17 hours ago
ጋምቤላና ደምቢዶሎ በአየር ሊገናኙ ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ የበረራ አገልግሎቱን በማስፋት ከጋምቤላ ወደ ደምቢዶሎ እና ከደምቢዶሎ ወደ ጋምቤላ የሚደረግ ቋሚ የበረራ መስመር ከነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሚጀምር አስታውቋል። ይህ አዲስ መስመር የአየር መንገዱ የሀገር ውስጥ ኔትወርኩን የማስፋትና የክልሎችን ትስስር የማጠናከር እቅድ አካል መሆኑ ተገልጿል።
አየር መንገዱ እንደገለጸው፣ አዲሱ የበረራ መስመር በጋምቤላና በደምቢዶሎ መካከል ያለውን የትራንስፖርት እንግልት በእጅጉ በመቀነስ ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንት፣ ለመንግሥታዊ አገልግሎቶች እና ለማኅበራዊ ግንኙነቶች አመቺ ሁኔታ ይፈጥራል።
በተጨማሪም ይህ አዲስ መስመር በሁለቱ አካባቢዎች መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ትስስር ይበልጥ እንደሚያጠናክር ተጠቁሟል። የኢትዮጵያ አየር መንገድም የዜጎችን የጉዞ ፍላጎት ለማሟላት የሀገር ውስጥ መዳረሻዎቹን በቀጣይነት እያሰፋ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።
#ethiopianairlines #gambella #dembidolo #domesticflights #ethiopianews #aviation #ጋምቤላ #ደምቢዶሎ

1 day ago
በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ ችግኞች የጋምቤላን ማህበረሰብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እያረጋገጡ ነው፦ ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ
**********************
በጋምቤላ ክልል በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ባለፉት ዓመታት የተተከሉ የደን እና የፍራፍሬ ችግኞች የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እያሳደጉ እንደሚገኙ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድሯ ይህንን ያብራሩት በዛሬው ዕለት ከፍተኛ የክልል አመራሮች እና በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት እየተካሄደ በሚገኘው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ነው።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ተሳትፎ 800 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀምበር ለመትከል የተያዘውን ታሪካዊ ግብ ለማሳካት፣ የጋምቤላ ክልል ማህበረሰብም ከማለዳው ጀምሮ በነቃ ተሳትፎ ልዩ ልዩ ጠቀሜታ ያላቸውን የደንና የፍራፍሬ ችግኞች በመትከል ላይ ይገኛል፡፡
ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ መርሃ ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት፣ ባለፉት ሰባት ዓመታት በክልሉ በአረንጓዴ አሻራ የተከናወኑ ተግባራት የደን ሽፋኑ እንዲጨምር እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ዓይነተኛ ሚና ተጫውተዋል።
በተለይም የተተከሉ የፍራፍሬ ችግኞች ለቤት ውስጥ ምግብነት ከመዋል አልፈው ለገበያ በመቅረብ ላይ እንደሚገኙ የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሯ፣ ይህም የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ መቻሉን አስረድተዋል።
በቀጣይም በክልሉ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲሁም ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ የደንና የፍራፍሬ ችግኞችን በስፋት የመትከል ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ችግኝ የመትከል እና የመንከባከብ ባህል በሚገባ እየዳበረ በመምጣቱ፣ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም የታቀደውን ግብ በማሳካት የላቀ ስኬት ይመዘገባል ተብሎ በከፍተኛ ተስፋ ይጠበቃል።
በሚፍታህ አብዱልቃድር
#greenlegacy #gambella #ethiopia #treeplanting #climateaction

1 month ago
በጋምቤላ ክልል ከ200 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርገው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት
