13 hours ago
በአዲስ አበባ በ 3 ወራት ውስጥ በአፈጻጸም ጉድለትና በብልሹ አሰራር 185 ሰዎች ተጠያቂ መደረጋቸው ተገለጸ
ጥቅምት 01ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በአዲስ አበባ በ 3 ወራት ውስጥ በተከናወነው የስራ አፈጻጸም ግምገማ ከአፈጻጸም ጉድለት እና ከብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ 185 የሚሆኑ ግለሰቦች ላይ ጥብቅ እርምጃ መወሰዱን የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አበቤ አስታወቁ።
ከንቲባዋ የከተማ አስተዳደሩን የሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንዳገለጹት ከዚህ ቀደም በከተማዋ "ጥሩ ሰው መባል በቂ የሚሆንበት" እና የአፈጻጸም ጉድለት እንደ ጥፋት የማይጠየቅበት አሰራር ነበር።
አሁን ግን ይህንን አዝማሚያ በመለወጥ በተደረገው ርብርብ ወደ 95 የሚሆኑ ሰዎች ከአፈጻጸም ጉድለት ጋር በተያያዘ ከቦታ መነሳት ፣ ማስጠንቀቂያ መስጠትንና ከኃላፊነት እንዲገለሉ ማድረግን ጨምሮ የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደውባቸዋል።
በተመሳሳይ ከብልሹ አሰራርና ከሙስና ጋር በተያያዘ ከ90 በላይ የሚሆኑ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ፣ ሰራተኞች እና ተገልጋዮች በህግ ተጠያቂ መደረጋቸውን ከንቲባዋ ጠቁመዋል።
ከቦታ ታነሳላችሁ እንጂ አትጠይቁም" የሚል ወቀሳ ከህዝብ እንዳይነሳ ማን ፣ የት እና እንዴት ተጠያቂ እንደሆነ የሚያሳዩ ዝርዝር መረጃዎች ለህዝብ ግልጽ መደረግ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
በፋሲል አረጋይ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

15 hours ago
በትምህርት ቤቶች የዓይን ምርመራ ሊደረግ እንደሚገባ ተገለፀ።
ጥቅምት 01ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በዓለም አቀፍ ደረጃ በተደረገ ጥናት አንድ ተማሪ የሚያገኘው እውቀት እና መረጃዎች ከ 80 በመቶ በላይ የሚሆነው በአይን ለመረዳት የሚያስችል በመሆኑ የእይታ ችግር ያለባቸው ተማሪዎች የሚፈለገውን ያህል ክህሎት እንዳይኖራቸው ተግዳሮት እንደሚሆን ተገልጿል።
በ ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራት ፕሮግራም ማሻሻያ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ዩሐንስ ወጋሶ
የማየት ችግር የሚያጋጥማቸው ተማሪዎች ችግር ለመፍታት በትምህርት ቤቶች የዓይን ምርመራ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
አንድ ተማሪ የዕይታ ችግር ካለበት የትምህርት አቀባበሉ ዝቅተኛ የሚሆንበት እድል በመኖሩ እንደሀገር አሉታዊ ተፅኖ እንደሚኖረው ተናግረዋል።
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በትምህርት ቤቶች የሚደረገው የአይን ምርመራ የሁሉም ዜጋ ቀዳሚ ትኩረት መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል።
በትምህርት ቤቶች ላይ የሚደረገው የዓይን ምርመራ ውጤታማ እንዲሆን መምህራን ማሰልጠን እንደሚገባ አንስተው በቀላሉ የተማሪዎች ችግር እንዲለዩ ያስችላል ብለዋል።
የዓይን ምርመራ ስራ በዘመቻ የሚካሄድ ሳይሆን መደበኛ በሆነ መንገድ ለነባር ተማሪዎች እና አዳዲስ ለሚገቡ ተማሪዎች ምርመራ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
ይሄ ተግባራዊ እንዲሆን ትምህርት ሚኒስቴር እና ጤና ሚኒስቴር በጋራ በመሆን የትምህርት ቤት ጤና እስትራቴጂ በማዘጋጀት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዓለም ለ 26 ተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ 18ተኛ ጊዜ የአለም አቀፍ የአይን ጤና ቀን ባለፈው ሳምንት በመከሩ ይታወቃል።
በህይወቴ ጌትነት

ንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሙያ ፈቃድ ብቻ ሲሰሩ ለነበሩ አካላት የግብር ስሌት አሰራር ተዘረጋ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የ2018 የግብር ዘመን ማስታወቂያን አስመልክቶ ይፋ ባደረገው አዲስ አሰራር በሙያ ፈቃድ ብቻ ሲሰሩ ለነበሩ አካላት የሚሆን የግብር ስሌት አሰራር መዘረጋቱን አስታውቋል።
አሐዱ ሬዲዮ በተመለከተው በዚህ አዲስ አሰራር መሠረት ንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሙያ ፈቃድ ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ጠበቆች ፣ የኢንሹራንስ ወኪሎች ፣ የኢንሹራንስ ጉዳት ገማቾች እና ሌሎች ተመሳሳይ ባለሙያዎች ይካተታሉ።
እነዚህ አካላት የሂሳብ መዝገብ የማቅረብ ሕጋዊ ግዴታ ቢኖርባቸውም፣ መዝገብ ሳያቀርቡ ሲቀሩ የነበረውን ክፍተት ለመሙላት መመሪያው ግልጽ የስሌት አሰራር አስቀምጧል።
በአሰራር ስርዓቱ መሠረት በሙያ ፈቃድ ብቻ ሲሰሩ የነበሩ ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብ ባላቀረቡበት ሁኔታ ከአጠቃላይ ገቢያቸው ላይ 35 በመቶው እንደ ወጪ ታስቦ ቀሪው 65 በመቶ ደግሞ ግብር የሚከፈልበት ገቢ እንደሆነ ተቆጥሮ ግብራቸው እንዲሰበሰብ ይደረጋል።
ይህ አሰራር ህጋዊ አሰራርን ለማስፈንና በሙያዊ አገልግሎቶች ዘርፍ ላይ የሚስተዋሉ የግብር ስወራዎችን ለመቀነስ አልሞ የተዘጋጀ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ለ2018 የግብር ዘመን ብቻ ተግባራዊ እንደሚሆን ቢሮው አመልክቷል።
እነዚህ ባለሙያዎች ወደፊት ህጋዊ የሂሳብ መዝገብ ይዘው እንዲንቀሳቀሱ የማስተካከያ እርምጃዎችና የቃል መሐላ ስነ ስርዓቶች እንደሚከናወኑ ተገልጿል።
አሐዱ ራዲዮ

