(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ አቃብያነ ህግ በሚኒሶታ ክፍለ ግዛት በተፈጸመው የ250 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ማጭበርበር ወንጀል ውስጥ ቁልፍ ተጠርጣሪ የሆነውን የ42 ዓመቱን አብዲከሪም አብዱላሂ ኤይድሌህን በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በቁጥጥር ስር አውለዋል። ሀሙስ ዕለት በቁጥጥር ስር የዋለው ይህ ግለሰብ፣ የተያዘው በአሜሪካው የፌደራል ምርመራ ቢሮ (FBI) እና በሶማሊያ ብሔራዊ የስለላ እና ደህንነት ኤጀንሲ ጥምር የኦፕሬሽን ስራ መሆኑን የአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ካሽ ፓቴል በኤክስ ገጻቸው ዛሬ ባሰፈሩት መግለጫ እርምጃውን ያደነቁ ሲሆን፣ አብዲከሪም ኤይድሌህ በሀገሪቱ ታሪክ ከተፈጸሙት ታላላቅ የማጭበርበር ቅሌቶች አንዱን የመራ ግለሰብ መሆኑን ገልጸዋል። ዳይሬክተሩ አክለውም ግለሰቡ ድጋፍ ለሚሹ እና ለተጋለጡ አሜሪካውያን የምግብ አቅርቦት የተመደበውን 250 ሚሊዮን ዶላር በመዝረፍ ለቅንጦት መኪናዎች እና ለግዙፍ ቪላ ቤቶች ማዋሉ እጅግ እፍረተ-ቢስ ተግባር እንደሆነ አስታውቀዋል። ኤፍቢአይ ይህንን "Feeding our Future" የተሰኘውን የሙስና ኔትወርክ ስልታዊ በሆነ መንገድ እያፈረሰው መሆኑን እና እስካሁንም ከ70 በላይ የቡድኑን አባላት በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጸዋል።
ወንጀሉ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ለችግረኛ ህጻናት ምግብ ማቅረቢያነት ከፌደራል መንግስት የተመደበውን የዕርዳታ ገንዘብ መዝረፍን ያካተተ ነው። ኤይድሌህ፣ ከ40 ዓመት በላይ እስራት የተፈረደባት እና የዚህ ማጭበርበር ዋና ጠንሳሽ የሆነችው ኤሚ ቦክ ምክትል ሆኖ ይሰራ እንደነበር አቃብያነ ህግ ይገልጻሉ። ተጠርጣሪው ሀሰተኛ የምግብ ማከፋፈያ ጣቢያዎችን በመክፈት፣ በቀን በሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናትን እንደመገበ በማስመሰል እና ያልቀረበ ምግብ ለመንግስት በማስከፈል በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ዘርፏል።
በሚኒሶታ የአሜሪካ አቃቤ ህግ ዳንኤል ሮዘን ግለሰቡን የህዝብን ገንዘብ በመዝረፍ እና ጉቦ በመቀበል ወንጀል የተካነ "ትልቅ ዓሳ" ሲሉ ገልጸውታል።
ይህ የማጭበርበር ወንጀል፣ የትራምፕ አስተዳደር በሚኒሶታ በሚኖረው እና በአሜሪካ ትልቁ የሶማሊያ-አሜሪካውያን ማህበረሰብ ላይ ጥብቅ እርምጃዎችን እንዲወስድ መነሻ ሆኗል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሶማሊያን የጉዞ እገዳ ከተጣለባቸው ሀገራት ተርታ የደለደሉ ሲሆን፣ በማጭበርበር ወንጀል የተፈረደባቸው ዜግነት ያገኙ አሜሪካውያንን ዜግነት እንደሚገፉ ዝተዋል።
የፌደራል የኢሚግሬሽን አስከባሪ ኤጀንቶች በሚኒያፖሊስ ያደረጉትን መጠነ-ሰፊ አፈሳ ተከትሎ በጸጥታ ኃይሎቹ ግለሰቦች መገደላቸው ለሳምንታት የዘለቀ ህዝባዊ ተቃውሞን አስነስቷል። በተጨማሪም ለ1,100 ያህል ሶማሊያውያን ከለላ ሲሰጥ የቆየውን ጊዜያዊ የጥበቃ ሁኔታ (TPS) ለማንሳት በመንግስት የተወሰደው እርምጃ በፌደራል ዳኛ ውድቅ ተደርጎ የህግ ክርክሩ ቀጥሏል።

3 months ago