Logo
Getu Temesgen
የአርሰናል እና የፒኤስጂ ጨዋታን የሚዳኙት ዳኛ ታወቁ
#ethiopia | ​በጉጉት ለሚጠበቀው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ፍልሚያ፣ በአርሰናል እና በፒኤስጂ መካከል የሚደረገውን ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ መታወቃቸው ተረጋግጧል።

​ጀርመናዊው የ42 ዓመቱ ዳኛ ዳንኤል ሴበርት ይህንን ታላቅ ጨዋታ በመሐል ዳኝነት እንዲመሩ በኃላፊነት ተሰይመዋል።

​ከ20 ዓመታት ረጅም ጥበቃ በኋላ ወደ ፍጻሜው የተመለሱት መድፈኞቹ፣ በግማሽ ፍጻሜው አትሌቲኮ ማድሪድን በድምር ውጤት በመርታት ነው ለዚህ ደረጃ የበቁት።

ክለቡ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ወደ ለንደን ለመውሰድ ቆርጦ ተነስቷል።

​የአምናው ውድድር አሸናፊው የፈረንሳዩ ክለብ፣ በግማሽ ፍጻሜው ባየርን ሙኒክን በማሸነፍ ለፍጻሜው ደርሷል።

ፒኤስጂ ክብሩን አስጠብቆ ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት ሻምፒዮን ለመሆን ይፋለማል።

​ይህ ተጠባቂ የፍጻሜ ጨዋታ በሀንጋሪ ቡዳፔስት በሚገኘው ፑሽካሽ አሬና ስታዲየም ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
​#championsleague #arsenal #psg #uclfinal #danielsiebert #footballnews #ethiopia

24 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.