጅግ ፈታኝ አድርጎታል።
ኤርትራ ካለችበት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውስ እንድትወጣ፣ የአንድ ፓርቲ አገዛዝን ወደ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት መመለስ፣ የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች ማስከበርና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን መተግበር የግድ ይላል።

9 days ago
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ምላሽና ቀጣናዊ ፋይዳው
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ባለፉት አስርት ዓመታት በሰላም ማስከበር፣ በግጭት አፈታት፣ በኤሌክትሪክ ኃይል ወጪ ንግድ፣ በቀጣናዊ ትስስር እና በንግድ ትብብር ረገድ ያበረከተችው አስተዋጽኦ ለጎረቤቶቿ ብሎም ለቀጣናው የምትሰጠውን ከፍ ያለ ትኩረት ያሳያል።
ኢትዮጵያ በታሪኳ የትኛውንም ጎረቤት ሀገር ወርራ አታውቅም፡፡ ከጎረቤቶቿ ጋር ያላት ግንኙነት ሰላማዊና በትብብር ላይ የተመሰረተ ሆኖ ቆይቷል፡፡
ጎረቤቶቿ ሰላም በራቃቸው ጊዜ ሁሉ፣ ሰላም ለማስከበር ቀድማ በመገኘት ትታወቃለች፡፡ ይህንንም በደቡብ ሱዳን፣ በሱዳን፣ በሶማሊያ እንዲሁም ከጎረቤቶቿ ራቅ ብላም በላይቤሪያ፣ በሩዋንዳ፣ በኮንጎ እና በሴራሊዮን በተግባር አስመስክራለች፡፡
በአህጉር ደረጃ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ቀንበር ሲማቅቁ የነበሩ አፍሪካውያን ወንድም እህቶች ነጻ ለመውጣት የሚያደርጉትን ጥረት በስልጠና፣ በሎጂስቲክስና በዲፕሎማሲ መስክ ጭምር መደገፏ አሌ የማይባል ሃቅ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ዛሬም የልማት ትሩፋቷን ለብቻዋ ዕድገትና ለውጥ የምትጠቀም ሀገር አይደለችም፡፡ ይልቁንም ልማቷን እና ለውጧን በማጋራት እና ለጎረቤቶቿ አብሮ መለወጥ እየሰራች ትገኛለች፡፡
በአፍሪካ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል አምራች ከሆኑ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ፤ ለጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ኤሌክትሪክ እየላከች ነው።
ይህ በአካባቢው የኢንዱስትሪ ልማት፣ የከተማ እድገት እና የህዝብ ኑሮ መሻሻል ላይ ቀጥተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ ነው።
በንግድ ረገድም ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና እና የአፍሪካ ህብረት "አጀንዳ 2063" የሚያስቀምጧቸውን የክልላዊ ውህደት ግቦች ለማሳካት የኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች፣ የድንበር ንግድ ማዕከላት እና የትራንስፖርት ኮሪደሮችን በማስፋፋት በቀጣናዊ ትስስር ማደግና መጠናከር ላይ ግዙፍ ኢንቨስትመንት እያካሄደች ነው።
ኢትዮጵያ ለጎረቤቶቿ ሰላምና ደህንነት፣ እድገትና ልማት አበክራ የሰራቻቸው ስራዎች ለቀጣናውና ለሀገራቱ ያላትን አዎንታዊ ሚና በግልፅ ያሳያል። ሀገሪቱ የባህር በር ጥያቄዋ ምላሽ ሲያገኝ ይህ ቀጣናዊ ገንቢ ሚናዋ በምን ያህል መጠን ሊያድግና ሊባዛ እንደሚችል ለመገመት አያዳግትም፡፡
በታሪክ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ህዝብ ህጋዊ ስልጣን በሌለው አካል ህጋዊ የባሕር በር ባለቤትነቷን እንድታጣ ተደርጓል፡፡ የመደመር መንግሥት የተፈጸመውን ኢፍትሃዊና ታሪካዊ በደል በሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ የማስመለስ ጥያቄ አቅርቦ የበርካታ ሃያላን ሀገራትን ድጋፍ አግኝቷል፡፡ ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ ካለው ኢኮኖሚዋና የህዝብ ቁጥሯ አንጻር የባሕር በር አማራጭ ሊኖራት ይገባል።
በ60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የባሕር በር እያለ ኢትዮጵያ ተዘግታ ትኑር የሚል ኢፍትሐዊነት ተቀባይነት የለውም።
የባሕር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ የንግድ መውጫ መግቢያ ብቻ ሳይሆን፤ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የብሔራዊ ደህንነት እና የጂኦፖለቲካ ስትራቴጂ ቁልፍ ጥያቄ በመሆኑ ጥያቄዋ መልስ እስኪያገኝ አበክራ ትሰራለች፡፡
ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘቷ ጥቅሙ ለእርሷ ብቻ አይደለም። በአፍሪካ ቀንድ እና በጎረቤት ሀገራት ዘንድ ከፍ ያለ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የመፍጠር ሚና ይኖረዋል፡፡
በአካባቢው የንግድ ኮሪደሮች ስለሚፈጠሩ የወደብ አገልግሎት እንዲስፋፋ፣ የተለያዩ የመሰረተ ልማት አውታሮች እንዲገነቡ በማድረግ የንግድ ትስስርና አዳዲስ የስራ ዕድሎች ለመፍጠር ያስችላል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከታዳሽ ኃይል የምታመነጨው ኤሌክትሪክ ለቀጣናው በበቂ ሁኔታ ማቅረቧ ኢንዱስትሪዎችን ለማስፋፋትና የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ ይረዳል።
ከዚህ ባሻገር የቀጣናዊ ሰላምና ጸጥታን በተመለከተ የጋራ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እያደገ ሲመጣ በሀገራት መካከል ከግጭት ይልቅ ትብብር እንዲጨምር ያደርጋል። ሀገራት በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በመሠረተ ልማት በተጠናከረ ሁኔታ ሲተሳሰሩ ሰላምን የመጠበቅ ፍላጎታቸውም በዛው ልክ ይጨምራል።
የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘት የአፍሪካ ህብረት "አጀንዳ 2063" የሚጠይቀውን ቀጣናዊ ትስስር ለማጠናከር፣ የነፃ ንግድ ቀጣና ለመመስረት እና የመሠረተ ልማት ትስስርን ለማሳካት ጠንካራ መሠረት ለመጣል ያግዛል።
በመሆኑም የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ አፋጣኝ መልስ እንዲያገኝ ለማድረግ ሀገራት፣ ዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊ እና ቀጣናዊ ተቋማት ድጋፋቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል፡፡
በቴዎድሮስ ሳህለ