*********************
በጋምቤላ ክልል "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል የዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ-ግብር በይፋ ተጀምሯል።
በክልሉ ጋምቤላ ከተማን እና የኢታንግ ልዩ ወረዳን ጨምሮ በሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች በሚከናወነው በዚህ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ ከ200 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ልዩ ልዩ የልማትና የድጋፍ ሥራዎች እንደሚከናወኑ ተገልጿል።
የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ቱት ጆክ ዛሬ በከተማ አስተዳደሩ የሚገኑ የአቅመ-ደካማ ወገኖችን የቤት ዕድሳት በይፋ በማስጀመር የክረምቱን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ አስጀምረዋል።
ከንቲባው መርሃ-ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት፤ ወጣቶችንና በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር ረዳት የሌላቸውን አረጋውያን ቤቶች የመገንባትና የማደስ፣ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ፣ የአካባቢ ጽዳት፣ የደም ልገሳ እንዲሁም የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፎችን የማበርከት ተግባራት በስፋት ይከናወናሉ።
የበጎ ፈቃደኝነት ተግባር የሁሉም ዜጋ ማኅበራዊ ኃላፊነት በመሆኑ፣ መላው የከተማዋ ነዋሪ በመርሃ-ግብሩ ላይ በንቃት መሳተፍ እንዳለበት አሳስበዋል።
አክለውም በጎነት የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህልን በማጎልበት የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያግዝ በመሆኑ፣ የሁሉም አካላት ቅንጅታዊ ተሳትፎ እንደሚያስፈልገው ከንቲባው ተናግረዋል።
በጋምቤላ ክልል በዘንድሮው የክረምት ወራት ከ90 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞችን በተለያዩ ዘርፎች በማሰማራት ከ218 ሺህ በላይ የሚሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ለማድረግ ታቅዶ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ተመላክቷል።
በሚፍታህ አብዱልቃድር
#ethiopianbroadcastingcorporation #ethiopia #gambella #voluntaryservice #communitysupport

በጋምቤላ ክልል ከ558 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት እየተከናወነ ነው
*******************
በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት (LLRP) የማኅበረሰቡን ኑሮ ለመለወጥ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።
የፕሮጀክቱ የጋምቤላ ክልል አስተባባሪ ዶ/ር ቢየል ቢቾክ እንደገለጹት፤ በክልሉ በቆላማ አካባቢዎች የሚኖሩ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው።
በዚህም መሠረት በተያዘው በጀት ዓመት ብቻ ከ558 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የትምህርት፣ የጤና፣ የመስኖ ፕሮጀክቶች እና የመንገድ መሠረተ-ልማትን ጨምሮ የማኅበረሰቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የሚያግዙ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አስታውቀዋል።
አስተባባሪው አክለውም፣ የአካባቢ ጥበቃ ሥራን ጨምሮ የተፈጥሮ አደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የሚያግዙ ተግባራትን ለማጠናከርና ለዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማስፋት በቀጣይነት በትጋት እንደሚሠራ ተናግረዋል።
የፕሮጀክቱን የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና ምክክር መድረክ በበላይነት የመሩት የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡቶው ኡኮት በበኩላቸው፤ በክልሉ ለሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ በመስጠት የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ታስቦ በፕሮጀክቱ እየተከናወኑ ያሉ አበረታች ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በሚፍታህ አብዱልቃድር
