1 month ago
"የመንገድ ትዝብት" ~ ሰለሞን ኦሊ
#ethiopia | ዛሬ ጠዋት ኮዬ ወደ ጎሮ የሚወስደዉ መንገድ ኪዳነ ምህረት ቤ/ክርስቲያን አካባቢ አንድ ከባድ የመንገድ ሥራ ማሽን በሚኒባስ ታክሲ ላይ ወድቆ ስድስት ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡበት አሳዛኝ አደጋ ተከስቷል::
ይህን ዓይነት አደጋ በ“ሾፌሩ ስህተት”፣ “የማሽኑ ብልሽት” ወይም “የመንገድ ሁኔታ” ብቻ መግለጽ በቂ አይደለም። የሚጠየቀው ጥያቄ፦
1. የመንገድ ሥራ ከመጀመሩ በፊት የአደጋ ግምገማ ያስፈልጋል
ማንኛውም የመንገድ ፕሮጀክት ከመጀመሩ በፊት የሚከተሉት ጥያቄዎች መመለስ አለባቸው:-
👉የሥራ ቦታው ምን ያህል የትራፊክ እንቅስቃሴ አለው?
👉ሠራተኞች ከተሽከርካሪ ጋር የመጋጨት አደጋ አለ?
👉ከባድ ማሽኖች ከሕዝብ ትራፊክ ጋር የሚገናኙት የት ነው?
👉የማሽን ክፍል ወደ ሕዝብ መንገድ ሊወድቅ ይችላል?
👉የመንገዱ አንድ ክፍል ቢዘጋ ትራፊኩ እንዴት ይመራል?
👉እግረኞች እንዴት ይጠበቃሉ?
👉አምቡላንስ ወይም የእሳት አደጋ መኪና እንዴት ይደርሳል?
ይህ የአደጋ ግምገማ ከሥራ በፊት ብቻ ሳይሆን የሥራው ሁኔታ ሲቀየር በየጊዜው መዘመን አለበት።
2. የጊዜያዊ ትራፊክ አስተዳደር ዕቅድ ያስፈልጋል
የመንገድ ሥራ በሚካሄድበት ጊዜ ትራፊክ እንዴት እንደሚቀጥል ከመጀመሪያው መወሰን አለበት።
የዕቅዱ አካላት:-
👉የሥራ ቦታ አቀማመጥ
👉የመንገድ መዘጋት
👉የመኪና መስመር መቀነስ
👉የትራፊክ ማዞሪያ
👉ጊዜያዊ ምልክቶች
👉የፍጥነት ቁጥጥር
👉የእግረኛ መንገድ
👉የከባድ ማሽን መግቢያና መውጫ
👉የአደጋ ጊዜ መድረሻ
👉 የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች
👉የአደጋ ምላሽ ሥርዓት
3. የሥራ ቦታ ከሕዝብ ትራፊክ መለየት
በመንገድ ሥራ ቦታ ላይ ኮኖችን መትከል ብቻ በቂ አይደለም።
እንደ ሁኔታው:-አጥር፣መከላከ፣የትራፊክ ምልክቶች፣የጊዜያዊ መንገድ መስመሮ፣አንጸባራቂ ምልክቶች፣የማታ መብራቶች እና የአደጋ መከላከያ ባሪየሮ መጠቀም ይገባል።
የሥራ ቦታው ለአሽከርካሪው ግልጽ፣ ቀድሞ ሊታይ የሚችል እና የማያሳስት መሆን አለበት።
4. የፍጥነት ቁጥጥር
በመንገድ ሥራ ቦታ የፍጥነት ቁጥጥር በጣም ወሳኝ ነው።
ምልክት ብቻ መትከል አይበቃም። አሽከርካሪው በቂ ርቀት ቀድሞ እንዲያውቅ፣ ፍጥነቱን እንዲቀንስ እና በሥራ ቦታው በደህንነት እንዲያልፍ የተቀናጀ ሥርዓት ያስፈልጋል።
5. ከባድ ማሽኖች ለብቻቸው የእንቅስቃሴ ዕቅድ ሊኖራቸው ይገባል
ኤክስካቫተር፣ ሎደር፣ ቡልዶዘር ወይም ሌላ ከባድ ማሽን ከሥራ ቦታ ወደ ሌላ ሲጓጓዝ ወይም ወደ ሥራ ቦታ ሲገባ የራሱ የእንቅስቃሴ ዕቅድ ሊኖረው ይገባል።
በተለይ፦
መጫን 👉መቆለፍ 👉ማሰር 👉 መፈተሽ 👉መጓጓዝ 👉ወደ ሥራ ቦታ መግባት እያንዳንዱ ደረጃ በቁጥጥር ሥር መሆን አለበት።
ኤክስካቫተር በሚጓጓዝበት ጊዜ ተንቀሳቃሽ ክፍሎቹ በትክክል መቆለፍ፣ በተገቢው የማሰሪያ መሳሪያ መጠበቅ እና ከመነሳቱ በፊት ሙሉ ምርመራ መደረግ አለበት።
Hydraulic ስርዓት ብቻ ላይ መተማመን በቂ አይደለም።
