Logo
YenetaTube
የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ለስድስት አገራት ዜጎች የተሰጠውን በአሜሪካ የመቆየትና የመሥራት ጊዜያዊ ሕጋዊ ከለላ ለተጨማሪ ቀናት አራዘመ።

የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ለስድስት አገራት ዜጎች የተሰጠውን በአሜሪካ የመቆየትና የመሥራት ጊዜያዊ ሕጋዊ ከለላ ለተጨማሪ ቀናት አራዘመ። በአሜሪካ የአገር ውስጥ ደሕንነት መሥሪያ ቤት ሥር የሚገኘው የዜግነትና የፍልሰት አገልግሎት በአገሪቱ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተሰጠው ከለላ በመጪው ሐምሌ 10 ቀን 2018 እንደሚያበቃ ትላንት አርብ አስታውቋል።

ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ለሶርያ፣ ሶማሊያ፣ የመን፣ ደቡብ ሱዳን እና ምያንማር ዜጎች የተሰጠው ጊዜያዊ ከለላ በተመሣሣይ ቀን ያበቃል። ውሳኔው የሚመለከታቸው የሔቲ ዜጎች ከቀሪዎቹ አምስት አገራት አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ በአሜሪካ ለመቆየትና ለመሥራት የሚፈቅድላቸውን ከለላ ያጣሉ።

ይህ ከለላ የተፈጥሮ አደጋ፣ የትጥቅ ግጭት ወይም ሌሎች ያልተለመዱ አስገዳጅ ሁኔታዎች ከገጠማቸው አገራት ወደ አሜሪካ የገቡ ሰዎች በአገሪቱ እንዲቆዩ እና በሕጋዊ መንገድ እንዲሠሩ የሚፈቅ ነው። ከለላው የተሰጣቸው በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ቢመለሱ “በግል ደሕንነታቸው ብርቱ ሥጋት አይገጥማቸውም” በሚል አመክንዮ በአገሪቱ የመቆየትና የመሥራት ዕድላቸው እንዲያበቃ የተወሰነው ባለፈው ታኅሳስ 2018 ነበር። ይሁንና ውሳኔው በቦስተን በሚገኝ የማሳቹሴትስ አውራጃ ፍርድ ቤት ታግዷል።

ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ሶማሊያና ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ የ10 አገራት ዜጎች ተመሳሳይ ሕጋዊ ጥበቃ ነበራቸው። የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባለፈው ወር የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የሔቲና የሶርያ ዜጎች የተሰጠውን ጊዜያዊ ከለላ ማብቃት እንደሚችል ውሳኔ አሳልፏል። የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕጋዊ ጥበቃ እንደሚያሳጣ የመብት ተሟጋቾችና በአሜሪካ የሚገኙ የተለያዩ ማኅበረሰቦች መሪዎች ሥጋት አላቸው
DW Amharic

27 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.