የጋምቤላ ኢንቨስትመንት እና ቱሪዝም ልማት በዓለም-አቀፍ እንዲተዋወቅ እየሠራን ነው!
- የጋምቤላ ሕዝቦች ክልል መንግሥት
#ethiopia | የጋምቤላ ክልል በሀብት ከከበሩ፣ በተፈጥሮ ከተሞሸሩ፣ በሰላም ከተቀመሩ፣ በታታሪ ሕዝብ ከተማገሩ የኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ አንዱና ቀዳሚው ነው።
ለአይን ማራኪ፣ መንፈስ የሚያድስና ታይቶ በማይጠገብ ውብ በሆነ መልክዓ-ምድር፣ ሠላማዊ ማኅበረሰብ፣ አስደናቂ የባሕል ስብጥር እና የልማት ፍላጎት ያለው ወጣት የሥራ ኃይል፣ በኢንቨስትመንት እንቅስቀሴዎችና መልማት የሚችል ዕምቅ ሐብት (እርሻ፣ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ፣ ደን ልማት፣ አግሮ-ፕሮሰሲንግ፣ ማዕድን ልማትና አገልግሎት) አቅፎ የያዘ፣ በምዕራብ ኢትዮጵያ በቅርቡ ለምቶ የአገር ትሩፋት የሚሆን (The Rising West) ክልል ነው።
ጋምቤላ በዝናብ ሊለማ የሚችለው የእርሻ መሬት ከጠቅላላው የቆዳ ስፋት ውስጥ 16 በመቶ ሲሆን ለዘመናዊ የመስኖ ኮመርሽያል እርሻ የሚሆነው ደግሞ 10 በመቶ ይሆናል። ይህ ማለት ለእርሻ ኢንቨስትመንት ሊውል የሚችለው 26 በመቶ (8,200 ስኩየር ኪሎ ሜትር) ነው። ለዚህ የዘመናዊ እርሻ ልማት የሚሆኑ ባሮ፣ አኮቦ፣ አልዌሮ እና ጊሎን የመሳሰሉ 4 ግዙፍ ወንዞች ከዓመት እስከ ዓመት የሚፈሱበት ክልል ነው።
እነዚህ ወንዞች ከአግሮ-ኢኮሎጂው ምቹነት አንጻር ሰፊ የዓሳ ሐብት ክምችት ያላቸው ሲሆን በዘመናዊ የዓሳ ልማት ዕቅድ ተመርቶ ለገበያ መቅረብ የሚያስችል ዐቅም አላቸው።
ክልሉ ባስጠናው የተቀናጀ የከተማና ገጠር መሬት አጠቃቀምና ልማት ፍኖተ-ካርታ (Integrated Urban and Rural Land-use Development Plan) መሠረትም የመሬት አጠቃቀም፣ የከተሞች ልማት እና የአካባቢ ጥበቃን አቀናጅቶ የመምራት ልምድ በክልሉ እየዳበረ መምጣቱ ለዘላቂ ዕድገት መሠረት ሆኗል።
በአግሮ-ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ክልሉ በሁሉም ዞኖች በቂ መጠን ዓመታዊ የዝናብ ውሃ የሚያገኙ በመሆኑ በቡና እና ሻይ ልማት፣ በእንስሳት ልማትና ተዋጽዖ ማቀነባበር፣ በኢንዱስትሪያል ደን ልማት፣ በንብ ማነብና የማር ምርት፣ በዓሳ ልማት፣ በዶሮ ሐብት ልማት፣ በጥራጥሬና የቅባት እህሎች ልማትና ማቀነባበር ዘርፍ ዕሴት በመጨመር ለአገር ውስጥና ለዓለም ገበያ ቢቀርቡ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ የሚያስገኝ ክልል ነው።
