ከገጽታ ግንባታ ባሻገር፦ ቱሪዝም የኢትዮጵያውያን አዲሱ የትስስር ድልድይ
*******************
ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ እያደረገችው ያለው አስደናቂ ጉዞ፣ ከተለመደው የኢኮኖሚ ትርፍ እና የገጽታ ግንባታ ትርክት የዘለለና እጅግ ጥልቅ ትርጉም ያለው ነው።
ሀገራችን እጅግ ገናና ታሪክ፣ ማራኪ የተፈጥሮ መልክዓ ምድር እና እምቅ የባህል ሀብት ባለቤት ናት።
ይሁን እንጂ ይህን ጸጋ አቀናጅቶ እና አልምቶ ለመጠቀም የሚያስችል ስልታዊ ዕቅድ እና ቁርጠኝነት ባለመኖሩ፣ የሀገራችን ብልጽግና ለዘመናት በምኞት ብቻ ሲታጠር ቆይቷል።
ባለፉት ዓመታት በሀገራችን ተግባራዊ የተደረጉት ዘርፈ ብዙ ማሻሻያዎች ይህን የቸልተኝነት ድባብ በመግፈፍ የእውነተኛ ውበታችንን እና አቅማችንን በር ከፍተዋል።
ይህ መነቃቃት ከመሠረታዊው የመደመር እሳቤ ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነው። መደመር የሀገርን ሙሉ አቅም በአንድ የጋራ ሕልም ዙሪያ አስተባብሮ ለአንድ ዓላማ እንዲውል የማድረግ ፍልስፍና ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ደጋግመው የሚያቀርቡትን "ሀገራችንን እንወቅ፣ እንውደድ፣ እንኩራባት፤ ይህ አስደናቂ ምድር የእኛው ነውና!" የሚለውን ብሔራዊ ጥሪ በቱሪዝም ልማት እያሳዩ ነው።
ከምንም በላይ አሁን የተጀመረው የቱሪዝም ልማት የብሔራዊ አንድነት ማጠናከሪያ እና የጠንካራ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ድልድይ ነው።
የሀገር ውስጥ ቱሪዝም ሲስፋፋ አንዱ ማኅበረሰብ ወደ ሌላው በማቅናት ባህልን ይለዋወጣል፣ ቋንቋን ያዳምጣል፣ አብሮ ማዕድ ይጋራል።
ይህ ደግሞ በዜጎች መካከል የተገነቡ የተዛቡ አመለካከቶችን በመስበር መተሳሰብን እና ሀገራዊ ባለቤትነትን ያጎለብታል። የቱሪዝም መዳረሻዎችም የልዩነት መገለጫ ሳይሆኑ የጋራ ማንነት መገለጫ ሆነው ያገለግላሉ።
ይህን እውነታ መሬት ላይ ለማውረድ፣ የመዲናችንን ገጽታ ከቀየረው የ“ገበታ ለሸገር” ፕሮጀክቶች ስኬት በመቀጠል፣ የ"ገበታ ለሀገር" እና የ"ገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክቶች ልማቱን ወደ ተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ይዘውት ዘልቀዋል።
በአፋር ክልል የተገነባው የ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ' በአካባቢው ያለውን ያልታየ እምቅ አቅም ወደ ልማት የቀየረ ታላቅ ሥራ ነው።
ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ስናቀና ደግሞ የአርባ ምንጭ ኮንፍረንስ ሪዞርት፣ የኮንፍረንስ ቱሪዝምን ከአዲስ አበባ ውጪ በማስፋት የሁሉም ኢትዮጵያውያን መገናኛ ማዕከል ሆኗል።
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በአማራ ክልል የተገነባው የ‘ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት' ቀደም ሲል ከቱሪስት እይታ ርቆ ለቆየው አካባቢ አዲስ ሕይወት የዘራ ነው።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የተገነባው የ‘ደንቢ ኢኮ ሎጅ' ደግሞ የኢትዮጵያን አረንጓዴ ውበት ዳግም የገለጠ ድንቅ ፕሮጀክት ነው።
እነ ጎርጎራ፣ ወንጪ ደንዲ፣ ጨበራ ጬርጩራ እና ሃላላ ኬላ ያሉ ኢኮ ለጆችም የኢትዮጵያውያንን ድንቅ የጋራ ሀብት ገልጠው አሳይተዋል።
እነዚህ ከመዲናዋ ውጭ የተገነቡ ውብ ሥፍራዎች ኢትዮጵያውያን ከጫፍ ጫፍ ተንቀሳቅሰው ሀገራቸውን እንዲያውቁ እና የኅብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን ማኅበራዊ ትስስር አጥብቀው እንዲገነቡ ታላቅ ዕድል ፈጥረዋል።
በማክሮ ኢኮኖሚ ረገድ እነዚህ ፕሮጀክቶች ቱሪዝምን ከባዶ እይታ አውጥተው ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ግብይት አሸጋግረውታል።
ቱሪስቶች አዳዲስ እና ማራኪ መዳረሻዎችን ሲጎበኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች ወጪ ያደርጋሉ፤ ይህም በየአካባቢው ማኅበረሰብ ውስጥ የገንዘብ ዝውውርን ያፋጥናል፤ የሥራ ዕድልን ይፈጥራል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ጎብኚዎች ይዘው የመጡትን ገንዘብ ወደ ከፍተኛ ደስታ ቀይረው፣ ላወጡት ወጪ ሳይቆጩ መመለስ አለባቸው።
ፕሮጀክቶቹ የየአካባቢውን ግብዓትና የሰው ኃይል በመጠቀም የውጭ ምንዛሬ ወጪን በመቀነስ በኩል ያላቸው አስተዋጽኦም ከፍተኛ ነው።
እነዚህ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎች ከተለመደው የፖለቲካ እና የቢሮክራሲ አሠራር በመውጣት ፈጣን እና ፈጠራ የተሞላበት አመራር መስጠት ከተቻለ ምን ያህል ርቀት መጓዝ እንደምንችል በተግባር አሳይተውናል።
አቧራ ተሸፍነው የነበሩ የሀገራችን ጸጋዎች ዛሬ በአዲስ ምናብ ደምቀው አይተናቸዋል። ይህ ስኬት የምትከበር፣ የምትወደድ እና በራሷ አቅም የምትቆም የበለጸገች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ የጀመርነው ታሪካዊ ጉዞ በትክክለኛ መንገድ ላይ ለመሆኑ ትልቅ ማረጋገጫ ነው።
ሀገራችንን እያወቅን፣ ውበቷን እያጣጣምን እና ትስስራችንን እያጠናከርን ወደ ኢትዮጵያ ከፍታ እንጓዛለን!
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #medemer #tourism #visitethiopia #landoforigins #ebc

25 days ago