በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ ችግኞች የጋምቤላን ማህበረሰብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እያረጋገጡ ነው፦ ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ
**********************
በጋምቤላ ክልል በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ባለፉት ዓመታት የተተከሉ የደን እና የፍራፍሬ ችግኞች የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እያሳደጉ እንደሚገኙ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድሯ ይህንን ያብራሩት በዛሬው ዕለት ከፍተኛ የክልል አመራሮች እና በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት እየተካሄደ በሚገኘው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ነው።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ተሳትፎ 800 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀምበር ለመትከል የተያዘውን ታሪካዊ ግብ ለማሳካት፣ የጋምቤላ ክልል ማህበረሰብም ከማለዳው ጀምሮ በነቃ ተሳትፎ ልዩ ልዩ ጠቀሜታ ያላቸውን የደንና የፍራፍሬ ችግኞች በመትከል ላይ ይገኛል፡፡
ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ መርሃ ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት፣ ባለፉት ሰባት ዓመታት በክልሉ በአረንጓዴ አሻራ የተከናወኑ ተግባራት የደን ሽፋኑ እንዲጨምር እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ዓይነተኛ ሚና ተጫውተዋል።
በተለይም የተተከሉ የፍራፍሬ ችግኞች ለቤት ውስጥ ምግብነት ከመዋል አልፈው ለገበያ በመቅረብ ላይ እንደሚገኙ የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሯ፣ ይህም የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ መቻሉን አስረድተዋል።
በቀጣይም በክልሉ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲሁም ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ የደንና የፍራፍሬ ችግኞችን በስፋት የመትከል ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ችግኝ የመትከል እና የመንከባከብ ባህል በሚገባ እየዳበረ በመምጣቱ፣ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም የታቀደውን ግብ በማሳካት የላቀ ስኬት ይመዘገባል ተብሎ በከፍተኛ ተስፋ ይጠበቃል።
በሚፍታህ አብዱልቃድር
#greenlegacy #gambella #ethiopia #treeplanting #climateaction

2 days ago