3 hours ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ሰኞ ዕለት በአማራ ክልል በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የ14 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፣ በሰባት ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት ደርሷል። የፍለጋ እና የነፍስ አድን ስራው አሁንም ቀጥሎ ባለበት በዚህ ወቅት፣ እስካሁን የገቡበት ያልታወቁ እና በፍርስራሹ ስር የተቀበሩ በርካታ ሰዎች እንዳሉ ተነግሯል።
አደጋው የተከሰተው በፃድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም ሲሆን፣ በወቅቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ለፀበል እና ለመንፈሳዊ ፈውስ በስፍራው ተሰብስበው ነበር። የሀገረ ስብከቱ ዋና ስራ አስኪያጅ መጋቤ ሐዲስ ነቃ ጥበብ አባቡ ለአሶሼትድ ፕሬስ እንደተናገሩት፣ "አደጋው የተከሰተው ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ገደማ ሲሆን፣ ከሟቾቹ መካከል አብዛኞቹ ፀበል ለመጠመቅ የተሰበሰቡ ነበሩ።" ስራ አስኪያጁ አክለውም፣ "ከሟቾቹ መካከል አስራ አንዱ በገዳሙ ውስጥ የተቀበሩ ሲሆን፣ የሌሎቹ አስከሬን ወደ ትውልድ ስፍራቸው ተልኳል፤ ይሁን እንጂ የአንዳንዶቹን ሟቾች ማንነት ለመለየት አስቸጋሪ ሆኗል" ብለዋል።
ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ከገዳሙ 70 ኪሎ ሜትር (43 ማይል) ርቀት ላይ ወደምትገኘው የሰሜን ሸዋ አስተዳደር ዞን ዋና ከተማ ደብረ ብርሃን ለህክምና ተወስደዋል። የመሬት መንሸራተቱ የተከሰተው ከተራራ አጠገብ በመሆኑ፣ ግዙፍ አለቶች ተገንጥለው በምዕመናኑ ላይ መውደቃቸው አደጋውን ይበልጥ አባብሶታል። የአካባቢው አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ፣ የፍለጋ እና አድን ስራዎችን ለማገዝ የአካባቢው የአደጋ መከላከል ጽህፈት ቤት ባለሙያዎች ቡድን ወደ ስፍራው መሰማራቱን አስታውቋል።
በኢትዮጵያ ከሰኔ እስከ መስከረም በሚዘልቀው የክረምት ወቅት ከባድ ዝናብ የሚያስከትለው የመሬት መንሸራተት እና ጎርፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለመደ መጥቷል። በሐምሌ 2024 በደቡብ ኢትዮጵያ በጣለ ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተ አሳዛኝ የመሬት መንሸራተት ቢያንስ 257 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። ከዚህ ቀደምም በዚህ ዓመት መጀመሪያ አካባቢ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ ጋሞ ውስጥ በተከሰተ ተመሳሳይ የመሬት መንሸራተት ከ100 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
በአፍሪካ ቀንድ የምትገኘው ኢትዮጵያ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዙ የከፋ የአየር ፀባይ ክስተቶች በከፍተኛ ሁኔታ እየተጠቃች ትገኛለች። በተለይም በገጠራማ አካባቢዎች ያለው ደካማ መሰረተ ልማት፣ በርካታ ማህበረሰቦችን ለጎርፍ፣ ለመሬት መንሸራተት እና ተደጋጋሚ ድርቅ በቀላሉ ተጋላጭ እንዲሆኑ ያደረጋቸው ሲሆን፣ ለእንደዚህ አይነት አደጋዎች ፈጣን ምላሽ የመስጠት አቅማቸውም እጅግ ውስን ሆኖ ቆይቷል።

4 hours ago
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ
📌 የ6ኛ ክፍል ውጤቱ ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ነው
#ethiopia |የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ይፋ አድርጓል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ አብዮት ደምሴ እንደገለጹት፣ የዘንድሮው ማለፊያ ነጥብ ለሁለቱም ክፍሎች ክልላዊ 50 እና ከዚያ በላይ እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን፣ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ አካባቢዎች ደግሞ 48 እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ተደርጓል።
በዚህም መሠረት በ8ኛ ክፍል ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡት 86 ሺህ 502 ተማሪዎች መካከል 78 ሺህ 203 የሚሆኑት ተፈትነው 47 ሺህ 307 ተማሪዎች ማለፊያ ነጥቡን በማስመዝገብ ወደ ቀጣይ ክፍል ተዛውረዋል።
ይህም የክልሉን አጠቃላይ የማለፍ ምጣኔ 60.4 በመቶ የሚያደርሰው ሲሆን፣ ከአምናው የ63 በመቶ ውጤት ጋር ሲነፃፀር የ3 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል።
በተቃራኒው በ6ኛ ክፍል ከተፈተኑት 110 ሺህ 566 ተማሪዎች ውስጥ 70 ሺህ 584ቱ ማለፊያ ነጥብ በማምጣት ያለፉ ሲሆን፣ የክልሉ የማለፍ ምጣኔ 63.8 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል። ይህ ውጤት ከአምናው የ56 በመቶ አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ እድገት የታየበት ነው።
ከትምህርት ቤቶች አፈፃፀም አኳያም በ8ኛ ክፍል 540 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ማሳለፍ ሲችሉ፣ 155 ትምህርት ቤቶች ግን አንድም ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም።
በ6ኛ ክፍል ደግሞ 476 ትምህርት ቤቶች 100 በመቶ የማሳለፍ ስኬት ሲያስመዘግቡ፣ 81 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ ሳያሳልፉ ቀርተዋል።
የክልል ትምህርት ቢሮ
#southethiopia #ethiopiaeducation #ministryofeducation #grade8exam #grade6exam

8 days ago
የአሸናፊዎች አሸናፊ ውጊያ ይደረጋል‼️
ህወሃት የ 1983 ታሪክን እንደግማሁ እያለ ነው።
የሕወሓት ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር (ሞንጆሪኖ) ከሰሞኑ በአንድ መድረክ ላይ አነጋጋሪ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ አሁን ከተጣመርናቸው ኃይሎች ጋር መዋጋታችን አይቀርም ብለዋል፡፡ የሀላፊዋ ንግግር የጽምዶ ኃይሎችን የትብብር መሰረት የሚያናጋ ነው ተብሏል፡፡
ወይዘሮ ፈትለወርቅ ቃል በቃል የተናገሩ፡-
‹‹ዋናው ነገር ብልፅግናን ለመጣል ፍላጎት ያሳይ እንጂ የትኛውም ስብስብ እርስ በራሱ እሳትና ጭድ ቢሆንም እንኳን አብረን እንሰራለን። ብልፅግናን ከጣልን በኃላ ደግሞ የአሸናፊዎች አሸናፊ ለመለየት ሌላ ዙር ፍልሚያ ይኖረናል።
ለዚህም እየተዘጋጀን ነው፤ ይህ በተለያየ መልክ የተጀመረውን ትብብራችንን ስናየው የተለያየ ፍላጎት ያለን ሃይሎች ሆነን ነው ትብብር እየፈጠርን ያለነው። በአላማ፣ በፕሮግም፣ ወደፊት በረዥም ጊዜ እቅድ ምናምን አንድ ነን ማለት አይደለም። ትብብራችን በዛች በምታገናኘን ነገር ብቻ ነው።
እኛ ከፋኖ የምንለይበት የፖለቲካ አቋም አለን። ከሻዕቢያ ይሁን ከሌሎች የተለያዩ ሃይሎች የምንለያይባቸው መዓት ጉዳዮች አሉ። አንድ የሚያደርገን ግን የብልፅግና ስርዓት የሁላችንም ስጋት ነው የሚለው ነው። ይቺ ብቻ ናት የምታገናኘን።
እንደ ተሞክሮ ልንወስደው የሚገባን ነገር ደግሞ እንኳን አሁን በብዙ ጉዳዮች ልዩነት ካለንና በዓላማ ከማንገናኛቸው የተለያዩ ሃይሎች ጋር የምንፈጥረው ትብብር ይቅርና ኢህአዴግም እኮ ፈርሷል።
ኢህአዴግ እኮ የኦሮሞ፣የአማራ፣የደቡብ ኢትዮጵያ ሃይሎች አራት ድርጅቶች አንድ ላይ ሆነን የፈጠርነውና በፕሮግራም ወይም አላማ አንድ የነበረ ድርጅት ነበር። ግንኙነታችንም ስትራቴጂካዊ ነበር[ታክቲካል አልነበረም] ፣ በተለያየ ቋንቋ የተፃፈች አንዲት ፕሮግራም ነበር የነበረችን።
ግንባር ከመሆናችን ውጭ አንድ ድርጅት ማለት ነበርን፤ በዚህ ደረጃ የነበርን ሰዎች እኮ ተካክደናል[እንኳን ይሄ በዓላማ ከማይመስሉን ሃይሎች ጋር የምንፈጥረው ትብብር ይቅርና]›› ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር
Via :- Andafta
Seledadotio