6. የጭነት ማሰሪያ በራሱ የደህንነት ስርዓት ነው
የከባድ ማሽን ክፍል በመንገድ ላይ ከተለቀ ወይም ከወደቀ ውጤቱ ከባድ ሊሆን ይችላል።
ስለዚህ የማሰሪያ ሰንሰለቶችና ሌሎች መሳሪያዎች፦
👉የጭነቱን ክብደት ሊቋቋሙ የሚችሉ
👉በተገቢ ቦታ የተያያዙ
👉 የማይበላሹ
👉የማይለቀቁ
👉በጉዞ ወቅት እንደገና የሚፈተሹ
መሆን አለባቸው።
7. እግረኞችን መርሳት የለብንም
የመንገድ ሥራ ዕቅድ መኪናን ብቻ ማስተናገድ የለበትም።
እግረኞች፣ ብስክሌተኞች፣ ሞተር ሳይክል ተጠቃሚዎች፣ አካል ጉዳተኞች እና ሌሎች የመንገድ ተጠቃሚዎች በዕቅዱ ውስጥ መካተት አለባቸው።
የእግረኛ መንገድ ከተዘጋ ደህንነቱ የተጠበቀ ጊዜያዊ መንገድ መሰጠት አለበት።
8. በሥራ ቦታ የማሽንና የሰው እንቅስቃሴ መለየት
በኤክስካቫተር ዙሪያ የሚንቀሳቀስ ሰው ለአደጋ በጣም ተጋላጭ ነው።
በሚያስፈልግበት ጊዜ ማሽኑን የሚመራ የመሬት ላይ አስተባባሪ መመደብ እና ማሽኑ የሚሰራበትን የአደጋ ክልል መለየት ያስፈልጋል።
9. የአደጋ ጊዜ ዕቅድ
አደጋ ከተከሰተ በኋላ ምን እናድርግ? የሚለው ጥያቄ ከአደጋው በፊት መመለስ አለበት።
የአደጋ ጊዜ ዕቅድ፦
ማስጠንቀቅ 👉 ትራፊክ ማቆም/መቆጣጠር 👉 አደጋውን መለየት → የሕክምና እርዳታ 👉 የእሳት አደጋ/ማዳን 👉ፖሊስ👉መንገዱን መልሶ ማስኬድየሚል ግልጽ ሂደት ሊኖረው ይገባል።
10. የሥራ ቦታ በየጊዜው መመርመር
የTraffic Management Plan አንድ ጊዜ ተዘጋጅቶ በፋይል ውስጥ የሚቀመጥ ሰነድ ብቻ መሆን የለበትም።
“ዕቅዱ አሁንም የሥራ ቦታውን ደህንነት ያረጋግጣል?” ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል።
11. ኃላፊነት በአንድ ሰው ላይ ብቻ አይጣልም
እንዲህ ያለ አደጋ ሲከሰት በአንድ ሾፌር ወይም ኦፕሬተር ላይ ብቻ ጥፋተኝነትን መጫን የስርዓቱን ችግር ሊደብቅ ይችላል። መመርመር ያለበት፦
ባለማሽኑ👉ኮንትራክተር 👉 የማጓጓዣ አካል 👉ሾፌር 👉የሥራ ቦታ አስተዳደር
12. የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪም ሚና አለው
ኢንሹራንስ ማለት አደጋ ከተከሰተ በኋላ ገንዘብ መክፈል ብቻ አይደለም።
‘’የመንገድ ሥራ የሚለካው በተሰራው ኪሎሜትር ብቻ ሳይሆን፣ ሥራው በምን ያህል ደህንነት እንደተከናወነ ጭምር መሆን አለበት።’’
ሰሎሞን ኦሊ
የኢንሹራንስና ሪስክ ማኔጅመንት አማካሪና ባለሙያ ተፃፈ #roadsafety #roadworksafety #trafficmanagement #riskmanagement #constructionsafety #ethiopia #insurance #publicsafety #roadinfrastructure

3 months ago
የተሰረቀው ገልባጭ መኪና በህዝብ ትብብር ተያዘ
#ethiopia | ትናንት በኮዬ ፈጨ አካባቢ የፀጥታ ኃይልን የሚመስል ልብስ የለበሱ ግለሰቦች ቀይ ሲኖ (Sino) ገልባጭ መኪናን በማስቆም ሾፌሩንና ረዳቱን ከተሽከርካሪው በኃይል አውርደው መኪናውን ይዘው መሰወራቸውን ዘግበን ነበር።
https://www.facebook.com/s...