19 hours ago
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 23 ሺህ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገለጸ
👉🏽 በ 2018 ዓ/ም ብቻ 86 ሺ ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ጥቅምት 01ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በሴቶች እና ማሀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል እና የተመላሽ ዜጎች ጉዳይ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ተግይበሉ በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በሳምንት ውስጥ 3 ቀን የ9 ዙር በረራዎች መኖሩን ገልጸዋል ።
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በትክክል መጥቀስ እንደማይቻል ገልጸው በርካታ ዜጎች ምቹ ባልሆነ እና አንድ ቦታ የሚቀመጡበት እስርቤት ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል ።
እኚሁ ኢትዮጵያውያን ለተለያዩ ስነ ልቦናዊ ችግር ሊጋለጡ እንደሚችሉ ጠቅሰው በአስቸኳይ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም በ2019 ዓ.ም በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ከሚገኙ መካከል ከ23 ሺ በላይ ዜጎች መመለሳቸውን ገልፀዋል።
ለተመላሽ ዜጎች ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ እንዲሁም የግንዛቤ ፈጠራ ፣ የስነ ልቦና ስልጠና እና ሌሎችንም ማህበራዊ ድጋፍ እንዲያገኙ እየተደረገ ነው ብለዋል።
በ ቃልኪዳን ኃይሌ

21 hours ago
ንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሙያ ፈቃድ ብቻ ሲሰሩ ለነበሩ አካላት የግብር ስሌት አሰራር ተዘረጋ
ጥቅምት 01ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የ2018 የግብር ዘመን ማስታወቂያን አስመልክቶ ይፋ ባደረገው አዲስ አሰራር በሙያ ፈቃድ ብቻ ሲሰሩ ለነበሩ አካላት የሚሆን የግብር ስሌት አሰራር መዘረጋቱን አስታውቋል።
አሐዱ ሬዲዮ በተመለከተው በዚህ አዲስ አሰራር መሠረት ንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሙያ ፈቃድ ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ጠበቆች ፣ የኢንሹራንስ ወኪሎች ፣ የኢንሹራንስ ጉዳት ገማቾች እና ሌሎች ተመሳሳይ ባለሙያዎች ይካተታሉ።
እነዚህ አካላት የሂሳብ መዝገብ የማቅረብ ሕጋዊ ግዴታ ቢኖርባቸውም፣ መዝገብ ሳያቀርቡ ሲቀሩ የነበረውን ክፍተት ለመሙላት መመሪያው ግልጽ የስሌት አሰራር አስቀምጧል።
በአሰራር ስርዓቱ መሠረት በሙያ ፈቃድ ብቻ ሲሰሩ የነበሩ ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብ ባላቀረቡበት ሁኔታ ከአጠቃላይ ገቢያቸው ላይ 35 በመቶው እንደ ወጪ ታስቦ ቀሪው 65 በመቶ ደግሞ ግብር የሚከፈልበት ገቢ እንደሆነ ተቆጥሮ ግብራቸው እንዲሰበሰብ ይደረጋል።
ይህ አሰራር ህጋዊ አሰራርን ለማስፈንና በሙያዊ አገልግሎቶች ዘርፍ ላይ የሚስተዋሉ የግብር ስወራዎችን ለመቀነስ አልሞ የተዘጋጀ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ለ2018 የግብር ዘመን ብቻ ተግባራዊ እንደሚሆን ቢሮው አመልክቷል።
እነዚህ ባለሙያዎች ወደፊት ህጋዊ የሂሳብ መዝገብ ይዘው እንዲንቀሳቀሱ የማስተካከያ እርምጃዎችና የቃል መሐላ ስነ ስርዓቶች እንደሚከናወኑ ተገልጿል።
በፋሲል አረጋይ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ጥቅምት 01ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የ2018 የግብር ዘመን ማስታወቂያን አስመልክቶ ይፋ ባደረገው አዲስ አሰራር በሙያ ፈቃድ ብቻ ሲሰሩ ለነበሩ አካላት የሚሆን የግብር ስሌት አሰራር መዘረጋቱን አስታውቋል።
አሐዱ ሬዲዮ በተመለከተው በዚህ አዲስ አሰራር መሠረት ንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሙያ ፈቃድ ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ጠበቆች ፣ የኢንሹራንስ ወኪሎች ፣ የኢንሹራንስ ጉዳት ገማቾች እና ሌሎች ተመሳሳይ ባለሙያዎች ይካተታሉ።
እነዚህ አካላት የሂሳብ መዝገብ የማቅረብ ሕጋዊ ግዴታ ቢኖርባቸውም፣ መዝገብ ሳያቀርቡ ሲቀሩ የነበረውን ክፍተት ለመሙላት መመሪያው ግልጽ የስሌት አሰራር አስቀምጧል።
በአሰራር ስርዓቱ መሠረት በሙያ ፈቃድ ብቻ ሲሰሩ የነበሩ ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብ ባላቀረቡበት ሁኔታ ከአጠቃላይ ገቢያቸው ላይ 35 በመቶው እንደ ወጪ ታስቦ ቀሪው 65 በመቶ ደግሞ ግብር የሚከፈልበት ገቢ እንደሆነ ተቆጥሮ ግብራቸው እንዲሰበሰብ ይደረጋል።
ይህ አሰራር ህጋዊ አሰራርን ለማስፈንና በሙያዊ አገልግሎቶች ዘርፍ ላይ የሚስተዋሉ የግብር ስወራዎችን ለመቀነስ አልሞ የተዘጋጀ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ለ2018 የግብር ዘመን ብቻ ተግባራዊ እንደሚሆን ቢሮው አመልክቷል።
እነዚህ ባለሙያዎች ወደፊት ህጋዊ የሂሳብ መዝገብ ይዘው እንዲንቀሳቀሱ የማስተካከያ እርምጃዎችና የቃል መሐላ ስነ ስርዓቶች እንደሚከናወኑ ተገልጿል።
በፋሲል አረጋይ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
Sponsored by
Surafel
1 day ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ለሚከተሉትን አመራሮች ሹመት ሰጥተዋል፦
ጥቅምት 01ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) አብዱልዋሳ አብዱላሂ (ዶ/ር) - የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት (IFA) ዋና ዳይሬክተር እና ካፒተን ተፈራ ካሳ - የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፓርት እና ሎጂስቲክስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሹመዋል።
#አሐዱ_ሬዲዮ_94
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ጥቅምት 01ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) አብዱልዋሳ አብዱላሂ (ዶ/ር) - የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት (IFA) ዋና ዳይሬክተር እና ካፒተን ተፈራ ካሳ - የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፓርት እና ሎጂስቲክስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሹመዋል።
#አሐዱ_ሬዲዮ_94
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
2 days ago
2 days ago
በአፋር ክልል በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ምክንያት ድጋፍ ለሚፈልጉ ወገኖች የሰብአዊ ድጋፍ እየተጓጓዘ መሆኑ ተገፁጿል።
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በአፋር ክልል በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ምክንያት ድጋፍ ለሚፈልጉ ወገኖች የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽ እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
ከአዳማ የእህል ማከማቻ ማእከላዊ መጋዘን የተጫነ አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ ወደ አፋር ክልል በመጓጓዝ ላይ መሆኑንም ነው የተገለፀው።
ለተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ክልሎች በራሳቸው አቅም ምላሽ ለመስጠት እየተረባረቡ መሆኑን ያነሳው ኮሚሽኑ የቅድሚያ ቅድሚያ በሚሰጣቸው አካባቢዎች ተጨማሪ የሰብአዊ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ሲል ነው ያስታወቀው።
በዚሁ መሠረትም በአፋር ክልል የቅድሚያ ቅድሚያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የሰብአዊ ድጋፍ በማድረስ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
የአፋር ክልል በራሱ አቅም የሚያደርገው ድጋፍ እና ክትትል እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሚሽኑም የቅርብ ድጋፍና ክትትል እያደረገ መሆኑንና ከአዳማ የመጠባበቂያ መጋዘን ሰብአዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ አፋር ክልል መንቀሳቀሳቸውን ጠቁሟል።

በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ መግባት እንዲችሉ በተለያዩ አካባቢዎች የቅበላ ማዕከላት ተዘጋጅተዋል። ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ መግባት እንዲችሉ በተለያዩ አካባቢዎች የቅበላ ማዕከላት መዘጋጀታቸውን ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን አስታወቀ።
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ መኩሪያው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በአሁኑ ወቅት በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች መንግስት ወደ አዘጋጀላቸው ማዕከላት ለመግባት ጥሪውን እየተጠባበቁ መሆኑ ታውቋል።
መንግሥት ወደ ሰላም አማራጭ የሚመጣ ማንኛውም አካል በተሃድሶ ሂደትን አልፎ፣ ወደ ማህበረሰቡ በመቀላቀል የተረጋጋ ሕይወት እንዲመራ ያለውን ጽኑ ፍላጎት ገልጸዋል፡፡
መከላከያ ሠራዊትም ወደ ሰላም የሚመጣውን ኃይል በአግባቡ የመቀበል፣ የማስተናገድ እና ወደ ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ማዕከላት የማድረስ ሥራውን በተደራጀ መንገድ እየተገበረ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
ኮሚሽኑ ታጣቂዎቹና አመራሮቻቸው በተሐድሶ ሂደት እንዲያልፉ የመቀበያ ማዕከላትን በዞኖችንና ከተሞችን ማዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡
በዚህም ደቡባዊ ዞን ራያ አካባቢ ማይጨው እና መሆኒ ከተሞች፤ ደቡብ ምስራቅ ዞን መቀሌና አካባቢው በመቀሌ ከተማ በሚገኘው የሰሜን እዝ ጠቅላይ መምሪያ፤ ምስራቃዊ ዞን በአዲግራት እና በውቅሮ ከተሞች የመቀበያ ማዕከላት መዘጋጀታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በተጨማሪም በማዕከላዊ ዞን በአድዋ፣ አክሱም እና አቢዓዲ ከተሞች እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ ዞን በሽሬ ከተማ በሚገኘው የቀድሞው ማዕከላዊ እዝ ጠቅላይ መምሪያ ላይ የመቀበያ ማዕከል መዘጋጀቱን ነው የገለፁት።
የመከላከያ ሠራዊት አባለት ታጣቂዎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን አንስተው ታጣቂዎች በእጃቸው የሚገኘውን ትጥቅና ወታደራዊ ቁሳቁስ በማስረከብ ወደ ተዘጋጀላቸው የተሃድሶ ማዕከላት እንደሚገቡ አስታውቀዋል።
#አሐዱ_ሬዲዮ_94
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ Photo

ኢትዮጵያ በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን ማጣራት የሚችል ፋብሪካ ሥራ አስጀመረች
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በሳም ፕሬሺየስ ሜታልስ አጋርነት በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና የተገነባው ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ ሥራ ጀምሯል ።
በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማጣራት አቅም ያለው ፋብሪካው፣ በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ማዕድናት ላይ እሴት በመጨመር የወጪ ንግድ ገቢን ለማሳደግ፣ የማዕድን ዘርፉን ለማጠናከርና የሰለጠነ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተገልጿል።
ፋብሪካው የጌጣጌጥ ኢንዱስትሪውን ከመደገፍ ባለፈ፣ በውድ ማዕድናት ማጣራት ዘርፍ ኢትዮጵያን የቀጣናው ማዕከል ለማድረግ እንዲሁም ግልጽና ተወዳዳሪ የወርቅ እሴት ሰንሰለት ለመገንባት እንደሚያግዝ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል ።