11 days ago
ፓን-አፍሪካዊ ኃይል የሆነው የመደመር ትውልድ
*******************
ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ለመላው ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ተምሳሌት በመሆን የፓን-አፍሪካኒዝም እሳቤ ተፈጥሯዊ ጉልበት ሆና ቆይታለች።
አውሮፓውያን አህጉሪቱን ለመቀራመት ሲነሡ፣ ኢትዮጵያ በከፍታ ላይ የቆመች እና ሥልጣኔን ያጣጣመች ዕድሜ ጠገብ ሀገር ናት።
ታሪካዊው የዓድዋ ድል እስከ አፍንጫው ታጥቆ የመጣውን የቀኝ ገዢ ኃይል በማንበርከክ የነጭ የበላይነትን እሳቤ ገልብጧል፤ የዓድዋ ድል ለፓን-አፍሪካኒዝም ንቅናቄ አዲስ ጉልበትና የይቻላል መንፈስን አጎናጽፏል።
የትናንቱ የፓን-አፍሪካኒዝም ትግል ማዕከል የፖለቲካ ነጻነት ሲሆን፣ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ዋነኛ ትግል የኢኮኖሚ ነጻነትን ማረጋገጥ ነው።
ታላቁ ፓን-አፍሪካኒስት ጁሊየስ ኔሬሬ እንዳስገነዘቡት፣ በመጀመሪያው የአፍሪካ ቅርምት ጎሳን ከጎሳ ያጋጨው የውጭ ኃይል፣ አሁን ደግሞ ሀገርን ከሀገር በማጋጨት አህጉሪቱን ደካማና የተከፋፈለች ለማድረግ ይጥራል። በእርግጥም በመከፋፈል ውስጥ የሚገኝ ክብርም ሆነ ታላቅነት የለም። ከተከፋፈልን ደካሞች እንሆናለን፤ ከተባበርን ግን በእኛ ላይ የሚመጡትን የጣልቃ ገብነት ኃይሎች አሳፍረን መመለስ እንችላለን።
በዚህ ታሪካዊ መጋጠሚያ ላይ፣ የኢትዮጵያ የመደመር ትውልድ ከራሱ አልፎ ቀጣናውን በፓን-አፍሪካዊ መንፈስ ለማስተሳሰር በጽናት ቆሟል። አፍሪካውያን የማይነጣጠሉ እና ዕጣ ፈንታቸው የተሣሠረ፣ የቀኝ ግዛት ድንበርን የሚሻገር የጠበቀ ወንድማማችነት ያላቸው ሕዝቦች ናቸው።
ለአብነት ያህል፣ ፉላኒ ጎሳ ከ19 በላይ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ሲገኝ፣ አካን በጋና እና አይቮሪኮስት፣ ኦሮሞ በኢትዮጵያ እና ኬንያ፣ አፋር በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ጅቡቲ፣ እንዲሁም ሶማሌ በቀጣናው የተለያዩ ሀገራት ተሰራጭቶ ይገኛል።
እ.አ.አ በ1902 በቅኝ ገዢዎች በተደረገ የድንበር ከለላ የበርታ ብሔረሰብ በሁለት ተከፍሎ በሱዳን እና በኢትዮጵያ እንዲኖር ተገዷል። ይህን ሐቅ ጠንቅቆ የተረዳው የመደመር ትውልድ፣ እነዚህን ሕዝቦች በፖለቲካ አጥር ማጠር እንደማይቻል በማመን፣ አፍሪካን እንደ አንድ ሕዝብ በማስተሣሠር የማበልጸግ ኃላፊነትን ወስዷል።
ኢትዮጵያ ይህንን የአብሮነት እና የመደመር እሳቤ በተግባር ለማሳየት የሰፋፊ መሠረተ ልማቶችን ትሥሥር እያከናወነች ትገኛለች። የአፍሪካ ኅብረትን አጀንዳ 2063 ለማሳካት እና ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውህደትን እውን ለማድረግ፣ ለጎረቤት ሀገራት ለምሳሌ ለጅቡቲ፣ ለሱዳን እና ለኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ የምጣኔ ሀብት ትሥሥር እያፋጠነች ነው።
ከኬንያ ጋር የተዘረጋው የመንገድ መሠረተ ልማት፣ እንዲሁም በውኃ ተፋሰሶች ላይ የሚሠሩ ታላላቅ ግድቦች የዚሁ ታላቅ ፓን-አፍሪካዊ አሰባሳቢ ትሥሥር አካላት ናቸው።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ባለፉት ሦስት ዐሥርት ዓመታት በሩዋንዳ፣ ላይቤሪያ፣ ሱዳን፣ ብሩንዲ እና ሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮውን በብቃት በመወጣት አህጉራዊ እና ቀጣናዊ መረጋጋትን አረጋግጧል። ይህም ኢትዮጵያ ለፓን-አፍሪካኒዝም ያላትን የተግባር ቁርጠኝነት ያረጋግጣል።
የ21ኛው ክፍለ ዘመን ፓን-አፍሪካኒዝም አፍሪካውያን በቅኝ ገዢዎች የተሰመሩላቸውን የፖለቲካ ድንበሮች በማንሣት፣ አህጉሪቱን ወደ አንድ የጋራ ነጻ ንግድ ቀጣና በማምራት የኢኮኖሚ ነጻነታቸውን የሚያረጋግጡበት ወሳኝ ምዕራፍ ነው።
የአፍሪካ ሕዝብ ብዛት ከ1.4 ቢሊዮን አልፎ ወደፊት በእጥፍ እንደሚያድግ ሲገመት፣ ይህ ታላቅ አምራች ኃይል እና ሰፊ ገበያ ትልቅ የመልማት አቅም ነው። በተጨማሪም አህጉሪቱ የተፈጥሮ ማዕድን፣ ነዳጅ፣ የውኃ ሀብት እና ሊታረስ የሚችል ሰፊ ለም መሬት፣ እንዲሁም የተለያዩ ማዕድናትን ጨምሮ የተትረፈረፈ ጸጋ ባለቤት ናት።
ከምዕራባውያን ገበያ ጥገኝነት ተላቅቀን ይህንን እምቅ ሀብት በማቀናጀት እና የምናመርተውን ምርት እርስ በርስ ብንለዋወጥ ታላቅ ስኬትን እንጎናጸፋለን።
ኢትዮጵያ ትናንት የፖለቲካ ነፃነት ዓርማ እንደነበረች ሁሉ፣ ዛሬ ደግሞ የመደመር ትውልድን በማስተባበር በቀጣናዊ ሰላም፣ በመሠረተ ልማት ዝርጋታ እና በአህጉራዊ ውህደት የላቀ ሚና በመጫወት ላይ ያለች ጽኑ ፓን-አፍሪካዊ ኃይል ናት።
አዲሱ ትውልድ አፍሪካውያን በመተባበር እና በወንድማማችነት ላይ የተመሠረተ ጠንካራ ኅብረት እንዲፈጥሩ በጽናት የቆመ ኃይል ሆኖ ይቀጥላል፤ ምክንያቱም ለአፍሪካውያን ችግር ብቸኛው መፍትሔ ያለው በራሳቸው በአፍሪካውያን እጅ በመሆኑ ነው።
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
#ethiopia #ebc #hornofafrica #medemer #medemergeneration #diplomacy

16 days ago
አሜሪካ ወደ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የ«አትሂዱ» ጥብቅ መመሪያ አስተላለፈች
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም ሀገራትን የፀጥታ ሁኔታ መነሻ በማድረግ በሚያወጣው መመሪያ፣ በርካታ የአፍሪካ ሀገራትን በከፍተኛው የደረጃ 4 የጉዞ ማስጠንቀቂያ ዝርዝር ውስጥ አስፍሯል።
ዋሽንግተን የራሷ ዜጎች ወደነዚህ ሀገራት ፍጹም ጉዞ እንዳያደርጉ ያሳሰበችው በእነዚህ ቀጠናዎች ባለው እጅግ አሳሳቢ የፀጥታ ችግር፣ የሽብርተኝነት ስጋት፣ የእርስ በርስ ግጭቶች፣ የታጠቁ አማፂያን ጥቃት እና ለአሜሪካ ዜጎች የሚሰጠው የቆንስላ ወይም የድንገተኛ ጊዜ ድጋፍ እጅግ ውስን በመሆኑ ነው።
በዚህ የዩናይትድ ስቴትስ የ«አትሂዱ» ጥብቅ መመሪያ ውስጥ ከተካተቱት የአፍሪካ ሀገራት መካከል ቡርኪና ፋሶ፣ ሊቢያ፣ ማሊ፣ ኒጀር፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳንና ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በዋናነት የሚጠቀሱ ሲሆን፣ እንደ ቻድ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያሉ ሀገራት ደግሞ በተለይ ከጎረቤት ሀገራት ጋር በሚያገናኟቸው ድንበሮችና የተወሰኑ ከፍተኛ ስጋት ያለባቸው ግዛቶቻቸው ላይ ተመሳሳይ የደረጃ 4 እገዳ ተጥሎባቸዋል።
በሌላ በኩል ዩጋንዳ በደረጃ 3 (Reconsider Travel ወይም ጉዞን መልሶ ማሰብ) ስር የምትገኝ ሲሆን፣ ዜጎች ወደ ሀገሪቱ ከመጓዛቸው በፊት በወንጀል እና በሽብርተኝነት ስጋቶች ዙሪያ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተመክሯል።
ይህ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየጊዜው የሚሻሻለው የደረጃ 4 የጉዞ ማስጠንቀቂያ ከአፍሪካ ውጭ እንደ ሩሲያ፣ ዩክሬን፣ አፍጋኒስታን፣ ሰሜን ኮሪያ፣ የመን፣ ሶሪያ፣ ቬንዙዌላ፣ ኢራን እና ጋዛን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የጦርነትና የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ያሉ የዓለማችን አካባቢዎችንም ያጠቃልላል።