ቱሪዝም፦ የመደመር እሳቤ የተፈጥሮ ጸጋዎቻችንን ወደ ኢኮኖሚ ሞተርነት የለወጠበት ተጨባጭ ማሳያ
***************************
ኢትዮጵያ እጅግ አስደናቂ የታሪክ፣ የተፈጥሮ፣ የመልክዓ ምድር እና እምቅ የባህል ሀብት ያላት ሀገር ብትሆንም፣ እነዚህን ጸጋዎች አቀናጅቶ እና አልምቶ ለመጠቀም የሚያስችል ሥልታዊ ዕቅድ እና ቁርጠኝነት ባለመኖሩ ለዘመናት ለሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ተጨባጭ አስተዋጽኦ ሳያበረክቱ ቆይተዋል።
ነገር ግን ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ በሀገራችን ተግባራዊ የተደረጉት ዘርፈ ብዙ ማሻሻያዎች ይህንን የአስተሳሰብ አጥር በመስበር፣ የሀገራችንን እውነተኛ አቅም ወደ መግለጥ ተሸጋግረዋል።
ይህ ስኬት የመጣው የመንግሥትን፣ የግሉን ዘርፍ፣ የማኅበረሰቡን እና የተፈጥሮን አቅም በአንድ የጋራ ሕልም ዙሪያ አስተባብሮ ከሚመራው የመደመር ፍልስፍና ነው። ዜጎች ሀገራቸውን እንዲያውቁ፣ እንዲወዱ እና እንዲኮሩባት የተደረገው ብሔራዊ ጥሪ ቱሪዝምን ከተለመደው የታሪክ ጥበቃ አልፎ ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ሞተርነት አሸጋግሮታል።
በቱሪዝም ዘርፍ የታየው ይህ ሥር ነቀል ለውጥ የመጣው ታዲያ ፈጣን እና ፈጠራ በተሞላበት የፕሮጀክት አመራር የተመራ ሥልታዊ ለውጥ ነው። ይህ ጉዞ በ2011 ዓ.ም አዲስ አበባን ለማስዋብ ከተጀመረው እና እንጦጦ እንዲሁም ሸገር ፓርኮችን እውን ካደረገው "ገበታ ለሸገር" መርሐ ግብር ጅማሮውን አድርጓል።
የዚህ ፕሮጀክት መሳካት በ2012 ዓ.ም ልማቱን ወደ ክልሎች በማስፋፋት በጎርጎራ፣ ወንጪ እና ኮይሻ የተፈጥሮ መዳረሻዎችን በከፍተኛ ጥራት ያለማውን "ገበታ ለሀገር" ፕሮጀክትን ወልዷል።
በአሁኑ ወቅት ደግሞ ስምንት አዳዲስ መዳረሻዎችን በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለማው "ገበታ ለትውልድ" መርሐ ግብር ሀገራዊ የቱሪዝም ገጽታን በመሠረታዊነት እየቀየረ ይገኛል።
የእነዚህን ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መዳረሻዎች አስተዳደር ለኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ለተመረጡ ባለሀብቶች መሰጠቱ ደግሞ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎችን ለመሳብ ሥልታዊ ድልድይ ሆኗል።
በእነዚህ መርሐ ግብሮች የተገነቡት ፕሮጀክቶች የመደመር እሳቤን በተግባር የሚያሳዩ ተጨባጭ የልማት ዕንቁዎች ናቸው።
በደቡብ ኢትዮጵያ የተመረቀው የአርባ ምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት የኮንፈረንስ ቱሪዝምን ከአዲስ አበባ ውጪ በማስፋፋት እና ከአባያ እንዲሁም ጫሞ ሐይቆች ተፈጥሯዊ ውበት ጋር በመዋሃድ ለአካባቢው ኢኮኖሚ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል።
በተመሳሳይ በአማራ ክልል የተገነባው የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት 13.3 ሔክታር ላይ ያረፈ ዘመናዊ መገልገያዎችን እና የሔሊኮፕተር ማረፊያን ያካተተ ሲሆን፣ የሰሜኑን የሀገራችን የቱሪስት መስመር የሚያስተሳስር ወሳኝ ማዕከል ሆኗል።
በአፋር ክልል የተገነባው የኒዒን ሌ ፓልም ስፕሪንግ ሎጅ ከአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ጋር ባለው ቅርበት የተፈጥሮ ፍል ውኃን እና ሐይቅን በማቀናጀት የቱሪዝም አቅምን እያጎላ ይገኛል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የተገነባው ደንቢ ኢኮ ሎጅ በበካ የቡና እርሻ አጠገብ ሙሉ በሙሉ ከአካባቢው የተገኙ የተፈጥሮ ቁሳቁሶችን በመጠቀም የተገነባ የዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ ሞዴል ነው። በዚሁ ክልል የሚገኘው የሀላላ ኬላ ሪዞርትም በጊቤ ሦስት ሰው ሠራሽ ሐይቅ ዳርቻ የተገነባ ሌላው አስደናቂ ማሳያ ነው።
እነዚህ ታላላቅ የቱሪዝም መዳረሻዎች በማክሮ ኢኮኖሚክስ ዕይታ የቱሪዝምን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ በከፍተኛ ደረጃ የሚያባዙ ናቸው። ፕሮጀክቶቹ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ቁሳቁሶች እና በኢትዮጵያውያን አቅም መገንባታቸው በአካባቢው ማኅበረሰብ ውስጥ የሚፈጠረውን የግብይት ዝውውር በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል።
ይህ ስትራቴጂ ኢትዮጵያ በ2018 በጀት ዓመት የ10.2 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ ከያዘችው ግብ ጋር በቀጥታ የሚጣጣም ሲሆን፣ ዘንድሮ ከቱሪዝም ዘርፍ ከ5.2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ የዚህ የመደመር ቀመር ተግባራዊ ስኬት ነው።
የገበታ መርሐ ግብሮች ከተለመደው የቢሮክራሲ አሠራር ወጥተው በፈጠራ የታገዘ የፕሮጀክት አመራርን በማሳየት፣ የኢትዮጵያን የተዳፈነ ጸጋ ወደ ተግባራዊ ሀብት በመቀየር ለቀጣዩ ትውልድ የበለጸገች ሀገርን ለማስረከብ የተጀመረው ጉዞ ስኬታማ ማሳያዎች ናቸው።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #tourism #medemer #gebetainitiatives #economicgrowth #landoforigins