የኢዜማው መሪ አቶ እዮብ መሳፍንት እና ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂምን ጨምሮ 44 ሚኒስትር ዴኤታዎች ተሾሙ
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ባደረጉት ሹመት 44 ሚኒስትር ዴኤታዎችን ለተለያዩ የሀገሪቱ የሥራ ሃላፊነቶች አሾመዋል።
በዚሁ ሹመት ውስጥ ከተካተቱት መካከል የኢዜማ መሪ እና የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ተጠቃሽ ናቸው።
በዕለቱ ከተከናወኑት ሹመቶች መካከል
1. የኢዜማ መሪ አቶ እዮብ መሳፍንት 👉🏽 የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሾመዋል።
2. ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም 👉🏽 የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተመድበዋል።
በተጨማሪም የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (ፋይዳ) ዳይሬክተር በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ዮዳሄ አርዓያስላሴ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸው ታውቋል።
በፋሲል አረጋይ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን አመራሮች በሚኒስትር ዴዔታነት ሾመዋል
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
Sponsored by
Surafel
2 days ago
የጋሞ ብሔረሰብ ባህላዊ የፍትሕና የእርቅ እሴት የሆነውን ዱቡሻ በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ሂደት ላይ መሆኑ ገለፀ ።
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የጋሞ ብሔረሰብከሚታወቅባቸው እሴቶች መካከል ዱቡሻ ባህላዊ የፍትሕ፣ የእርቅና የሕዝብ መሰብሰቢያ እና መገለጫ አንዱ ነው።
የጋሞ ዞን ወጣቶች ጉዳይና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ግባዬ ግልጮ ዱቡሻ ለትውልድ ለማስተላለፍ እና ወጣቶች እንዲያውቁት እና እንዲጠብቁት እየተሰራ ነው ብለዋል።
ዱቡሻ በማኅበረሰቡ ውስጥ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት፣ ሕግና ደንብ ለማውጣት እንዲሁም የማኅበረሰቡን አንድነት ለማጠናከር ጉልህ ሚና እንዳለው ገልፀዋል ።
የዱቡሻ ስርዓትን በአለምአቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ እና በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ሂደት መጀመሩን ተናግረዋል ።
ግጭት እና አለመግባባቶች በሽምግልናና በእርቅ ሥርዓት እንዲፈቱ የሚያደርግ እንዲሁም መረጃ ያልተሟላባቸው ወይም በድብቅ የተፈጸሙ የወንጀል በማጣራትና በመሃላ ሥርዓት የሚመረመርበት ባህላዊ እሴት መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ተናግረዋል ።
ዱቡሻ የጋሞ ብሔረሰብ ባህላዊ ዕውቀት ፣ የማኅበረሰብ አንድነትን የሚያንጸባርቅ እንዲሁም የጋሞ ሕዝብ ባህልና ትውፊት ሚገለጽበት መንገድ መሆኑ ተመላክቷል ።
በቃልኪዳን ኃይሉ

የአቢሲኒያ ባንክ አጠቃላይ የሀብት መጠን ከ 381 ቢሊየን ብር በላይ ደረሰ
👉 ባንኩ በ 2018 ብቻ ከ 143 ሚሊየን ብር በላይ ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) አቢሲኒያ ባንክ 30ኛ መደበኛ እና 17ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዎኖች ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ በአድዋ ሙዚየም እያካሄደ ይገኛል።
በዚህ ወቅት የባንኩን የ2018 አመታዊ ሪፖርት ያቀረቡት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድሊቀመንበር አቶ መኮንን ማንያዘዋል “የ 2018 የሒሳብ አመት በሀገርም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ የኢኮኖሚ ጫናዎች የነበሩ ቢሆንም ተቋቁመን ማሳለፍ ችለናል” ብለዋል።
ባንኩ በዓመቱ 15.85 ቢሊየን ያልተጣራ ትርፍ ያገኘ ሲሆን ጠቅላላ ሀብት መጠን 381.5 ቢሊየን ብር መድረሱን አስታውቋል።
አቢሲኒያ ባንክ ማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት ከተለያዩ ማህበራት ጋር እንደሚሰራ ጠቅሰው በዓመቱ በአጠቃላይ 143.7 ሚሊየን ብር ድጋፍ እንደተደረገ ተናግረዋል።
በመሰረት ሙሉ

በብልሽት ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በአዲስ ዌስት ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ የትራንስፎርመር ብልሽት ምክንያት ዛሬ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም የኃይል አቅርቦት የተቋረጠባቸው እና የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፡፡
ከጠዋት 12፡00 - ቀኑ 8፡00
👉እህል በረንዳ፣ አማኑኤል ቤ/ክ ፊትለፊት፣ ሻንቅላ ወንዝ፣18 ማደያው ጋር፣ ፈጥኖ ደራሽ፣ ኮልፌ ኮምርሄንሲቭ ት/ቤት እና አካባቢው
ከቀኑ 8፡00 - ምሽት 4፡00
👉 አማኑኤል ሆስፒታል ፊት ለፊት፣ ሰባተኛ፣ ድሬ ህንጻ ፊት ለፊት፣ ኮልፌ 18 ጤና ጣቢያ፣ ኮልፌ 18 ድልድዩ ድረስ፣ አውጉስታ፣ ወይራ ሰፈር፣ ወይራ ኮንዶሚኒየም፣ ሞቢል፣ ራሺያ ካምፕ የነበረው፣ ተዘንአ ሆስፒታል፣ ሙስና ሰፈር፣ ጦር ኃይሎች ጎልፍ ክለብና አካባቢው፣ እና አካባቢው
ከምሽት 4፡00 - ጠዋት 12፡00

ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ እስኪመለስ ድረስ በትእግስት እንድትጠብቁ በአክብሮት እናሳውቃለን ሲል የኢትዮጱያ ኤሌትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

በኢትዮጱያ ዓመት 19 ሺ ሴቶች በጡት ካንሰር ሲያዙ ከ9 ሺ በላይ የሚሆኑት ህይወታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ ተገለፀ።
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ህይወት ሰለሞን 70 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ወደ ጤና ተቋም የሚሄዱት የካንሰር በሽታው ከፍተኛ ደረጃ ከደረሰ በኋላ በመሆኑ የሞት መጠኑ ከፍ እንዲል አድርጎታል ብለዋል።
የጡት ካንሰርን ለመከላከልም ሆነ በጊዜ ለማከም መደበኛ በሆነ መልኩ የቅድመ ምርመራ ሊደረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በኢትዮጱያ በዓመት 19 ሺ ሴቶች በጡት ካንሰር ሲያዙ ከ9 ሺ በላይ የሚሆኑት ሂወታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ ገልፀዋል።
የህመም ስሜት ከመጀመሩ በፊት ሴቶች ራሳቸውን በራሳቸው የሚመረምሩበት እንዲሁም በጤና ተቋም በመሄድ ቅደመ ካንሰር ምርመራ የሚያገኙበት ምቹ ሁኔታ ስላለ ይህን እድል ሊጠቀሙ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የሞት ቁጥሩ ከፍተኛ መሆኑ ህመሙ ከተባባሰ በኋላ ወደ ህክምና ተቋም መሄዳቸው የሚያሳየው በማህበረሰቡ ዘንድ ያለው ግንዛቤ አነስተኛ መሆኑን ነው ብለዋል።
በመሰረት ሙሉነህ