17 days ago
ተስፋን በምድራችን፦ የ50 ቢሊዮን ችግኝ ራዕይ
**********************
(የዕለቱ መልዕከት)
የዘንድሮው ክረምት የሀገራችንን የ50 ቢሊዮን ችግኞች ተከላ ግዙፍ ራዕይ ሙሉ በሙሉ እውን በማድረግ የምናጠናቅቅበት ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።
ዛሬ በምድራችን ላይ የምናኖረው እያንዳንዱ አረንጓዴ ዐሻራ፣ ዓለም አቀፉን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ከመቋቋም ባለፈ ታላቅ ሀገራዊና አሕጉራዊ የኢኮኖሚ ፋይዳ አለው።
ይህ ግዙፍ ብሔራዊ ንቅናቄ አሁን እንደ ጀመርነው ሀገራዊ ምክክር ሁሉ ልዩነቶቻችንን ወደ ጎን ትተን ኢትዮጵያን በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት የሚያስችለን ታላቅ ፕሮጀክት ነው።
ቀደም ባሉት ዘመናት እጅግ ሰፊ የደን ሽፋን የነበራት ሀገራችን፣ በሕዝብ ቁጥር መጨመርና በደን ምንጣሮ ምክንያት ሀብቷ ተመናምኖ፣ ለአፈር መሸርሸርና ለግብርና ምርታማነት መቀነስ ተጋልጣ መቆየቷ ይታወሳል።
ይህን ፈተና ለመቀልበስ በ2011 ዓ.ም የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ እስካሁን ከ40 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት ቀዳሚ ተዋናይ አድርጓታል።
በዚህ ንቅናቄ እየተተከሉ ያሉ ችግኞች የደን ዛፎች ብቻ ሳይሆኑ እንደ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ አፕል፣ ቡናና ሻይን የመሳሰሉ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው በመሆናቸው የአርሶ አደሩን የኑሮ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀየሩት ይገኛሉ።
ለሚሊዮኖች የሥራ ዕድል የፈጠረው ይህ ፕሮጀክት ለሀገር በቀል የአግሮ-ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪዎች ወሳኝ የጥሬ ዕቃ ግብዓት ምንጭ በመሆን ላይ ነው።
የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄያችን ከአየር ንብረት ጥበቃና ከምግብ ዋስትና ባሻገር እጅግ ግዙፍ ከሆነው ዓለም አቀፉ የካርበን ገበያ (Carbon Market) በትልቁ ተጠቃሚ እንድንሆን በሩን ከፍቶልናል።
በአረንጓዴ ዐሻራ የምንተክላቸው ቢሊዮን ዛፎች ከከባቢ አየር ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው በካይ ጋዝ የመምጠጥ አቅም ስላላቸው፣ ለሀገራችን አዲስና ዘላቂ የውጭ ምንዛሬ ማግኛ መስመር እየከፈቱ ነው።
የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ ቀጣናዊ ትስስርን በማጠናከር ረገድም የጎላ ድርሻ አለው። ለጅቡቲ፣ ለኬንያ፣ ለሶማሊያ እና ለደቡብ ሱዳን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በነፃ በማካፈል የጋራ ዕድገት ራዕያችንን በተግባር እያሳየን እንገኛለን።
ከዚህ ጎን ለጎን መርሐ-ግብሩ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶቻችንን ከጎርፍ እና ከደለል በመጠበቅ የአገልግሎት ዘመናቸውን ያራዝማል።
የሕዝብን ንቁ ተሳትፎ በማረጋገጥ ከ80 በመቶ በላይ የጽድቀት ምጣኔን ያስመዘገበው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ከተለመደው ዓይነት ችግኝ ተከላ በእጅጉ የላቀ አንደምታ ያለው ነው።
አረንጓዴ ዐሻራችን የተፈጥሮ ጸጋችንን በአግባቡ በመጠቀም ለተተኪው ትውልድ የሚበቅል፣ የሚለምልምና የሚጠቅም ሕያው ቅርስ የምናወርስበት የአዲሱ አረንጓዴ ኢኮኖሚያችን ጽኑ መሠረት በመሆኑ፣ ሁላችንም በአንድነት ዐሻራችንን ማኖራችንን እንቀጥል!
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

24 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በሶማሊያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ፣ አንዳንድ የሶማሊያ የጸጥታ ኃይል አባላት የአሜሪካን ብሔራዊ ባንዲራ ሲያዋርዱ (ሲያረክሱ) የሚያሳይ ቪዲዮ መውጣቱን ተከትሎ፣ ይህ አይነቱ ፀረ-አሜሪካ ድርጊት የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት በእጅጉ እንደሚጎዳ አስጠነቀቀ።
ኤምባሲው በኤክስ ገጹ ባወጣው መግለጫ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለሶማሊያ በቢሊዮን የሚቆጠር የግብር ከፋዮቿን ገንዘብ በእርዳታ መልክ ስትሰጥ መቆየቷን አስታውሷል። በተለይም የአሜሪካ ህዝብ በቅን ልቦና፣ አሜሪካንን እና በቀጥታ ደግሞ የሶማሊያን ህዝብ ኢላማ የሚያደርጉ አሸባሪ ድርጅቶችን ለማጥፋት ለሚደረገው ወታደራዊ እርምጃ የረጅም ጊዜ ጽኑ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አብራርቷል።
ይሁንና ይህንን አሳፋሪ ድርጊት በፈጸሙት የጸጥታ ኃይል አባላት ላይ የሶማሊያ ፌደራላዊ መንግስት የወሰደውን ፈጣን ምላሽ እና ቆራጥ እርምጃ ኤምባሲው እንደሚያደንቅ ገልጿል።
መግለጫው "በሶማሊያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማበላሸት የሚንቀሳቀሱ እኩይ ኃይሎች የሚጎዱት የሶማሊያን ህዝብ ነው፤ ስለሆነም እነዚህ አካላት በሕግ ተጠያቂ መሆናቸው ሊቀጥል ይገባል" ሲል ጥብቅ መልእክት አስተላልፏል።