ይሁን እንጂ የተሰረቀውን ተሽከርካሪ መረጃ በማየት የገላን ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎችና በአካባቢው የነበሩ ሾፌሮች በፍጥነት በመተባበር መንገዱን በተሽከርካሪዎች በመዝጋት ተሽከርካሪውን ሲነዳ የነበረውን ተጠርጣሪ መያዛቸው ተነግሯል።
ይህ ክስተት የህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ ወንጀልን በመከላከልና ለፍትሕ በማቅረብ ረገድ ያለውን ከፍተኛ ሚና በድጋሚ አሳይቷል።
በተለይም በተሽከርካሪው መያዝ የተሳተፉ የገላን ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎችና ሾፌሮች ምስጋና ይገባቸዋል።
በተጨማሪም የፀጥታ ኃይል መስለው በመንቀሳቀስ ወንጀሉን የፈጸሙትን ግለሰቦች፣ እንዲሁም ከስርቆቱ ጀርባ ያለውን ሙሉ የወንጀል መረብ በጥልቀት በማጣራት ሁሉንም ተሳታፊዎች ለህግ ማቅረብ አስፈላጊ መሆኑ ተጠቁሟል።
ሾፌሩና ረዳቱ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአቃቂ ቃሊቲ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
የ Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) ፌስቡክ ገጽ ቤተሰቦች መልዕክቱን በማጋራታችሁ ውጤት አስገኝቷል።
እንኳን ደስ አላችሁ።
#ethiopia #addisababa #crime #publicsafety #getutemesgen

5 months ago
በአዲስ አበባ በውጭ ሀገር ዜጋ ላይ ስርቆት የፈጸሙ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ
#ethiopia | በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አንድ የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ዜጋን በማዋከብ ስልክ የሰረቁ ሁለት ግለሰቦች፣ በአዲስ አበባ ፖሊስ ፈጣን ክትትል በሰዓታት ልዩነት ውስጥ ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጠ።
ድርጊቱ የተፈጸመው ሚያዚያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣ ልዩ ስሙ ኢሰመኮ (ባምቢስ) አካባቢ ነው። ተበዳዩ ኢብራሂም ሀሰን የተባሉ የውጭ ሀገር ዜጋ ከሱፐር ማርኬት ዕቃ ገዝተው ወደ አረፉበት ሐያት ሪጀንሲ ሆቴል በእግራቸው በመጓዝ ላይ ሳሉ ነበር ጥቃቱ የደረሰባቸው።
አብዲ ሀሰን እና ቃልዓብ ወርቁ የተባሉ ሁለት ተጠርጣሪዎች ግለሰቡን ግራና ቀኝ በመሆን ካዋከቡ በኋላ፣ አንደኛው "ሄድፎን ግዛን" በማለት ትኩረት ሲሰርቅ፤ ሁለተኛው ተጠርጣሪ ግምቱ 200 ሺህ ብር የሚሆን iPhone 15 Pro Max ስልክ ከኪሳቸው ሰርቆ ለመሰወር መሞከሩ ተመልክቷል።
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የባምቢስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ከአቤቱታው መነሻ በማድረግ ባከናወነው ፈጣን ኦፕሬሽን፣ ሁለቱንም ተጠርጣሪዎች ስልኩን እንደያዙ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ባስተላለፈው መልእክት፣ በወንጀል ተግባር ራስን ለማበልጸግ የሚሞክሩ አካላት ከህግ ተጠያቂነት እንደማያመልጡ አውቀው ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ አሳስቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #መናኸሪያfm #addisababapolice #crimenews #ethiopia #publicsafety #kirkossubcity #newsupdate