10 days ago
ሕፃናትን በማታለል የደፈሩ ጥበቃ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ
#ethiopia | በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በዎላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ ሶዶ በር ቀበሌ በሚገኘው የንጋት ትምህርት ቤት ጥበቃ ሆኖ የሚሠሩት ታዲዎስ ሞታ የተባለ ግለሰብ፣ የ5 እና 7 ዓመት ሕፃናት ላይ ግብረ-ሥጋ ድፍረት በመፈጸማቸው የ25 ዓመት ጽኑ እስራት ቅጣት ተጣለባቸው።
ተከሳሹ ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. ሕፃናቱን “ዥዋዥዌ ትጫወታላችሁ” በማለት በማታለል በሚሠሩበት ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ወደሚገኝ ማደሪያ ክፍል በማስገባት ወንጀሉን ፈጽመዋል።
ፖሊስ በሰበሰበው ማስረጃ ድርጊቱ መፈጸሙን ማረጋገጥ ተችሏል።
ጉዳዩን ሲመረምር የቆየው የቦዲቲ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. በዋለው ችሎት፣ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ተከሳሹ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀጽ 60/ሀ እና 627/1 መሠረት ጥፋተኛ መሆኑን አረጋግጧል።
ፍርድ ቤቱ ተከሳሹን እንዲሁም መሰል ወንጀል ፈጻሚዎችን ለማስተማርና ለመከላከል በሚል የ25 ዓመት ጽኑ እስራት ቅጣት ወስኖበባቸዋል።
የቦዲቲ ከተማ ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት

Sponsored by
Surafel
22 days ago
የ69 ዓመታቸው አዛውንት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን ገብተዋል።
በትምህርት ዓለም ውስጥ ዕድሜ ገደብ እንደሌለው በተግባር ያሳዩት የ69 ዓመቱ አዛውንት አባባ ወልደየስ አያና አሻቦ ዘንድሮ በሚሰጠው 4ኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ላይ በመቀመጥ አዲስ ታሪክ አስመዝግበዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ልዩ ስሟ ዳንጋራ ሳላጣ በተባለች ቀበሌ ተወልደው ያደጉት አባባ ወልደየስ፣ ቀደም ሲል ማህበረሰባቸውን በቀበሌ አስተዳዳሪነት ከስድስት ዓመታት በላይ በታማኝነት ያገለገሉ የሀገር ሽማግሌ ናቸው።
በደርግ ዘመን በትውልድ አካባቢያቸው እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ ተምረው ቢያጠናቅቁም፣ በወቅቱ በነበረው የትምህርት አደረጃጀት፣ የአገዛዝ ሥርዓትና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአቅራቢያቸው አለመኖር ምክንያት ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገደው ነበር።
ይሁን እንጂ ለትምህርት ያላቸው ፍቅርና ቁጭት ሳይቀንስ ከረጅም ዓመታት ቆይታ በኋላ በ2015 ዓ.ም ወደ ገበታ በመመለስ ከ9ኛ ክፍል ጀምረው በመማር ዛሬ ለዚህ ትልቅ ሀገር አቀፍ ፈተና ለመብቃት ችለዋል።
አባባ ወልደየስ የ6 ልጆች አባት ሲሆኑ፣ የቤተሰብ ኃላፊነትንና የማህበረሰብ አገልግሎትን ከትምህርት ጉዟቸው ጋር ጎን ለጎን አስማምተው ማስኬዳቸው ልዩ ያደርጋቸዋል።
ይበልጡኑ ደግሞ ከገዛ ልጆቻቸው ጋር በአንድ የመማሪያ ክፍል ውስጥ ተቀምጠው መማራቸውና ለፈተናውም በጋራ መዘጋጀታቸው ልዩ ደስታ እንደፈጠረላቸው ይናገራሉ።
እኩዮቻቸው ወደ ጡረታ በሚገቡበት ዕድሜ መጽሐፍ አንግበው ወደ ትምህርት ቤት የተመላለሱበት ዋና ዓላማ በመንግሥት ተቀጥሮ ለመሥራት ሳይሆን፣ አሁን የሚሰሩትን የግብርና ሥራ በዘመናዊ መንገድ ለማሻሻልና በተሻለ ሁኔታ ለማምረት የሚያስችላቸውን ሳይንሳዊ ዕውቀት ለማግኘት እንደሆነ ያስረዳሉ።
ይህ አስደናቂ ታሪክ “የተማረ ሰው የሥራ ዕድል ፈጣሪ እንጂ ተቀጣሪ ብቻ መሆን የለበትም” የሚለውን ዘመናዊ ትርክት በተግባር የሚያሳይ ነው።
በትጋትና በጽናት ከተጓዙ ዕድሜ ለማንኛውም ስኬት እንቅፋት ሊሆን እንደማይችል ለሚያነበውና ለወጣቱ ትውልድ ትልቅ መነሳሻ እንደሚሆን ይታመናል።
የዩኒቨርሲቲው ህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኝነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት እንዲሁም መላው የፈተና አስተባባሪ ግብረ-ሃይል ለአባባ ወልደየስ መልካም ምኞቱን እየገለጸ፣ ይህ ፈተና የረጅም ጊዜ ራዕያቸውን የሚያሳኩበት እንዲሆን ተመኝቷል።
Via ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ

ግልግል
ግብር በቴሌብር!
ሰነድ ማዘጋጀትና ሰልፍ መሰለፍ ቀረ፤ የዓመቱን ግብር በቴሌብር አሁኑኑ እንክፈል!
የገቢዎች ሚኒስቴርን፣ የአዲስ አበባ (ከፍተኛ፣ መካከለኛና አነስተኛ)፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን እንዲሁም የኦሮሚያ፣ የአማራ፣ የሲዳማ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦችን፣ የሱማሌ፣ የሐረሪ፣ የአፋር እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ገቢዎች የግብር ክፍያ በአስተማማኝ ሁኔታ አሁኑኑ በቴሌብር ይክፈሉ!
ቴሌብር ሱፐርአፕን https://bit.ly/telebirr_Su... ጭነን ስንከፍል እንዲህ ነን!
#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን #ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን #ስንጭን_እንዲህ_ነን #ስናስጀምር_እንዲህ_ነን