#ethiopia #gambella #llrp #lowlanddevelopment #infrastructure

4 months ago
አኮቦ ሚኒራልስ በሦስት ወራት ውስጥ 23 ኪሎ ግራም ወርቅ ማምረቱን አስታወቀ
#ethiopia | መቀመጫውን ኖርዌይ ያደረገውና በኢትዮጵያ የጋምቤላ ክልልን በማዕድን ልማት ላይ የተሰማራው አኮቦ ሚኒራልስ (Akobo Minerals) ፣ ባለፉት ሦስት ወራት 23 ኪሎ ግራም ወርቅ ማምረት መቻሉን ይፋ አደረገ።
ኩባንያው ባወጣው መረጃ መሠረት፣ ካመረተው አጠቃላይ የወርቅ መጠን ውስጥ 7.5 ኪሎ ግራም የሚሆነው በመጋቢት ወር ብቻ የተመረተ ነው። አኮቦ ሚኒራልስ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወርቅን በቀጥታ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችለውን ፈቃድ ማግኘቱን ተከትሎ፣ በአሁኑ ወቅት ምርቱን ለዓለም አቀፍ ገበያ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።
ሆኖም ኩባንያው በሥራው ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋቶችን በሚመለከት የሚከተሉትን ነጥቦች አንስቷል፡-
በመካከለኛው ምሥራቅ ካለው ወቅታዊ ጦርነት ጋር ተያይዞ የነዳጅ እጥረት ከተባባሰ፣ በማዕድን ማውጣት ሥራው ላይ መስተጓጎል ሊፈጠር እንደሚችል አመልክቷል።
ኩባንያው ተግዳሮቶች ቢኖሩም ምርቱን ለውጭ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ ግኝቱን አጠናክሮ ለመቀጠል እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
አኮቦ ሚኒራልስ በጋምቤላ ክልል በሚያከናውነው የቁፋሮና የማምረት ተግባር ከፍተኛ ጥራት ያለው ወርቅ በማግኘት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ethiopia #mining #gold #akobominerals #gambella #economy #businessnews #ኢትዮጵያ #ማዕድን #ወርቅ #ኢኮኖሚ #አኮቦሚኒራልስ

5 months ago
ጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ
#ethiopia | የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ፣ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችንና የአፍሪካን ፓርክስ (African Parks) ተወካዮችን በማስከተል በጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ ያደረጉት የመስክ ምልከታ ትልቅ ትኩረት ስቧል።
ይህ ጉብኝት ብዙ ጊዜ ትልልቅ ባለሥልጣናት በፓርኮችና በጥብቅ ደኖች ውስጥ ለሥራ ሲገኙ የማይታይበትን ልምድ የሰበረና ለቱሪዝም ዘርፉ የተሰጠውን ልዩ ትኩረት የሚያሳይ ነው ተብሏል።
የርዕሰ መስተዳድሯ ዋና ዋና መልዕክቶች
* የቱሪዝም ቁርጠኝነት፦
የጋምቤላ ክልል በብሔራዊ ፓርኮች፣ በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ሐይቆች፣ በወንዞችና በባህላዊ እሴቶች የበለፀገ በመሆኑ እነዚህን ሀብቶች ለዓለም ማስተዋወቅ የመንግሥት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ገልጸዋል።
* የመሠረተ ልማት ዝግጅት፦
የቱሪዝም ልማት ሰፊ የመሠረተ ልማት አውታሮችን የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የማሳተፍ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።
* ከአፍሪካን ፓርክስ ጋር ያለ ቅንጅት፦
በአሁኑ ወቅት ፓርኩን በዘመናዊ መንገድ ለማልማት ከአፍሪካን ፓርክስ ጋር የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል።
🐘 ስለ ጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ አስገራሚ እውነታዎች
የጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ በኢትዮጵያ ካሉ ጥብቅ ስፍራዎች መካከል በስፋቱና በተፈጥሮ ሀብት ክምችቱ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል፦
* ስፋት፦
4 ሺሕ 575 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ይሸፍናል፡፡
* የዱር እንስሳት ሀብት፦