ይህን ለማሳካትም የምርት-ግብይት ትሥሥሩን ከእርሻ መዘመን እና ሜካናይዜሽን እስከ ግዙፍ የተቀናጀ የአግሮ-ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርክ (Integrated Agro-Processing Industrial Park) በክልሉ እንዲቋቋም ምክረ-ሐሳብ የሚቀርብ ይሆናል።
ከማዕድን ልማት አኳያም በምስራቅ አፍሪካ፣ ጋምቤላ—ምናልባትም በተፈጥሮ የተጌጠ የማዕድን ሐብት ማማ ሊባል የሚችል ነው። ይህን የማዕድን ሐብት ለአገር ልማት እንዲውል፣ ሕጋዊ የአስተዳደር ሥርዓት እንዲዘረጋለት እና ልማታዊ ባለሐብቶች እንዲሰማሩበት ልዩ ልዩ የማትጊያ ሥርዓት ተዘርግቶ እየተሰራበት ይገኛል።
ጋምቤላ ቱሪዝም ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው። የጋምቤላ ክልል በሀብት ከከበሩ፣ በተፈጥሮ ከተሞሸሩ፣ በሰላም ከተቀመሩ፣ በታታሪ ሕዝብ ከተማገሩ የኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ አንዱና ቀዳሚው ነው።
የጋምቤላ ክልል የዳበረ ባህል፤ ቀደምት ታሪክና መልክአ-ምድራዊ አሰፋፈር፤ የስነ ልቦና አንድነት፤ በጋራ ኤኮኖሚ (Shared Economy) ርዕይ የተዋቀረ የመልማት ፍላጎት ያለው እንዲሁም ጠንካራ የእርስ በእርስ ትስስር ያላቸው የአካባቢው ብሄረሰቦችንና ሌሎች የሀገራችንን ማኅበረሰቦች በጋራ ይዞ የሚገኝ ክልል ነው።
ክልሉ በቱሪስት መስህብነታቸው ተወዳጅ ተብለው ከተያዙት የኢትዮጵያ አካባቢዎች ውስጥ ተጠቃሽ ኮሪደር የያዘ ነው። በሆቴል ልማት፣ በባሮ እና አልዌሮ ወንዞች ላይ ዘመናዊ የሪዞርት ልማትና የጀልባ መዝናኛዎች፣ በኮንፈረንስ ቱሪዝም እና መሰል ተግባራት ሐብት ማመንጨት የሚችል ጸጋ የተላበሰ ነው።
ይህን የክልሉን ሐብት ፍትሐዊነት በታከለበት መንገድ ለማልማትና ለኢትዮጵያ የሕዳሴና ብልጽግና ዘመን እንደ አንድ ቁልፍ አሻጋሪ ድልድይ ለመጠቀም ይረዳ ዘንድ የጋምቤላ ክልል መንግሥት ከሕዝቡ የዕድገት አጋሮች ጋር በመተባበር ‹‹ጋምቤላ ይለማል (Gambella is Rising)›› የኢንቨስትመንት ልማት ዓለም-አቀፍ ንቅናቄ መርሐ-ግብር አዘጋጅቷል።
ክልላዊ ንቅናቄውንም ዛሬ፣ መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ለመላው ኢትዮጵያውያን፣ ደጋፊዎቻችን እና ዓለም-አቀፍ አጋሮቻችን በይፋ መጀመራችንን እናበስራለን።
የንቅናቄ መርሐ-ግብሩም ለሁለት ወራት የሚዘልቅ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የክልሉን ኢንቨስትመንት በማሳደግ፣ ኢትዮጵያውያን እና የውጪ አልሚ ባለሐብቶች (FDI) በስፋት የሚሳተፉበት፣ ዓለም-አቀፍ የልማት ድርጅቶች፣ ኢምባሲዎች እና ከፍተኛ የፌደራልና የክልል መንግሥታት መሪዎች የሚገኙበት የክልሉን ገጽታ ከመቸውም ጊዜ በላቀ መንገድ የሚያጎላ ሆኖ ይጠናቀቃል።

1 year ago