25 days ago
የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ለስድስት አገራት ዜጎች የተሰጠውን በአሜሪካ የመቆየትና የመሥራት ጊዜያዊ ሕጋዊ ከለላ ለተጨማሪ ቀናት አራዘመ።
የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ለስድስት አገራት ዜጎች የተሰጠውን በአሜሪካ የመቆየትና የመሥራት ጊዜያዊ ሕጋዊ ከለላ ለተጨማሪ ቀናት አራዘመ። በአሜሪካ የአገር ውስጥ ደሕንነት መሥሪያ ቤት ሥር የሚገኘው የዜግነትና የፍልሰት አገልግሎት በአገሪቱ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተሰጠው ከለላ በመጪው ሐምሌ 10 ቀን 2018 እንደሚያበቃ ትላንት አርብ አስታውቋል።
ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ለሶርያ፣ ሶማሊያ፣ የመን፣ ደቡብ ሱዳን እና ምያንማር ዜጎች የተሰጠው ጊዜያዊ ከለላ በተመሣሣይ ቀን ያበቃል። ውሳኔው የሚመለከታቸው የሔቲ ዜጎች ከቀሪዎቹ አምስት አገራት አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ በአሜሪካ ለመቆየትና ለመሥራት የሚፈቅድላቸውን ከለላ ያጣሉ።
ይህ ከለላ የተፈጥሮ አደጋ፣ የትጥቅ ግጭት ወይም ሌሎች ያልተለመዱ አስገዳጅ ሁኔታዎች ከገጠማቸው አገራት ወደ አሜሪካ የገቡ ሰዎች በአገሪቱ እንዲቆዩ እና በሕጋዊ መንገድ እንዲሠሩ የሚፈቅ ነው። ከለላው የተሰጣቸው በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ቢመለሱ “በግል ደሕንነታቸው ብርቱ ሥጋት አይገጥማቸውም” በሚል አመክንዮ በአገሪቱ የመቆየትና የመሥራት ዕድላቸው እንዲያበቃ የተወሰነው ባለፈው ታኅሳስ 2018 ነበር። ይሁንና ውሳኔው በቦስተን በሚገኝ የማሳቹሴትስ አውራጃ ፍርድ ቤት ታግዷል።
ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ሶማሊያና ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ የ10 አገራት ዜጎች ተመሳሳይ ሕጋዊ ጥበቃ ነበራቸው። የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባለፈው ወር የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የሔቲና የሶርያ ዜጎች የተሰጠውን ጊዜያዊ ከለላ ማብቃት እንደሚችል ውሳኔ አሳልፏል። የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕጋዊ ጥበቃ እንደሚያሳጣ የመብት ተሟጋቾችና በአሜሪካ የሚገኙ የተለያዩ ማኅበረሰቦች መሪዎች ሥጋት አላቸው
DW Amharic

26 days ago
ከፖለቲካ ሽኩቻ የላቀው የጋራ ተቋማችንን እናክብር
****************
የአንድ ሀገር ጥንካሬ ከሚገለጽባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች መካከል አንዱ ዜጎች በጋራ የሚግባቡባቸው እና በኩራት የሚጠሯቸው ጠንካራ ብሔራዊ ተቋማት መኖራቸው ነው።
ከእነዚህ ተቋማት መካከል ደግሞ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀዳሚውን እና የክብር ማማውን ስፍራ ይይዛል።
የዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ስንመለከት፣ በሠለጠኑ ዴሞክራሲያዊ ሀገራት የሠራዊት አባላትን ማክበር ከፖለቲካዊ ሽኩቻዎች የላቀ ብሔራዊ መግባባት የተገነባበት ጉዳይ ሆኖ እናገኘዋለን።
በአሜሪካ የፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ በፓርቲዎች መካከል የጎላ ርዕዮተ ዓለማዊ ልዩነት ቢኖርም፣ ሠራዊቱን ከፖለቲካ ፉክክር ውጪ የማድረግ ብሔራዊ ስምምነት አለ።
የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንግሥትን ፖሊሲ በሚተቹበት ወቅት እንኳ በጦር ግንባር የተሰማሩትን ወታደሮች እንደ ጀግና በመቁጠር ውዳሴ እና ክብር ያቀርባሉ።
በዩናይትድ ኪንግደም "የጦር ኃይሎች ቃል ኪዳን" (Armed Forces Covenant) የተሰኘው ብሔራዊ ሰነድ የሠራዊት አባላት ልዩ ክብር እንዲያገኙ ያደርጋል።
ካናዳ ለአርበኞች ልዩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ስታቋቁም፣ ፈረንሳይ ደግሞ ሠራዊቷን የሀገሯ የክብር እና የአጋርነት ብሔራዊ ተምሳሌት በማድረግ በትልቅ ማዕረግ ትዘክራለች።
ወደ ሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ስንመጣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በባሕርይው እጅግ ሕዝባዊ የሆነ፣ ከሀገር አልፎ ለዓለም የሰላም ዘብ በመሆን ደሙን የገበረ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው።
የኢትዮጵያ ወታደር በኮሪያ ልሳነ ምድር በቃኘው ሻለቃ አማካኝነት "አንድም ወታደር አልተማረከም፤ የሞተ ጓዱንም ጥሎ አልመጣም" የሚል የዓለምን አስደናቂ ሪከርድ ያስመዘገበ ጀግና ነው።
በኮንጎ፣ በሩዋንዳ፣ በቡሩንዲ፣ በላይቤሪያ፣ በአብዬ፣ በዳርፉር እና በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ላይ በመሰማራት አፍሪካውያን ወንድሞቹን ከእልቂት የታደገ፣ የራሱን ሬሽን እያካፈለ የውጭ ሀገር ዜጎችን ያኖረ የሰብአዊነት ተምሳሌት ነው።
ይህ ሠራዊት በሀገር ውስጥም ቢሆን ጦር መሣሪያውን አስቀምጦ በክረምት የገበሬውን ማሳ ሲያርስ እና በመኸር ሲያጭድ፣ የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ከነፍስ አድን ሥራ እስከ አንበጣ መንጋ ማባረር ድረስ ከሕዝቡ ጎን የቆመ ታላቅ አለኝታ ነው።
ነገር ግን አለመታደል ሆኖ፣ የሀገራችን መከላከያ ሠራዊት በፖለቲካ ኃይሎች መካከል በሚደረጉ ፍልሚያዎች ውስጥ የከፉ ምኞቶች ሰለባ ሲሆን ይስተዋላል።
አንዳንዴም የፖለቲካ ልዩነትን እና የሀገርን የፀጥታ ምሰሶ መለየት ያቃታቸው አካላት ሠራዊቱን የማንቋሸሽ አዝማሚያ ያሳያሉ።
የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ማክበር እና ለሀገር ሕልውና የሚከፍለውን ዋጋ ማወቅ የአንድ ማኅበረሰብ የሥልጣኔ መገለጫ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተደጋጋሚ አስገንዝበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ በፓርላማ ባደረጉት ንግግር፣ ሀገርን ጠብቆ የሚያኖርን ኃይል እንደ "ገዳይ" መፈረጅ እና ተቋማዊ ክብሩን አለማወቅ የሲቪል-ወታደራዊ ግንኙነትን አለመረዳት እና ያለመሠልጠን ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
መንግሥት እና ፖሊሲ አውጪዎችን በጥብቅ መተቸት የዴሞክራሲ አካል ነው። ነገር ግን ለሀገር ሕልውና አጥንቱን የሚከሰክሰውን ሠራዊት ከተቋማዊ ትችት ነፃ አድርጎ በጀግንነት መዘከር ይገባል።
በመሠረቱ ሠራዊቱ ሕዝብን የመጠበቅ ግዴታ ሲኖርበት፣ መንግሥት እና ሕዝብ ደግሞ የሠራዊቱን መሥዋዕትነት የመካስ የሞራል ግዴታ አለባቸው።
ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ትኩረት አድርጋ ከሠራችባቸው የሪፎርም ሥራዎች መካከል የፀጥታ ተቋማት ግንባታ ዋነኛው የሆነውም ለዚሁ ነው።
ሠራዊታችን ከፖለቲካ ልዩነቶቻችን በላይ የሆነ የጋራ የብረት አጥራችን እና የሕልውናችን ምሰሶ በመሆኑ ዘወትር ክብር እና ሞገስ ይገባዋል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #endf #nationalpride #standwithourtroops

