በጋምቤላ ክልል ከ200 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርገው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት
*********************
በጋምቤላ ክልል "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል የዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ-ግብር በይፋ ተጀምሯል።
በክልሉ ጋምቤላ ከተማን እና የኢታንግ ልዩ ወረዳን ጨምሮ በሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች በሚከናወነው በዚህ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ ከ200 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ልዩ ልዩ የልማትና የድጋፍ ሥራዎች እንደሚከናወኑ ተገልጿል።
የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ቱት ጆክ ዛሬ በከተማ አስተዳደሩ የሚገኑ የአቅመ-ደካማ ወገኖችን የቤት ዕድሳት በይፋ በማስጀመር የክረምቱን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ አስጀምረዋል።
ከንቲባው መርሃ-ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት፤ ወጣቶችንና በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር ረዳት የሌላቸውን አረጋውያን ቤቶች የመገንባትና የማደስ፣ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ፣ የአካባቢ ጽዳት፣ የደም ልገሳ እንዲሁም የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፎችን የማበርከት ተግባራት በስፋት ይከናወናሉ።
የበጎ ፈቃደኝነት ተግባር የሁሉም ዜጋ ማኅበራዊ ኃላፊነት በመሆኑ፣ መላው የከተማዋ ነዋሪ በመርሃ-ግብሩ ላይ በንቃት መሳተፍ እንዳለበት አሳስበዋል።
አክለውም በጎነት የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህልን በማጎልበት የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያግዝ በመሆኑ፣ የሁሉም አካላት ቅንጅታዊ ተሳትፎ እንደሚያስፈልገው ከንቲባው ተናግረዋል።
በጋምቤላ ክልል በዘንድሮው የክረምት ወራት ከ90 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞችን በተለያዩ ዘርፎች በማሰማራት ከ218 ሺህ በላይ የሚሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ለማድረግ ታቅዶ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ተመላክቷል።
በሚፍታህ አብዱልቃድር
#ethiopianbroadcastingcorporation #ethiopia #gambella #voluntaryservice #communitysupport

1 month ago