69 የአጥቢ እንስሳት ዝርያዎችና 7 የተሳቢ እንስሳት ዝርያዎች ይገኙበታል።
* የአእዋፋትና ዓሣ ዝርያዎች፦
ከ327 በላይ የአእዋፍ ዝርያዎችና 97 የዓሣ ዝርያዎች መገኛ ነው።
* ዕፅዋት፦
ከ420 በላይ የተለያዩ የዕፅዋት ዓይነቶች የሚገኙበት ለምለም ስፍራ ነው።
ይህ ፓርክ በተለይ ከሰው ቁመት በሚረዝም ሣር ውስጥ በሚርመሰመሱ እንስሳትና በአይነተ ብዙ አእዋፋት ክምችት የሚታወቅ እጅግ አስደናቂ የተፈጥሮ ገጸ-በረከት ነው።
#ጋምቤላ #ኢትዮጵያ #ቱሪዝም #ብሔራዊፓርክ #አለሚቱኡሞድ #gambella #ethiopia #tourism #africanparks #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

6 months ago
በጋምቤላ ክልል በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት የስራ ሰዓት ማሻሻያ ተደረገ
#ethiopia | የጋምቤላ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በክልሉ እያጋጠመ ያለውን ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ከመጪው ሰኞ የካቲት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት የሚቆይ አዲስ የስራ ሰዓት መወሰኑን አስታውቋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡቶው ኡኮት እንደገለጹት፣ ማሻሻያው የተደረገው ወቅታዊው ሙቀት ለስራ ምቹ ባለመሆኑ ሰራተኛው ስራውን በብቃትና በጤናማ ሁኔታ ማከናወን እንዲችል ለማገዝ ነው።
አዲሱ የስራ ሰዓት ዝርዝር
በውሳኔው መሰረት የቀድሞው የስራ ሰዓት በሚከተለው መልኩ ተቀይሯል፦
* የጠዋት የስራ ሰዓት፦ ከጠዋቱ 1፡00 እስከ 5፡30 (ቀደም ሲል እስከ 6፡30 ነበር)።
* ከሰዓት በኋላ የስራ ሰዓት፦ ከሰዓት 10፡00 እስከ 12፡30 (ቀደም ሲል ከ9፡00 እስከ 11፡30 ነበር)።
ይህ የአሰራር ለውጥ በክልሉ አብዛኛው አካባቢዎች ላይ ተግባራዊ የሚደረግ ቢሆንም፣ በአንጻራዊነት ቀዝቃዛ አየር ባላቸው በማጃንግ ዞን የሚገኙት የመንገሺ እና የጎደሬ ወረዳዎች ላይ ግን ተፈጻሚ አይሆንም።
የክልሉ የመንግስት ሰራተኞች በተጠቀሰው አዲስ የሰዓት ሰሌዳ መሰረት በመስሪያ ቤቶቻቸው በመገኘት አገልግሎት እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጋምቤላ #የስራሰዓት #የአየርለውጥ #ሙቀት #ኢትዮጵያ #gambella #ethiopia

🚨 በጋምቤላ ከተማ የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ ታገደ፤ በሆቴሎች ላይም የሰዓት ገደብ ተጣለ
#ethiopia | በጋምቤላ ከተማ እየታየ ባለው ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ምክንያት፣ የከተማው አስተዳደር ጥብቅ የሆኑ አዳዲስ ክልከላዎችን ማውጣቱን አስታውቋል። እነዚህ ውሳኔዎች ከነገ አርብ ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በተግባር ላይ ይውላሉ።
የተጣሉ ዋና ዋና ገደቦች፦
* የሞተር ሳይክል እገዳ፦ የመንግስትም ሆኑ የግል ሞተር ሳይክሎች በከተማይቱ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ "ላልተወሰነ ጊዜ" በጥብቅ ታግደዋል።
* የባጃጅ የሥራ ሰዓት፦ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጆች) አገልግሎት መስጠት የሚችሉት ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል።
* ሆቴሎች እና ግሮሰሪዎች፦ ማንኛውም የመዝናኛ እና የምግብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ክፍት እንዲሆኑ ተወስኗል።
የከተማው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መግለጫ እንዳመለከተው፣ ውሳኔው የተላለፈው በከተማው ሰላም እና ደህንነት ዙሪያ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ ነው።
አስተዳደሩ አክሎም እነዚህን ክልከላዎች ጥሶ በሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ ላይ ጥብቅ "አስተዳደራዊ እርምጃ" እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል። የከተማው ነዋሪዎችም ለጸጥታው መከበር ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#gambella #ethiopia #securityalert #breakingnews #gambellacity #publicsafety #ጋምቤላ #ኢትዮጵያ

7 months ago
ጋምቤላ ውስጥ ምን እየሆነ ነው?