6 months ago
መኪና ለመግዛት የግል ፓርኪንግ ማረጋገጫ ግዴታ ነው ተባለ
#ethiopia | በቴክኖሎጂ ምጥቀቷ የምትታወቀው ጃፓን፣ በዓለም ላይ እጅግ ጥብቅ የሚባል የመኪና ባለቤትነት ሕግ ከሚከተሉ አገራት መካከል ዋነኛዋ ናት። በጃፓን ማንኛውም ሰው የግል መኪና ለመግዛትም ሆነ በራሱ ስም ለማስመዝገብ፣ መኪናውን የሚያቆምበት አስተማማኝ ቦታ እንዳለው የሚያረጋግጥ "ሻኮ ሾሜ-ሾ" (Shako Shomei-sho) የተባለ የፓርኪንግ ምስክር ወረቀት ከፖሊስ ማቅረብ ይኖርበታል።
ይህ ሕግ እ.ኤ.አ. ከ1962 ጀምሮ ተግባራዊ መሆን የጀመረ ሲሆን፣ ዋነኛ ዓላማውም በከተሞች ውስጥ ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ መቀነስ ነው። መኪናዎች በየመንገዱ ዳር እንዳይቆሙ በማድረግ፣ መንገዶች ለተሽከርካሪዎችና ለእግረኞች ክፍት እንዲሆኑ ለማድረግ ታስቦ የተቀረጸ ነው።
አንድ የመኪና ገዢ ከፖሊስ ጣቢያ የፓርኪንግ ማረጋገጫ ለማግኘት የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፦
የመኪና ማቆሚያ ቦታው ከመኖሪያ ቤቱ በ2 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውስጥ መሆን አለበት።
የመኪና ማቆሚያው መኪናውን ሙሉ በሙሉ ማስተናገድ የሚችል መሆኑ በፖሊስ በአካል ተገኝቶ ይረጋገጣል።
ይህ የምስክር ወረቀት ከሌለ፣ አንድ ሰው መኪና ቢገዛ እንኳ የሰሌዳ ቁጥር ማውጣትም ሆነ በሕጋዊ መንገድ መኪናውን መንዳት አይችልም።
ምንም እንኳ ሕጉ ጥብቅ ቢሆንም፣ "ኬ-ካርስ" (Kei cars) ተብለው የሚጠሩትና ቢጫ ሰሌዳ ያላቸው ትናንሽ መኪኖች በገጠርማ አካባቢዎች ሲገዙ ሕጉ በከፊል ላላ ሊል እንደሚችል ይነገራል። ይሁን እንጂ በትልልቅ ከተሞች ውስጥ መኪናን በመንገድ ዳር አሳድሮ ማግኘት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው።
የጃፓን መንግሥት ይህንን ሥርዓት በጥብቅ መተግበሩ ከተሞቿ ንጹህ፣ ሰላማዊ እና ለመንገደኞች ምቹ እንዲሆኑ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #menahhriafm #japan #trafficlaw #urbanplanning #carownership #shakoshomei #innovation #publicsafety #transportsystem

8 months ago
🍺 ሰክሮ በታንክ ከተማዋን ያወከው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ!
#ethiopia | በፖላንድ ማዕከላዊ ግዛት በምትገኘው ፓይንችኖ ከተማ፣ አንድ የ49 ዓመት ግለሰብ በከፍተኛ ስካር ውስጥ ሆኖ 36 ቶን የሚመዝን የጦር ታንክ በከተማዋ ጎዳናዎች ላይ ሲያሽከረክር ተገኝቶ በቁጥጥር ስር ውሏል።
⚠️ የድንጋጤ ምሽት
ክስተቱ የተፈጠረው በምሽት ሲሆን፣ የከተማዋ ነዋሪዎች T-55 የተሰኘ ግዙፍ የሶቪየት ዘመን ታንክ በመኖሪያ መንገዶች ላይ ሲንቀሳቀስ በመመልከታቸው በከፍተኛ ድንጋጤ ለፖሊስ ጥቆማ ሰጥተዋል። ፖሊስ ስፍራው ላይ ሲደርስ አሽከርካሪው በስካር መንፈስ ታንኩን መንገድ ላይ አቁሞት ተገኝቷል።
🚜 ለምን ታንኩን ነዳው?
እንደ ፖሊስ ሪፖርት፣ ግለሰቡ ታንኩን በጭነት መኪና የማጓጓዝ ኃላፊነት ነበረበት። ሆኖም፦
* ታንኩን የጫነው መኪና በመበላሸቱ ጥገና መጠበቅ ሰልችቶታል።
* በመሆኑም ታንኩን በቀጥታ አስነስቶ በከተማዋ መሃል መንዳት ጀምሯል።
⚖️ ቅጣቱ ምንድነው?