የካሽ ሬጂስተር እና የተነጣጠሉ መሣሪያዎችን የአሠራር ፈተና የሚቀርፈው ንብተራ-ደረሰኝ ዲጂታል የክፍያ ደረሰኝ አገልግሎት በይፋ ሥራ ጀመረ
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከፕራይም ኦል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ጋር በመተባበር፣ በዘርፉ የመጀመሪያ የሆነውን ንብተራ-ደረሰኝ የተሰኘ የተቀናጀ የዲጂታል ክፍያና የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ አገልግሎት መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. በትናትናው እለት በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በይፋ አስጀምሯል።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የሪቴይልና ኤስኤምኢ ባንኪንግ ዋና ሀላፊ አቶ ሙሉቀን ደምሴ የንብተራ-ደረሰኝ አገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸውንና እርስ በእርስ የማይገናኙ የሽያጭ መመዝገቢያ ካሽ ሬጂስተሮችን በአንድ እጅ ብቻ በሚያዝ ዘመናዊ ስማርት ፖስ በመተካት፣ ነጋዴዎች ለደንበኞቻቸው የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲሰጡ ያስችላቸዋል ብለዋል።
አክለውም፣ ቴክኖሎጂው በገቢዎች ሚኒስቴር ዕውቅና የተሰጠውን የፕራይም ኦል ትሬዲንግ የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ እና የድርጅት ሀብት አስተዳደር ሥርዓት ከባንኩ የዲጂታል መሠረተ ልማት ጋር በማቀናጀት፣ በአንድ ነጻ ስማርት ፖስ አማካኝነት የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ ለማውጣት፣ የክፍያና የንግድ ሥርዓትን ለማዘመን የሚያስችል አስተማማኝ አሠራር መሆኑን ገልፀዋል።
የፕራይም ኦል ትሬዲንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ውብሸት አዝመራው በበኩላቸው፤ ንብተራ-ደረሰኝ ነጋዴዎች በርካታና የተለያዩ መሣሪያዎችን በመጠቀም ሲሰጡ የነበረውን ኋላቀር አገልግሎት በማስቀረት፣ በንግዱ ዘርፍ ሲስተዋሉ የነበሩትን የአሠራር ፈተናዎች በዘላቂነት ለመፍታት እንደሚያስችል ተናግረዋል።
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በንብተራ ዬዲጂታል የባንክ አገልግሎት ስር በርካታ መተግበሪያዎችን በማካተት፣ ለኅብረተሰቡ ዘመናዊና የተቀላጠፉ የክፍያ አማራጮችን እያቀረበ እንደሚገኝ ተገልጿል።

አቶ ጌታቸው ረዳ በድጋሚ ተሾሙ
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከዛሬ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ጌታቸው ረዳን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አድርገው በድጋሚ ሾመዋል።
አቶ ጌታቸው ከሚያዚያ 3 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በዚሁ ሹመት እያገለገሉ እንደሆነ ይታወቃል።

3 days ago
በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ)
1. ዳንኤል ክብረት - በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ - የዴሊቨሪ ክትትል ዘርፍ ኃላፊ
2. አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ - በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ - የENFI ክትትል ዘርፍ ኃላፊ
3. ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ
4. አቶ ፍሰሃ ደሳለኝ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ
5. ዶ/ር ደረጀ ድጉማ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ
6. አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ
7. አቶ ሀብታሙ ሲሳይ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ)
1. ዳንኤል ክብረት - በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ - የዴሊቨሪ ክትትል ዘርፍ ኃላፊ
2. አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ - በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ - የENFI ክትትል ዘርፍ ኃላፊ
3. ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ
4. አቶ ፍሰሃ ደሳለኝ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ
5. ዶ/ር ደረጀ ድጉማ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ
6. አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ
7. አቶ ሀብታሙ ሲሳይ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
Sponsored by
Surafel
3 days ago
ካፒታል ሆቴል እና ሆሴ ሪል እስቴት ለሜቄዶንያ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) መስከረም 29 "የካፒታል ሆቴል ቀን" ተብሎ መሰየሙን የሜቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበር ገልጿል።
ካፒታል ሆቴል ከሆሴ ሪል እስቴት ጋር በመተባበር ለማህበሩ በጥሬ ገንዘብ እና በዓይነት በአጠቃላይ የ4.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን የሜቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር አስታውቋል።
የካፒታል ሆቴል ዋና ስራ አስኪያጅ አ/ቶ ተስፉ ፍፅም እንደገለጹት፤ ሆቴሉ በጥሬ ገንዘብ አንድ ሚሊዮን ብር እንዲሁም በዓይነት 1.5 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።
በተጨማሪም ሆሴ ሪል እስቴት የ2 ሚሊዮን ብር ጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 4.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል ።
ከዚህ በተጨማሪም ከ350 በላይ የሚሆኑ የካፒታል ሆቴል ሰራተኞች እና አስተዳደር አባላት ከደመወዛቸው በመለገስ ማህበሩን ለመደገፍ ቃል ገብተዋል ።
የሜቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራች ቢንያም በለጠ በበኩላቸው፣ ተቋማቱ እና ሰራተኞቻቸው ላደረጉት ቀጣይነት ያለው አጋርነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ማህበሩ ቋሚ የውጭ ፈንድ ወይም ገቢ የለውም ያሉት መስራቹ ከ9 ሺህ በላይ ሰዎችን ለመመገብና ለመንከባከብ የሁሉም አጋርነት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።
በደረጄ መንግስቱ