24 days ago
ከገጽታ ግንባታ ባሻገር፦ ቱሪዝም የኢትዮጵያውያን አዲሱ የትስስር ድልድይ
*******************
ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ እያደረገችው ያለው አስደናቂ ጉዞ፣ ከተለመደው የኢኮኖሚ ትርፍ እና የገጽታ ግንባታ ትርክት የዘለለና እጅግ ጥልቅ ትርጉም ያለው ነው።
ሀገራችን እጅግ ገናና ታሪክ፣ ማራኪ የተፈጥሮ መልክዓ ምድር እና እምቅ የባህል ሀብት ባለቤት ናት።
ይሁን እንጂ ይህን ጸጋ አቀናጅቶ እና አልምቶ ለመጠቀም የሚያስችል ስልታዊ ዕቅድ እና ቁርጠኝነት ባለመኖሩ፣ የሀገራችን ብልጽግና ለዘመናት በምኞት ብቻ ሲታጠር ቆይቷል።
ባለፉት ዓመታት በሀገራችን ተግባራዊ የተደረጉት ዘርፈ ብዙ ማሻሻያዎች ይህን የቸልተኝነት ድባብ በመግፈፍ የእውነተኛ ውበታችንን እና አቅማችንን በር ከፍተዋል።
ይህ መነቃቃት ከመሠረታዊው የመደመር እሳቤ ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነው። መደመር የሀገርን ሙሉ አቅም በአንድ የጋራ ሕልም ዙሪያ አስተባብሮ ለአንድ ዓላማ እንዲውል የማድረግ ፍልስፍና ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ደጋግመው የሚያቀርቡትን "ሀገራችንን እንወቅ፣ እንውደድ፣ እንኩራባት፤ ይህ አስደናቂ ምድር የእኛው ነውና!" የሚለውን ብሔራዊ ጥሪ በቱሪዝም ልማት እያሳዩ ነው።
ከምንም በላይ አሁን የተጀመረው የቱሪዝም ልማት የብሔራዊ አንድነት ማጠናከሪያ እና የጠንካራ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ድልድይ ነው።
የሀገር ውስጥ ቱሪዝም ሲስፋፋ አንዱ ማኅበረሰብ ወደ ሌላው በማቅናት ባህልን ይለዋወጣል፣ ቋንቋን ያዳምጣል፣ አብሮ ማዕድ ይጋራል።
ይህ ደግሞ በዜጎች መካከል የተገነቡ የተዛቡ አመለካከቶችን በመስበር መተሳሰብን እና ሀገራዊ ባለቤትነትን ያጎለብታል። የቱሪዝም መዳረሻዎችም የልዩነት መገለጫ ሳይሆኑ የጋራ ማንነት መገለጫ ሆነው ያገለግላሉ።
ይህን እውነታ መሬት ላይ ለማውረድ፣ የመዲናችንን ገጽታ ከቀየረው የ“ገበታ ለሸገር” ፕሮጀክቶች ስኬት በመቀጠል፣ የ"ገበታ ለሀገር" እና የ"ገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክቶች ልማቱን ወደ ተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ይዘውት ዘልቀዋል።
በአፋር ክልል የተገነባው የ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ' በአካባቢው ያለውን ያልታየ እምቅ አቅም ወደ ልማት የቀየረ ታላቅ ሥራ ነው።
ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ስናቀና ደግሞ የአርባ ምንጭ ኮንፍረንስ ሪዞርት፣ የኮንፍረንስ ቱሪዝምን ከአዲስ አበባ ውጪ በማስፋት የሁሉም ኢትዮጵያውያን መገናኛ ማዕከል ሆኗል።
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በአማራ ክልል የተገነባው የ‘ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት' ቀደም ሲል ከቱሪስት እይታ ርቆ ለቆየው አካባቢ አዲስ ሕይወት የዘራ ነው።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የተገነባው የ‘ደንቢ ኢኮ ሎጅ' ደግሞ የኢትዮጵያን አረንጓዴ ውበት ዳግም የገለጠ ድንቅ ፕሮጀክት ነው።
እነ ጎርጎራ፣ ወንጪ ደንዲ፣ ጨበራ ጬርጩራ እና ሃላላ ኬላ ያሉ ኢኮ ለጆችም የኢትዮጵያውያንን ድንቅ የጋራ ሀብት ገልጠው አሳይተዋል።
እነዚህ ከመዲናዋ ውጭ የተገነቡ ውብ ሥፍራዎች ኢትዮጵያውያን ከጫፍ ጫፍ ተንቀሳቅሰው ሀገራቸውን እንዲያውቁ እና የኅብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን ማኅበራዊ ትስስር አጥብቀው እንዲገነቡ ታላቅ ዕድል ፈጥረዋል።
በማክሮ ኢኮኖሚ ረገድ እነዚህ ፕሮጀክቶች ቱሪዝምን ከባዶ እይታ አውጥተው ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ግብይት አሸጋግረውታል።
ቱሪስቶች አዳዲስ እና ማራኪ መዳረሻዎችን ሲጎበኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች ወጪ ያደርጋሉ፤ ይህም በየአካባቢው ማኅበረሰብ ውስጥ የገንዘብ ዝውውርን ያፋጥናል፤ የሥራ ዕድልን ይፈጥራል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ጎብኚዎች ይዘው የመጡትን ገንዘብ ወደ ከፍተኛ ደስታ ቀይረው፣ ላወጡት ወጪ ሳይቆጩ መመለስ አለባቸው።
ፕሮጀክቶቹ የየአካባቢውን ግብዓትና የሰው ኃይል በመጠቀም የውጭ ምንዛሬ ወጪን በመቀነስ በኩል ያላቸው አስተዋጽኦም ከፍተኛ ነው።
እነዚህ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎች ከተለመደው የፖለቲካ እና የቢሮክራሲ አሠራር በመውጣት ፈጣን እና ፈጠራ የተሞላበት አመራር መስጠት ከተቻለ ምን ያህል ርቀት መጓዝ እንደምንችል በተግባር አሳይተውናል።
አቧራ ተሸፍነው የነበሩ የሀገራችን ጸጋዎች ዛሬ በአዲስ ምናብ ደምቀው አይተናቸዋል። ይህ ስኬት የምትከበር፣ የምትወደድ እና በራሷ አቅም የምትቆም የበለጸገች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ የጀመርነው ታሪካዊ ጉዞ በትክክለኛ መንገድ ላይ ለመሆኑ ትልቅ ማረጋገጫ ነው።
ሀገራችንን እያወቅን፣ ውበቷን እያጣጣምን እና ትስስራችንን እያጠናከርን ወደ ኢትዮጵያ ከፍታ እንጓዛለን!
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #medemer #tourism #visitethiopia #landoforigins #ebc

27 days ago
የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ወሳኝ መሠረት እንደሚጥል ተመካካሪዎች ገለፁ
**********************
ዋናዉ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ መሠረታዊ ሀገራዊ ችግሮችን በውይይት በመፍታትና የተረጋጋች ሀገር ለመገንባት ወሳኝ መሠረት የሚጥል መሆኑን በጉባኤው ላይ የሚሳተፉ ተመካካሪዎች ገለፁ።
ከሐምሌ 8 ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በሚካሄደው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሚሳተፉ ተመካካሪዎች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።
ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ላይ ምክክር የሚካሄድባቸው ስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች የተለዩ ሲሆን በእነዚህም ላይ በዝርዝር ለመምከርና ዘላቂ መፍትሔዎችን ለማስቀመጥ፣ ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢ የተወከሉ 4 ሺህ ተመካካሪዎች ወደ አዲስ አበባ በመግባት ላይ ይገኛሉ።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የክልሎች የከተማ አስተዳደሮች እና የዳያስፖራ አስተባባሪ አቶ ረታ ጌራ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፤ ከየክልሎቹና ከዳያስፖራው ማህበረሰብ የተወከሉ ተመካካሪዎች ለዋናው ጉባኤ አዲስ አበባ እየገቡ መሆኑን አስታዉቀዉ፤ ኮሚሽኑ ለተሳታፊዎቹ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ እና በሌሎችም ምቹ ቦታዎች ላይ ደማቅ አቀባበል እያደረገላቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ተመካካሪዎች በበኩላቸው፤ ለዘመናት የዘለቁ አለመግባባቶችንና ስር የሰደዱ ልዩነቶችን በሰለጠነ መንገድ ለመፍታት በሚደረገው በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ ለመሳተፍ ዕድል በማግኘታቸው የተሰማቸውን ላቅ ያለ ደስታ ገልጸዋል።
ከፌደራል ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ወገን የተወከሉት አቶ ሀንፍሬ ከዳፎ ይህ ታሪካዊ መድረክ በአለመግባባቶች ላይ በጠረጴዛ ዙሪያ በመመካከር ጠንካራ አንድነት ያላት ሀገር ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ከኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን የመጡት የማህበረሰብ መሪ ወይዘሮ ዘርፌ በቀለ በበኩላቸው በዚህ ታሪካዊ ወቅት ተመካክረን ተደማምጠንና ተቀራርበን ጠንካራ ሀገር ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ትልቅ ተስፋ ሰንቀናል ብለዋል።
በተመሳሳይ ከአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን የወጣቶች ተወካይ ያረጋል ታደሰ የምክክር ጉባኤው ህብረ ብሔራዊ አንድነት ይበልጥ ለማጠናከር ትልቅ አቅም እንደሚሆን ገልፀዋል።
እንዲሁም ምክክሩ ለዘላቂ ሀገራዊ ስምምነትና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ታላቅ አስተዋፅኦ ያበረክታል ሲሉ ከጋምቤላ ክልል የመጡት ተመካካሪ አቶ ሉክ ኬዌ አብራርተዋል።
ከደቡብ ኢትዮጵያ የመጡት ተመካካሪ ኢንጂነር ምንትዋብ ምንጃር እና ከአዲስ አበባ የተወከሉት አቶ ገረመው ጫልቃ በበኩላቸው መድረኩ ተመካካሪዎች ሀሳባቸውን በነጻነትና በሀላፊነት በማንሸራሸር ለቀጣይ ትውልድ የምትሆን አስተማማኝና ጠንካራ ሀገር የሚገነቡበት ታሪካዊ አጋጣሚ መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜኣ ዘግቧል።

1 month ago
Sponsored by
Surafel
1 month ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በምዕራብ አባያ ወረዳ ያደረጉት የገጠር ኮሪደር ጉብኝት
#ruralcorridor #pmabiyahmed #southethiopia
#ethiopia #medemer
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...