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የፈረንሳዩ ሉ ሞንድ ጋዜጣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በሶማሊላንድ ለአሜሪካ እና ለእስራኤል ወታደራዊ የጦር ሰፈር በድብቅ እየገነባች ነው የሚል ርዕስ ያለው ዘገባ አሳትሟል። ዘገባው እንደሚያመለክተው፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና በሌላት ሶማሊላንድ ውስጥ የሚገኘው የበርበራ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ለውቅያኖስ ትራንስፖርት እጅግ አስፈላጊ ከሆኑት የዓለም የባህር መስመሮች አቅራቢያ ለአቡ ዳቢ፣ ቴል አቪቭ እና ዋሽንግተን ጥቅም ሲባል ወደ ወታደራዊ የጦር ሰፈርነት እየተቀየረ ይገኛል።
ዋና ከተማዋ ሀርጌሳ የሆነችው ሶማሊላንድ፣ በዓለም ላይ እጅግ ከሚበዛባቸው የባህር ላይ የንግድ መስመሮች አንዱ በሆነው የኤደን ባህረ ሰላጤ ላይ ትገኛለች። ወደ ስምንት መቶ ኪሎ ሜትር የሚጠጋ የባህር ዳርቻ ያላት ሲሆን፣ የበርበራ ወደብ በእስያ እና በአውሮፓ መካከል ለሚደረገው ዓለም አቀፍ ንግድ እና የኃይል አቅርቦት እጅግ ወሳኝ ከሆኑት የዓለም የውሃ መስመሮች አንዱ ለሆነው የባብ አል ማንደብ ባህረ ሰላጤ ቅርብ የሆነ ስትራቴጂካዊ ቦታን ይዟል። በአስራ ዘጠኝ ዘጠና አንድ (እ.ኤ.አ) ከሶማሊያ ነፃነቷን ያወጀችው ይህች ቀጠና፣ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የቀጠናው እና የዓለም አቀፍ ኃይሎች የትኩረት ማዕከል ሆናለች። የግብጽ፣ የአረብ እና የእስልምና ሀገራት ተቃውሞ ቢያሰሙም፣ ይህ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታዋ እስራኤል ቀጠናዋን እንደ ነፃ ግዛት እንድትገነዘብ ገፋፍቷታል።
ሉ ሞንድ አክሎ እንደዘገበው በእስራኤል እና በሶማሊላንድ መካከል ያለው የደህንነት ትብብር በወታደራዊ እና የስለላ ልዑካን የጋራ ጉብኝቶች፣ የሶማሊላንድ መኮንኖች በቴል አቪቭ በሚያደርጉት ስልጠና፣ እንዲሁም የእስራኤል ወታደራዊ ቡድኖች በበርበራ የጦር ሰፈር በሚያደርጉት ጉብኝት ምክንያት እያደገ መጥቷል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በሰብአዊ ጥበቃ መርሃ-ግብር (TPS) ስር አሜሪካ ውስጥ ለሚኖሩ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ስደተኞች የተሰጠው የሥራ ፈቃድ ሊያበቃ ጥቂት ሰዓታት ሲቀሩት ማራዘሚያ መስጠቱን የአሜሪካ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
የሥራ ፈቃዱ መቋረጥ ለዓመታት አሜሪካ ውስጥ በሕጋዊ መንገድ ሲኖሩና ሲሰሩ የነበሩ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የጊዜያዊ መከላከያ ሁኔታ (TPS) ተጠቃሚዎች ሥራቸውንና ገቢያቸውን እንዲያጡ ሊያደርግ ይችል ነበር። ይህ የሥራ ፈቃድ ማራዘሚያ የተሰጠው፣ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለፈው ወር የትራምፕ አስተዳደር እስከ 1.3 ሚሊዮን ለሚደርሱ ስደተኞች የተሰጠውን ሰብአዊ ጥበቃ እንዲሰርዝ እና በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ወደ ሀገራቸው እንዲባረሩ መንገድ የሚከፍት ውሳኔ ባሳለፈበት ማዕቀፍ ውስጥ ነው።
የአሜሪካ የዜግነት እና የስደተኞች አገልግሎት (USCIS) ባወጣው አዲስ መረጃ መሠረት፣ የሄይቲ ስደተኞች የሥራ ፈቃድ እስከ ጁላይ 24 የተራዘመ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ፣ ሚያንማር፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶርያ፣ የመን እና ሶማሊያ የቲፒኤስ (TPS) ተጠቃሚዎች የሥራ ፈቃድ ደግሞ እስከሚቀጥለው ሳምንት ዓርብ ድረስ እንዲያበቃ ተወስኗል።
እነዚህን ሰራተኞች ቀጥረው የሚያሰሩ የተለያዩ ዘርፎች; ከአረጋውያን መንከባከቢያ እና ሆስፒታሎች እስከ ትምህርት ቤቶች እና አውሮፕላን ማረፊያዎች- ከፍተኛ ውጥንቅጥ ውስጥ የገቡ ሲሆን፣ ከትራምፕ አስተዳደር መፍትሄ እንዲሰጣቸው በስተጀርባ እየተማጸኑ ይገኛሉ። እንደ ሰራተኞች ማህበራት መረጃ ከሆነ አንዳንድ ቀጣሪዎች ከዛሬው ዕለት በፊት የቲፒኤስ ባለመብቶችን ከሥራ ማሰናበት ጀምረው ነበር።
የፍሎሪዳ ትልቁ የጤና ጥበቃ ሰራተኞች ማህበር (1199SEIU) መሪ የሆኑት ማርጋሬት ኔሬት በጉዳዩ ላይ ሲናገሩ “በጣም ከፍተኛ የሆነ ግራ መጋባት ነው ያለው፤ እኛ ሰራተኛ ህዝቦች ነን፣ እነሱ ግን እንደ ቆሻሻ እያዩን ነው” ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

1 month ago
በ #ሱዳን በተፈጸሙ አስከፊ ወንጀሎች ውስጥ እጃቸው አለበት የተባሉ ከፍተኛ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣የ #ኢትዮጵያ እና የቀጠናው ባለሥልጣናት ላይ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ምርመራ እንዲደረግ ተጠየቀ‼️
ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች እና የሕግ ድርጅቶች ጥምረት፤ በሱዳን ዳርፉር ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ለተፈጸሙ አስከፊ ወንጀሎች ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ረገድ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ፣ የኢትዮጵያን ጨምሮ የቻድ፣የሶማሊያ፣ የሊቢያ እና የኬኒያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ምርመራ እንዲያደርግ ጠየቀ።
ሚድል ኢስት አይ ባወጣው ዘገባ መሠረት፤ ይህ ጥሪ ሰኞ ዕለት የቀረበው፤ ራውል ዋለንበርግ የሰብአዊ መብቶች ማዕከል (RWCHR) ከተለያዩ የሕግ፣ የምርመራ እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት ጋር በመሆን የቀረበ ነው። አቤቱታው የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዓቃቢያነ ሕግ የውጭ አገር ባለሥልጣናትና አሸማጋዮች በሱዳን ተፋላሚ ወገኖች የተፈጸሙ ወንጀሎችን ሆን ብለው በማገዝ ወይም በማበረታታት ረገድ የተሳተፉ መሆኑን እንዲመረምሩ ይጠይቃል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ በነጻነት ቀን ንግግራቸው ላይ ያነሱት "የታላቋ ሶማሊያ" ሀሳብ፣ ይህ ርዕዮተ ዓለም ሀገሪቱን ወደ አስከፊ ግጭት ከከተታት ከአስርት ዓመታት በኋላ ዳግም የተነሳ ነው። ይህ የሆነውም የሶማሊያ ጦር በአንድ ወቅት 'የኔ ናቸው' ብላ በምትሞግታቸው የጎረቤት ሀገራት ጦር ከተተካ ከረጅም ጊዜ በኋላ መሆኑ አነጋጋሪ አድርጎታል።
ንግግሩ በአቀራረቡ የተመጠነ ቢመስልም፣ አንድምታው ግን እጅግ ስሜት ቀስቃሽ ነበር። የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ በዚህ ሳምንት በተከበረው የሀገሪቱ የነጻነት በዓል ላይ ለህዝባቸው ባደረጉት ንግግር፣ አሁን ስላችው እና ከሶስት አስርት ዓመታት የእርስ በርስ ጦርነት ገና እያገገመች ስላችው ሶማሊያ ብቻ አልተናገሩም፤ ይልቁንም በብሔርተኞች አስተሳሰብ ገና ስላልተጠናቀቀችው "ታላቋ ሶማሊያ" ጭምር እንጂ።
"ዛሬ በሶማሊያ የሚታየው ተስፋ እ.ኤ.አ. በ1960 በውህደት በተመሰረተችው የሶማሊያ ሪፐብሊክ ላይ ብቻ የተወሰነ አይደለም፣" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ። በማከልም "ይህ ተስፋ ሌሎች ሶስቱ የጠፉ የሀገሪቱ አካላትም በተመሳሳይ ጉጉት እና ተስፋ የሚጠባበቁት እና የሚጋሩት ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
በሶማሊያ የፖለቲካ ታሪክ አውድ ውስጥ በስፋት እንደሚታወቀው፣ እነዚህ "ሶስት የጠፉ አካላት" የተባሉት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል፣ የኬንያ ሰሜን ምስራቅ ግዛት እና የጅቡቲ ሪፐብሊክ ናቸው። የሶማሊያ ብሔርተኞች እነዚህን ግዛቶች የቅኝ ግዛት ድንበሮች እንዳይዋሃዱ ያደረጓቸው እና የተቆረጡ የሀገሪቱ አካላት አድርገው ለረጅም ጊዜ ሲቆጥሯቸው ቆይተዋል።
ፕሬዝዳንቱ በዚህ ንግግራቸው ምን ማለታቸው እንደሆነ በዝርዝር አላብራሩም፤ ማብራራትም አላስፈለጋቸውም። ሀሳቡ በራሱ እጅግ የቆየ እና ትልቅ ትርጉም የሚሰጥ በመሆኑ፣ ጉዳዩን ማንሳታቸው ብቻ የራሱ የሆነ ከባድ ፖለቲካዊ እና ቀጠናዊ ክብደት አለው።

"ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ መሃሙድ ጋር በኢኮኖሚያዊ ትስስር፣ ደኅንነት እና የቀጠናዊ መረጋጋት ዙሪያ በመተማመንና በመከባበር ላይ የተመሠረተ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል።" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
1 month ago
“ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከድንበር በላይ የሚጋሩት ነገር አለ፤ እሱም እጅግ ውድ የሆነውን ሕዝባችንን እና የጋራ ዕጣ ፈንታችንን ነው”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#ethiopia #ebc #ebcdotstream #diplomacy #pmoethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#ethiopia #ebc #ebcdotstream #diplomacy #pmoethiopia
1 month ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ አቃብያነ ህግ በሚኒሶታ ክፍለ ግዛት በተፈጸመው የ250 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ማጭበርበር ወንጀል ውስጥ ቁልፍ ተጠርጣሪ የሆነውን የ42 ዓመቱን አብዲከሪም አብዱላሂ ኤይድሌህን በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በቁጥጥር ስር አውለዋል። ሀሙስ ዕለት በቁጥጥር ስር የዋለው ይህ ግለሰብ፣ የተያዘው በአሜሪካው የፌደራል ምርመራ ቢሮ (FBI) እና በሶማሊያ ብሔራዊ የስለላ እና ደህንነት ኤጀንሲ ጥምር የኦፕሬሽን ስራ መሆኑን የአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ካሽ ፓቴል በኤክስ ገጻቸው ዛሬ ባሰፈሩት መግለጫ እርምጃውን ያደነቁ ሲሆን፣ አብዲከሪም ኤይድሌህ በሀገሪቱ ታሪክ ከተፈጸሙት ታላላቅ የማጭበርበር ቅሌቶች አንዱን የመራ ግለሰብ መሆኑን ገልጸዋል። ዳይሬክተሩ አክለውም ግለሰቡ ድጋፍ ለሚሹ እና ለተጋለጡ አሜሪካውያን የምግብ አቅርቦት የተመደበውን 250 ሚሊዮን ዶላር በመዝረፍ ለቅንጦት መኪናዎች እና ለግዙፍ ቪላ ቤቶች ማዋሉ እጅግ እፍረተ-ቢስ ተግባር እንደሆነ አስታውቀዋል። ኤፍቢአይ ይህንን "Feeding our Future" የተሰኘውን የሙስና ኔትወርክ ስልታዊ በሆነ መንገድ እያፈረሰው መሆኑን እና እስካሁንም ከ70 በላይ የቡድኑን አባላት በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጸዋል።
ወንጀሉ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ለችግረኛ ህጻናት ምግብ ማቅረቢያነት ከፌደራል መንግስት የተመደበውን የዕርዳታ ገንዘብ መዝረፍን ያካተተ ነው። ኤይድሌህ፣ ከ40 ዓመት በላይ እስራት የተፈረደባት እና የዚህ ማጭበርበር ዋና ጠንሳሽ የሆነችው ኤሚ ቦክ ምክትል ሆኖ ይሰራ እንደነበር አቃብያነ ህግ ይገልጻሉ። ተጠርጣሪው ሀሰተኛ የምግብ ማከፋፈያ ጣቢያዎችን በመክፈት፣ በቀን በሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናትን እንደመገበ በማስመሰል እና ያልቀረበ ምግብ ለመንግስት በማስከፈል በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ዘርፏል።
በሚኒሶታ የአሜሪካ አቃቤ ህግ ዳንኤል ሮዘን ግለሰቡን የህዝብን ገንዘብ በመዝረፍ እና ጉቦ በመቀበል ወንጀል የተካነ "ትልቅ ዓሳ" ሲሉ ገልጸውታል።
ይህ የማጭበርበር ወንጀል፣ የትራምፕ አስተዳደር በሚኒሶታ በሚኖረው እና በአሜሪካ ትልቁ የሶማሊያ-አሜሪካውያን ማህበረሰብ ላይ ጥብቅ እርምጃዎችን እንዲወስድ መነሻ ሆኗል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሶማሊያን የጉዞ እገዳ ከተጣለባቸው ሀገራት ተርታ የደለደሉ ሲሆን፣ በማጭበርበር ወንጀል የተፈረደባቸው ዜግነት ያገኙ አሜሪካውያንን ዜግነት እንደሚገፉ ዝተዋል።
የፌደራል የኢሚግሬሽን አስከባሪ ኤጀንቶች በሚኒያፖሊስ ያደረጉትን መጠነ-ሰፊ አፈሳ ተከትሎ በጸጥታ ኃይሎቹ ግለሰቦች መገደላቸው ለሳምንታት የዘለቀ ህዝባዊ ተቃውሞን አስነስቷል። በተጨማሪም ለ1,100 ያህል ሶማሊያውያን ከለላ ሲሰጥ የቆየውን ጊዜያዊ የጥበቃ ሁኔታ (TPS) ለማንሳት በመንግስት የተወሰደው እርምጃ በፌደራል ዳኛ ውድቅ ተደርጎ የህግ ክርክሩ ቀጥሏል።

የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ሶማሊያ ዜጎች ወደ ምሥራቅ ሊቢያ ግዛት እንዳይገቡ ታገዱ።
ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ጨምሮ ወደ አውሮፓ መሻገር የሚፈልጉ የአራቱ አገራት ፍልሠተኞች በሊቢያ በኩል በሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት እንደሚያልፉ ይታወቃል።
የምሥራቅ ሊቢያ ባለሥልጣናት ይህን እገዳ የጣሉት፣ የውጭ ዜጎች ወደ አገሪቱ የሚገቡበትን ሁኔታ ለመቀየር በማስፈለጉ እንደሆነ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
እገዳው፣ ዲፕሎማቶችን፣ የቆንስላ ሠራተኞችንና ቤተሰቦቻቸውን እንዲኹም የቅጥር ፍቃድ ያላቸው በትምህርትና ሕክምና ዘርፍ የተሠማሩ የአገራቱን ሠራተኞች እንደማይመለከት ተገልጧል።
ባሁኑ ወቅት 900 ሺሕ ያህል የውጭ ዜግነት ያላቸው ፍልሠተኞች ሊቢያ ውስጥ እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።

