የአርባ ምንጭ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተገልጋዮችን እንግልት ለማስቀረት…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአርባ ምንጭ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመንግስት አገልግሎቶችን ለማግኘት የነበረውን እንግልት የሚያስቀር ነው አሉ የከተማዋ ነዋሪዎች፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በዛሬው ዕለት የአርባ ምንጭ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎች ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት፥ ቀደም ሲል የመንግስት አገልግሎቶችን ለማግኘት ወደተለያዩ ቢሮዎች በመመላለስ ለከፍተኛ እንግልትና ለገንዘብ ብክነት ይዳረጉ ነበር።
ሁሉንም የመንግስት አገልግሎቶች በአንድ ጣራ ስር በአጭር ጊዜ በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማግኘት የሚያስችለው የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ በመጀመሩ መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡
ማዕከሉ በተለይም የንግድ ፈቃድ ለማውጣትና ተያያዥ ሂደቶችን ለማስፈጸም ይወስድ የነበረውን ረጅም ቀጠሮና ቢሮክራሲ የሚያቃልል ነው ብለዋል፡፡
ይህ አይነቱ አሰራር ለአካባቢው የንግድ እንቅስቃሴ መነቃቃትና ለኢንቨስትመንት ፍሰት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ነው ያሉት፡፡
በቴክኖሎጂ የተደገፈው ይህ አዲስ አሰራር የህዝብን አመኔታ ከመጨመሩም በላይ ሙስናና አድሏዊነትን እንደሚያስቀር ተገልጿል፡፡
በመለሰ ታደለ

6 days ago