የታካሚዎች ዲጂታል መረጃ አያያዝ እና ጥበቃ የዓለም ጤና ድርጅትን መስፈርት ያሟላ እንደሆነ ተገለጸ
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በኢትዮጵያ የታካሚዎች ዲጂታል መረጃ አያያዝ፣ ደህንነት እና ሚስጥራዊነት ጥበቃ የዓለም ጤና ድርጅትን መስፈርት እንደሚያሟላ በጤና ሚኒስቴር የዲጂታል ጤና መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ገመቺስ መልካሙ ለአሐዱ ሬድዮ ተናግረዋል።
በተጨማሪም፤ ሀገሪቱ ሁለት ዓይነት የታካሚዎች መረጃ ማሰባሰቢያ ሥርዓቶች እንደምትከተል አብራርተዋል።
የመጀመሪያው "ዲ ኤች አይ ኤስ ቱ" የተባለው ሥርዓት ሲሆን፣ በጤና ተቋማት የታካሚዎችን ጠቅላላ መረጃ የሚሰበስብና በሚመለከታቸው አካላት ብቻ የሚጋራ ነው።
ሁለተኛው "ኤሌክትሮኒክ ኮሚኒቲ ኸልዝ ኢንፎርሜሽን ሲስተም" ደግሞ በገጠር ጤና ኬላዎች የሚያገለግል ሲሆን፣ እስከ አሁን የ31 ሚሊዮን ሰዎችን የግል መረጃ መመዝገቡ ተጠቅሷል።
የታካሚዎችን የግል የጤና መረጃ ባለሙያዎች ብቻ እንዲመለከቱት ይደረጋል የተባለ ሲሆን፤ በብሔራዊ ደረጃ ቁጥራዊ መረጃዎችን ብቻ የሚያሳየው ይህ አሠራር፣ የዓለም ጤና ድርጅት የታካሚዎች መረጃ ደኅንነት ጥበቃ መስፈርትን እንደሚያሟላ ተገልጿል።
ሥርዓቱ የታካሚዎች የግል የጤና መረጃ ከጤና ተቋሙ ውጪ አገልግሎት ላይ እንዳይውል በቪፒኤን በተሰኘ ኢንተርኔት በሌለባቸው አካባቢዎች ኢንተርኔት ለመጠቀም በሚያስችል ኔትወርክ እንዲሠራ መደረጉንም አቶ ገመቺስ አብራርተዋል።

የምክር ቤት አባላት የዜጎችን ድምፅ በማስተጋባት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ገለፁ
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የምክር ቤት አባላት የወከሉትን ማህበረሰብ ችግርና ፍላጎት በማዳመጥ፣ የዜጎችን ድምፅ በምክር ቤት ማስተጋባትና የሚወሰኑ ፖሊሲዎች የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጡ መስራት ይገባቸዋል ሲሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ተናግረዋል ።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዘላለም በቀለ የምክር ቤት አባላት የሚወክሉትን ማህበረሰብ ችግርና ፍላጎት በመለየት፣ ለመንግስት በማሳወቅና በውሳኔ ሰጪ መድረኮች የህዝቡ ድምፅ እንዲሰማ በማድረግ ተገቢውን ሚና መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አመላክተዋል ።
በማህበረሰቡ የሚነሱ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በቂ ትኩረትና ተጨባጭ መፍትሄ እንዲያገኙ የመከታተል ሚና እንዳላቸውም ገልጸዋል።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በረኸተስፋ ዜጎች በኢኮኖሚው ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚወጡ ፖሊሲዎች ውጤታማ በሆነ መልኩ ተግባራዊ መደረጋቸው ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
የሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና የዜጎች ተጠቃሚነት ከሰላም ጋር የተያያዘ መሆኑን ጠቁመው የምክር ቤት አባላት ለሀገር ሰላም ቅድሚያ በመስጠት የሚጠበቅባቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል ።
ሙስና የሀገር የኢኮኖሚ ላይ ሙስና ያለውን ተፅዕኖ የገለፁት ባለሙያው ሙስናን ለመከላከል እና ተጠያቂነትን ለማጠናከር የሚያስችሉ ውጤታማ ስርዓቶችን መዘርጋት እንደሚያስፈልግ አፅንዖት ሰጥተዋል።
የምክር ቤት አባላት የወከሉትን ማህበረሰብ ድምፅ በታማኝነት ማንፀባረቃቸው፣ የዜጎች ችግር በውሳኔ ሰጪ መድረኮች ትኩረት እንዲያገኝ ከማድረግ ባለፈ፣ የህዝብ ሀብት ለህዝብ ጥቅም እንዲውልና ዜጎች በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንደሚረዳ አስረድተዋል ።
በቃልኪዳን ኃይሌ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖስታ ሙዚየም ወደ ታሪካዊ ስፍራው ተመልሶ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት የተቋሙ መነሻ እና ታሪካዊ ስፍራ የሆነው ብሔራዊ ፓስታ ሙዚየም ወደ ቀድሞው እና ታሪካዊ ቦታው ተመልሶ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን መደረጉን አስታውቋል፡፡
ተቋሙ ይህንን ያስታወቀው በዛሬው ዕለት መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም " አንድ የፖስታ አውታረ መረብ ገደብ የለሽ ዕድሎች " በሚል መሪ ቃል የዓለም የፖስታ ቀንን ባከበረበት ወቅት ነው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖስት ሙዚየም በዋናው የፖስታ አገልግሎት ተቋም ውስጥ ከ50 ዓመታት በላይ አገልግሎት ሲሰጥና ታሪካዊ ነገሮችን ለጎብኚዎች ሲያስተዋውቅ እንደነበር የኢትዮጵያ ፖስታ የአቅርቦትና አስተዳደር ሃላፊ አ/ቶ ጋሻው መርሻ ተናግረዋል።
በተለይም ከዛሬ ጀምሮ ክፍት የተደረገው ይህ የብሔራዊ ፖስታ ሙዚየም ለተማሪዎች ፣ ለተመራማሪዎች እንዲሁም ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ አገር ጎብኝዎች ምቹ በሆነ ሁኔታ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉን አብራርተዋል።
የማሻሻያ ስራው የታሪክ ቁሳቁሶችን እና የቴምብር ስብስቦችን ለጎብኚዎች በጥራት ለማቅረብ እንዲሁም የዲጂታል እና የተቋሙ ሀብቶችን በጥቅም ላይ በማዋል ዘመናዊ እና ምቹ አከባቢን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ገልፀዋል።
ታሪክን ጠብቆ ማቆየትና ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የተቋሙ ትልቅ ኃላፊነት መሆኑን ጠቅሰው ተቋሙ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን የተደረገው በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት እምብርት እና የሀገሪቱ የመገናኛ ታሪክ የጀመረበት ትልቅ ታሪካዊ ቦታ ላይ ነው ብለዋል።
በተመስገን ተጋፋው