#ሀሰተኛ - ይህ ከላይ በምስሉ የሚታየው " ፂም ያለው እና ሽማግሌ የሚመስል ሕጻን በጋሞ ዞን ቦረዳ ወረዳ ተወለደ " እየተባለ የሚነገረው ሀሰት ነው።
በርካቶች መረጃውን ሳያረጋግጡ በችኮላና አንዳንዶች ደግሞ ሆን ብለው የሰዎችን እይታ ለማግኘት ሲሉ ብቻ " በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጋሞ ዞን፣ ቦረዳ ወረዳ ጭላሼ ቀበሌ ልዩ ስሙ ወቆ በተባለ ሥፍራ፣ ሙሉ ፂም ያለውና መልኩ ሽማግሌ የሚመስል ሕፃን ተወለደ " ሲሉ ሀሰተኛ መረጃ አሰራጭተዋል።
Seledadotio
Seledadotio
በርካቶች መረጃውን ሳያረጋግጡ በችኮላና አንዳንዶች ደግሞ ሆን ብለው የሰዎችን እይታ ለማግኘት ሲሉ ብቻ " በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጋሞ ዞን፣ ቦረዳ ወረዳ ጭላሼ ቀበሌ ልዩ ስሙ ወቆ በተባለ ሥፍራ፣ ሙሉ ፂም ያለውና መልኩ ሽማግሌ የሚመስል ሕፃን ተወለደ " ሲሉ ሀሰተኛ መረጃ አሰራጭተዋል።
Seledadotio
Seledadotio
Sponsored by
Surafel
1 month ago
የ6 ወር ነፍሰ ጡር ባለቤቱን የገደለው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ
በጎፋ ዞን በላሃ ከተማ አስተዳደር የ6 ወር ነፍሰ ጡር ባለቤቱን የገደለው ተከሳሽ ጀማል ሁሴን በሞት እንዲቀጣ መወሰኑን ፖሊስ አስታውቋል።
ተከሳሹ በጎፋ ዞን በላሃ ከተማ አስተዳደር ሀብት-ምንጭ ቀበሌ ውስጥ ከባለቤቱ ጋር በነበረ የፍትሐ ብሔር ክስ ምክንያት ቂም በመያዝ በስለታማ መሣሪያ በመውጋት
ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጉን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ሀይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ያቀረባቸው የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ክሱን ከጥርጣሬ በላይ እንደሚያስረዱ በመግለጽ ተከሳሹ እንዲከላከል ብይን ሰጥቶ ነበር። ተከሳሹም "የመከላከያ ማስረጃ የለኝም" በማለቱ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ብሎ ወስኗል።
በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ የቅጣት አስተያየቶችን ከተቀበለ በኋላ ተከሳሹ በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ ማስተላለፉንየደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ሀይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
Via_dagu

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ መፀር መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ከአካባቢ ሱቅ የተገዛን ኦሬንጅ ጁስ በመበጥበጥ የጠጡና ያሸተቱ ቁጥራቸው ወደ 200 የሚጠጉ ተማሪዎች ራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተገለፀ።
በዞኑ ደቡብ አሪ ወረዳ ሜፀር ትምህርት ቤት በደረሰው ይህንን ድንገተኛ የጤና መታወክ ዙሪያ የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አስቸኳይ መግለጫ ሰጥቷል።
ራሳቸውን ስተውና ሲያስመልሳቸው የነበሩ ወደ 200 የሚጠጉ ተማሪዎች የድንገተኛ ህክምና እርዳታ የተደረገላቸው ሲሆን፣ እስካሁን የህይወት ማጣት አደጋ አልገጠመም።
አብዛኞቹ በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ አንዲት ፅኑ ታካሚ ተማሪ ለተሻለ ክትትል ወደ ጂንካ ሆስፒታል ተልካለች።
የህመሙ መነሻ ምክንያት ከጁስ ዱቄቱ ወይም ከሌላ ነገር ጋር የተያያዘ መሆኑን ለማረጋገጥ የላብራቶሪ ምርመራ እየተካሄደ ነው።
ማህበረሰቡ ሳይደናገጥ እንዲረጋጋ የጠየቀው ሆስፒታሉ፣ በማህበራዊ ሚዲያ በሚናፈሱ የሀሰት ወሬዎች እንዳይመራ አሳስቧል።

ሜፀር የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የተከሰተው ድንገተኛ የጤና እክል በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ
#ethiopia | በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ አሪ ወረዳ ሜፀር የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በዛሬው ዕለት በተከሰተ ድንገተኛ የሕመም ስሜት ሳቢያ ራሳቸውን የሳቱና የማስመለስ ምልክት የታየባቸው በግምት እስከ 200 የሚደርሱ ተማሪዎች ወደ ጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመግባት አስቸኳይ የሕክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ሆስፒታሉ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
የሆስፒታሉ የሕክምና ባለሙያዎች በሙሉ አቅማቸው ባደረጉት ፈጣንና ያልተቆጠበ ጥረት አብዛኞቹ ተማሪዎች በአሁኑ ወቅት በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል።
ከተማሪዎቹ መካከል ከፍተኛ ክትትል የሚያስፈልጋት አንዲት ተማሪ ብቻ ለተሻለ ሕክምና እና ጥንቃቄ ሲባል ወደ ጅንካ አጠቃላይ ሆስፒታል የተላከች ሲሆን፣ እስካሁን ባለው መረጃ ሕይወቱ ያለፈ ምንም ተማሪ አለመኖሩን የሆስፒታሉ አስተዳደር በይፋ አረጋግጧል።
ይህን ድንገተኛ ሕመም የቀሰቀሰው መንስኤ ምን እንደሆነ ከተወራው የጁስ ዱቄት ወይም ከሌላ ነገር ጋር የተያያዘ መሆኑን ለማረጋገጥ የሕክምና ባለሙያዎችና የሕብረተሰብ ጤና ቡድኑ በጥልቀት ምርመራ እያደረጉ ይገኛሉ።
የላብራቶሪና የሙያዊ ምርመራው ውጤት ተጠናቆ እውነታው ይፋ እስኪሆን ድረስ ማኅበረሰቡ በትዕግሥት እንዲጠባበቅ የጠየቀው ሆስፒታሉ፣ ሁኔታው ሙሉ በሙሉ በሕክምና ባለሙያዎች ቁጥጥር ሥር በመሆኑ ወላጆችና የአካባቢው ነዋሪዎች ያለምንም መደናገጥ ራሳቸውን እንዲያረጋጉ ጥሪ አቅርቧል። በተጨማሪም ተማሪዎቹን በፍጥነት ወደ ሕክምና ተቋም በማምጣት ረገድ ለታየው የሕዝብ ትብብር ሆስፒታሉ ምስጋና አቅርቧል።
ጌትነት ተመስገን
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

