Logo
SeledaPost
የ6 ወር ነፍሰ ጡር ባለቤቱን የገደለው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ

በጎፋ ዞን በላሃ ከተማ አስተዳደር የ6 ወር ነፍሰ ጡር ባለቤቱን የገደለው ተከሳሽ  ጀማል ሁሴን በሞት እንዲቀጣ መወሰኑን ፖሊስ አስታውቋል።

ተከሳሹ በጎፋ ዞን በላሃ ከተማ አስተዳደር ሀብት-ምንጭ ቀበሌ ውስጥ ከባለቤቱ ጋር በነበረ የፍትሐ ብሔር ክስ ምክንያት ቂም በመያዝ  በስለታማ መሣሪያ በመውጋት
ህይወቷ  እንዲያልፍ ማድረጉን  የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ሀይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ያቀረባቸው የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ክሱን ከጥርጣሬ በላይ እንደሚያስረዱ በመግለጽ ተከሳሹ እንዲከላከል ብይን ሰጥቶ ነበር። ተከሳሹም "የመከላከያ ማስረጃ የለኝም" በማለቱ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ብሎ ወስኗል።

በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ የቅጣት አስተያየቶችን ከተቀበለ በኋላ ተከሳሹ በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ ማስተላለፉንየደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ሀይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
Via_dagu

Seledadotio
Seledadotio
1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.