የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ወሳኝ መሠረት እንደሚጥል ተመካካሪዎች ገለፁ
**********************
ዋናዉ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ መሠረታዊ ሀገራዊ ችግሮችን በውይይት በመፍታትና የተረጋጋች ሀገር ለመገንባት ወሳኝ መሠረት የሚጥል መሆኑን በጉባኤው ላይ የሚሳተፉ ተመካካሪዎች ገለፁ።
ከሐምሌ 8 ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በሚካሄደው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሚሳተፉ ተመካካሪዎች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።
ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ላይ ምክክር የሚካሄድባቸው ስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች የተለዩ ሲሆን በእነዚህም ላይ በዝርዝር ለመምከርና ዘላቂ መፍትሔዎችን ለማስቀመጥ፣ ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢ የተወከሉ 4 ሺህ ተመካካሪዎች ወደ አዲስ አበባ በመግባት ላይ ይገኛሉ።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የክልሎች የከተማ አስተዳደሮች እና የዳያስፖራ አስተባባሪ አቶ ረታ ጌራ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፤ ከየክልሎቹና ከዳያስፖራው ማህበረሰብ የተወከሉ ተመካካሪዎች ለዋናው ጉባኤ አዲስ አበባ እየገቡ መሆኑን አስታዉቀዉ፤ ኮሚሽኑ ለተሳታፊዎቹ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ እና በሌሎችም ምቹ ቦታዎች ላይ ደማቅ አቀባበል እያደረገላቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ተመካካሪዎች በበኩላቸው፤ ለዘመናት የዘለቁ አለመግባባቶችንና ስር የሰደዱ ልዩነቶችን በሰለጠነ መንገድ ለመፍታት በሚደረገው በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ ለመሳተፍ ዕድል በማግኘታቸው የተሰማቸውን ላቅ ያለ ደስታ ገልጸዋል።
ከፌደራል ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ወገን የተወከሉት አቶ ሀንፍሬ ከዳፎ ይህ ታሪካዊ መድረክ በአለመግባባቶች ላይ በጠረጴዛ ዙሪያ በመመካከር ጠንካራ አንድነት ያላት ሀገር ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ከኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን የመጡት የማህበረሰብ መሪ ወይዘሮ ዘርፌ በቀለ በበኩላቸው በዚህ ታሪካዊ ወቅት ተመካክረን ተደማምጠንና ተቀራርበን ጠንካራ ሀገር ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ትልቅ ተስፋ ሰንቀናል ብለዋል።
በተመሳሳይ ከአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን የወጣቶች ተወካይ ያረጋል ታደሰ የምክክር ጉባኤው ህብረ ብሔራዊ አንድነት ይበልጥ ለማጠናከር ትልቅ አቅም እንደሚሆን ገልፀዋል።
እንዲሁም ምክክሩ ለዘላቂ ሀገራዊ ስምምነትና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ታላቅ አስተዋፅኦ ያበረክታል ሲሉ ከጋምቤላ ክልል የመጡት ተመካካሪ አቶ ሉክ ኬዌ አብራርተዋል።
ከደቡብ ኢትዮጵያ የመጡት ተመካካሪ ኢንጂነር ምንትዋብ ምንጃር እና ከአዲስ አበባ የተወከሉት አቶ ገረመው ጫልቃ በበኩላቸው መድረኩ ተመካካሪዎች ሀሳባቸውን በነጻነትና በሀላፊነት በማንሸራሸር ለቀጣይ ትውልድ የምትሆን አስተማማኝና ጠንካራ ሀገር የሚገነቡበት ታሪካዊ አጋጣሚ መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜኣ ዘግቧል።

27 days ago