ተስፋን በምድራችን፦ የ50 ቢሊዮን ችግኝ ራዕይ
**********************
(የዕለቱ መልዕከት)
የዘንድሮው ክረምት የሀገራችንን የ50 ቢሊዮን ችግኞች ተከላ ግዙፍ ራዕይ ሙሉ በሙሉ እውን በማድረግ የምናጠናቅቅበት ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።
ዛሬ በምድራችን ላይ የምናኖረው እያንዳንዱ አረንጓዴ ዐሻራ፣ ዓለም አቀፉን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ከመቋቋም ባለፈ ታላቅ ሀገራዊና አሕጉራዊ የኢኮኖሚ ፋይዳ አለው።
ይህ ግዙፍ ብሔራዊ ንቅናቄ አሁን እንደ ጀመርነው ሀገራዊ ምክክር ሁሉ ልዩነቶቻችንን ወደ ጎን ትተን ኢትዮጵያን በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት የሚያስችለን ታላቅ ፕሮጀክት ነው።
ቀደም ባሉት ዘመናት እጅግ ሰፊ የደን ሽፋን የነበራት ሀገራችን፣ በሕዝብ ቁጥር መጨመርና በደን ምንጣሮ ምክንያት ሀብቷ ተመናምኖ፣ ለአፈር መሸርሸርና ለግብርና ምርታማነት መቀነስ ተጋልጣ መቆየቷ ይታወሳል።
ይህን ፈተና ለመቀልበስ በ2011 ዓ.ም የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ እስካሁን ከ40 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት ቀዳሚ ተዋናይ አድርጓታል።
በዚህ ንቅናቄ እየተተከሉ ያሉ ችግኞች የደን ዛፎች ብቻ ሳይሆኑ እንደ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ አፕል፣ ቡናና ሻይን የመሳሰሉ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው በመሆናቸው የአርሶ አደሩን የኑሮ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀየሩት ይገኛሉ።
ለሚሊዮኖች የሥራ ዕድል የፈጠረው ይህ ፕሮጀክት ለሀገር በቀል የአግሮ-ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪዎች ወሳኝ የጥሬ ዕቃ ግብዓት ምንጭ በመሆን ላይ ነው።
የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄያችን ከአየር ንብረት ጥበቃና ከምግብ ዋስትና ባሻገር እጅግ ግዙፍ ከሆነው ዓለም አቀፉ የካርበን ገበያ (Carbon Market) በትልቁ ተጠቃሚ እንድንሆን በሩን ከፍቶልናል።
በአረንጓዴ ዐሻራ የምንተክላቸው ቢሊዮን ዛፎች ከከባቢ አየር ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው በካይ ጋዝ የመምጠጥ አቅም ስላላቸው፣ ለሀገራችን አዲስና ዘላቂ የውጭ ምንዛሬ ማግኛ መስመር እየከፈቱ ነው።
የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ ቀጣናዊ ትስስርን በማጠናከር ረገድም የጎላ ድርሻ አለው። ለጅቡቲ፣ ለኬንያ፣ ለሶማሊያ እና ለደቡብ ሱዳን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በነፃ በማካፈል የጋራ ዕድገት ራዕያችንን በተግባር እያሳየን እንገኛለን።
ከዚህ ጎን ለጎን መርሐ-ግብሩ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶቻችንን ከጎርፍ እና ከደለል በመጠበቅ የአገልግሎት ዘመናቸውን ያራዝማል።
የሕዝብን ንቁ ተሳትፎ በማረጋገጥ ከ80 በመቶ በላይ የጽድቀት ምጣኔን ያስመዘገበው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ከተለመደው ዓይነት ችግኝ ተከላ በእጅጉ የላቀ አንደምታ ያለው ነው።
አረንጓዴ ዐሻራችን የተፈጥሮ ጸጋችንን በአግባቡ በመጠቀም ለተተኪው ትውልድ የሚበቅል፣ የሚለምልምና የሚጠቅም ሕያው ቅርስ የምናወርስበት የአዲሱ አረንጓዴ ኢኮኖሚያችን ጽኑ መሠረት በመሆኑ፣ ሁላችንም በአንድነት ዐሻራችንን ማኖራችንን እንቀጥል!
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

16 days ago