ዛሬ የሚተከሉ ችግኞች፣ የነገ የሀብት ምንጭ ናቸው፦ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
******************
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።
ተከላውን በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ፣ ኦቾሎ ላንቴ ቀበሌ ያስጀመሩት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፥ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት የተከናወነው የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል።
ዛሬ የሚተከሉ ችግኞች፣ የነገ የሀብት ምንጭና የሥራ ዕድል መፍጠሪያ መሆናቸውን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ መርሐ ግብሩን ውጤታማ ለማድረግ በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
በተለይም ክልሉ ለናዳ እና ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በመሆኑ በተራራማ አካባቢዎች የአረንጓዴ ልማት ሥራው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ አንደኛ ሽናሌ በበኩላቸው፥ ባለፉት 8 ዓመታት የክልሉን የደን ሽፋን ከነበረበት 19 በመቶ፣ ወደ 24.5 በመቶ ማሳደግ መቻሉን ጠቅሰዋል።
"ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ፣ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በልዩ ንቅናቄ የሚከናወነው የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራ፣ ችግኝ ከመትከል ያለፈ የተስፋ ምልክት መሆኑ ተገልጿል።
በተመስገን ተስፋዬ
#ethiopia #climateaction #environmentalprotection #greenlegacy #southethiopia #ebc

ግልግል!
ግብር በቴሌብር!
ሰነድ ማዘጋጀትና ሰልፍ መሰለፍ ቀረ፤ የዓመቱን ግብር በቴሌብር አሁኑኑ እንክፈል!
የገቢዎች ሚኒስቴርን፣ የአዲስ አበባ (ከፍተኛ፣ መካከለኛና አነስተኛ)፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን እንዲሁም የኦሮሚያ፣ የአማራ፣ የሲዳማ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦችን፣ የሱማሌ፣ የሐረሪ፣ የአፋር እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ገቢዎች የግብር ክፍያ በአስተማማኝ ሁኔታ አሁኑኑ በቴሌብር ይክፈሉ!
ቴሌብር ሱፐርአፕን https://bit.ly/telebirr_Su... ጭነን ስንከፍል እንዲህ ነን!
#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን #ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን #ስንጭን_እንዲህ_ነን #ስናስጀምር_እንዲህ_ነን
ግብር በቴሌብር!
ሰነድ ማዘጋጀትና ሰልፍ መሰለፍ ቀረ፤ የዓመቱን ግብር በቴሌብር አሁኑኑ እንክፈል!
የገቢዎች ሚኒስቴርን፣ የአዲስ አበባ (ከፍተኛ፣ መካከለኛና አነስተኛ)፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን እንዲሁም የኦሮሚያ፣ የአማራ፣ የሲዳማ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦችን፣ የሱማሌ፣ የሐረሪ፣ የአፋር እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ገቢዎች የግብር ክፍያ በአስተማማኝ ሁኔታ አሁኑኑ በቴሌብር ይክፈሉ!
ቴሌብር ሱፐርአፕን https://bit.ly/telebirr_Su... ጭነን ስንከፍል እንዲህ ነን!
#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን #ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን #ስንጭን_እንዲህ_ነን #ስናስጀምር_እንዲህ_ነን
Sponsored by
Surafel
1 month ago
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለ45 የፓርላማ መቀመጫዎች አጠቃላይ የምርጫ ውጤት
Ethiopian Broadcasting Corporation #ኢትዮጵያ #ፓርላማ #የደቡብኢትዮጵያ
Ethiopian Broadcasting Corporation #ኢትዮጵያ #ፓርላማ #የደቡብኢትዮጵያ
1 month ago
በ11 የምርጫ ክልሎች የድጋሜ ምርጫ እንዲደረግ በቦርዱ ተወሰነ።
አምስቱ የምርጫ ክልሎቹ በሶማሌ ክልል የሚገኙ መሆናቸዉን ቦርዱ ይፋ እያደረገ ባለዉ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዉጤት ማሳወቂያ መርሃ ግብር ላይ ተገልፆል።
ሀማሬ፥ ዳራቶሬ፥ ሀርገሌ፥ ባቱ ዝዋይ፥ ቤጊ፥ አርሆሳ፥ ጨንቻ፥ ሶሮ 1፥ ጠንባሮ ፥ ሀደካላ፥ ሀደካለ ምርጫ ክልሎች የድጋሜ ምርጫ ይደረግባቸዋል ተብሏል።
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ሶሬ1 እና ጠምባሮ ምርጫ ክልሎች ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የድጋሜ ምርጫ ይደረግላቸዋል።
ሀርገሌ ፥,ዳሮር፥ ሀደካላ ፥ ሀማሬ እና ዳራቶሬ የተባሉ በሶማሌ ክልል የሚገኙ የምርጫ ክልሎች የድጋሜ ምርጫ ያደርጋሉ።
ባቱ ዝዋይ እና ቤጌ ምርጫ ክልሎች በኦሮሚያ ክልል ለህዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክርቤት የድጋሜ ምረጫ የሚደረግበት ይሆናል ተብሏል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ጨንቻ ምርጫ ክልል ለክልል ምክርቤት የድጋሜ ምርጫ ይካሄዳል።

ዘገባው የኢትዮ ኤፍ ኤም ነው!

2 months ago
ወላይታ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ
ከወላይታ ሶዶ ወደ ገሳ ከተማ 50 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ “ዛሮ ቁልቁለት” ኤልፋ በተባለ አስቸጋሪ መንገድ ላይ ተገልብጧል።
በአደጋው የ4 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ያለፈ ሲሆን፣ በ22 ሰዎች ላይ ከባድ እና በ24 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን እንደገለፀው፣ ተጎጂዎች ወደ ህክምና ተቋማት ተወስደዋል።
ይሁን እንጂ በደረሰው የጉዳት መጠን ምክንያት የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተገልፇል።
የአካባቢው አስቸጋሪ መልክዓ ምድር ለክስተቱ መንስኤ ሳይሆን እንዳልቀረ የተጠቆመ ሲሆን፣ ፖሊስ ስለ አደጋው ዝርዝር ምርመራ እያደረገ ይገኛል።

7 ሺህ 187 መወጣጫ ደረጃዎች እየተገነቡለት የሚገኘው ዳሞታ ተራራ
********************
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኘው እና የወላይታዎች መገለጫ የሆነው የዳሞታ ተራራ እንዲለማ ኅብረተሰቡ ለረጅም ጊዜ ጥያቄ ሲያቀርብ ቆይቷል።
ተራራው የተለያዩ የብዝኃ ሕይወት መገኛ፣ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው መስህብ ስፍራዎች የሚገኙበት ነው።
በመሆኑም ተራራውን ማልማት በአካባቢው የቱሪዝም ዘርፍን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል።
እንደ ሀገር በተጀመረው የቱሪዝም መዳረሻዎችን የማልማት እና የማሳደግ ኢኒሼቲቭ አካል በማድረግ የዳሞታ ተራራን የማልማት ተግባር ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ ይገኛል።
በዚህም እስከ ተራራው ጫፍ በመድረስ በተራራው ላይ የሚገኙ ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ ቦታዎችን ለመጎብኘት የሚያስችሉ 7 ሺህ 187 መወጣጫ ደረጃዎችን የመገንባት ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።
ከ5.34 ኪሎ ሜትር በላይ የሚረዝመው ይህ ፕሮጀክት፣ በውስጡ ታሪካዊውን የሞቼና ቦራጎ ዋሻ፣ የዳሞታ ካርበን ፕሮጀክትን፣ በተራራው ጫፍ የምትገኘውን የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን፣ ከተራራው የሚፈልቁ የውኃ ምንጮችን እና ሰባቱን የዳሞታ ተራራ ሰንሰለቶች በማካተት ነው እየተገነባ የሚገኘው።
የዳሞታ ተራራ 12 ሺህ 500 ሔክታር መሬት የሚሸፍን ሲሆን፣ ከባሕር ጠለል በላይ 2 ሺህ 750 ሜትር ከፍታ እንዳለው እና ዙሪያው ከ68 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት እንደሚሸፍን ይነገራል።
እንደ ሀገር የተለያዩ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎችን ማልማት እና የቱሪዝም ሀብትን የማበልጸግ ስትራቴጂ ትኩረት ተሰጥቶታል።
በትዕግሥቱ ቡቼ
#ethiopia #ebc #damota #heritage

