Logo
FastMereja
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ መፀር መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ከአካባቢ ሱቅ የተገዛን ኦሬንጅ ጁስ በመበጥበጥ የጠጡና ያሸተቱ ቁጥራቸው ወደ 200 የሚጠጉ ተማሪዎች ራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተገለፀ።

በዞኑ ደቡብ አሪ ወረዳ ሜፀር ትምህርት ቤት በደረሰው ይህንን ድንገተኛ የጤና መታወክ ዙሪያ የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አስቸኳይ መግለጫ ሰጥቷል።

ራሳቸውን ስተውና ሲያስመልሳቸው የነበሩ ወደ 200 የሚጠጉ ተማሪዎች የድንገተኛ ህክምና እርዳታ የተደረገላቸው ሲሆን፣ እስካሁን የህይወት ማጣት አደጋ አልገጠመም።

አብዛኞቹ በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ አንዲት ፅኑ ታካሚ ተማሪ ለተሻለ ክትትል ወደ ጂንካ ሆስፒታል ተልካለች።

የህመሙ መነሻ ምክንያት ከጁስ ዱቄቱ ወይም ከሌላ ነገር ጋር የተያያዘ መሆኑን ለማረጋገጥ የላብራቶሪ ምርመራ እየተካሄደ ነው።

ማህበረሰቡ ሳይደናገጥ እንዲረጋጋ የጠየቀው ሆስፒታሉ፣ በማህበራዊ ሚዲያ በሚናፈሱ የሀሰት ወሬዎች እንዳይመራ አሳስቧል።

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.