Logo
Getu Temesgen
ፒኤስጂ ሻምፒዮን መሆኑን ተከትሎ በፓሪስ ሁከት ተቀሰቀሰ
#ethiopia | ​የፓሪሰን ዠርሜን (PSG) የሻምፒዮናነት ድልን ተከትሎ በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ እና በተለያዩ አካባቢዎች በተቀሰቀሰ ስርዓት አልበኝነት እስካሁን 416 ደጋፊዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

​ከታሰሩት ደጋፊዎች መካከል 283ቱ በፓሪስ ከተማ ውስጥ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፥ ድርጊቱን ለማስቆም በነበረው ግጭት ሰባት የፖሊስ አባላት ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል።

​የክለቡ ደጋፊዎች በደስታ ስሜት ውስጥ ሆነው አራት ዋና ዋና የቀለበት መንገዶችን ለመዝጋት ሙከራ ያደረጉ ሲሆን፥ በፓሪስ ጎዳናዎች ላይ የነበረው የእልልታና የደስታ አገላለጽ እስከ ንጋት ድረስ ቀጥሎ አድሯል።

​በሌላ በኩል ፒኤስጂ ይፋዊ የዋንጫ ድሉን በፓሪስ በሚገኘው "Champ-de-Mars" ክፍት የሕዝብ መናፈሻ በጎዳና ላይ እንደሚያከብር ታውቋል።

​በዚህ ታላቅ የጎዳና ላይ የድል ክብረ በዓል ላይ እስከ 90,000 የሚደርሱ የክለቡ አድናቂዎችና ነዋሪዎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
​#psg #paris #ligue1 #footballnews #france #breakingnews

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.