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ስር በሚገኙት ጉራጌ እና ምሥራቅ ጉራጌ ዞኖች ውስጥ በተካሄደው ምርጫ፣ አጠቃላይ ውጤቱን ሙሉ በሙሉ ሊቀለብሱ የሚችሉ እና ዴሞክራሲያዊ ሂደቱን ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ከባድ የህግ ጥሰቶች መፈጸማቸውን "ጎጎት ለጉራጌ አንድነትና ፍትሕ ፓርቲ" አስታወቀ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም በስምንት የምርጫ ክልሎች ላይ የቀረበለትን ይህንን አሳሳቢ አቤቱታ መቀበሉን አረጋግጧል።
ጎጎት ፓርቲ ያወጣው መግለጫ አሁን ላይ በምርጫ ስርአቱ ላይ ያለውን መዋቅራዊ ችግር በግልጽ የሚያሳይ ነው። ፓርቲው ገዢውን ፓርቲ በዋናነት የሚከሰው የዴሞክራሲን መሰረታዊ መርሆች በመጣስ ራሱ ተወዳዳሪ፣ ራሱ የምርጫ አስፈጻሚ፣ ራሱ ድምጽ ሰጪ እንዲሁም ራሱ የድምጽ ቆጣሪ ሆኖ ቀርቧል በማለት ነው። ይህ አይነቱ አካሄድ ምርጫውን ከነጻ እና ፍትሃዊ ውድድርነት አውጥቶት የህዝብን እውነተኛ የድምጽ ውሳኔ ወደሚያፍን አሰራር ቀይሮታል የሚል ትልቅ ትችት አስነስቷል።
ፓርቲው በዝርዝር ያቀረባቸው ክሶች የምርጫ ሂደቱን ተአማኒነት ክፉኛ የሚጎዱ ናቸው። ከተፈጸሙት ጥሰቶች መካከል ድምጽ ሰጪዎችን በተደራጀ መልኩ ከቦታ ቦታ በማመላለስ አንድ ግለሰብ ከአንድ በላይ ድምጽ እንዲሰጥ ማድረግ፣ በብዛት የሐሰተኛ ድምጽ መስጫ ወረቀቶችን ወደ ስራ በማስገባት የምርጫውን ውጤት ለመቀልበስ መሞከር፣ እንዲሁም መራጮች በነጻነት የመምረጥ መብታቸው ተገፎ የትኛውን ፓርቲ እንደሚመርጡ በአስገዳጅ ሁኔታ መጠየቅ ይገኙበታል።
ከዚህም ባሻገር የምርጫውን ግልጽነት ማረጋገጥ በሚገባቸው የድምጽ ቆጠራ ሂደቶች ላይ የጎጎት ፓርቲ ወኪሎች በማስፈራራት እና በኃይል ከምርጫ ጣቢያዎች እንዲወጡ መደረጉን ፓርቲው አጋልጧል። ይህ ድርጊት የቆጠራ ሂደቱን ሙሉ በሙሉ ሚስጥራዊ እና ገለልተኛ ታዛቢ የሌለበት ያደርገዋል።
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በስምንቱ የምርጫ ክልሎች ላይ የተፈጸሙትን እነዚህን ጥሰቶች አስመልክቶ የቀረበውን አቤቱታ ተቀብሎ በእጁ ይገኛል። ቦርዱ አቤቱታውን አጣርቶ የሚሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ፣ ምርጫ ቦርድ እንደ ተቋም ያለውን ገለልተኝነት እንዲሁም በዞኑ ያለውን ቀጣይ የፖለቲካ እና የሰላም ሁኔታ የሚወስን ወሳኝ ምዕራፍ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ለቤተሰቦቿ መልዕክት ልታደርስ የሄደችውን ታዳጊ በመጥለፍ ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለመፈጸም ሙከራ ያደረገዉ ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ
በጌዴኦ ዞን ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክልን በመጠቀም የጠለፋ እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ለመፈፀም ሙከራ ያደረገዉ ተከሳሽ በእስራት መቀጣቱ ተገልጿል።
ተከሳሽ ዮሴፍ ምትኩ የተባለ ሲሆን የግል ተበዳይ ታዳጊ በረከት ተስፋዬ ለቤተሰቦቿ መልዕክት ልታደርስ ገበያ ስትሄድ ካልተያዙ ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን በያዙት ሞተር ሳይክል በመጠቀም የወንጀል ድርጊት መፈፀሙን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ሀይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በዚህም ፖሊስ ተከሳሽ ጥፋተኛ መሆኑን በማረጋገጥ በፈፀመው የጠለፋ ወንጀል እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ወንጀል ጥፋተኛ መሆኑን በማረገጥ ክስ መስርቶ ለወናጎ ወረዳ ፍርድ ቤት ያቀርባል።
ጉዳዩን የተመለከተዉ የወናጎ ወረዳ ፍርድ ቤት የቀረበለትን የክስ አቤቱታ ሲመረምር ቆይቶ ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት ተከሳሹ በተከሰሰበት በሁለቱም ወንጀሎች ጥፋተኛ መሆኑን ፍርድ ቤቱ በማረጋገጥ ተከሳሽ ዮሴፍ ምትኩን በ9 ዓመት ከስምንት ወር እስር እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ መወሰኑን ኢንስፔክተር አሸናፊ ሀይሌ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

የጭቃ ቤት ግንባታ ተከለከለ‼
አሁን ላይ ተፈፃሚ የሆነው በአንድ ክልል ነው በቀጣይ ግን በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እንደሚተገበር ተነግሯል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ከተሞችን ለማዘመን እና ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የተጣጣመ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት አዲስ ጥብቅ መመሪያ አስተላልፏል።
ደብዳቤው ከደረሰበት ቀን ጀምሮ በማንኛውም ማዘጋጃ ቤት በኩል የጭቃ ቤት ግንባታ ፈቃድ ማጽደቅ ሙሉ በሙሉ ታግዷል።
በእንጨትና ጭቃ ግንባታ ሳቢያ የሚመጣውን የደን መመናመን ለመግታት እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን የድርቅና የጎርፍ አደጋ ለመከላከል ነው።
ማንኛውም ግንባታ ከተማን በሚያዘምኑና ደረጃቸውን በጠበቁ ግብዓቶች ማለትም በብሎኬት፣ በጡብ እና በተሻሻሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ብቻ መከናወን እንዳለበት ታዟል።

የአርባ ምንጭ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተገልጋዮችን እንግልት ለማስቀረት…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአርባ ምንጭ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመንግስት አገልግሎቶችን ለማግኘት የነበረውን እንግልት የሚያስቀር ነው አሉ የከተማዋ ነዋሪዎች፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በዛሬው ዕለት የአርባ ምንጭ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎች ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት፥ ቀደም ሲል የመንግስት አገልግሎቶችን ለማግኘት ወደተለያዩ ቢሮዎች በመመላለስ ለከፍተኛ እንግልትና ለገንዘብ ብክነት ይዳረጉ ነበር።
ሁሉንም የመንግስት አገልግሎቶች በአንድ ጣራ ስር በአጭር ጊዜ በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማግኘት የሚያስችለው የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ በመጀመሩ መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡
ማዕከሉ በተለይም የንግድ ፈቃድ ለማውጣትና ተያያዥ ሂደቶችን ለማስፈጸም ይወስድ የነበረውን ረጅም ቀጠሮና ቢሮክራሲ የሚያቃልል ነው ብለዋል፡፡
ይህ አይነቱ አሰራር ለአካባቢው የንግድ እንቅስቃሴ መነቃቃትና ለኢንቨስትመንት ፍሰት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ነው ያሉት፡፡
በቴክኖሎጂ የተደገፈው ይህ አዲስ አሰራር የህዝብን አመኔታ ከመጨመሩም በላይ ሙስናና አድሏዊነትን እንደሚያስቀር ተገልጿል፡፡
በመለሰ ታደለ