የሊቢያ መንግሥት ባለሥልጣናት የአራት አጎራባች የአፍሪቃ ሃገራት ዜጎች ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ አገዱ
የምሥራቅ ሊቢያ መንግሥት ባለሥልጣናት የአራት አጎራባች የአፍሪቃ ሃገራት ዜጎች ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ አገዱ። የባለሥልጣናቱ እርምጃ በምዕራባዊ የሊቢያ የባሕር ወደብ በኩል ወደ አውሮጳ ለመሻገር የሚያልሙ ተሰዳጆችን ቁጥር ለመቀነስ ያለመ መሆኑ ተገልጿል። በሊቢያ ባለሥልጣናት እገዳ የተጣለባቸው የሱዳን፤ የኤርትራ፣ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ዜጎች መሆናቸው ተገልጿል። የሊቢያ የባሕር ወደብ የተሻለ ሕይወትን አልመው ወደ አውሮጳ ለመሰደድ የሚሞክሩ በርካታ የአፍሪቃ ተሰዳጆች የሚያዘወትሩት መሸጋገሪያ መስመር ነው።
ተሰዳጆቹ በሕገወጥ ሰው አሸጋጋሪዎች አማካኝነት ለጉዞ አስተማማኝ ባልሆኑ ትናንሽ ጀልባዎች ከመጠን በላይ ተጠቅጥቀው የሚሳፈሩ ሲሆን ባሕር ላይ በሚያጋጥመው አደጋ በሺህዎች የሚቆጠሩት ካሰቡበት ሳይደርሱ ሕይወታቸው እንደሚቀጠፍ በየጊዜው ይዘገባል። ትናንት ይፋ የተደረገው እገዳ የሱዳን፤ የኤርትራ፤ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ተሰዳጆች በየብስም ሆነ በባሕር እና በአየር ወደ ሊቢያ ግዛት እንዳይገቡ ከልክሏል። መግለጫው አክሎም ክልከላው ዲፕሎማቶች፤ የጤና እና የትምህርት ዘርፍ ሠራተኞችን እንደማይመለከት አስታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ ከሌላ ሃገር ወደ ሊቢያ የሚላኩ ስደተኞችን ጉዳይ በተመለከተ በምሥራቅ እና ምዕራብ የሊቢያ መንግሥታት መካከል ላለፉት ወራት ውጥረት አስነስቷል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንደሚለው ስደተኞች ላይ በተደረገው ክትትል በሺህዎች የሚቆጠሩ በዚሁ ምክንያት ታስረዋል። የተመድ መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ሊቢያ ውስጥ ከ900 ሺህ በላይ ስደተኞች ይገኛሉ። ከእነዚህ መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት የሱዳን ዜጎች ናቸው። አብዛኞቹ ስደተኞች ወደ አውሮጳ ለመሻገር የሚፈልጉ ቢሆንም ስደተኞችን የጫኑ ጀልባዎች በባሕር ላይ ቃኚዎች እየተያዙ ወደ ሊቢያ እንዲመለሱ እየተደረገ ነው። ስደተኞቹ በሊቢያ መንግሥታት እስር ቤቶች የሚያዙ ሲሆን እንግልት፤ የግዳጅ የጉልበት ሥራ፤ ድብደባ፣ አስገድዶ መድፈር እና ማሰቃየት እንደሚፈጸምባቸው ተገልጿል። የተመድ መርማሪ ኮሚሽንም ስደተኞቹ ላይ የሚደርሰውን እንግልት በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል ነው ብሎታል።

"በጣሊያን የሚገኝ አንድ ጥንታዊ የኦስትሮ-ሀንጋሪ ቤተ መንግስትን በጎበኘሁበት ወቅት፣ ከዘመናት በፊት የተሳለ አንድ ታሪካዊ የአፍሪካ ቀንድ ካርታን አየሁ። እናም እውነታው ምን መሰላችሁ... ልክ እንደ ዛሬው ሁሉ፣ በዚያን ጊዜም ቢሆን ሶማሊያ ሶማሊላንድን በውስጧ አላካተተችም ነበር!"
- አምባሳደር ቲቦር ናጅ የምታዩትን ካርታ ለጥፈው ያስተላለፉት መዕልክት

2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት አብዱራህማን መሀመድ አብዱላሂ (ኢሮ)፣ አስተዳደራቸው ተጨማሪ ዓለም አቀፍ እውቅና ለማግኘት በማለም ከአሜሪካ እና ከኢትዮጵያ ጋር ክፍት የሆነ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዳለው አስታወቁ።
ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያስታወቁት በኢየሩሳሌም ከሚገኘው 'አይ24ኒውስ' የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ነው። የፕሬዝዳንት ኢሮ ይፋዊ ጉብኝት፣ እስራኤል ባለፈው ዓመት መገባደጃ ላይ ለሶማሌላንድ ይፋዊ እውቅና መስጠቷን ተከትሎ የተካሄደ ነው።
የዲፕሎማሲያዊ እውቅናን በተመለከተ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ስላላቸው የግንኙነት መስመር ተጠይቀው፣ ፕሬዝዳንት አብዱላሂ "ክፍት የሆኑ የግንኙነት መስመሮች አሉን" ሲሉ መልሰዋል። አክለውም እንደ ኢትዮጵያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ኬንያ የመሳሰሉ የቀጠናው አገራት አሁንም የሃርጌሳ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ቀዳሚ ትኩረቶች መሆናቸውን አረጋግጠዋል። "አዎ ናቸው፤ ለእነሱም ቢሆን ክፍት የግንኙነት መስመሮች አሉን" ብለዋል።
ይህ የዲፕሎማሲያዊ ግፊት የሚመጣው ሶማሌላንድ በእስራኤል ህልውናዋን እያጠናከረች ባለችበት ወቅት ነው። ፕሬዝዳንቱ በቃለ ምልልሳቸው የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት በማንሳት፣ ሶማሌላንድ ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነጻ በወጣችበት እ.ኤ.አ ሰኔ 26 ቀን 1960 እስራኤል እውቅና ሰጥታት እንደነበር አስታውሰዋል።
በግንቦት 2025 ሃርጌሳ ለ193 አገራት በጻፈችው ጥያቄ መሰረት፣ እስራኤል በታህሳስ 26 ቀን 2025 ለሶማሌላንድ ለሁለተኛ ጊዜ እውቅና ሰጥታለች። ፕሬዝዳንት አብዱላሂ እንዳሉት፣ እስራኤል የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ውሳኔዎቿን በቀጠናዊ እውነታዎች ላይ በመመስረት ለጥያቄው ምላሽ የሰጠች ብቸኛ አገር ሆናለች። በመሆኑም ሃርጌሳ ስትራቴጂዋን ለማስፈጸም በኢየሩሳሌም ኤምባሲዋን እየከፈተች ሲሆን፣ በአንጻሩ ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ ቀንድ የንግድ በር የሆነውን የበርበራ ወደብ መጠቀም የሚያስችል እድል እያቀረበች ትገኛለች።
ፕሬዝዳንት አብዱላሂ ሶማሌላንድ "ከሶማሊያ የተገነጠለች ክልል ነች" ተብላ የምትጠራበትን አገላለጽ ውድቅ በማድረግ፣ ግዛቷ በ1960 ሶማሊያ መንግስት ከመመስረቷ በፊት የራሷን ሉዓላዊነት ተቀዳጅታ እንደነበር ሞግተዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በተመለከተ፣ ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የባህር በር ተደራሽነትን እና የፖለቲካ እውቅናን ያካተተ የመግባቢያ ስምምነት (MoU) እ.ኤ.አ ጥር 1 ቀን 2024 መፈራረማቸው ይታወሳል። ይሁን እንጂ ከአፍሪካ ህብረት እየጨመረ የመጣው ቀጠናዊ የዲፕሎማሲ ጫና፣ እንዲሁም በአንካራው ስምምነት መሰረት በቱርክ አሸማጋይነት በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተካሄደው ድርድር የስምምነቱን ትግበራ አግዶታል። ይህ ሁኔታ ኢትዮጵያን የቀይ ባህር ተደራሽነት ለማግኘት ሌሎች ስትራቴጂካዊ አማራጮችን እንድትመረምር አስገድዷታል።

ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ተምሳሌት ያደረገው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአረንጓዴ ዐሻራ ሀገራዊ ንቅናቄ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ከማረጋገጥ እና ብልጽግናን ከማምጣት የረጅም ጊዜ ሀገራዊ ሕልም ጋር በቀጥታ የተቆራኘ አንኳር ጉዳይ ነው።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ አርዓያ ያደረገ እና የምትታወቅበት መገለጫ ሆኗል፡፡
መርሐ ግብሩ የተመጣጠነ ዝናብ እንዲኖር፣ ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ ለመኖር እና በምግብ ራስን ለመቻል ትልቅ እገዛ እያደረገም ይገኛል፡፡
ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ ዐሻራ ተግባራት እንደ ሀገር በተጨባጭ የደን መመናመንን በማስቀረት ሽፋኑን ማሳደግ ተችሏል፡፡
ለካርበን ሽያጭና ዛፍ መትከል ስለሚያስገኘው የቢሊየን ዶላሮች የኢኮኖሚ ምንጭ ማወቅ የአሁኑ ዘመን የሕልውና እና የብልጽግና መሠረትን ለመረዳት ወሳኝ መነሻ ነው።
አረንጓዴ ዐሻራ የዓለም አቀፉን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ከመቋቋም ባለፈ ታላቅ ሀገራዊና አሕጉራዊ ፋይዳ ያለው ሲሆን÷ ይህ ታሪካዊ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት በማሳደግ አዲስ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ምዕራፍ ከፍቷል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ጊዜያዊ ዘመቻ ሳይሆን የሀገርን የነገ ዕጣ ፈንታ የሚወስን ሆኖ ቀጥሏል።
በዚህም ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸውና የምግብ ዋስትናን በተግባር የሚያረጋግጡ የፍራፍሬ ዝርያዎችን ጨምሮ የተለያዩ ችግኞች በመተከላቸው የአርሶ አደሩን የኑሮ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀየሩ ይገኛሉ።
ከተከላው ጎን ለጎን ችግኞችን በማፍላትና በመንከባከብ ሂደት ውስጥ ለሚሊየኖች ሰፊ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።
በአረንጓዴ ዐሻራ የሚተከሉ ችግኞች ከከባቢ አየር ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው በካይ ጋዝ የመምጠጥ እና የማከማቸት አቅም ስላላቸው ለኢትዮጵያ አዲስ እና ዘላቂ የዶላር መገኛ መስመር እየከፈቱም ይገኛሉ።
መርሐ ግብሩ ከሀገራዊ ፋይዳው ባሻገር የኢትዮጵያን ስልታዊ የውጭ ፖሊሲ እና ቀጣናዊ ትስስር የሚያጠናክር የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ መሳሪያ ሆኗል።
ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ለጂቡቲ፣ ለኬንያ፣ ለሶማሊያ እና ለደቡብ ሱዳን በሚሊየን የሚቆጠሩ ችግኞችን በነጻ በማካፈል በጋራ የመልማትና ድንበር ተሻጋሪ የተፈጥሮ ሀብትን በጋራ የመጠበቅ ራዕይን በተግባር አሳይታለች።
የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ዛፍ ከመትከል በእጅጉ የላቀ፣ ሀገራዊ ብልጽግናን ከዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ጋር ያስተሳሰረ ታላቅ ስትራቴጂካዊ ርምጃ ነው። ይህ ንቅናቄ ለተተኪው ትውልድ የሚለምልም እና የሚጠቅም ሕያው ቅርስ እና የማያረጅ ውርስ ጥሎ የሚያልፍ የአዲሱ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ማሳያ ነው።
የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄው ኢትዮጵያን በአፍሪካና በዓለም አቀፍ መድረክ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ተምሳሌት እያደረገም ይገኛል።
በወንድማገኝ ጸጋዬ

ፊፋ ወደ አሜሪካ እንዳይገባ የተከለከለውን ሶማሊያዊ ዳኛ ሙሉ የዓለም ዋንጫ ደመወዝ ሊከፍል ነው
የዓለም ዋንጫን ለመዳኘት በአሜሪካ ክልከላ የተደረገበት ሶማሊያው ዳኛ ኦማር አርታን የውድድሩ ሙሉ ደመወዙን ያገኛል ተባለ።
ባለፈው ሰኞ በአሜሪካ የኢምግሬሽን ባለሥልጣናት የዲፕሎማቲክ ፓስፖርቱ እና ቪዛው ውድቅ የተደረጉበት ዳኛው በሚያሚ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ለ11 ሰዓታት ተመርምሯል።
የአሜሪካ መንግሥት አርታን አገር ውስጥ እንዳይገባ የተከለከለው "ከሽብር ድርጅት ተጠርጣሪ አባል ጋር ባለው ግንኙነት" እንደሆነ አስታውቋል።
አርታን በድንበር ባለሥልጣናት ከሶማሊያው አል ሸባብ ቡድን ጋር ባለው ግንኙነት ዙሪያ እንደመረመረ እና ስለ ቡድኑ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ተናግሯል።
"ትክክለኛው ሰነድ እና ሁሉም ነገር ነበረኝ፤ ትክክለኛው ቪዛ ነበረኝ" ሲል አርታን ተናግሯል።
"እኔ ህልሙን ለመኖር እየሞከረ ያለ ተራ ዳኛ ነኝ፤ ለዓለም ዋንጫ መምጣት ትልቁ የሕይወቴ ህልም ነው" ብሏል።
ወደ ቱርክ እንዲመለስ ከተደረገ በኋላ አርታን ወደ ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ከማምራቱ በፊት በኢስታንቡል ከፊፋ እርዳታ ተደርጎለታል።
ምንጮች ለቢቢሲ ምንም እንኳ አርታን በዓለም ዋንጫ ተሳታፊ ባይሆንም ፊፋ ደመወዙን ለመክፈል ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል።
ዳኞች በዓለም ዋንጫ ጨዋታዎችን ለዳኙበት ምን ያህል እንደሚከፈላቸው አያውቁም። ክፍያቸው ከውድድሩ ፍፃሜ በኋላ ነው የሚከፈላቸው።
የ2025 የአፍሪካ እግር ኳስ ፌደሬሽን (ካፍ) የዓመቱ ምርጥ ዳኛ የሆነው ኦማር አርታን፤ በሚቀጥለው ሐምሌ በፓሪስ ሴንት ዠርሜን እና አስቶን ቪላ መካከል በአውስትራሊያ የሚደረገውን የአውሮፓ የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን እንዲዳኝ ተጋብዟል።
በሶማሊያ የጀግና አቀባበል የተደረገለት የ34 ዓመቱ ዳኛ አገሩን እና ሕዝቦቹን አመስግኖ የ2030ውን የዓለም ዋንጫ ለመዳኘት ቃል ገብቷል።
ለአርታን 2025 ታሪካዊ ዓመት የነበረ ሲሆን አህጉራዊውን የፍፃሜ ጨዋታ በመዳኘት መጀመሪያው ሶማሊያዊ ለመሆን በቅቷል።
በሰኔ 2025 የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታንም ዳንቷል።
ፊፋ በቺሊ በተካሄደው ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ኦማር አርታንን የሾመ ሲሆን፤ በዚህ ውድድር ሦስት ጨዋታዎችን መዳኘት ችሏል።
በዓመቱ ፍፃሜ በአፍሪካ ዋንጫ ሁለት የምድብ ጨዋታዎችን የዳኘ ሲሆን፤ በ2024 በተመሳሳይ ውድድሩን ዳኝቷል።
BBC

Comments