ጋምቤላ ከኢትዮጵያ ክልሎች አንዱ ነው። ጋምቤላ ዳር አገር ነው። ጋምቤላ ብዙ ወርቅ እንዳለ ይነገራል። ነዳጅ አለ ሲባልም ቆይቷል። አሁን ስለጋምቤላ ነዳጅ ብዙም አይወራም።
ስለጋምቤላ ነዳጅ መዜ አንዴ ተጠይቆ ሲመልስ eventhough we don't know whether it is a blessing or a curse ማለቱ ትዝ ይለኛል። ነዳጁ ይዞ የሚመጣው በረከት ይሁን እርግማን እርግጠኛ አይደለንም ማለቱ ነው። እውነቱን ነው።
የደቡብ ሱዳን ነዳጅ በ1960ዎቹ ከተገኘ በኋላ፣ በነዳጁ ጦስ በሱዳን የተፈጠረው ሁኔታ ሱዳንን ከሁለት ከፍሎ፣ ደቡብ ሱዳን የምትባል አዲስ አገር ፈጥሮም ይኸው አሁንም ድረስ አልበረደም።
ቀደም ባለው ጊዜ በጋምቤላ ሰፋፊ እርሻዎች ተጀምረው ብዙ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር እንደባከነ ሲነገር ነበር። አሁን ስለጋምቤላ ይሁን ስለጉራ ፈርዳ እርሻ ሲወራ አይሰማም።
ካራቱሪ የተባለ ትልቅ ነው የተባለ አንድ የህንድ ኩባንያም ጋምቤላ ለኢንቨስትመንት ገብቶ ብዙም ሳይቆይ መውጣቱንም ሰምተናል። ካራቱሪ ለምን ገባ? ምን ሠራ? ለምን ወጣ? ብዙም አይታወቅም።
ጋምቤላ በአንድ ወቅት ከባድ የፀጥታ ችግር ነበር። ሙርሌ የሚባሉ ጎሳዎችም ህጻናትን ሰርቀው ወደ ደቡብ ሱዳን ይወስዱ እንደነበር ከመስማት ባለፈ በምን ምክንያት ህጻናቱን እንደሚወስዱ አልሰማንም።
ስለጋምቤላ የምናውቀው ውስን ነው። ጋምቤላ የደቡብ ሱዳን አዋሳኝ ዳር አገር ነው። ተደጋጋሚ ግጭቶች አሉበት። ሀብት አለው። ግን አልለማም። ለምን?
በጋምቤላ ውስጥ የተለያዩ ብሔረሰብ ዝርያዎች ይኖራሉ። በዋነኛነት አኝዋክ፣ ኑኤር፣ ዲንካ፣ ሽሎክ የሚባሉ ጎሳዎች አሉ። የሚበዙት አኙዋኮች ናቸው ይባላል። እነዚህ ብሔረሰቦች በዋነኛነት የሚለዩት ግንባራቸው ላይ ባሉት ምልክቶች ነው።
ጋምቤላ ብዙውን ጊዜ ከዜናዎቻችን ውጭ ነው። ትግራይ ዳር አገር ቢሆንም ከዜና ላይ አይጠፋም። ስለሌሎቹ የዳር ክልሎች ግን ብዙም አይወራም። ስለ ጋምቤላ፣ አፋር፣ ሶማሊ፣ ቤኒሻንጉል ክልሎች ብዙ አይወራም። ስለ አዲሱ ደቡብ ምዕራብ ክልልም ሲወራ አይሰማም።
ዜናው ሁሉ በዋነኛነት ስለ 3 ክልሎች ብቻ ነው። ትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ አዲስ አበባ ነው። በተወሰነ ደረጃ ስለ ሲዳማ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረሪ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎችም አልፎ አልፎ ይወራል። ሌላው ግን ተረስቷል ማለት ይቻላል።
ስለ ዋርደር ምን ይወራል? ስለቀላፎ፣ ስለ ቀብሪ ደሃር፣ ስለደገ ሀቡር፣ ስለ ቶጎጫሌ ምን ወሬ አለ?
የሜይንስትሪም ሚድያዎቹና ጋዜጠኞቹ የት ናቸው?
ሰሞኑን ጋምቤላ ውስጥ የፀጥታ ችግር እንዳለ ይሰማል። የከተማው የፖሊስ አዛዥ ተገድለዋል፣ የሰዓት እላፊም ታውጇል።
ወርቅና ነዳጅ ካለ ችግር አለ። የውጭ ምንዛሪ ችግር አለብኝ የሚል መንግስት እንዴት ወርቅ ያለበትን ክልል ችላ ይላል?
የኢትዮጵያ ሀገረ-መንግስት ግንባታ ተጠናቋል ወይ? የውጭ እጆች በዳር ዳር ክልሎች እንዳይገቡ እንዴት እንጠብቃለን?
ጋምቤላ የተፈጠረው ችግር በምን ምክንያት ነው?
What is happening in Gambella?