ምንም እንኳን በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም፣ ግለሰቡ "ለሕዝብ ደህንነት ስጋት የሚፈጥር አደገኛ ሁኔታ በመፍጠር" እና "በስካር በማሽከርከር" ክስ ተመስርቶበታል። ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘም፦
> እስከ 8 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ሊጠብቀው እንደሚችል ተገልጿል።
>
ታንኩ በማግስቱ ጠዋት በልዩ ባለሙያዎች ተነድቶ ወደ መከላከያ ይዞታ እንዲዛወር ተደርጓል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #poland #t55tank #strangenews #publicsafety #drunkdriving #worldnews #amharicnews

ለመዝረፍ የሞከሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ፖሊስ በእንጦጦ ፓርክ አካባቢ ጎብኝዎችንና ስፖርተኞችን ኢላማ በማድረግ ወንጀል ለመፈጸም የሞከሩ ሶስት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።
የክስተቱ ዝርዝር
ተጠርጣሪዎቹ በዛሬው ዕለት በሽሮ ሜዳ ቁስቋም በኩል ወደ እንጦጦ ፓርክ በመግባት ላይ የነበሩ የሆላንድ ዜጎችን ለመዝረፍ ሲንቀሳቀሱ በፖሊስ ክትትል ደርሶባቸዋል። ፖሊስ ባደረገው ከፍተኛ ማሳደድ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን፣ በወቅቱ ተጠርጣሪዎቹ ለማምለጥ ሲሞክሩ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ተገልጿል።
ፖሊስ በምርመራው የደረሰባቸው ነጥቦች፦
* የማንነት ማጭበርበር፦ ከተያዙት ግለሰቦች መካከል አንዱ የፎርጅድ የመከላከያ መታወቂያ ይዞ ተገኝቷል።
* የወንጀል ስልት፦ ወንጀለኞቹ እንደ ስፖርተኛ ወይም ጎብኝ በመምሰል እንዲሁም በአሳቻ ቦታዎች በመደበቅ ጥቃት እንደሚያደርሱ ተጠቁሟል።
* የቀጠለ ምርመራ፦ ፖሊስ የሁለቱን ተጠርጣሪዎች ማንነትና የቀድሞ የወንጀል ሪከርድ እያጣራ ይገኛል።
> "ህብረተሰቡ መሰል ጥርጣሬዎችን በመከታተል ትብብር እንዲያደርግ፣ አካባቢውን እንዲጠብቅ እና ወንጀልን በጋራ እንዲከላከል ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።"
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #addisababapolice #crimeprevention #entotopark #publicsafety #ethiopia

9 months ago
🚨 በጋምቤላ ከተማ የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ ታገደ፤ በሆቴሎች ላይም የሰዓት ገደብ ተጣለ
#ethiopia | በጋምቤላ ከተማ እየታየ ባለው ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ምክንያት፣ የከተማው አስተዳደር ጥብቅ የሆኑ አዳዲስ ክልከላዎችን ማውጣቱን አስታውቋል። እነዚህ ውሳኔዎች ከነገ አርብ ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በተግባር ላይ ይውላሉ።
የተጣሉ ዋና ዋና ገደቦች፦
* የሞተር ሳይክል እገዳ፦ የመንግስትም ሆኑ የግል ሞተር ሳይክሎች በከተማይቱ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ "ላልተወሰነ ጊዜ" በጥብቅ ታግደዋል።
* የባጃጅ የሥራ ሰዓት፦ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጆች) አገልግሎት መስጠት የሚችሉት ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል።
* ሆቴሎች እና ግሮሰሪዎች፦ ማንኛውም የመዝናኛ እና የምግብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ክፍት እንዲሆኑ ተወስኗል።
የከተማው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መግለጫ እንዳመለከተው፣ ውሳኔው የተላለፈው በከተማው ሰላም እና ደህንነት ዙሪያ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ ነው።
አስተዳደሩ አክሎም እነዚህን ክልከላዎች ጥሶ በሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ ላይ ጥብቅ "አስተዳደራዊ እርምጃ" እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል። የከተማው ነዋሪዎችም ለጸጥታው መከበር ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#gambella #ethiopia #securityalert #breakingnews #gambellacity #publicsafety #ጋምቤላ #ኢትዮጵያ

Sponsored by
Surafel
Comments