የሻምፒዮንስ ሊግ ምሽት
የፓሪስ ፈተና ለሊቨርፑልና የስፔኖቹ ፍጥጫ በካታላን
#ethiopia | ትላንት አርሰናል ድል ቀንቶት ምሽቱን በደስታ ብናሳልፍም፣ ዛሬ ደግሞ ሌሎች ታላላቅ ክለቦች ለግማሽ ፍጻሜ አልጋ ለመለየት ይፋለማሉ።
. 🇫🇷 ፒኤስጂ ከ ሊቨርፑል 🏴 (ምሽት 4፡00)
በኤፍ ኤ ዋንጫ በማንችስተር ሲቲ የ 4 ለ 0 መራር ሽንፈት የደረሰባቸው አርን ስሎት፣ ዛሬ በፓሪስ ራሳቸውን ማዳን ይኖርባቸዋል።
ለሦስት ወራት በጉዳት ተለይቶ የነበረው ስዊዲናዊው አጥቂ አሌክሳንደር ኢሳቅ ወደ ስብስብ መመለሱ ለመርሲሳይዱ ክለብ ትልቅ የምስራች ነው።
ፒኤስጂ በቅርብ ጊዜያት ከእንግሊዝ ክለቦች ጋር ባደረጋቸው 6 ጨዋታዎች ሽንፈት አላስተናገደም። ብራድሊ ባርኮላና ፋቢያን ሩይዝ በዛሬው ጨዋታ አይሰለፉም።
🇪🇸 ባርሴሎና ከ አትሌቲኮ ማድሪድ 🇪🇸 (ምሽት 4፡00)
ባርሴሎና በሜዳው ባደረጋቸው ያለፉት 25 ጨዋታዎች በአትሌቲኮ ተሸንፎ አያውቅም። ከሦስት ቀን በፊትም በላሊጋው 2 ለ 1 ማሸነፉ ለዛሬው ጨዋታ የሥነ-ልቦና የበላይነት ይሰጠዋል።
አትሌቲኮ ማድሪድ በሻምፒዮንስ ሊግ የስፔን ክለቦችን ከሜዳው ውጪ አሸንፎ የማያውቅበትን ታሪክ ለመቀየር ይፋለማል።
ባርሴሎና ራፊንሀና ዲዮንግን ቢያጣም ሮናልድ አራውሆ ለጨዋታው ደርሶለታል። በአንጻሩ ያን ኦብላክ ለአትሌቲኮ ዝግጁ መሆኑ ተረጋግጧል።
#getu #championsleague #psg #liverpool #barcelona #atleticomadrid #arneslot #alexanderisak #footballnews #uclquarterfinals #ጌጡተመስገን #getutemesgen #ስፖርት #ሻምፒዮንስሊግ

2 months ago