በኢትዮጵያ ደኅንነቱ ያልተጠበቀ ፅንስ ማቋረጥ ምጣኔ ከ4% በላይ መሆኑ ተገለጸ
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በኢትዮጵያ ደኅንነቱ ያልተጠበቀ ፅንስ ማቋረጥ ሕጉ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ከነበረው ቢቀንስም፣ አሁንም ከ4% በላይ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በጤና ሚኒስቴር የስነ-ተዋልዶ፣ የቤተሰብ እቅድ እና አፍላ ወጣቶች ባለሙያ አቶ በሪሁን ስባጋዲስ እንደገለጹት፣ ከ60% በላይ የሚሆኑ የጤና ተቋማት ደኅንነቱ የተጠበቀ ፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።
እንደ ሀገር ደኅንነቱ የተጠበቀ ፅንስ ለማቋረጥ ፆታዊ ጥቃት ሲያጋጥም፣ የእናትየውን ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑ ከተረጋገጠ እና ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት እንዳለባቸው አቶ በሪሁን አስገንዝበዋል።
በአይፓስ ኢትዮጵያ አዘጋጅነት በተከበረው ዓለም አቀፍ ደህንነቱ የተጠበቀ ፅንስ ማቋረጥ ቀን ላይ የአይፓስ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶክተር ደመቀ ደስታ፣ ተቋማቸው ደኅንነቱ ያልተጠበቀ ፅንስ ማቋረጥ የሚያስከትለውን ጉዳት እና የተዋልዶ ጤና ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እየሠራ እንደሆነ ተናግረዋል።
ደኆንነቱ የተጠበቀ ፅንስ ማቋረጥን ተደራሽ ለማድረግ አይፓስ ከ20 ሺህ በላይ ባለሙያዎችን በማሰልጠን እንዲሁም ከ1,600 በላይ የሚሆኑ ጤና ተቋማትን በመደገፍና ግብዓት በማሟላት ላይ ይገኛል።
በተጨማሪም ድርጅቱ ያልተፈለገ እርግዝናን መከላከል፣ የስነ-ተዋልዶ ጤናን ለወጣቶች እና ለአካል ጉዳተኞች ማዳረስ እንዲሁም ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን በመከላከል ረገድ እየሰራ እንደሆነ ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቋርጦ የነበረውን የመቐለ በረራ ሊጀምር ነው
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቐለ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የሚጀምር መሆኑን አስታውቋል፡፡
አየር መንገዱ ደንበኞች በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ በመሄድ ወይም ወደ ጥሪ ማዕከል 6787 በመደወል የጉዞ ምዝገባ ማስያዝ እንደሚችሉም አሳውቋል።
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቐለ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የሚጀምር መሆኑን አስታውቋል፡፡
አየር መንገዱ ደንበኞች በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ በመሄድ ወይም ወደ ጥሪ ማዕከል 6787 በመደወል የጉዞ ምዝገባ ማስያዝ እንደሚችሉም አሳውቋል።
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
3 days ago
ከ4.2 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የወተት ጥራት መመርመሪያ መሳሪዎች በ11 ክፍለ ከተሞች መሰራጨት ጀመረ
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በአዲስ አበባ ለህብረተሰቡ የሚቀርበውን ወተት ጥራት እና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ከ4.2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ዘመናዊ መመርመሪያ መሳሪያዎች በ11ዱም ክፍለ ከተሞች መሰራጨት መጀመሩን የአዲስ አበባ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አስታውቋል።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር ጸጋ ለማ ለአሐዱ ሬዲዮ እንደገለጹት ወተትን ከባዕድ ነገር ጋር ተቀላቅሎ ለገበያ ሲቀርብ በዓይን አይቶ ለመለየት እጅግ አስቸጋሪ በመሆኑ ቴክኖሎጂን መጠቀም የግድ ይላል።
በመሆኑም ከጥርጣሬ የጸዳ እና ውጤታማ የሆነ የቁጥጥር ስራ ለመስራት የሚያስችሉ እና ከፍተኛ ካፒታል የሚጠይቁ ዘመናዊ መፈተሻ መሳሪያዎችን ለሁሉም ክፍለ ከተሞች የማከፋፈል ስራ ተጀምሯል።
የመሳሪያዎቹ አቅርቦት SNV ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በተደረገ ትብብር የተገኘ መሆኑን የገለጹት ምክትል ኮሚሽነሩ ከቁሳቁስ አቅርቦቱ ጎን ለጎን የቁጥጥር ስራውን የሚያከናውኑ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መውሰዳቸውን ተናግረዋል።
በዚህም መሰረት ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ 22 ተቆጣጣሪዎች በዘርፉ በታወቁ ሀገር አቀፍ አሰልጣኞች አማካኝነት ለአምስት ተከታታይ ቀናት ተግባር ተኮር ስልጠና ተሰጥቷቸዋል።
ከዚህ ቀደም የወተትን ደህንነት እና ጥራት ነባራዊ ሁኔታ ለማጥናት ከተለያዩ የከተማው እና የፌደራል ባለድርሻ አካላት ጋር የዳሰሳ ጥናት መደረጉን ያስታወሱት ዶክተር ጸጋ በጥናቱ ላይ በመመስረትም የወተት ጥራትን የሚቆጣጠር የህግ ማዕቀፍ የማዘጋጀት ስራ መሰራቱን አብራርተዋል።
በአሁኑ ሰዓትም በሰለጠነ የሰው ሀይል እና በተሟላ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የከተማዋን የወተት ጥራትና ደህንነት የማስጠበቅ ስራን በስፋት ለመጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ መሆኑ ተገልጿል።

19ኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን የፊታችን ሰኞ ይከበራል
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) 19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ/ም “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባት እና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል ይከበራል::
ዕለቱ ዜጎች ለሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር በመስጠት የጋራ እሴቶቻቸውን የሚያጠናክሩበት እና በሀገራዊ አንድነትና ኅብረ ብሔራዊነት የሚስማሙበት ቀን ነው።
ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተሻሻለው የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 863/2006 አንቀጽ 2 መሰረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ሰኞ ይከበራል።
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) 19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ/ም “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባት እና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል ይከበራል::
ዕለቱ ዜጎች ለሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር በመስጠት የጋራ እሴቶቻቸውን የሚያጠናክሩበት እና በሀገራዊ አንድነትና ኅብረ ብሔራዊነት የሚስማሙበት ቀን ነው።
ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተሻሻለው የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 863/2006 አንቀጽ 2 መሰረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ሰኞ ይከበራል።
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
3 days ago
ሴንቸሪ ሪልስቴት ድምፃዊ ዳዊት ጽጌን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሰየመ
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በሪል እስቴትና በሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች ያከናወናቸውን ሥራዎችና ዕቅዶች ይፋ አድርጓል።
በመርሐ-ግብሩ ላይ አዲስ የብራንድ አምባሳደር ስምምነት ከድምፃዊ ዳዊት ፅጌ ጋር ተፈራርሟል ።
የሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተፈራ ለማ ሴንቸሪ በሪል እስቴትና በኮንስትራክሽን ግብዓት፣ ብረታ ብረት፣ ኬሚካልና ማዕድን ዘርፎች ላይ በመስራት ለሀገራዊ ልማት አስተዋፅዖ ማድረጉን ገልጸዋል።
የሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከፍተኛ አማካሪና የቦርድ አባል ፕሮፌሰር አበበ ድንቁ በበኩላቸው፣ ተቋሙ ላለፉት 70 ዓመታት በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች መስራቱን ገልጸዋል።
የሴንቸሪ ሪል እስቴት ዋና ኦፕሬቲንግ ኦፊሰር አቶ ፈለቀ ሹሜ፣ ድርጅቱ ላለፉት 10 ዓመታት በአዲስ አበባ ለመኖሪያ፣ ለንግድና ለቢሮ የሚውሉ ሕንፃዎችን መገንባቱን ገልጸዋል። የግንባታ ግብዓቶችን በራሱ ማምረቱ የተለየ ጥቅም እንደሚሰጠው ጠቁመዋል።
በመርሐ-ግብሩ ላይ ሴንቸሪ ሪል እስቴት የድምፃዊ ዳዊት ጽጌን ብራንድ አምባሳደር በማድረግ “ደግሞ በዚህ ላይ... ሥራዎቻችን ምስክሮቻችን!” በሚል አዲስ ዘመቻ መጀመሩ ተገልጿል።
ድምፃዊ ዳዊት ጽጌ በበኩሉ፣ ድርጅቱ በሪል እስቴት ዘርፍ ከሚያከናውነው ሥራ ባሻገር በማህበራዊ ኃላፊነትና በበጎ አድራጎት ሥራዎች የሚያደርገውን ተሳትፎ በመመልከት ከሴንቸሪ ሪል እስቴት ጋር ለመስራት መስማማቱን ገልጿል።

በወተት ምርትና ስርጭት ላይ የሚታዩ የጥራት ችግሮችን ለመቆጣጠር አዲስ ረቂቅ ደንብ እየተዘጋጀ ነው
#ethiopia | በወተት ምርት፣ አያያዝና ስርጭት ላይ የሚታዩ የጥራትና የንፅህና ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ ረቂቅ የሕግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑን የአዲስ አበባ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ በ2018 በጀት ዓመት ባካሄደው ጥናት ከወተት እርባታ ሼዶች እስከ ችርቻሮ መሸጫ ሱቆች ድረስ የንፅህና ጉድለቶች መኖራቸውን መለየቱን ገልጿል።
በእርባታ ቦታዎች አላቢዎች ተገቢውን የደንብ ልብስ አለመልበሳቸውና የንፅህና አጠባበቅ ክፍተቶች መኖራቸው በጥናቱ ከተለዩ ችግሮች መካከል ተጠቅሰዋል። በተጨማሪም ላሞች ሲታመሙ የሚሰጣቸው መድኃኒት ከሰውነታቸው ሙሉ በሙሉ ሳይወጣ ወተቱ ለገበያ የሚቀርብበት ሁኔታ መኖሩ ተመልክቷል።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር ጸጋ ለማ እንደገለጹት፣ ወተት ለማለብ፣ ለማጠራቀምና ለማጓጓዝ ተገቢውን የምግብ ደህንነት መስፈርት የማያሟሉ የፕላስቲክ ጀሪካኖች በስፋት እየተጠቀሙ ነው። ይህም ለማፅዳት አስቸጋሪ በመሆኑ በወተት ጥራትና ደህንነት ላይ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ጠቁመዋል።
ከዚህም በተጨማሪ፣ ወተት ውስጥ ውሃ በመጨመር ተፈጥሯዊ ይዘቱን የማዛባት ሕገወጥ ድርጊት በአንዳንድ አካላት እየተፈጸመ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነሩ አመልክተዋል።
ኮሚሽኑ እነዚህን የምግብ ደህንነትን የሚጎዱ ተግባራት ለመቆጣጠር፣ ሕጋዊ እርምጃዎችን ለመውሰድና በወተት ምርት ሰንሰለት ውስጥ የሚታዩ ክፍተቶችን ለማስተካከል አዲስ ረቂቅ ደንብ አዘጋጅቶ ለማስጸደቅ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።
ረቂቅ ደንቡ ጸድቆ ወደ ተግባር ሲገባ፣ ከእርባታ ጀምሮ እስከ ምርት ማጓጓዝ፣ ማከማቸትና ለሸማቾች ማቅረብ ድረስ ባለው የንግድ ሰንሰለት ውስጥ የጥራትና የንፅህና መስፈርቶችን ለማስጠበቅ አስፈላጊ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።
ይህም ለህብረተሰቡ ጤናማ፣ ጥራቱ የተጠበቀና ደህንነቱ የተረጋገጠ ወተት እንዲደርስ እንደሚያግዝ ይጠበቃል።
ፋሲል አረጋይ — አሐዱ

4 days ago
አዲሱ ካቢኔ በተቻለ መጠን አካታች እንዲሆን ተደርጓል ሲሉ ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ ተናገሩ
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት መደበኛ ጉባኤውን ሲያካሂድ አዳዲስ የካቢኔ ዕጩዎችን ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የካቢኔ አባላት ሹመት በተቻለ መጠን አካታች እንዲሆን ጥረት መደረጉን ተናግረዋል።
በዚህም መሰረት ከዚህ ቀደም አንድ የካቢኔ አባል ብቻ የነበረው የትግራይ ክልል አሁን ሁለት አባላት እንዲኖሩት መደረጉን ጠቅሰዋል። በተጨማሪም በዚሁ ሹመት ለመጀመሪያ ጊዜ የሐረሪ ክልል ተወላጅ በሚኒስትር ደረጃ እንዲሾሙ መደረጉን ጠቁመዋል።
ከአካታችነት አንጻር አሁንም ያልተሟሉ ነገሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሆኖም ከዚህ ቀደም ከነበረው ሁኔታ ጋር ሲነጻጸር ትልቅ መሻሻል መኖሩን ገልጸዋል።
አክለውም ሹመቱ ቅድመ ሁኔታዎችና መስፈርቶች ግምት ውስጥ የገቡበት መሆኑን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹመታቸው ለጸደቀላቸው አዳዲስ ሚኒስትሮች መጪው የስራ ጊዜ ቀላል የሚባል እንዳልሆነ በመጠቆም በትኩረትና በትጋት እንዲሰሩ አሳስበዋል።

Comments