8 months ago
#gambella : በዛሬው ዕለትም በጋምቤላ ከተማ በተለያዩ አቅጣጫዎች የተኩስ እሩምታ ሲሰማ እንደዋለ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
" ተኩስ በተለያዩ አቅጣጫዎች ቀጥሎ እየተሰማ ነው የዋለው " ያሉን ነዋሪዎቹ " ሁኔታዎቹ የሚያስፈሩ ናቸው ፤ ከቤት ለመውጣትም ከፍተኛ ስጋት ነው ያለው " ብለዋል።
" አሁንም ያለው ሁኔታ ከዚህ እጅግ ሳይከፋ አንድ ነገር ሊደረግ ይገባል " ሲሉ አሳስበዋል።
አንድ የጤና ተቋም ምንጭ " ዛሬ ቀን ሙሉ ተኩስ ነበር የተጎዱ ሰዎችም ወደ ጤና ተቋም ሲመጡ ነበር " ብለዋል።
#tikvahethiopia
tikvahethiopia

Sponsored by
Surafel
11 months ago
የጋምቤላ ኢንቨስትመንት እና ቱሪዝም ልማት በዓለም-አቀፍ እንዲተዋወቅ እየሠራን ነው!
- የጋምቤላ ሕዝቦች ክልል መንግሥት
#ethiopia | የጋምቤላ ክልል በሀብት ከከበሩ፣ በተፈጥሮ ከተሞሸሩ፣ በሰላም ከተቀመሩ፣ በታታሪ ሕዝብ ከተማገሩ የኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ አንዱና ቀዳሚው ነው።
ለአይን ማራኪ፣ መንፈስ የሚያድስና ታይቶ በማይጠገብ ውብ በሆነ መልክዓ-ምድር፣ ሠላማዊ ማኅበረሰብ፣ አስደናቂ የባሕል ስብጥር እና የልማት ፍላጎት ያለው ወጣት የሥራ ኃይል፣ በኢንቨስትመንት እንቅስቀሴዎችና መልማት የሚችል ዕምቅ ሐብት (እርሻ፣ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ፣ ደን ልማት፣ አግሮ-ፕሮሰሲንግ፣ ማዕድን ልማትና አገልግሎት) አቅፎ የያዘ፣ በምዕራብ ኢትዮጵያ በቅርቡ ለምቶ የአገር ትሩፋት የሚሆን (The Rising West) ክልል ነው።
ጋምቤላ በዝናብ ሊለማ የሚችለው የእርሻ መሬት ከጠቅላላው የቆዳ ስፋት ውስጥ 16 በመቶ ሲሆን ለዘመናዊ የመስኖ ኮመርሽያል እርሻ የሚሆነው ደግሞ 10 በመቶ ይሆናል። ይህ ማለት ለእርሻ ኢንቨስትመንት ሊውል የሚችለው 26 በመቶ (8,200 ስኩየር ኪሎ ሜትር) ነው። ለዚህ የዘመናዊ እርሻ ልማት የሚሆኑ ባሮ፣ አኮቦ፣ አልዌሮ እና ጊሎን የመሳሰሉ 4 ግዙፍ ወንዞች ከዓመት እስከ ዓመት የሚፈሱበት ክልል ነው።
እነዚህ ወንዞች ከአግሮ-ኢኮሎጂው ምቹነት አንጻር ሰፊ የዓሳ ሐብት ክምችት ያላቸው ሲሆን በዘመናዊ የዓሳ ልማት ዕቅድ ተመርቶ ለገበያ መቅረብ የሚያስችል ዐቅም አላቸው።
ክልሉ ባስጠናው የተቀናጀ የከተማና ገጠር መሬት አጠቃቀምና ልማት ፍኖተ-ካርታ (Integrated Urban and Rural Land-use Development Plan) መሠረትም የመሬት አጠቃቀም፣ የከተሞች ልማት እና የአካባቢ ጥበቃን አቀናጅቶ የመምራት ልምድ በክልሉ እየዳበረ መምጣቱ ለዘላቂ ዕድገት መሠረት ሆኗል።
በአግሮ-ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ክልሉ በሁሉም ዞኖች በቂ መጠን ዓመታዊ የዝናብ ውሃ የሚያገኙ በመሆኑ በቡና እና ሻይ ልማት፣ በእንስሳት ልማትና ተዋጽዖ ማቀነባበር፣ በኢንዱስትሪያል ደን ልማት፣ በንብ ማነብና የማር ምርት፣ በዓሳ ልማት፣ በዶሮ ሐብት ልማት፣ በጥራጥሬና የቅባት እህሎች ልማትና ማቀነባበር ዘርፍ ዕሴት በመጨመር ለአገር ውስጥና ለዓለም ገበያ ቢቀርቡ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ የሚያስገኝ ክልል ነው።