የአርባ ምንጭ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የክልሉን የአርባ ምንጭ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው አገልግሎት አስጀመሩ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ በክልሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና አገልግሎት አሰጣጡን ለማሳደግ እየተሰራ ነው።
በዚህም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አካል የሆነውን የክልሉን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል በብቃት ማጠናቀቅ ተችሏል ብለዋል።
ማዕከሉ 4 የፌዴራል እና 6 የክልል ተቋማት አገልግሎትን በአንድ ጣሪያ ስር በማጣመር ከ15 በላይ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት አመላክቷል።

ሀገራዊ ምክክር እና ሀገር በቀል የእርቅ ዕሴቶች...
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት፣ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር እንዲሁም ታሪካዊና መዋቅራዊ ቅሬታዎችን በውይይት ለመፍታት ታላቅ የብሔራዊ ምክክር ሂደት እያካሄደች ትገኛለች።
የዚህ ጉዞ ስኬት የሚወሰነው ከውጭ በሚቀዱ የፖለቲካ ቀመሮች ሳይሆን ማህበረሰቡ ለዘመናት ጠብቆ ባቆያቸውና ከማንነቱ ጋር በተሳሰሩ የሰላምና የዕርቅ ዕሴቶች ላይ መመስረት ሲችል ብቻ ነው።
ኢትዮጵያ ከ80 በላይ ብሔረሰቦች የሚኖሩባት የባህልና የማንነት ሕብረቀለም እንደመሆኗ መጠን እያንዳንዱ ማህበረሰብ ግጭቶችን የሚፈታበት፣ ፍትህን የሚያሰፍንበት እና የተናጋ ማህበራዊ ትስስርን የሚያድስበት የራሱ የሆነ ሀገር በቀል የዕርቅ ሥርዓት አለው።
ከእነዚህ ውድና ሕያው ማህበራዊ ዕሴቶች መካከል በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኘው የደራሼ ብሔረሰብ ባህላዊ የዕርቅ ሥርዓት “ደሃ” ተጠቃሽ ነው።
በደራሼ ማህበረሰብ ዘንድ “ደሃ” ወይም ሽምግልና ማለት እንዲሁ ግጭት ሲከሰት ብቻ የሚደረግ የጊዜያዊ ስምምነት ሂደት አይደለም። ይልቁንም ፍትህ የሚረጋገጥበት፣ የበደለ የሚጠየቅበት፣ የተበደለ የሚካስበትና ጠቅላላው ማህበራዊ ኑሮ ሕጋዊና ሞራላዊ እውቅና የሚያገኝበት ጠንካራ ዕሴት ነው።
ይህንን ሥርዓትን የሚመሩትና የሚያስፈጽሙት መሪዎች “ካዳያ” በመባል ይታወቃሉ። እነዚህ መሪዎች የሚመረጡት በማህበረሰቡ ሕገ-ህሊና ውስጥ ባሉ ጥብቅ መስፈርቶች ሲሆን÷ የካዳያዎች የሥልጣን ዘመን ሁለት ዓመት ብቻ ነው።
ይህ የሚያሳየው በባህላዊ ሥርዓት ውስጥ የሥልጣን ሽግግርና ለሌሎች ዕድል የመስጠት የዴሞክራሲ መርህ ቀድሞውኑ የነበረ መሆኑ ነው።
የደራሼ የዕርቅና የፍርድ ተግባር የሚከናወነው የማህበረሰቡ መረጃ የሚለዋወጥበት፣ ወጣቶችና አዛውንቶች የሚገናኙበት ዋነኛ ማዕከል በሆነው “ሞራ” በሚባል ጥላ በሚሰጡ ታላላቅ ዛፎች ሥር ድንጋዮች እንደ እርከን ከፍ ተደርገው በተዘጋጁ የሸንጎ ስፍራዎች ላይ ነው።
በደራሼ ባህል ሞራ ላይ ተከስሶ መቆም ትልቅ ማህበራዊ ውርደት ተደርጎ ይቆጠራል። ይህ ማህበራዊ ሞራል ሰዎች ወንጀልና ጥፋት ከመስራታቸው በፊት ራሳቸውን እንዲገቱ ያደርጋቸዋል።
የደሃ የዳኝነት ሂደት ፍፁም ሰላማዊና ሥርዓታዊ ሲሆን÷ ተበዳዩ አቤቱታውን ካቀረበ በኋላ ተከሳሹ በምስክሮች ፊት እንዲቀርብ ይጠራል። ተከሳሹ የቀረበውን ጥሪ አሻፈረኝ ካለ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ሳይኖር ማህበረሰባዊ ማዕቀብ ይጣልበታል።
በዳዩ በጥፋቱ ካመነ ደግሞ ሌላው አስደናቂ እሴት ይታያል፤ የካሳውን ክፍያ ጥፋተኛው ግለሰብ ብቻውን ሳይሆን የጎሳው አባል በሙሉ አዋጥቶ እንዲከፈል ይደረጋል።
ይህ እኔነትን ወደ እኛነት የሚቀይርና የአንዱ ጥፋት የሁሉንም ትኩረት እንዲስብ የሚያደርግ የጋራ ኃላፊነት መገለጫ ሲሆን÷ ዕርቁ የሚደመደመው ፍፁም ማህበራዊ ትስስርን በሚያድስ ታላቅ በዓል ነው።
ለዕርቁ ማሳረጊያ የሚሆን “ጨቃ” የተባለው ባህላዊ መጠጥና ምግብ የሚዘጋጀው የጎሳ አባላት እህል አዋጥተው በጋራ በመሥራት ነው።
በዕርቁ ቀን ከተበዳይና ከበዳይ ወገን የመጣው ምግብና መጠጥ አንድ ላይ ተደባልቆ በአንድ ማዕድ ይበላል። ፅዋቸውን ካነሱበት ሰዓት ጀምሮ ቁርሾው ሙሉ በሙሉ ተረስቶ ቀኑን በደስታ ያሳልፋሉ።
የደራሼ “ደሃ” ሥርዓት አሁን ኢትዮጵያ ለጀመረችው ብሔራዊ የምክክር ሂደት እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ስልቶችንና ፍልስፍናዎችን ማበርከት ይችላል።
የዘመናዊው የፍትህ ሥርዓት ጥፋተኛውን መቅጣት ላይ ብቻ ሲያተኩር÷ የደሃ ሥርዓት ግን ትኩረቱ የተበላሸውን ግንኙነት ማደስ ላይ ነው።
ሀገራዊ ምክክሩም እንደ ደራሼ ዕርቅ ሥርዓት ይቅርታንና ማህበራዊ ፈውስን ማምጣት ላይ ሊያተኩር ይገባል።
ዘመናዊነት ማለት የራስን መልካም እሴት መጣል ሳይሆን ባለው ሀገር በቀል እውቀት ላይ ሳይንሳዊ ጥናት በማድረግ እሴት መጨመር መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንም ሆነ መላው ሕዝብ እነዚህን ሕያው የሆኑ የባሕል ዕሴቶችን ለሀገራዊ መግባባት ሊጠቀምባቸው ይገባል።
የደራሼ ባህላዊ የዕርቅ ሥርዓት የሚያስተምረን ታላቅ እውነት ቢኖር ችግሮቻችንን እኛው ራሳችን በራሳችን መድረክ በጥበብና በፍቅር መፍታት እንችላለን የሚለውን ዘላለማዊ ሀቅ ነው።

Comments