ይህን ለማሳካትም የምርት-ግብይት ትሥሥሩን ከእርሻ መዘመን እና ሜካናይዜሽን እስከ ግዙፍ የተቀናጀ የአግሮ-ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርክ (Integrated Agro-Processing Industrial Park) በክልሉ እንዲቋቋም ምክረ-ሐሳብ የሚቀርብ ይሆናል።
ከማዕድን ልማት አኳያም በምስራቅ አፍሪካ፣ ጋምቤላ—ምናልባትም በተፈጥሮ የተጌጠ የማዕድን ሐብት ማማ ሊባል የሚችል ነው። ይህን የማዕድን ሐብት ለአገር ልማት እንዲውል፣ ሕጋዊ የአስተዳደር ሥርዓት እንዲዘረጋለት እና ልማታዊ ባለሐብቶች እንዲሰማሩበት ልዩ ልዩ የማትጊያ ሥርዓት ተዘርግቶ እየተሰራበት ይገኛል።
ጋምቤላ ቱሪዝም ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው። የጋምቤላ ክልል በሀብት ከከበሩ፣ በተፈጥሮ ከተሞሸሩ፣ በሰላም ከተቀመሩ፣ በታታሪ ሕዝብ ከተማገሩ የኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ አንዱና ቀዳሚው ነው።
የጋምቤላ ክልል የዳበረ ባህል፤ ቀደምት ታሪክና መልክአ-ምድራዊ አሰፋፈር፤ የስነ ልቦና አንድነት፤ በጋራ ኤኮኖሚ (Shared Economy) ርዕይ የተዋቀረ የመልማት ፍላጎት ያለው እንዲሁም ጠንካራ የእርስ በእርስ ትስስር ያላቸው የአካባቢው ብሄረሰቦችንና ሌሎች የሀገራችንን ማኅበረሰቦች በጋራ ይዞ የሚገኝ ክልል ነው።
ክልሉ በቱሪስት መስህብነታቸው ተወዳጅ ተብለው ከተያዙት የኢትዮጵያ አካባቢዎች ውስጥ ተጠቃሽ ኮሪደር የያዘ ነው። በሆቴል ልማት፣ በባሮ እና አልዌሮ ወንዞች ላይ ዘመናዊ የሪዞርት ልማትና የጀልባ መዝናኛዎች፣ በኮንፈረንስ ቱሪዝም እና መሰል ተግባራት ሐብት ማመንጨት የሚችል ጸጋ የተላበሰ ነው።
ይህን የክልሉን ሐብት ፍትሐዊነት በታከለበት መንገድ ለማልማትና ለኢትዮጵያ የሕዳሴና ብልጽግና ዘመን እንደ አንድ ቁልፍ አሻጋሪ ድልድይ ለመጠቀም ይረዳ ዘንድ የጋምቤላ ክልል መንግሥት ከሕዝቡ የዕድገት አጋሮች ጋር በመተባበር ‹‹ጋምቤላ ይለማል (Gambella is Rising)›› የኢንቨስትመንት ልማት ዓለም-አቀፍ ንቅናቄ መርሐ-ግብር አዘጋጅቷል።
ክልላዊ ንቅናቄውንም ዛሬ፣ መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ለመላው ኢትዮጵያውያን፣ ደጋፊዎቻችን እና ዓለም-አቀፍ አጋሮቻችን በይፋ መጀመራችንን እናበስራለን።
የንቅናቄ መርሐ-ግብሩም ለሁለት ወራት የሚዘልቅ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የክልሉን ኢንቨስትመንት በማሳደግ፣ ኢትዮጵያውያን እና የውጪ አልሚ ባለሐብቶች (FDI) በስፋት የሚሳተፉበት፣ ዓለም-አቀፍ የልማት ድርጅቶች፣ ኢምባሲዎች እና ከፍተኛ የፌደራልና የክልል መንግሥታት መሪዎች የሚገኙበት የክልሉን ገጽታ ከመቸውም ጊዜ በላቀ መንገድ የሚያጎላ ሆኖ ይጠናቀቃል።

Comments